ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብሰበው ስዊድን ገቡ!!

 

(ዘ-ሐበሻ) የጦር ሃይሎች የሎጂስቲክስ ዋና ሐላፊ የነበሩት ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብስበው ስዊድን መግባታቸውን አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ባስተላለፈው መረጃ አመለከተ። አብርሃም ገዛኢ ከሃገር የወጡት በጡረታ ለተገለሉ በኋላ ነው  በማላት  ”የህወሓት ሃላፊዎችማ የያዙትን ይዘው ከሀገር እየወጡ ነው። የተቸገሩ ታችኞቹ ካድሬዎች ናቸው። እንደ አለቆቻቸው ወደ ዉጭ በመኮብለል የግል ደህንነታቸው መጠበቅ አይችሉም።” ሲል ትችቱን አስፍሯል።
ጄነራል ገዛኢ አበራ በሱዳን አቢ ግዛት ሰፍሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የመሩ ናቸው።

ከአንድ ዓመት በፊት የግንቦት 7 የኢትዮጵያ የጥናት ቡድን ባሰራጨው ምስጢራዊ መረጃ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን የጦር አለቆች ከፍተኛ የሆነ ሃብት እንዲያካብቱና ዘረፋ እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ለተለያዩት የጦር መኮንኖች ሟቹ ጠ/ሚ/ር በ1989 ለአ/አበባ አስተዳደርና ለመከላከያ ሚ/ር መ/ቤት ለ25 የወያኔ የጦር መኮንኖች፣ ለእያንዳንዳቸው በሽልማት በአዲስ አበባ ውስጥ 500 ካሬ ሜትር 1ኛ ደረጃ መሬት እንዲሰጣቸው ትእዛዝ በሰጡት መሰረት ይህን መሬት የተቀበሉት ሌ/ጄነራል ገዛኢ አበራ በወር 170 ሺህ ብር የሚከራይ ቤት ቦሌ አካባቢ ሠርተው እንደሚያከራዩ ተጋልጦ ነበር።

ግንቦት 7 በአንድ ዓመት በፊት እንዳጋለጠው፦

የወያኔ የጦር መኮንኖች የአዲስ አበባን ከተማ በመዝረፍ ያከማቹት ሃብት

ተራ/ቁ ማእረግ ስም ቦታው የሚገኝበት ወርሃዊ ኪራይ በብር የዘውግ መግለጫ
1 ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ቦሌ 25,000 ከ4 ዓመት በፊት ትግሬ
2 ጄኔ ሳሞራ የኑስ ቦሌ 28,000 ትግሬ
3 ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ ቦሌ 38,000 ትግሬ
4 ሌ/ጄ ገዛኢ Aበራ ቦሌ 170.000 ትግሬ
5 ሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ ቦሌ 38,000 ትግሬ
6 ሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ቦሌ 35,000 ትግሬ
7 ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ቦሌ 1,2 ሚሊየን መሬቱን የሽጠ አገው
8 ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት ቦሌ 2.5 ሚሊዮን መሬቱን የሽጠ ትግሬ
9 ሜ/ጄ አብርሃ ው/ገብርኤል ቦሌ 34,000 ትግሬ
10 ሜ/ጄ ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ 28,000 ትግሬ
11 ሜ/ጄ አባ ዱላ ገመዳ ቦሌ 45,000 ትግሬ/ኦርሞ
12 ሜ/ጄ አለሙ አየለ ቦሌ መሬቱን በ1.7 ሚሊዮን የሸጠ አገው
13 ሜ/ጄ ስዮም ሃጎስ ቦሌ 28,000 ትግሬ
14 ሜ/ጄ ሃየሎም አርAያ ቦሌ ? ትግሬ
15 ሜ/ጄ ገ/እግዚአብሄር መብራቱ ቦሌ 40,000 ትግሬ
16 ሜ/ጄ ባጫ ደበሌ ቦሌ 20,000 ኦሮሞ
17 ብ/ጄ ታደሰ ጋውና ቦሌ መሬቱን 1.2 ሚሊዮን ብር የሽጠ ትግሬ
18 ብ/ጄ ተክላይ አሽብር ቦሌ 60,000 ትግሬ
19 ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳነ ቦሌ 30,000 ትግሬ
20 ብ/ጄ ፓትሪስ ቦሌ 34,000 ትግሬ
21 ብ/ጄ መስፍን አማረ ቦሌ 23,000 ትግሬ
22 ብ/ጄ ምግበ ሃይለ ቦሌ 20,000 ትግሬ
23 ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ ቦሌ 22,000 ትግሬ
24 ኮ/ል ታደስ ንጉሴ ቦሌ 48,000 ትግሬ
25 ኮ/ል ጸሃየ መንጁስ ቦሌ መሬቱን 1.2 ሚሊዮን የሽጠ ትግሬ
ከእነዚህ የጦር አለቆች ውስጥ ባሁኑ ሰዓት በተራ ቁጥር 1, 8, እና 17 ከስርአቱ ውጭ ሲሆኑ፣ በተራ ቁጥር 14 እና 24 ያሉት ደግሞ በህይወት የሌሉ ናቸው።
ከላይ  ከተጠቀሰው  በተጨማሪ  ወያኔ  ለጦር  አለቆቹ  የሚሰጠው  ጥቅማ  ጥቅም  የሚከተለውን  ይመስላል።
  1. እነዚህ የጦር አለቆች በነጻ መሬት ወስደው ቤት በዘረፋ ከሰሩ በህዋላም በከተማው ውስጥ በመንግስት እጅ ከሚገኙ ምርጥ ቪላዎች መሃል ተመርጦ በተሰጣቸው ቤቶች ውስጥ በነጻ መኖር ቀጥለዋል።
  2. የውሃ የመብራት የስልክ ወጭዎችን ሙሉ በሙሉ የወያኔ መንግስት ይከፍላል። እነዚህ ሞልቃቃና ቅምጥል የጦር አለቆች በሚኖሩበት ቪላ ውስጥ ብርዱን አልቻልንም በማለት ቤታችውን ሙሉ በሙሉ በውድ ምንጣፍ ማሽፈናቸው አልበቃ ብሉዋቸው ከፍተኛ የኤሌትሪክ ሃይል ፍጆታ የሚያስፈልጋችው የኤሌትሪክ የቤት ማሞቂያ መሳሪያዎች በየክፍሉ አስገጥመዋል። ምንጣፍ ለሚጠርገው የኤሌትሪክ መጥረጊያ ሆነ ለኤሌትሪክ ማሞቂያዎቹ የሚወጣው ክፍተኛ ወጪ፣ እንዲሁም እንዳሻቸው ለሚያፈሱት ውሃ በነጻ ተገልጋዮች እንዲሆኑ ተደርገዋል። በእዚህ ላይ ነጻ የሆነውን የሞባይልና የቤት ስልክ አገልገሎት ስንጨምርው በነጻ የሚያገኙት አገልግሎት በሽዎች የሚቆጠር ብር ይደርሳል።
  3. የጦር አለቆቹ ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው፣ ከእዚህም አልፎ አባትና እናቶቻቸው ሳይቀሩ እሰከ ውጭ ሃገር ድረስ በመሄድ የሚሰጥ ነጻ ህክምና ያገኛሉ።
  4. ሁሉም የጦር አለቆች ተጨማሪ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በመቀሌ በባህር ዳር፣ አንዳንዶቹም በአ/አበባ ከተማ፣ በድጋሚ መሬት እንዲወስዱና እንዲገነቡ ተደርገዋል። ከእዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ በዱከም በናዝሬትና በሌሎች ቦታዎች ለንግድና ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ ቦታዎች በመውሰድ ይህን መሬት በቀላሉ ለማያገኙ ሌላ የሃገሪቱ ዜጎች በከፍተኛ ዋጋ በመቸብቸብ ያካበቱት ሃብት ገደብ የሌለው ሆንዋል። ታደስ ወረደ፣ ወዲ እምቤቲ፣ ፍስሃ ኪዳነ፣ ገዛኢ አበራ የተባሉት የጦር አለቆች በዚህ ድርጊት በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መሃል ናችው።
  5. ይህ አልብቃ ብሎ እነዚህ የጦር አለቆች በመከላከያ ሚኒስትር በተያዘ ከፍተኛ የመስተንገዶ በጀት በመጠቀም የሚኖሩትን የቅንጦት ኑሮ ለተመለከተ ሃገራችን በምን አይነት የቀን ጅቦች እንደተወረረች ለማየት የሚያስችል ይሆናል። በ1992 ዓ/ም መከላከያ ሚኒስቴረ ለመስተንግዶ ብቻ የመደበው በጀት 280,000,000 (280 ሚሊዮን) ብር ነበር። በእዚሁ በ1992 ዓ/ም የሶማሊያ ክልል አመታዊ በጀት በተመሳሳይ 280 ሚሊዮን ብር እንደነበር ስናስታውስ፣ ይህ ለጦር አለቆቹ የተመደበው በጀት ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ መረዳት ይችላል የሚል እምነት አለን። በእዚህ የመስተንግዶ በጀት በመጠቀም የጦር አለቆቹ በየቀኑ ብፌ እያዘጋጁ ራሳቸውን ሲቀልቡ ከእዚህም አልፈው እንደጥንቶቹ መሳፍንት ግብር እንዲያበሉ፣ ውድ የሆኑ የውስኪ አይነቶች እንደ ውሃ እያፈሰሱ የሚኖሩበትን ሁኔታ አመቻችቶላቸዋል።
  6. በእዚህ የመስተንግዶ በጀት አማካይነት የወያኔ የጦር አለቆች ከትንሹ ሹካና ማንኪያ ጀምሮ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ሶፋዎች የምግብ ጠረጴዛዎች አልጋዎችና ሌሎችም በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ታዋቂ ሃብታም ዘፋኞችና የፊልም ተዋንያኖች የሚገልገሉባቸውን የቤት ቁሳቁሶች መግዛት ችለዋል። የጦር አለቆቹ እነዚህን የቤት ቁስቁሶች በየአመቱ የመቀየር መብት ስለተሰጣችው በእዚህ መብት ስም የሚያባክኑት የህዝብ ሃብት እጅግ በርካታ ነው።
  7. እያንዳንዱ የወያኔ የጦር አለቃ ከሁለት በላይ ውድና ዘመናዊ መኪናዎች ተሰጥቶታል። እነዚህ መኪናዎች በየአመቱ በአዲስ ሞዴል መኪናዎች ይተካሉ። የወያኔ ጄኔራል አንድ መኪና ለራሱ ሌላ መኪና ለሚስቱና ለልጆቹ በመውሰድ፣ እነዚህን መኪናዎች በግላቸው ያለምንም ወጪ እንዳሻቸው ከመገልገል አልፎ የኮንትሮባንድ እቃዎች ማመላለሻ አድርገው ይገለገሉባቸዋል። የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከድሬደዋ፣ ሃረር፣ ጅጅጋ አርቲሸክና ሞያሌ በማመላለሱ ስራ ተሰማርተው ከሚገኙት መሃል ጎልተው የሚታወቁት ሌ/ጄ ታደስ ወረደ፣ ሌ/ጄ ሳረ መኮንን፣ ሌ/ጄ አበባው ታደሰ፣ ሜ/ጄ ሙሉጌታ በርሀ፣ ሜ/ጄ አለሙ አየለና ሌሎችም በርካታዎች ናቸው። በሌላ መንገድም የተሰጣቸውን መኪና፣ ከመንግስት ያለምንም ገደብ ከሚወስዱት ነጻ ነዳጅ ጋር እያከራዩ የሚጠቀሙ ጄነራሎች ብዙ ናቸው። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት በርካታዎች መሃል ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ፣ ብ/ጄ ተክላይ አሽብርን መጥቀስ ይቻላል። የመከላከያ ሚኒስቴር በ1993 አ/ም ብቻ በአንድ ግዜ ለመለስ የጦር አለቆች መገልገያ የሚሆኑ 300 ኮብራ ቶዮታ ላንድ ክሩዘር አስገብተዋል። ኢትዮጵያን በመሰለ ደሃ ሃገር ውስጥ በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በአንድ ግዜ ብቻ ይህንን ያህል የውጭ ምንዛሪ ሲባክን አይቶ የማይደነግጥ ሃገር ወዳድ ዜጋ ይኖራል የሚል እምነት የለንም።
  8. ከእዚህ በተጨማሪ በመከላከያ ስር ያሉ ወታደራዊ መደቦችና ክበቦች የወያኔ የጦር አለቆች የግል ንብረቶችና መገልገያዎች እንዲሆኑ ተደርገዋል። የጎልፍ ክበብ፣ መኮንኖች ክበብ፣ ደብረዘይት የአየር ሃይል ክበብና በየክልሉ የሚገኙ ትላልቅ ክበቦችን ጨምሮ እነዚህ የጦር መኮንኖች እንዳሻችው ያለምንም ወጪ የሚሰክሩባቸውና የሚዝናኑባቸው ናቸው። ወታደራዊ መደብሮቹ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲያስግቡ የተፈቀደላቸው በመሆናቸው ማንኛውም የውስጥ እቃዎቻቸውና ድርጅታቸው በልዩ በጀት የተሙዋሉላቸው በመሆናቸው ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አትራፊዎች ናቸው። ይህ ትርፍ፣ በየጦር ሰፈሩ የሚሸጠው ሳር፣ ዛፍ፣ አትክልት፣ ውዳቂ ብረታ ብረትና አላቂ እቃዎች፣ የሚረቡ የወተት ከብቶችና የሚደልቡ የስጋ በሬዎች በሙሉ የውያኔ የጦር አለቆች ተጨማሪ የግል ገቢዎች ምንጮች ናቸው።
posted by Aseged Tamene

ጌሾና ጫት – በአውስትራልያ (ዳንኤል ክብረት)

አሁን አብዛኛው አውስትራልያ የገባ ኢትዮጵያዊ በሚገኝባት የሜልበርን ከተማ ውስጥአበሻው ሰብሰብ ብሎ በሚኖርባትና በሚሠራባት ፉትስክሬይ በተባለችው መንደር እንገኛለን፡፡ ይህች የሜልበርን ምዕራባዊ ቀበሌየሆነች መንደር ጥንት የኤስያውያን መናኸርያ ነበረች ይባላል፡፡ ዛሬ ግን ዋናዋ የአፍሪካውያን ስደተኞች መሰባሰቢያ ናት፡፡በዚህች ከ74000 ትንሽ ከፍ የሚል ሕዝብ በሚኖርባት መንደር ውስጥ ከ135 ሀገሮች የመጡ ስደተኞች ይኖሩባታል፤ ከ85 ቋንቋበላይ ይነገርባታል፡፡ እንዴው መርካቶ በሏት፡፡

በአውስትራልያ ታሪክ የመጀመሪያው የእንጀራ መሸጫ ሱቅ የተከፈተው እዚህ ነው፡፡በነገራችን ላይ እዚህ ሀገር እንጀራ በዋናነት ከስንዴ ወይም ከሩዝ ዱቄት ተቦክቶ የማሽላ ዱቄት ይቀላቀልበታል፡፡ የታደሉትደግሞ ከሀገር ቤት የመጣ የጤፍ ዱቄት ለአመል ይጨምሩበታል፡፡ ስፋቱ የአገር ቤት እንጎቻ የሚያህል ሲሆን ውፍረቱ የሰንበት ቂጣታናሽ ወንድም ነው፡፡ ኮከብ የመሰለ ዓይን ባያገኝም፣ ሞጭሟጫ ከመባል ለጥቂት ይተርፋል፡፡ በብዛት የሚጋገረው ከብረት በተሠራምጣድ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ግን ከሀገር ቤት የሸክላ ምጣድ የሚያመጡ አሉ፡፡ ሳይሰበር ከደረሰላቸው፡፡

በፉት ስክሬይ ከደርዘን በላይ የኢትዮጵያውያን ሱቆች፣ ከአምስት በላይ ምግብ ቤቶችእንዳሉ ይነገራል፡፡ በአካባቢው ስትዘዋወሩ ቢያነጥሳችሁ ‹ይማርህ› የሚል አታጡም ይባላል፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን እናቶችና አባቶች ስለሚዘዋወሩበት፡፡ በርግጥ ወጣቶቹና ጎልማሶቹ እንዲህ ያለ ነገር አያውቁም፡፡የሚገርማችሁ እንዲያውም እዚህ አካባቢ አበሻና አበሻ ሲገናኝ ቁጣ እንጂ ሰላምታ አይሰጣጥም፡፡ ሁለቱም ፊታቸውን ኮስተርአድርገው ነው የሚተላለፉት፡፡ እኔ እንዲያውም ‹እዚህ ሀገር የመጣው ያኮረፈው ተመርጦ ነው እንዴ› ብዬ ነበር፡፡

በፉት ስክሬይ የሚጠፋ ቅመማ ቅመም የለም፡፡ በተለይም ሕንድ ሱቅ ውስጥ በሀገራችንየጠፋው ቅመም ሁሉ ይገኛል፡፡ ሞያ በሜልበርን በሽ በሽ ነው፡፡ በርበሬ ከሀገር ቤት ለማስመጣት የአውስትራልያ የምግብ ሕግሲያስቸግር እዚሁ ሌላ በርበሬ ተፈጥሯል፡፡ ከሕንዶች ሱቅ የሚገዛ የሚያቃጥል ቀይ ቃሪያ አለ፡፡ እርሱን በኮረሪማ መፍጫ መፍጨትነው፡፡ ከዚያ ደግሞ ቅመማ ቅመሙን ለብቻ ፈጭቶ መጨመር፡፡ በመጨረሻም አውስትራልያ ሠራሽ ምርጥ ድልህ ይሆንላችኋል፡፡

አንድ ወዳጃችን ‹ሽሮ እኛን ስላሳደገች በክብር ጡረታ ወጥታ ትቀመጥ› ቢልም ከሀገር ሲወጡ አንዱ የሚናፍቀው ግን ሽሮነው፡፡ በአውስትራልያ ልዩ የሆነ የሽሮ አዘገጃጀት ተፈጥሯል፡፡ የባቄላው ዱቄት ከሕንድ ሱቅ ይገዛል፡፡ ከዚያም አመስ አመስ ይደረጋል፡፡ለቅመማው አስፈላጊ የሆነውን ቅመምም ሕንዶቹ ያመጡታል፡፡ እርሱንም በቡና መፍጫ ፈጭቶ በመጠኑ ማመስ ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱን በባለሞያእጅ ደባልቆ ምርጥ የውጭ ሀገር ሽሮ ማግኘት፡፡ ችግር ብልሃትን ይፈጥር የለ፡፡

ለኢትዮጵያውያንእዚህ አንዱ ፈተና ከሀገር ቤት ባህላዊ ምግቦችን ማስመጣት ነው፡፡ የሀገሩ ሕግ ጥብቅ ስለሆነ፡፡ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉግን እንደ ካልዲ(የቡናን ፍሬ ያገኘው እረኛ) አዳዲስ ቅጠላ ቅጠሎችን የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን እዚህ ሞልተዋል፡፡ አንድ ቀንነው አሉ፡፡ መቼም እኛ ታሪክን በጊዜና በሰዓት የመመዝገብ ችግር አለብን፡፡ (ተረቱም ታሪኩም ከዕለታት በአንድ ቀን ብሎ ነውየሚጀምረው) አንዲት የሀገሬ ሰው በግቢዋ ውስጥ ስትዘዋወር አንድ የምታውቀውን ቅጠል የሚመስል ነገር ታያለች፡፡ ጠጋ ብላቆረጠችውና መዳፏ ላይ አሸችው፡፡ ልክ ነው፤ እርሱ ነው፡፡ ወስዳ ለጓደኛዋ አሳየቻት፡፡ ሁለቱም ርግጠኞች ሆኑ፡፡ ጉዳዩን ወደልጅቱ እናት ‹ሪፈር› አደረጉት፡፡ እርሳቸውም እየተገረሙ ‹እርሱ ነው› አሉ፡፡ ለካስ ጌሾ ኖሯል፡፡ ጠላ ለመጥመቅ ችግርየነበረው ጌሾ በአውስትራልያ ምድር በቅሎ ተገኘ፡፡ ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያውያን ግቢ ውስጥ ጌሾ በቅሎ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

በዚህች ምድር በቅሎ የተገኘው ግን ጌሾ ብቻ አይደለም፡፡ መቼም አገር ደግ ነገር ብቻአታበቅል፡፡ አንድ ወዳጃችን ሁል ጊዜ አንድ ቦታ እየሄደ ቅጠል ሸምጥጦ ሲወጣ ይታያል አሉ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ማንም ከቁምነገር አልወሰደውም ነበር፡፡ በኋላ ግን ሸምጣጩ በዛ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ግራ ገባቸው፡፡ በከተማዋ ውስጥም ወሬው ተባዛ፡፡የሚሸመጠጥበት ቦታም በአንዳንድ ሰዎች መዘውተር ጀመረ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከሥሩ እየነቀሉ ወስደው በጓሯቸው ተከሉት፡፡ ከጥቂት ጊዜበኋላ የአውስትራልያ ፖሊሶች ጉዳዩን ሰሙትና ክትትል አደረጉ፡፡ ለካስ ያ በወፍ ዘራሽ በቅሎ አገር እየተራኮተ የሚሸመጥጠው ጫትኖሯል፡፡ ፖሊሶቹ እዚያ ቦታ የነበረውን መድምደው አጠፉት፡፡ ችግሩ ግን እነርሱ ሳይደርሱ በፊት በየግቢው ተዛምቷል፡፡ አንዳንድቤት ስትሄዱ ጫት በኩራት በቅሎ ታዩታላችሁ፡፡

ፉት ስክሬይ በአበሾች ዘንድ ከምትታወቅበት ሀብቷ አንዱ ምርጥ የሆነ ቁርጥ ሥጋ መሸጫስለሆነች ነው፡፡ መቼም ቁርጥ እየበላን ቁርጥ ነገር አለመቻላችን የሚገርም ቢሆንም የሀገሬ ሰው የትም ቦታ ቢሄድ፣ ምንምዓይነት ትምህርት ቢማር ሊያጣው የማይፈልገው ነገር ቢኖር ቁርጥ ሥጋ ነው፡፡ ከነአባባሉም ‹የተማረ ሰውና የተሳለ ቢላዋ ሥጋአያጣም› አይደል የሚባለው፡፡ እዚህ ከተማ በጥሬ ሥጋ ሻጭነታቸው የታወቁ ቤቶች አሉ፡፡ ነጭ፣ ቀይ፣ ጎድን፣ ዳቢት፣ ሻኛ፣ለቁርጥ፣ ለወጥ እያሉ የሚያስተናግዱ፡፡ እነርሱ ጋ ገብቶ አለበለዚያም ደግሞ ሰፈር ይዞ መጥቶ ቁርጥ በኅብረት መብላት እዚህየተለመደ ነው፡፡ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ አውስትራልያ ዘመድ ለመጠየቅም ሆነ ለመዝናናት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን በአውስትራልያቁርጥ ፍቅር ተነድፈው ነው የሚመለሱት፡፡ አንዳንድ የአውሮፓና የአሜሪካ ወዳጆቼ ጋር ስንጻጻፍ እንዲያውም ‹የአውስትራልያን ቁርጥ ሳትበላ እንዳትመጣ› ይሉኛል፡፡ እስቲ ቀምሼ እመሰክርለታለሁ፡፡

‹አይ እኔ ማን እንደነካው የማይታወቅ ሥጋ አልበላም› ለሚሉ አለያም ደግሞ ‹የተሸረፈ ጥርስ፣ ደልደል ያለም ላትአይቶ መርጦ ተከራክሮ መግዛት› ለሚያምራቸው ወደ ገጠሩ ክፍል ወጣ ማለት ነው፡፡ ከበግ አርቢ ገበሬዎች ጋር ምን የመሰለ የደብረብርሃን በግ ይገኛል፡፡ ማረዱን ባይፈቅዱላችሁም መባረኩን ይፈቅዱላችኋል፡፡ እነርሱ ደግሞ ገፍፈውና ቆራርጠው ይሰጧችኋል፡፡ ከዚያበኋላማ ‹አቤት ባለፈው ለፋሲካ የገዛሁት ምን የመሰለ በግ› እያላችሁ ሾላ ገበያ የሄዳችሁ ማስመሰል ነው፡፡

ሜልበርን አውስትራልያ፡፡

posted by Aseged Tamene

ኮ/ል መንግስቱ ከዙምባብዌ ባለስልጣናት ጋር በምስጢር መከሩ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2005 ፕሮግራም

<<…ፍቼ ላይ ካድሬዎች ለበላዮቻቸው በመለስ ስም እየቀሰቀሱ ሕዝቡን ሊያስወጡ ሲሉ ከሰውናል ።የእኛ ጉዳይ የመለስ ሳይሆን የነጻነት ጥያቄ ነው ብለናቸዋል.

.ተጽኖውን ሁሉ ተቋቁሞ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ገልጿል…>> አቶ አበበ አካሉ የአንድነት የም/ቤት አባል ከፍቼ የሰጡት ማብራሪያ ሙሉውን ያዳምጡት

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ንግግር ያደረገበት አደባባይ ኦባማ ምን አይነት ንግግር ያደርጋሉ? የማርቲን ሉተር ኪንግን ሰላማዊና ጉዞ

ወደ ዋሽንግተን ሰልፍ ቃኝተናል፡ በ<<ህልም አለኝ ንግግሩ>> ምን ብሎ ነበር(ወቅታዊ ዘገባ አለን

ስትሮክ ራሱ ብቻውን በሽታ አይደለም የሌሎች በሽታዎች ውጤት ነው።የልብ ህመምና ስትሮክን ማምታታት አያስፈልግም።…የወሊድ መከላከያ የሚወስዱ

ሴቶች ሊጠነቀቁ ይገባል…የተለያዩ ሱሶች ስትሮክን ያመጣሉ…ውፍረት ደግሞ …>>

ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ስለ ስትሮክ መንስኤና መከላከያ ለህብር ከሰጡት ሰፋ ያለ ሙያዊ ማብራሪያ የተወሰደ

(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)

ዜናዎቻችን
– የኦሮሞ መብት ተሟጋች የሆነው ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳ ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ሞተ

– አሟሟቱ እንዲጣራ ለእንግሊዝ ፓርላማ ጥያቄ ቀርቧል

– የታሰሩት የሙስሊሙ መሪዎች ነገ ፍ/ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል

– መንግስት ሙስሊሙን የሚቃወም ሰልፍ በአዲስ አበባ ሊያደርግ ነው

– በሚኒሶታ ለአባይ ቦንድ ግዢ የተጠራ ስብሰባ በውዝግብ በጸጥታ ሀይሎች ውሳኔ ተቋረጠ

– ኮ/ል መንግስቱ ከዙምባብዌ ባለስልጣናት ጋር በምስጢር መከሩ

– ሙጋቤ ቃለ መሀላ ፈጸሙ

– ጅቡቲ አንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከመስጠም ታደገች

– ኤርትራ ከኢትዮጵያ ወገን ጦርነት ሊከፈትብኝ ነው የሚል ስሞታ እያሰማች መሆኑ ተገለጸ

– አገዛዙን ለመጣል ያሰቡ ተቃዋሚዎች ጣሊያን ሰሞኑን ይሰበሰባሉ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን click here http://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-082513-090113

Short URL: http://www.zehabesha.

posted by Aseged Tamene

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ሊፈቱ ይሆን?

ዘጋቢ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስ

በእነ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሽብርተኝነት ክስ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት ከሚገኙት አራቱ ኢትዮጵያውያን መሀከል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌና አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር በ2004 ዓ.ም ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን ምላሽ ሳያገኙ ለረዥም ጊዜ መቆየታቸው ሲያነጋግር ሰንብቷል፡፡ በተለይ ሲውዲናውያኑ ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያውያኑ ጋር በተመሳሳይ ወቅት ይቅርታ ጠይቀው አፋጣኝ ምላሽ ማግኘታቸውና በአንጻሩ የእነውብሸት ይቅርታ ከአመት በላይ መዘግየቱ ተገቢ አለመሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ከአንድ አመት በላይ ቆይታ በኋላ ሐምሌ 25 2005 ዓ.ም የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ማህተም አርፎበት ለወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ በተላከ ደብዳቤ የይቅርታ ጥያቄያቸው ለፕሬዝዳንቱ ቀርቦ ውድቅ መደረጉ ተገልጾላቸዋል፡፡ ወ/ሮ ሂሩት ከእነ ውብሸት ጋር ባንድ መዝገብ ተከሰው 19 አመት የተፈረደባቸው ሲሆን የይቅርታ ጥያቄውንም ያቀረቡት በተመሳሳይ ወቅት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ ህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ለጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ለአቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር የደረሳቸው ደብዳቤ አለመኖሩን አረጋግጠናል፡፡

የወ/ሮ ሂሩት ይቅርታ በፕሬዝዳንቱ ውድቅ መደረጉን አስመልክቶ ልጃቸው ፍጹም መሰለ እናቱ ከተፈረደባቸው በኋላ ይግባኝ ከማለት ይልቅ ይቅርታ መጠየቅ የወሰኑበት ምክኒያት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ቀርበው “እንኳን ሀገር ውስጥ ያሉት ውጪ ያሉትም ቢሆኑ ዛሬ ይቅርታ ከጠየቁ ከነገ ጀምሮ ነጻ ናቸው” የሚል ቃል መግባታቸው እንደሆነ ገልጾ ይግባኝ የምንልበት አማራጭም አልፎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገቡት ቃል በተቃራኒ ይቅርታው ውድቅ ተደርጓል መባሉ እንዳሳዘነው ተናግሯል፡፡ ፍጹም አክሎም “ለሲውዲናውያን የተሰጠው ዕድል ለኢትዮጵያውያን ጨርሶ ይከለከላል የሚል ዕምነት ስለሌለን የይቅርታ ጥያቄውን በድጋሚ በሽማግሌዎች በኩል እናቀርባለን” ብሏል፡፡

የአቶ መለስ ዜናዊን ሙታመት አስመልክቶ በርካታ እስረኞችን ለመፍታት መንግስት በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ያረጋገጡት ምንጮቻችን ጋዜጠኛ ውብሸትና አቶ ዘሪሁን ደብዳቤ ያልደረሳቸው ከሚፈተቱት እስረኞች ዝርዝር ውስጥ ገብተው ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

Short URL: http://www.zehabesha.com

posted by Aseged Tamene

ድምጻዊያን አምና በዳላስ ዘንድሮ በሜሪላንድ

ጥበቡ ተቀኘOptimized-DSC01841
ባለፈው አመት የአሜሪካን እትዮጵያዊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሁለት በተከፈለበት ጊዜ ብዙ አርቲስቶቻችን ጥሩ ጥሩ ዳጎስ ያለ ብር በአላሙዲን ተከፍሏቸው ዲሲ ሲመጡ ያዩትን ውርደትና ቅሌት እነሱም ብሩን የሚያፈስላቸውም የማፍያ ግሩፕ የሚረሱት አይመስለኝም:: በተቃራኒው ደግሞ ዳላስ የነበረውን ዋናውን ፌዴሬሽን ለማገዝ ጥበብን ከህዝብ ጋር ካልሆነ በምንም አይነት ለብር አንገዛም በማለት የፈጣሪ ስጦታቸውን ተጠቅመው ህዝቡን ያዝናኑት እና ከጎኑ የቆሙት ያዩትን ደስታ እና አለም ታሪክ ሁልጊዜ በመልካም ሲያነሳው ይኖራል::
የጥበብ ባለሙያዎች ከህዝብ ውጭ ሌላ ምንም ሃብት እንደሌላቸው የታወቀ ነው:: ሲዲያቸውን የሚገዛው ኮንሰርታቸውን የሚታደመው በጭብጨባ የሚያበረታታቸው ህዝብ ብቻ ነው:: አላሙዲን የሚባለው ክፉ ጦስ ኪሳቸውን በጉርሻ ሲያሳብጠው ህዝብ ምን ያደርጋል? ብለው ለሃብታሞች ብቻ ለመዝፈን መወሰናቸው በጣም የሚያሳፍርና የሚያኮላሽ ተግባር ነው:: ዛሬ እንዲህ አይነት ተራ አስተሳሰብ ይዘው የሚጓዙትን እድሜ ይስጠንና እናያቸዋለን ነገ ስራዬን አድምጡልኝ ማለታቸው አይቀርምና::
ባለፈው አመት ዳላስ ከህዝባቸው ጎን በመቆም መከፋፈልን ሳይሆን አንድነትን ሲዘምሩና ሲዘፍኑ ከነበሩት ስመ ጥር ድምጻዊያን መካከል ማህሙድ አህመድ ጸሃይ ዮሃንስ አብዱ ኪያር እና ጎሳዬ ተስፋዬ ይጠቀሳሉ:: እነዚህ ታላላቅና ዝነኛ የኪነ ጥበብ ሰዎች የሚከፈላቸው ተራ የአላሙዲን ጉርሻ ሳያዝጎመዣቸው ህዝቡን ሲያዝናኑና አደራቸውን ሲወጡ ምን ያህል ክብርና ፍቅርን እንደሚያካብቱ ማሰብ የሚከብድ አይመስለኝም:: አንዳንዶቹ ድምጻዊያን ደግሞ ከሁለቱም ኳስ አንወግንም ብለው እንዳልሰሩ የማይካድ ሃቅ ነው ዛሬ ግን ድል ከህዝቡ ጋር እንደሆነ አውቀው ተቀላቅለውናል እናከብራቸዋለን:: ለክፉ ጊዜ ባይሆኑም ከመሰሪው አላሙዲን ጋር ባለመሆናቸው አስደስቶናል::

ዘንድሮ ያለፈውን ውርደት ለመድገም ወደ ዲሲ የመጡት ድምጻዊያኖችም ዲሲ አካባቢ በነጻነት የሚዟዟሩ አይመስለኝም ምክንያቱም ግልምጫውንና ስድቡን የሚችል አቅም ያላቸው ስለማይመስለኝ ነው:: ለነገሩ እንኳን እነሱ ዋና አዘጋጆቹም ቢሆን የአበሻውን ተቃውሞ እንደ ጦር እየፈሩ እንደሚጓዙ በአይናችን እያየነው ነው:: እንደውም እዚ ጋር አንድ ወዳጄ ያጫወተኝ ትዝ አለኝ:: ባለፈው መለስ ዜናዊ እዚህ አሜሪካ በአበበ ገላው ድምጽ እንደደነገጠ በዛው ሞቷል አሁን ደግሞ አላሙዲን ይሰደብና ደንግጦ አገር ቤት ሲመለስ ይሞታል ተብሎ እነደሚቀለድ ነግሮኛል:: ይህ መቼም የሚያሳየው ሰዎቹ ምን ያህል ህዝብን አንቀጥቅጠው እንደሚገዙ ነው አንድ ሰው እነሱን ክፉ መናገር አይፈቀድለትም:: ወይኔ ያገሬ ሰው!! 
የኔ እምነት ማንም ሰው የፈለገውን የመደገፍና የመቃወም መብት እንዲሰጠው ነው ግን 30 አመት ያደረገን አንድ የኢትዮጵያውያን መገናኝ ኳሳችንን ለመበተን ለመከፋፈል እና ለወያኔ አላማ ለማዋል የሚደረገውን ጥረት እቃወማለሁ:: የሚደግፉትም አምነውበት ከሆነ ግድ የለኝም ውጤቱ እንዲህ 30 ሺ ለ ዜሮ መሆኑን ሲያውቁት ስህተት መሆኑን ሊረዱት ይገባል ባይ ነኝ::
የመደገፍና የመቃወም መብቴንም እያየሁት ያለሁት እዚህ አሜሪካ ነው እንጂ አገር ቤትማ ያለው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ይህን እድል አላገኘውም የኢህአዴግ ደጋፊ ወይም አባል ካልሆነ አይማርም ቢማርም አይመረቅም ቢመረቅም ስራ አያገኝም ቢያገኝም አያድግም…. ኢህአዴግን መቃወም ሙሉ በሙሉ ወንጀል በመሰለበት በዚህ ጊዜ የአገር ውስጡ አልበቃ ብሏቸው ውጭ አገር ያውም አሜሪካ መጥተው ያልንህን ታደርጋለህ በሚል ማን አለብኝነት ሊበትኑን እና አፋችንን ሊያዘጉ ሲፈልጉ በጣም ይገርመኛል:: ታዲያ እነዚህን በመናቅና በብዙ ሚሊዮን ዶላር ያዘጋጁትን ድግስ ባለመሄድ ኢትዮጵያዊው ሁሉ ሲቀጣቸው ማየትና የታሪክ ምስክር መሆን እንዴት ደስ ይላል?
የተቆጣን እና በአላሙዲን የክፋት ተግባር የተናደድን ህዝቦች በመተባበር የምናደርገው ነገር ሁሉ ስሜት የሚነካ ነው ባለፈው አመት ዳላስ ላይ ስታዲየሙ በህዝብ ሞልቶ ሆ ሲል በአይኔ አይቻለው አሁን ደግሞ ሜሪላንድ የመክፈቻውን ስነስርአት የነበረው ዝናብና የተፈራው ስቶርም ሳይበግረው ይሄ ሁሉ ህዝብ ባንዲራውን ለብሶና ይዞ ሲከታተለው አይቻለው:: በጣም የሚይስደንቅና በቃላት ሊገለጽ የማይችል ከባድ የአገር ፍቅር ስሜትም ተሰምቶኛል::
መቼም ፈጣሪ ለኪነጥበብ ሰዎች የሰጣቸው የተፈጥሮ ስጦታ ይገርመኛል:: ያንን ሁሉ ሺ ህዝብ እያስደሰቱ መኖር ምን ያህል መታደልን እንደሚጠይቅ መቼም ለሁሉም ግልጽ ነው:: ባለፈው አመት ዳላስ ላይ ገጣሚ የዜማ ደራሲ እና ድምጻዊው አብዱ ኪያር እየዘፈነ የተሰማኝን ስሜት በምንም መልኩ ልገልጸው አልችልም:: መላ አካላቴን ውርር አድርጎኝ እንባ እንባ ይለኝም ነበር:: ህዝቡ በሙሉ ከዘፈኑ ጋር ያሳየው የነበረው እንቅስቃሴ ሁሉ አይኔ ላይ አለ::
ያልገቡበት የለም ያልገቡበት የለም
ሙቀትና ብርዱን ችለው በዚች አለም
ይቺ ቀን ታልፋለች እያሉ በማለም
ስትጣሪ ያልመጡት ጠልተውሽ አይደለም
እናቱን ሚጠላ ካንቺ አልተፈጠረም

የከዳማ እናቱን
እንጃ አበሻነቱን…..
ዘንድሮ ደግሞ በሜሪላንድ የመክፈቻው ስነ ስርአት ላይ እነዛን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያላቸው አፉፋዎች የባህል ቡድኑ ወደ ሰማይ ሲለቋቸው ሳይ ይኸው ከባድ የአገር ፍቅር ስሜት መልሶ ነፍሴን ሲተናነቃት ይታወቀኝ ነበር:: ስሜቴን ደግሞ ይባስ ያወጣው የድምጻዊው ብርሃኑ ተዘራ(ያምቡሌ) የዘፈን ግጥም ነበር
ይሄ ሰው አማራ እረ ሚለው ማነው
ይሄ ሰው ኦሮሞ እረ ሚለው ማነው
ይሄ ሰው ከትግራይ እረ ሚለው ማነው
ይሄ ሰው ከደቡብ እረ ሚለው ማነው
ቢለያይም ቋንቛው ደማችን አንድ ነው

በናቴም አንድ ነኝ ባባቴም አንድ ነኝ
ከኢትዮጵያ አገሬ የለም የሚለየኝ….
የጥበብ ሰዎች ይህን ሁሉ የአምላክ ስጦታ ይዘው ከህዝባቸው ጎን ካልቆሙ በጣም የመሸማቀቅና የውርደት እድሜ እንደሚገፉ በታሪክ ያየነው ነው:: አላሙዲንም ወያኔም ያልፋሉ ያኔ ከህዝብ ፊት እንዴት ልትቆሙ ነው ምንስ ልትሉ ነው ማለት ይኖርብኛል ብዬ አምኛለሁ::
ይሄንን ጽሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት ኳስና ዘፈን እንዲህ የህዝቡን ልብ ማማለል ከቻሉ ፖለቲከኞቻችንም ይህንን ጥበብ ሊካኑት ይገባል ባይ ነኝ:: መልካም የፍቅር እና የደስታ ኳስ ያርግላችሁ::

ጥበቡ ተቀኘ
July 01 2013

Short URL: http://www.zehabesha.com

posted by Aseged Tamene