ኢትዮጵያ ከግብፅ የሚገነቡ የመድሃኒት ምርቶችን አገደች

በመንገባት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ፕሮጄክት ከግብፅ ጋር አለመግባባት ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያው ከግብፅ የሚገነቡ የመድሃኒት ምርቶችን አገደች።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በ11 ኩባንያዎች ላይ የተጣለው እገዳ የሃገሪቱን መስፈርት የማያሟሉ ሆነው ስላልተገኙ ነው ሲል ምላሽን መስጠቱን አል-ማስሪ የተሰኘ የግብፅ ጋዜጣ ዘግቧል።

በቅርቡ ወደ ግብጽ በመጓዝ በ13 የሃገሪቱ የመድሃኒት አምራት ፋብሪካዎች ላይ ጉብኝትን ያደረጉ የጤና ጥበቃ ተወካዮች 11ዱ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሆነው የተገኙ ናቸው ሲሉ በእገዳው ዙሪያ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል።

ይሁንና የመድሃኒት አምራቾችና ላኪዎች ምክር ቤት ሃላፊ የሆኑት ማጅድ ጂዮርጅ ኢትዮጵያ እገዳ የጣለችባቸው ኩባንያዎች ከ15 ሃገራት መድሃኒትን የሚያቀርቡ ተቋማት እንደሆኑ ለጋዜጣው ገልጸዋል።

ከኢትዮጵያ በኩል የቀረቡ ምክንያቶች በአግባቡ ለመመርመር የምክር ቤቱ አባላትን ጨምሮ በግብፅ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደርን በማሳተፍ በጉዳዩ ዙሪያ አስቸኳይ ምክክር እንደሚካሄድ ሃላፊው አስታውቀዋል።

በርካታ የግብፅ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች የተለያዩ መድሃኒቶችን ለኢትዮጵያ ከአሰር አመት በላይ ሲያቀርቡ መቆየታቸው የታወቅ ሲሆን ሁለቱ ሃገራት በአባይ ግድብ ዙሪያ ያላቸው ልዩነት መፍትሄን ሳያገኝ በሌላ ጉዳይ አለመግባባታቸው ያላቸው ልዩነት ያሰፋዋል ተብሎ ተሰግቷል።

ኢትዮጵያ ከግብጽ ከምታስገባው መድሃኒት በተጨማሪ በርካታ የሃገሪቱ ኩባንያዎች መድሃኒትን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራ ላይ በኢትዮጵያ ተሰማርተው እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

እንደፈረንጆቹ 2013 ዓም ኢትዮጵያና ግብፅ የንግድ ልውውጣቸው ወደ 140 ሚሊዮን አካባቢ ደርሶ የነበር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ድርሻ ወደ 30 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ብቻ መሆኑን ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ባለፈው ወር የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ስምምነትን አድርገው የነበሩት ሁለቱ ሃገራት የንግድ ልውውጡ ገቢን ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር ለማድረስ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ስጋን፣ ጥራጥሬን እንዲሁም የቁም እንስሳትና ቡናን ወደ ግብፅ የምትልክ ሲሆን ግብፅ በበኩሏ የተለያዩ መድሃኒቶችንና ኬሚካሎችን ለኢትዮጵያ በማቅረብ ላይ ትገኛለች።

በ11ዱ የመድሃኒት ኩባንያዎች ላይ የተጣለው እገዳ እስመቼ ድረስ የሚቆይ እንደሆ የተገለጸ ነገር የለም።

በኤርትራ ምድር በምርኮ ተይዘው የሚገኙ የወያኔ ወታደሮች አርበኞች ግንቦት ለመቀላቀል እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

በቅርቡ በፆረና ግንባር ወያኔ በቆሰቆሰው ጦርነት በኤርትራ ወታደሮች ተማርከው በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያወታደሮች የኦሮሞና የአማራ እንዲሁም ከተለያዩ ብሄሮች የተውጣጡት ወደዚህ ጦርነት የገቡት በትግሬ የጦር አዛዦች አስገዳጅነት መሆኑን በመናገር

የኤርትራ መንግሥት ይቅርታ የሚያደርግላቸው ከሆነ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ዘረኛውን ገዳዩን የወያኔ ስርዓት ለመዋጋት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ከኤርትራ ምድር የወጣው መረጃ በታማኝ ምንጮቻችን በኩል ሊረጋገጥ ችሎዋል።

የጦር ምርኮኞቹን ጉዳይ አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ በአቶ ጌታቸው ረዳ‬ በኩል የተሰጠው ምላሽ

<<ምንም የተማረከ ወታደር የለም እንዲያው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እስከ 200 ሜትር ድረስ ለትንኮሳ የመጡትን የኤርትራን ወታደሮች እያሳደደ አጥቅቷል>>

የሚል እንደነበር የሚታወስ ነው።

የነዚህን የኢትዮጵያ ምርኮኛ ወታደሮች የወደፊት እጣ ፈንታ አስመልክቶ የኤርትራ መንግስት ምን ሊወስን እንደሚችል እስካሁን ድረስ ምንም የታወቀ ነገር ባይኖርም በጉዳዩ ዙሪያ የኤርትራ ባለስልጣናት ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር ሊነጋገሩበት እንደሚችሉ መረጃውን ካደረሱንታማኝ ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።

Aseged Tamene pictursAseged Tamene pictur

Aseged Tamene

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት ኰሚቴ፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ አዲስ ህግ አጸደቀ

እአአ ባለፈው ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በ114ኛው ኮንግሬስ ላይ የቀረበውና የጸደቀው ህግ፣ በኢትዮጵያ ሁሉን ያካተተ አስተዳደር እንዲኖርም ያበረታታል። የቴኔሲው ሬፓብሊካን ሴናተር ቦብ ኮርከር ህጉን በመደገፍ፣ ዋናውን የህጉን አቅራቢ ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲንን፣ እንዲሁም ተባባሪ አቅርቢ ሴናተሮችን አመስግነዋቸዋል።

የS.Res.432 የሰብዓዊ መብት ማስከበሪያ ህግን ከሜሪላንዱ ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲን ጋር በመተባበር ያቀረቡት፣ የዴልዌሩ ዲሞክራት ክሪስቶፈር ኮንስ፡የማሳቹሴትሱ ዲሞክራት ኤድዋርድ ማከርይ፡ የኒው-ጄርሲው ዲሞክራት ቦብ መንደዝ እንዲሁም የፍሎሪዳውን ሬፓብሊካን ሴናተር ሩብዮ ናቸው፣ የሴናተር ኮርከርን ምስጋና ያገኙት።

የቴኔሲው ሬፓብሊካን ሴናተርና የውጪ ግንኙነቱ ኰሚቴ ሊቀ-መንበር ሴናተር ቦብ ኮርከር ስለ ህጉ በሰጡት አስተያየት፣ ይህን ብለዋል።

“ይህ ውሳኔ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ባለን የጋራ ግንኙነት ውስጥ ጠቃሚ ናቸው ለምንላቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጥ ህግን ያካተተ ነው። ሁሉን ያካተተ የመልካም አስተዳደርና የሰብዓዊ መብት አያያዝ ማሻሻል የመሰሉ፡ ከኢትዮጵያ በኩል መሰራት ያለባቸው ገና ብዙ ጉዳዮች አሉ።”

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በደቡብ ሱዳን የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን በመጠበቅ ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስደተኞቹ በታጣቂዎች ሲጠቁ ካምፑን ጥለው መሄዳቸውን ተነገረ

በደቡብ ሱዳን የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን በመጠበቅ ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስደተኞቹ በታጣቂዎች ሲጠቁ ካምፑን ጥለው መሄዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪ ቡድን አጋለጠ። የሩዋንዳ ወታደሮችም ስደተኞቹን ለመታደግ ያልተገባ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተመልክቷል። ይሕም ለ40 ሰዎች መገደልና ለ20ሺ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። አልጀዚራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ድርጊቱ የተፈጽመው በዚህ በፈረንጆቹ አመት መጀመሪያ በየካቲት 2016 ሲሆን የስደተኞቹ ካምፕ የሚገኘውም ማላከል ተብላ በምትጠራው የደቡብ ሱዳን ከተማ ነው። የደቡብ ሱዳን ሰራዊት ዩኒፎርምን የለበሱ ታጣቂዎች 48 ሺ ስደተኞች ወደተጠለሉበት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጣቢያ ለጥቃት ሲመጡ፣ በተባበሩት መንግስታት ደሞዝ የሚከፈላቸውና ስደተኞቹን ከጥቃት የመከላከል ሃላፊነት የተጣለባቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች አካባቢውን ጥለው ሄደዋል። እልጀዚራ ያነጋገራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ አዛዦች ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል። የሰላም አስከባሪዎች ተግባር ለአደጋ የተጋለጡ ሰዎችን መጠበቅ እንደሆነ ቢታመንም፣ የሩዋንዳ ወታድሮች ደግሞ ታጣቂዎች ላይ ለመተኮስ የጽሁፍ ትዕዛዝ መጠበቃቸው አነጋጋሪ መሆኑም በሪፖርቱ ተመልክተዋል። ይህ 40 ስደተኞች የተገደለበትና 20ሺህ የሚሆኑት ደግሞ መኖሪያቸው የተቃጠለበት ድርጊት በተባበሩት መንግስታት መርማሪ ቡድን ቢመረመርም ጉዳዩ ለጸጥታው ም/ቤት እንዳይቀርብ ወይንም ለህዝብ እንዳይገለጽ ጥረቶች መደረጋቸውም በአልጀዚራ ሪፖርት ተመልክቷል። በጥቃቱ ሁለት አባላቱን ያጣው ዶክተርስ ዊዝ አውት (Médecins Sans Frontières) ቦርደርስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ ለብዙሃን ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል በማለት ወቅሰዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች የተሰጣቸውን ሃላፊነት ትተው፣ ስደተኞቹን ለአደጋ አጋልጠው መሄዳቸውን የተመለከተው ሪፖርት በአሁኑ ወቅት ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት መቅረቡንም ከአልጀዚራ ዘገባ መረዳት ተችሏል።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ስደተኞችን ከሰሰ!

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ላይ የሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ ከፍተኛ የሆነ ስህተት በመስራት ላይ ይገኛል! ይህዉም በዚያ በደቡብ አፍሪካ በስደት የሚገኙ በተለይም የወያኔን ስርአት በመቃወም የሚኖሩ ወገኖች በህጋዊ መንገድ በሐገሪቷ የስደተኞች ቢሮ ( DAPARTMENT OF HOME AFFAIR ) የመታወቂያ ወረቀት ወይም የመኖሪያ ፍቃድ የተሰጣቸዉ ግለሰቦች ለንግድና ለተለያየ የአገልግሎት ጥቅም ወደ ሌሎች ሐገር ሊያሸጋግር የሚችል የጉዞ ሰነድ ( PASPORT ) እንዳያገኙ ፈጽሞም ኢንዳይሰጣቸዉ የወያኔዉ ተላላኪ የሆነዉ የኢትዮጵያ እንባሲ ክስ አቅርቧል!
በመሆኑም አንድ ስደተኛ ወረቀት ሊያሰጠዉ ከሚችለዉ መስፈርት አንዱ የወያኔን ስርአት በመቃወሙ ምክንያት መሰደዱን ማረጋገጥ ከመፋሉ የተነሳ በመሆኑ ማንኛዉም ስደተኛ በስደተኝነት እያለ የጉዞ ሰነድ ( Pasport ) የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
የህጉ አንክዋር እንዲህ ይላል “አንድ ስደተኛ ግለሰብ ለደህንነቱ ሲባል ከኢትዮጵያ ዉጭ በጉዞ ሰነዱ የትም ሐገር የመጓዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ”
ነገር ግን የኢትዮጵያ ኢንባሲ በክሱ ላይ እንዳስቀመጠዉ መረጃ አለኝ እያለ ሙግት ጀምሯል! ይህዉም በተባበሩት መንግስታት ዉል መሰረት የደቡብ አፍሪካ የስደተኞች ቢሮ የጉዞ ሰነድ ( passport ) የሚሰጣቸዉ ኢትዮጵያዊያኖች ፓስፖርቱን የሚፈልጉት ወደ ኤርትራ በመጓዝ አርበኞች ግንቦት 7 የተባለ የሽብር ቡድንn ለመቀላቀል ነዉ! ። የሚል ተልካሻ መነሻ ሐሳብ ሲሆን ክሱ በጥንቃቄ እንዲታይለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
ይህን መሰል ክህደት በገዛ ሕዝቡ ላይ የሚፈጽመዉ ተላላኪዉ የወያኔ ኢንባሲ በሰሞኑ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የደቡብ ተወላጆች በተለይም የከንባታና ሐዲያ ልጆችን ሰብስቦ አስገራሚ የሆነ የዉንብድና የሐሰት ስራ በገዛ ወገኖቹ ላይ ሊፈጽም ተዘጋጅቷል!
አምባሳደር ሙሉጌታ የተገኙበት የደቡብ ህዝቦች ስብሰባ ላይ የተገለጸዉ ተንኮል… በስደተኝነት ህጋዊ ወረቀት አግኝታችሁ ከኢትዮጵያ ዉጭ የትም መሄድ የሚያስችል የጉዞ ሰነድ ( Pasport ) ያላችሁ የደቡብ ተወላጆች ሐገራችሁ ገብታችሁ ገንዘባችሁን ተጠቀሙ ወረቀታችሁ እንዳይበላሽ ከዚህ ወደ ሱዳን ወይም ኬንያ ወይም ደግሞ ጅቡቲ ትሄዱና ከዚያ ደግሞ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ወደ ሐገራችሁ መግባት ትችላላችሁ በማለት ስደተኞችን ለከሰሱት የኤርትራ ጉዞ መረጃ መሰብሰቢያ በማድረግ ለመጠቀም እያመቻችሁ ይገኛሉ።
በመሆኑም በዚህ እኩይ ተግባር የተበሳጩ ኢትዮጵያዊያን የወያኔ ኢንባሲ ያደረጋቸዉን ገለጻዎች በሙሉ በድምጽና በምስል በመያዝ ለሚመለከተዉ አካል አስተላልፈዉ ጉዳዩ በተለየ መልኩ እየታየ እንደሚገኝ መረጃ የደረሰዉ የወያኔ ኢንባሲ ወደ ሐገር ቤት የላከዉን ሪፖርት የዉስጥ ምንጮች አሳልፈዉ ሰጥተዋል።
ማሳሰቢያ….. በደቡብ አፍሪካ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ ይህን የወያኔ ተንኮል ግምት ዉስጥ በማስገባት ከተጠነሰሰባችሁ ሴራ እንድትጠነቀቁ እና እራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

poster-with-pic-a-ማይ-14-

%d bloggers like this: