ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው – የሜቴክ ጉድ አይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጥጦ ከች ብሏል።

ጉደኛው ኢህአዴግ በስኳር ፋብሪካዎች ላይ ያለውን አቋም መሰረታዊ በሆነ መልኩ መቀየሩን የዛሬው የፋና ዜና ገልጿል። የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ መጓተት ያስከተለውን ምስቅልቅል ሜቴክም ሆነ ኢህአዴግ ሊደብቁት ከማይችሉበት ደረጃ ደርሷል።

የስኳር ኮርፖሬሽኑ ቃል አቀባይ እንደሚሉት ከሆነ ለግንባታዎቹ መጓተት ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው። 1ኛው የኮንትራት አስተዳደር ችግር ፣2ኛው ደግሞ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር። የነዚህን ፕሮጀክቶች ሂደት ከመጀመሪያው ጀምሮ ለተከታተልን ሰዎች እነዚህ ሁለት ምክንያቶች እጅግ በጣም አስቂኝ አናዳጅና ሲበዛ የሚያስቆጩ ናቸው።

ዛሬ ችግሩ የኮንትራት አስተዳደር ነው የሚሉት የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ከሰባት አመት በፊት የግንባታ ስራው ለሜቴክ ያለምንም ጨረታ በተሰጠበት ወቅት አሰራሩ ህገወጥ ነው ስንል ፀረ ልማት የሚል ስም ሰጥተውን ነበር። ዛሬ የኮንትራት ችግር ማነቆ ሆነብን የሚሉት የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ባለፈው አመት ፓርላማ ቀርበው ፕሮጀክቶቹ ቢጓተቱም የሜቴክ ጀነራሎችን ደፍሮ መናገር አይቻልም በማለት እንባ እየተናነቃቸው ሲናገሩ ሰምተናቸው ነበር። የኮንትራት ችግሩን የፈጠረው ሜቴክ ቢሆንም አሁንም ደፍሮ ተጠያቂ ያደረገው የለም። ይልቁንም ለሌላ ዙር ዘረፋ ይመች ዘንድ የሽርክና አሰራር የሚል ሌላ ማወናበጃ ሃሳብ ይዘው ቀርበዋል። የሚገርመው ፕሮጀክቶቹ በመንግሥት ባለቤትነት ይገነባሉ የተባልነው ካላቸው ስትራቴጂክ አገራዊ ጠቀሜታ አኳያ ወሳኝ በመሆናቸውና የግል ባለሃብቶች ብዙ ፍላጎት ያላሳዩባቸው በመሆኑ በመንግሥት መሰራት ያለባቸው ናቸው በሚል ነበር። አሁን ደግሞ ጭንቅ ውስጥ ሲገቡና ማጣፊያው ሲያጥራቸው የግል ባለሃብቶች ሽርክና አስፈላጊ ነው ተባለ። አጃኢብ እኮ ነው!!!!

ሌላው ገራሚው ነገር ፕሮጀክቶቹ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ገጥሟቸዋል መባሉ ነው። ልብ በሉ ይህንን የሚሉት እስካሁን ለፕሮጀክቶቹ ተብሎ 77 ቢሊዮን ብር የሚበልጥ ገንዘብ ወጪ መሆኑን ሳይክዱ ነው። ይህ ሁሉ ብር የት ገባ የሚለውን ጥያቄ እኛ እንጂ እነሱ መጠየቅም ማንሳትም አይፈልጉም። ባለፈው አመት እኮ 25% እንኳን አፈፃፀም ላላሳየ ፕሮጀክት ሜቴክ 96% ክፍያ መውሰዱን ራሳቸው የኮርፖሬሽኑ ሰዎች ሲያወሩ ነበር። ያው እነሱ ቢረሱትም እኛ እናስታውሳለን። ከዚህ በፊት ከቻይናና ከሌሎች የተወሰደው ብድር የት እንደገባ ሳይናገሩ የመክፈያው ጊዜ ስለደረሰ ሽርክና ያስፈልገናል ሲሉ ትንሽ እንኳ ሽክክ አይላቸውም።

ለማንኛውም እንደዚህ ጭምልቅልቁ በወጣ ፕሮጀክት ውስጥ ሽርክና ለመመስረት የሚፈልገውን ባለሃብት ለማየት ጓጉቻለሁ።

እሸቱ

ሰበር ዜና! ቤታቸው በክረምት የሚፈርስባቸው ወገኖች በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እናደርጋለን አሉ፡፡

ሰሞኑን በቃሊቲ ገብርኤል ወረዳ.07 ቀበሌ10/11-ልዩ ስሙ ጨሬ ሰፈር በመባል የሚታወቀው ኣካባቢ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ በአፍራሽ ግብረ ሃይል ምልክት ተደርጎባቸው በሁለት ቀን አፍረስው ካልጨረሱ በዶዘር ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው፡፡ በሁኔታው የተቆጡ ነዋሪዎች መንግስት በዜጎቹ የሚፈጽመው ጭካኔ እንግዲህ በቃ,ሞት ተፈርቶ ውርደት መቀበል አንችልም እያሉ ይገኛል፡፡ በዚህ ክረምት የት እንሄዳለን በማለት የተቆጡ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡም እንዳሰብ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ አንድ ነዋሪ ሲናገሩ በቅርቡ ወረገኑ በርካታ ሰዎች ሜዳ ላይ ወደቁ በን/ስ/ላ ቀበሌ01 ቀርሳ ኮንቶማ ማንጎ ከ20 ሺህ በላይ ቤቶች አፈረሱ ሕጻናት አረጋዊያን ያለ መጠለያ በሜዳ ላይ በዚህ ክረምት ለጎርፍና ለጅብ ቀለብ ተሰጥተዋል፡፡ መንግስት የሌለው ሕዝብ መሆናችን በደንብ አይተናል፡፡ እነሱ ከበርሃ አዲስ አበባ በኮንጎ መጥተው ባለ ፎቅ ሲሆኑ እኛ ተወልደን ባደግንበት ምድር እንዴት ቤት እናጣለን? በማለት በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ከዚህ መኖር ሞታችን ይመረጣል የሚሉት ሌላው ነዋሪ ከዚህ በላይ ሞት ምን አለ? ሁል ጊዜ ቤታችን አፈረሱት በማለት ማልቀስ አንፈልግም የጎንደር ሕዝብ አሳይቶናል በቃ..ሰልፍ እንወጣለን መንዱን በተቃውሞ ይዘጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እነ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ያለቀጠሮአቸው ተገደው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ፍርድ ቤቱ የተክሳሽኦችን የመክላክያ ምስክሮች በምን ጭብጥ ላይ እንደሚያስመሰክሩ ከምስክሮቹ ቀጠሮ አስቀድሞ እንዲገለፅ ጠይቃል።
–ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ እና ማረሚያ ቤት ህገወጥ ጫናና ወከባ እየፈጠሩብን ነው ብለዋል የክስ መዝገባቸው በከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት
በመታየት ላይ የሚገኘው 4 ተከሳሾች ብርሀኑ ተ/ያሬድ ፤እየሩሳሌም ተስፋው፤ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ
ብይን በሰጠባቸው ጉዳአዮእ ላይ የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ ከግንቦት 30-ሰኔ 8 ክትሮ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግንቦት 23 ቀን ያለቀጠሮዋቸው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጋል ተከሳሾቹ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሌላቸው ለማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች የገለፁ ቢሆንም በማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ሃላፊዎች
ወከባና ግፍተራ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችላል። ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ከቀረቡም በኃላም ለፍርድ ቤቱ ይህንን ያስረዱ ሲሆን የፍርድ ቤቱም ዳኛም “ዛሬ ቀጠሮ ባይኖራችሁም ፍርድ ቤቱ ማጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ነው የጠራናችሁ”በማለት የተከሳሾቹ መከላከያ ምስክሮች የሚመሰክሩበትን ጭብጥ ተከሳሾቹ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ
እንዲያስረዱ ጠይቀዋል ተከሳሾቹም ምስክሮቻቸው የሚመሰክሩበት ጭብጥ ምስክርነት በሚሰጥበት እለት እንጂ ምስክሮቹ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ለፍርድ ቤቱ የማሳወቅ ህጋዊ ግዴታ የሌለባቸው መሆኑን የገለፀ ሲሆን ዛሬ በፍርድ ቤቱ እየተጠየቁ ያለው ቅድመ ሁኔታ ግን ህጋዊ መሰረት የሌለው እና ፍርድ ቤቱም የሌሎች የገዢው ፓርቲ የአፈና መዋቅርት ተፅእኖ እንዳረፈበት የሚያሳይ ነው ብለዋል. ተከሳሾቹ አያይዘው እንደገለፁትም ለምስክሮች የተዘጋጀው መጥሪያ በፍርድ ቤቱ ዳኛ ተፈርሞ ለምስክሮቻቸው እንዲሰጥ ማረሚያ በት ለሚገኙ ተከሳሾች ከደረሳቸው በሀላ በድጋሚ“በፍርድ ቤት ትእዛዝ ነው” በሚል ምክንያት መጥሪያዎቹን
የተነጠቁ ሲሆን በማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች በኩልም መከላከያ ምስክሮቻቸውን በተመለከተ በተለይም የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለምስክርነት ማስጠራታቸውን ተከትሎ ማስፈራርያና ወከባ እየደረሰባቸው ነው በመጨረሻም ተከሳሾቹ የምስክሮቻቸውን ጭብጥ ለፍርድ ቤቱ እንደማያሳውቁ በአፅንኦት የገለፁ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ዳኛ “ከአነጋገራችሁ የምስክሮቹን ጭብጥ ለመረዳት ጭለናል በመሆኑም ይህኑኑ ጉዳይ መርምረን ለግንቦት 30-2008 ብይን እንሰጥበታለነረ “ በማለት ተከሳሾቹን በተጠቀሰው ቀን እንዲርቡ ትእዛዝ ሰጥተዋል።

አቦይ ፀሀዬ በህወሀት ሲብሰባ ላይ ከተናገሩት የወልቃይት ህዝብ ጦርነት ሊከፍትብን ይችላል

” የወልቃይት ጉዳይ ለእኛ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ጥያቄያቸውም ህገ-መንግስታዊ ሽፋን ያለው በመሆኑና የተለያዩ ሚዲያዎች ሽፋን ስለሰጡት በቀላሉ ለማጥቃት ቢያስቸግረንም የስልክ ኔትዎርክና የመረጃ መረቡን በመዝጋት የሚቻለንን ያህል እይደረግንን ነው። ህዝቡም በጣም እልኸኛና ቆራጥ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ህጋዊ የፌደረሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ በትዕግስት መስማት ስለፈ ለገ ነው እንጂ ውሳኔው አይሆንም ከተባለ በቀላሉ ወደ ጦርነት ገብቶ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያደርስብን የሚችል ህዝብ ስለሆነ የፌደርሽኑ ውሳኔ በማዘግየት ወደ ሗላ በሳል ስራዎችን ከመስራት በቀር ምንም ልናደርገው አንችልም። ነገር ግን ይህ ኦፕሬሽን በወልቃይት ተፈጻሚ ሲሆን በዛ አካባቢ ያሉ ሙስሊምና ክርስቲያኖች በመተማመን ስለሚኖር በህዝቡ መከፋፈል ለመፍጠር መሞከር ኪሳራ እንጂ ውጤት አያመጣም፤ ግን ደግሞ የአካባቢው ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ኦፕሬሽን ለየት ባለ መልኩ ነው ባስቸኳይ መፈጸም ያለበት።
ህዝቡ በቀላሉ የመባነን ባህሪ ስላለው በህዝቡ እማኝነት እንዲኖረው ለማድረግ አካባቢው ክርስቲያን የበዛበት እንደመሆኑ መጠን የታጠቁ አክራሪ እስላሞች ከሰሜን ሱዳን እንዲዘልቁ በማድረግ የድንበር ችግር ያለባቸው በማስመሰል እዛ በአከባቢው ያሉ የትግራይ ተወላጆችና ባለ የመከላከያ እዝ ተመጣጣኝ ስትራተጂያዊ ዋጋ በመክፈልና የሚዲያ ሽፋን በማሰጠት ሌላ ቋሚ መፍትሔ እስኪገኝለት ድረስ ጉዳዩ እንዲበርድ ማድረግ ይቻላል። የህወሃት መቃብር የተቆፈረው በመቀሌ ሳይሆን በወልቃይት እንደመሆኑ መጠን ከሁኔታው አንገብጋቢነት አንጻር ይህ የምናወራው ኦፕሬሽን ባስቸኳይ መፈጸም ያለበት በዚህ መልኩ ከሆነ ፍጹም አመርቂ የሆነ ግን ደግሞ ያለተባነነበት ሁኔታውን ያገናዘበ ኦፕሬሽን ተካሔደ ማለት ነው።”

አሰግድ ታመነ

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን ለቀቁ::

ፎርቹን ጋዜጣ እንዳስነበበን በ2001 በሟች መለስ ዜናዊ የተሾሙት አቶ ተገኔ በጤና እክል ምክንያት ሥራቸውን ሊለቁ መወሰናቸውን ገለጹ ቢባልም በመልካም አስተዳደር ላይ የተንሰራፋው ችግር አለመፈታት ከውሳኔ አንዳደረሳችው ጉዳዩን በቅርብተ የሚያውቁ ገልጸዋል::

ሥራቸውን የለቀቁት የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ ከታኅሳስ 3-5 የህወሓት ሠራዊት በጋምቤላ ያደረሰውን ጭፍጨፋንዲያጣራ በተመረጠው ኮሚቴ ውስጥ ጸሐፊ ነበሩ::
በወቅቱ 416 የአኙዋክ ብሔር ተወላጆች ቢገደሉም አቶ ተገኔ የተገደሉት 50 ሲሆኑ መንግስት ያልተገባ ኃይል አልተጠቀመም በማለት ከፈረሙት ዳኞች መካከል አንዱ ናቸው። ከ3000-5000 የሚሆኑት ቤት-ንብረታቸውን ጥለው ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ደቡብ ሱዳን መሸሻቸው ይታወሳል::

አቶ ተገኔ ከቀድሞው የጠቅላይ ፍርድቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ህወሓቱ መንበረፀሐይ ታደሰ እና አሁን ምክትል ከሆኑት ሌላኛው ህወሓት መድህን ኪሮስ እንዲሁም ከመጀመርያ ደረጃ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት ደሳለኝ በርሄ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንዳላቸው ይነገራል። አቶ ተገኔ በምርጫ ቦርድ ውስጥ ከእነ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ጋር ሠርተዋል::
በመለስ የጠቅላይ ፍርድቤቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ሲመረጡም ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ታይቶ እንደነበር በቅርበት የሚያውቋቸው ሰዎች ይገልጻሉ::
አሁን ምን ተገኘ?

 
Aseged Tamene
%d bloggers like this: