አርባምንጭ የነጭ ሳር ፓርክ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ከ20 ያላነሱ የመንግስት ታጣቂዎች ተገደሉ

ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት 20 የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል የአካባቢው ወታደራዊ አዛዥም ይገኝበታል። የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ሰአታት የቀዬ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ህክምና ተወስደዋል።
የመንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ የተንቀሳቀሱ ሃይሎች በሞያሌ በኩል ወደ አርባምንጭ ጫካ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ገልጿል። መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉና የተገደሉ ታጣቂዎች መኖራቸውን ቢገልጽም ፣ በአሃዝ ከመግለጽ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድንገተኛ ጥቃቱን የፈጸሙት የታጠቁ ሃይሎች፣ ጥቃቱን ካደረሱ በሁዋላ ከአካባቢው ተሰውራል። ይህን ተከትሎም ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የከተማው ሰዎች እየታፈሱ ተወስደዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃቱን እንደፈጸመ በከተማው እየተወራ ቢሆንም፣ ንቅናቄው እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

Gudish Weyane's photo.

በጎንደር ከተማ ከተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ጦር ሁለት ኃይል አመራሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ገዱ፡፡

በጎንደር ከተማ ከተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ጦር ሁለት ኃይል አመራሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ከዱ፡፡
አገዛዙን በመቃወም ድንገት ከጦር ሰፈር የተሰወሩት ሳጅን ጥበቡ ስብሃት እና ሳጅን አበበ ረዳይ የተሰኙ ኃይል አመራሮች ናቸው፡፡
የስማዳ ተወላጅ የሆነው ሳጅን ጥበቡ ስብሃት መጋቢት 24 2008 ዓ.ም ከነሙሉ ትጥቁ ስርዓቱን ሲከዳ አለማጣ ተወልዶ ያደገው ሳጅን አበበ ረዳይ ደግሞ ከሳምንት በኋላ ማለትም መጋቢት 30 2008 ዓ.ም የሳጅን ጥበቡ ስብሃትን ፈለግ ተከትሏል፡፡

 

በአርማጭሆ እና በሁመራ ዙሪያ የተሰማራዉን የ24ተኛ ክፍለ ጦር እየከዱ ነው

በአርማጭሆ እና በሁመራ ዙሪያ የተሰማራዉን የ24ተኛ ክፍለ ጦር እንዲያግዝ ከሸዋሮቢት ተንቀሳቀሶ በስብጥር የተዋሃደዉ የመከላከያ አብቫላት እየከዱ ወደ ጎረቤት ሐገር በመግባት ላይ ናቸዉ።
አዲስና ልምድ አልባ የሆነዉ ወጣት ወደ ግንባር እንዲሰማራ በማድረግ የጥይት ማብረጃ እያደረገዉ ነዉ የሚሉት ወገኖቻችን እጃቸዉን ለአማጺያን በመስጠትና ሾልኮ በመዉጣት የህዝብ አለኝታነታቸዉን አስመስክረዋል።
ወያኔ ከዚህ ቀደ 43ተኛ ክፍለ ጦርን ከሶማሌያ በማምጣት አዘዞ ላይ አስቀምጦት የነበረ ሲሆን ሰራዊቱ በመክዳት ምክንያት ተመናምኖ ስለነበር አፍርሶ ወደ ምስራቅ እዝ በመዉሰድ ሁለተኛ ብርጌድን ያቋቋመ መሆኑ ይታወቃል!! ያም ሆኖ የሁለጠኛ ብርጌድ ወታደራዊ አመራሮችና አስተኳሾች ባጠቃላይ በመኮብለላቸዉ ብርጌዱ እንደገና እንዲፈርስና ወደ ሌሎች እንዲጠቃለል መመሪያ መዉረዱን መረጃዎቻችን ጠቁመዋል።
ባሳለፍነዉ ሳምንት ከ24ተኛ ክፍለ ጦር ጋር የተዋጋ ሐላፊነቱን ያልወሰደ የነጻነት ሐይል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የሁመራ አካባቢ ወታደራዊ ዘመቻ ስምሪቱ ለመከላከያ አዛዙ በላከዉ መልእክት ለማወቅ ተችሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )

በወልቃይት ጸገዴ ጉዳይ የፌደሬሽን ምክር ቤት አስገራሚ ምላሽ

በወልቃይት ጸገዴ ህዝብ ውክልና ተሰጥቷቸው በሁለት የተለያዩ ወቅቶች ለፌደሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን በማቅረብ የህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብት ተከብሮ ለማንነታቸው እውቅና እንዲሰጥ ለጠየቁ ተወካዩች ምክር ቤቱ በሰጠው ምላሽ ‹‹እንዲህ አይነት ጥያቄዎች በመጀመሪያ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የመስተዳድር እርከኖች ቀርበው መፍትሔ የሚሰጣቸው ሲሆን ቀጥታ ለምክር ቤቱ የማይቀርቡ በመሆናቸው በአቤቱታ አቅራቢዎች የቀረበው የማንነትና ሌሎች ተያያዥ የመብት ጥያቄዎች  በክልሉ መፍትሔ እንዲሰጠው የመለስን መሆኑን እናስታውቃለን››ማለቱን ከምክር ቤቱ የወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ የተቋቋመው እንዲህ አይነት ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎችን በመመርመር አቤቱታዎቹን በመከታተልና የህገ መንግስት ትርጓሜ በመስጠት ጥያቄዎቹ አግባብ ባላቸው ደረጃዎች የሚመረመሩበትንና እልባት የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ቢሆንም ምክር ቤቱ ጉዳዩን የማንነታችን ተጨፍልቆ የሌሎችን ማንነት እንድንለብስ አድርገውናል በማለት ወደሚከሷቸው መስተዳድሮች ዘንድ ሄዳችሁ ጉዳያችሁን አሳዩ ማለቱ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ከምክር ቤቱ የወጣውን ደብዳቤ አባሪ በማድረጋችንም ይመለከቱት ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡

ሰበር መረጃ የኮንሶ ህዝብ ለነፃነቱ የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ፍርሃት ውስት የከተታቸው የህወሓት ቅጥረኞች አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ

የኮንሶ ህዝብ ለነፃነቱና ለዲሞክራሲ የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ፍርሃት ውስት የከተታቸው የህወሓት ቅጥረኞች የሆኑት የደህዴን ካድሬዎች በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ነበር። የኮንሶ ህዝብ አስራ ሁለት የጎሳ መሪዎችን ጨምሮ ከ’60000 በላይ (በግምት ከበፊቱ የበለጠ) ህዝብ የተሳተፈበት የዛሬው ህዝባዊ ስብሰባ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለኮሚሽነር ለማ ገዙማ ማንሳቱን ከኮንሶ ያገነኛቸው መረጃዎች ያመላክታሉ። ከ’#KonsoProtests ጋር በተያያዘ :
➤ የታሰሩ ግለሰቦች በአስቸኳይ እንዲፈቱ
➤ የቆሰሉትና የተደበደቡትን በአስቸኳይ እንዲታከሙ
➤ ለሞቱት ግለሰቦች ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው
➤ ልዩ ሀይል የተባለው ሰው በላ ሰራዊት ከኮንሶ በአስቸኳይ እንዲወጣ
➤ ፍስሀ ጋረደው ፡ ዳዊት ኩሰያ፡ ኩሴ ፒሴ፡ ጋሻው፤ ኩስያ እና ተባባርዎቻቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ
➤ የኮንሶ ህዝብ ዋናና መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቄ ፤ ልዩ ወረዳ ሳይሆን በዞን ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ
የኮንሶ ህዝብ ከላይ የተጠቀሱት የነፃነት ፣ የፍትህ ፣ የእኩልነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እስካተመለሱት ድረስ በማንናቸውም ማማለያዎች እንደማይታለልና የአንባገነን አገዛዙን ጥቃቶችን ፈርቶ ከትግሉ ወደ ኋላ እንደማያፈገፍግ በስብሰባው ላይ አሳውቋል።
ድል ለኮንሶ ህዝብ ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

%d bloggers like this: