በዶ/ር አቢይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳ ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቶላቸው እንደነበር ተናገሩ

በዶ/ር አቢይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳ ላይ የወጣው የእስር ትእዛዝ ጠ/ምኒስትሩ ቃለ መሀላ ከመፈጸማቸው አምስት ቀናት በፊት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ህወሃት በጄኔራል ሳሞራ የኑስ ግንባር ቀደም መሪነት እነ አቶ ለማንና ዶ/ር አቢይን በወታደራዊ ኋይል አስገድዶ ዝም ለማሰኘት ሞክሮ እንደከሸፈበት ከዚህ በፊት ገልጸናል (የመጨረሻ የኢህአዴግን ሊቀመንበር ለመምረጥ በሚራኮቱበት ደረጃና እነ አባይ ጸሃዬ ሃይላንድ ውሃ እየተወራወሩ ልዳባደብ ብለው የተፍጨረጨሩበት ወቅት ማለት ነው)

ይህን ወታደራዊ አፈናቸው እንደከሸፋባቸው ሌላ ዙር የእስር ትእዛዝ በእነ ዶ/ር አቢይና አቶ ለማ ላይ መውጣቱ ለእኔ ባያስገርምም ይህን ክስተት ጠ/ምኒስትሩ ዛሬ ይፋ ማድረጋቸውና ብሎም ይህንን ትእዛዝ አስተላላፊዎችን ምንም ሳያደርጉ ባሉበት ስራና ኋላፊነት መተዋቸው (ለጊዜውም ቢሆን ) የገረመኝ ጉዳይ ሆኗል፡፡

እነሱ ለእስር ሲያዘጋጁት ዶ/ሩ ግን ወደ ቤተ መንግስት -ይህ በዘመነ ወያኔ እማይታሰብ ግን የሆነ የአምላክ ስራ እንጂ እነ ዶ/ር አቢይ ጥንካሬና እስማርትነት ብቻውን በቂ ሆኖ ይህን ውጤት አያሳየንም፡፡

ብቻ የዚህ ሁሉ ልዩ ክስተት መጨረሻውን ለማየት ናፍቄያለሁ- ምን ይወጣው ይሆን ያስብላል!!

የአማራ ወጣቶችን የሚያስገደሉ 72 ባለሥልጣናትና ደኅንነቶች ተለይተው ታወቁ!

በአሁኑ ስዓት በመላው የአማራ ክልል እየተቀጣጠለ ያለውን አመፅ እና ከግብ እንዳይደረስ ሕወሓት አዋቅሮ እያሰራቸው የሚገኙ የክልሉ 72 ባለስልጣናት እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ከማነደር ኢሳያስ ገ/ ኪዳን ከብሄራዊ ደህንነት መረጃ

2. አቶ ይርሳው ታምሬ

3. አቶ ብናልፍ አንዷለም

4. አቶ አለምነው መኮንን

5. ዶ/ር ተሾመ ዋለ

6. አቶ ፍርዴ ቸሩ

7. አቶ አወቀ እንየው

8. አቶ አየልኝ ሙሉዓለም

9. አቶ አየነው በላይ

10. አቶ ደሴ አሰሜ

11. አቶ ዘመነ ፀሃይ

12. አቶ ንጉሱ ጥላሁን

13. አቶ ተስፋየ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ገበያልማት ቢሮ ኃላፊ

14. አቶ ፈንታ ደጀን 15. አቶ ደሳለኝ ወዳጀ 16. አቶ በላይ በጤና ቢሮ የወባ መከላከል የስራ ሂደት መሪ 17. አቶ ሃብቴ በትምህርት ቢሮ የአይሲቲ ክፍል ኃላፊ 18. አቶ ማማሩ ጽድቁ 19. ም/ኮሚሽነር ደስየ ደጀን 20. አቶ መኮንን የለውምወሰን የአብቁተ ዋና ዳይሬክተር 21. አቶ መላኩ አለበል የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ 22. አቶ ምስራቅ የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ 23. አቶ ምትኩ የጥረት ኮርፖሬት ምክትል ስራ አስፈፃሚ 24. አቶ ስዩም አዳሙ 25. አቶ ሙሉጌታ ደባሱ 26. አቶ ስዩም አድማሱ 27. አቶ ተፈራ ፈይሳ 28. አቶ ሺፈራው ግብርና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ 29. አቶ ተስፋየ የልህቀት ማዕከል ኃላፊ 30. አቶ ቴዎድሮስ የቀድሞ ጣና ሃይቅ ትራንስፖርት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረ አሁን መቅደላ ኮንስትራክሽን 31. አቶ ዘላለም ህብስቱ 32. አቶ የማነ ነጋሽ 33. አቶ ጌትነት የገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ 34. አቶ ስለሺ ተመስገን 35. አቶ ዘላለም የግብይት ልማት የስራ ሂደት መሪ 36. አቶ ዳንኤል የሆቴሎች ማህበር ፕሬዚደንት 37. አቶ ኃ/ኢየሱስ ፍላቴ 38. አቶ ብርሃኑ የባህል፣ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ 39. አቶ ላቀ ጥላየ 40. አቶ ሙሃመድ አልማ ምክ/ስራ አስፈፃሚ 41. አቶ አለማየሁ ሞገስ 42. አቶ አጉማስ የከተሞች ልማትና ግንባታ አክስዮን ማህበር ኃላፊ 43. አቶ ደመቀ የከተሞች ልማትና ግንባታ አክስዮን ማህበር ባለሙያ 44. አቶ አሻግሬ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የህፃናት የስራ ሂደት መሪ 45. ዶ/ር ፋንታሁን መንግስቱ 46. አቶ አየለ አናውጤ 47. አቶ ሃብታሙ የርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮቶኮል 48. ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሄር 49. ወ/ሮ አበራሽ በክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረች ነባር ታጋይ 50. አቶ ፈለቀ ተሰማ 51. አቶ ጌታ ኪዳነ ማርያም 52. አቶ ገሰሰው ግብርና ሜካናይዜሽን ተመራማሪ 53. አቶ ዳኜ በጤና ቢሮ የሃይጅንና ሳኒቴሽን ባለሙያ 54. አቶ ፈንታው አዋየው 55. ወ/ሮ ዝማም አሰፋ 56. ዶ/ር አምላኩ አስረስ 57. አቶ ደጀኔ ምንልኩ 58. ወ/ሮ ትልቅ ሰው ይታያል 59. አቶ ላቀ አያሌው 60. አቶ ባይህ ጥሩነህ 61. አቶ ጥላሁን የክልል ም/ቤት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ 62. አቶ ፍስሃ ወ/ሰንበት 63. አቶ ጌታቸው በት/ት ቢሮ የፈተና ኤክስፐርት 64. ዶ/ር ይበልጣል ቢያድጌ 65. አቶ አቃኔ አድማሱ 66. አቶ የኔነህ ስመኝ 67. ኮማንደር ሰይድ የፖሊስ ኮሚሽን 68. አቶ አስናቀ በኢት. ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ኃላፊ 69. አቶ ሙሉጌታ ከግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት 70. አቶ ባየ ከልህቀት ማዕከል ኃላፊ 71. አቶ አምባው አስረስ

72. ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ 

የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት “አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት አድማ መጀመራቸውን ተሰማ

ፖሊሶቹ አድማውን የሚያደርጉት ቢሮአቸው ውስጥ ያለ ስራ በመቀመጥ መሆኑን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። የአድማው መነሻ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንደማይሰጣቸው መታወቁን ተከትሎ ነው። የከተማው አስተዳደር የልዩ ሃይል እና የፖሊስ አባላት መሬት እንደሚሰጣቸው ከገለጸ በሁዋላ፣ ረዳት ኮሚሽነር ደስዬ ደጀኔ ለከተማ አስተዳደሩ ትዕዛዝ በመስጠት ቦታ እንዳናገኝ አስከልክሎናል በሚል አድማ መጀመራቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

አድማውን የሚያስተባብሩ አካላት “ እኛ መሬት ለማግኘት ስንል ግደሉ ስንባል መግደል?” አለብን ወይ በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ “ መሬት ለማግኘት ስንል ህዝብን አንጨፈጭፈም” የሚል አቋም በመያዛቸው ከአዛዦች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ችግሩን በሽምግልና ለመፍታት በሚል የተወሰኑ ሰዎች እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

የክልሉ ፖሊሶች ከዚህ ቀደም የህወሃት የበላይነት ይብቃ በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር መዘጋቡ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ የመጀመሪያው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደታወጀ፣ የክልሉን ፖሊስ እንደገና የማደራጀት ስራ ተሰርቷል። የህወሃትን የበላይነት ይቃወማሉ የተባሉ የፖሊስ አዛዦች ከስራ እንዲባረሩ ወይም እንዲታሰሩ ተደርጓል።

በኢአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ የስራ አስፈጻሚ አባል ያልሆኑ መገኘት አነጋጋሪ ነው ተባለ

ባሁን ሰሃት የወያኔ ኢአደግ ስርሀትን ለማስቀጠል ስራ አስፈጻሚዉ ስብሰባ ላይ መጠመዳቸው ይታወቃል።
ይህ ስራ አስፈጻሚ  ነባር የሆኑትን ባሁን ሰሃት ግን ከስራ አስፈጻሚነት የተነሱት የህወሀት ባለስልጣኖችና ሌሎችም መገኘት የህወሀትን ጭንቀትና የቀድሞው ተሰሚነቱን ማጣቱ አስቆጭቶት ያንን ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑ ተነግራል።
ህወሀት ከገባበት አጣብቂኝ ያወጡኛል ያላቸውን በስብሰባው ላይ መገኘት የማይገባቸው እንደ በረከትና አባይ ፀዐዬ የመሳሰሉትን አስቀምጦ ውጥረት በተሞላው መልኩ ጭቅጭቁ ተጣጡፋል የተለመደው ማስፈራርያ በኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ይሰነዘራል ።

ህወሓቶች የመጣው ይምጣ እያሉ ያስፈራራሉ። ኦህዴድን በተደጋጋሚ ይከሳሉ። ብአዴንንም አልፎ አልፎ ያነሳሉ። በህወሃቶች ዘንድ ኦሮሚያ ውስጥ ያለውን ምስቅልቅል ሁኔታ ኦህዴድን ተጠያቂ እያደረጉ ተናግረዋል። አባይ ጸሃዬ እና ደብረጺዮን በዋናነት ኦህዴድ ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል።

አቶ በረከት ስምዖን አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አያስፈልግም መጀመሪያ መከላከያ አገሪቱን ያረጋጋና ከዛ ብኋላ ይመረጣል እያለ ነው። በእሱ ስሌት መሰረት ወታደሩ እዛም እዛም የሚታዩትን ተቃውሞዎች ደብዛቸውን ካጠፋ ብኋላ ለምን ብሎ የሚጠይቅ ማንም ስለሌለ የዛንጊዜ የፈለግነው ጠቅላይ ሚኒስተር መሰየም እንችላለን ከሚል ነው፡፡

በረከት ዶ/ር አቢይ ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን የለበትም የሚል አቋም ይዞ በስብሰባው እና ከስብሰባው በኋላ ባለው የእረፍት ጊዜ ሌሎችን ሎቢ ሲያደርግ ተስተውሏል። የተወሰኑ የህወሃት አባላት ደብረጺዮን ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁን እያሉ ነው። ይህ የማይሆን ከሆነ ምክትሉ ከኛ ይሁን በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል። ጌታቸው አሰፋ አሁን ደብረጺዮንን ጠቅላይ ሚኒስተር ማድረግ አሁን ካለው የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ፈጽሞ መሆን የሌለበት ነው በማለት አቋሙን ገልጿል። በህወሃት መካከል ቀጣይ ማን ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ ሙሉ በሙሉ አንድ አይነት አቋም እንደሌለ ታይቷል::

እስካሁን ያለውን የሃገሪቱ ሁኔታም እየገመገሙ ነው፡፡ በረከተ በስብሰባው ላይ ዋና ተዋናይ ሆኗል።ስብሰባው እንደቀጠለ ነው።

 

በእስር ላይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድረሱልን እያሉ ነው

ቦረና አበራ፣ ወየቻ ታምሩ፣ ወሰኑ ገረመው፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ፣ ገዳ ገመቹ፣ እዮብ ሙሊሳ እና ሳሎ ነጋሳ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን በሚከታተሉበት ወቅት ለእስር ተዳርገዋል።

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ምክንያት በነበረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ አራት ወራት ከታሰሩ በኋላ “ወንጀሉ በተፈፀመበት አካባቢ ይዳኙ” ተብሎ ሚያዝያ 28/2008 ወደ ዲላ ከተማ ተዛውረዋል። ሀምሌ 7/2008 ዓም ወደ ሀዋሳ ተዛውረው በእስር ላይ ይገኛሉ።

የካቲት 7/2010 በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ቦረና አበራ በነፃ ሲሰናበት፣ ቀሪዎቹ እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል። ተከላከሉ ከተባሉት 6 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ሳሎ ነጋሳ (4ኛ አመት ተማሪ የነበረ) ብቻ “እከላከላለሁ” ሲል ወየቻ ታምሩ (የ3ኛ አመት ተማሪ)፣ ወሰኑ ገረመው (3ኛ አመት)፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ (3ኛ አመት)፣ ገዳ ገመቹ (3ኛ አመት) “አንከላከልም” ብለዋል።

ተከሳሾቹ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው የታሰሩ በመሆናቸው ችግር ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። “የሚረዳን የለም፣ ሚዲያም እያስታወሰን አይደለም” ሲሉም ገልፀዋል።በጌታቸው ሺፈራው