የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ6 አየር ሃይል አባላት ላይ የእስራት ቅጣት አስተላለፈ

የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ስድስት የአየር ሃይል አባላት ላይ ከሶስት እስከ 10 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት አስተላለፈ።
ከሳሽ አቃቤ ህግ በሰኔ 2007 አም ተከሳሾቹ የአየር ሃይልን በመክዳት ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ እንደተያዙ በክሱ አመልክቶ እንደነበር ይታወሳል።
የቀድሞው የአየር ሃይል አባላት ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል የማፍረስ አላማ ይዘው በሽብር ድርጅት ውስጥ አባላት በመሆንና በሽብር ድርጊት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው የሚል ክስን አቅርቦ እንደነበርም በወቅቱ መዘገባችን አይዘነጋም።
ይሁኑ የክስ ሁኔታ ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ በስድስቱ ተከሳሾች ላይ ከሶስት አመት እስከ 10 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ማስተላለፉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ መ/አ ብሩክ አጥናዬ፣ መ/አ ዳኔኢል ግርማ፣ መ/አ ጋዘኸኝ ድረስ እንዲሁም አቶ ተስፋዬ እሸቴ እና አቶ ሰይፉ ግርማ ስድስቱ ተከሳሾች ናቸው።
ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያሉት መቶ አለቀ ተከሳሾች በ10 አመት አምስተኛና ስድስተኛ ተከሳሾች ደግሞ በሶስት አመት ከስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ታውቋል።
ከተከሳሾቹ መካከል መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤና ስደተኛ ተከሳሽ ሰይፉ ግርማ በሃምሌ ወር በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት አደጋ እጃቸው አለበት ተብሎ ተደራራቢ ክስ ከተመሰረተባቸው በርካታ እስረኞች ጋር እንደሚገኙበትም ለመረዳት ተችሏል።
የፍርድ ውሳኔው ሰኞ በተላለፈበት ወቅት አንደኛ ተከሳሽ ከግንቦት ወር 2008 አም ጀምሮ በጨለማ ክፍል እንዲቆዩ መደረጋቸውንና ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተገናኝተው እንደማያውቁ ለችሎት አስረድተዋል።
ከእነዚህም በተጨማሪ በምርመራ ወቅት ከባድ ድብደባ ሲፈጸምባቸው መቆየቱንና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጸምባቸው እንደነበር አቤቱታቸውን አሰምተዋል።

15542125_1875786285986970_8207959935562296567_n

በሊቢያ የውሃ ዳርቻ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች ከመስመጥ አደጋ መትረፋቸው ተዘገበ ፡፡

በሊቢያ የውሃ ዳርቻ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች ከመስመጥ አደጋ መትረፋቸው ተዘገበ ፡፡

ኢትዮጵያውያንስ ይገኙበት ይሆን?፡፡CGTN Africa ዝርዝሩን ይከታተሉ

ዶ/ር መረራ ጉዲና ለሦስተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው – ታምሩ ጽጌ

ዶ/ር መረራ ጉዲና
በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ፣ ፖሊስ ለሦስተኛ ጊዜ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት፡፡

የመድረክ የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ላይ፣ ብዙ ምርመራዎችን ማድረጉን ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ፖሊስ አስረድቷል፡፡ ነገር ግን ቀሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን ገልጾ፣ ተጨማሪ 28 ቀናት እንዲቀፈድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

የዶ/ር መረራ ጠበቆች ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመቃወም፣ ደንበኛቸው ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ የተጠየቀውን የዋስትና መብት በማለፍ ፖሊስ የጠየቀውን የ28 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ ለየካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 መሠረት ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመጠየቅ አንድ ዕድል ይቀረዋል፡

16266251_1248266475267774_2596220851978438808_n

የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ደረጃ ወደ ውጭ መውጣት መቀጠሉን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን ዘገባዎች ይገልጻሉ።

የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ደረጃ ወደ ውጭ መውጣት መቀጠሉን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን ዘገባዎች ይገልጻሉ። በተለያዩ መስኮች የንግድና የልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ ዜጎች ንብረታቸውን በመሸጥ ገንዘብ ለማስወጣት እየጣሩ ሲሆን የአገሪቱን አንጡራ ሀብት በተለያዩ መንገዶች ሲዘርፉ የቆየቱም የወያኔ ባለስልጣኖች የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ገንዘብ እያስወጡ መሆናቸው ታውቋል። የወያኔ ባለስልጣኖች በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሁኔታ እንዳለና ሁሉም ነገር
በቁጥጥር ስር እንደሆኑ ነጋ ጠባ ቢደሰኩሩም ጥርጣሬና ፍርሃት ያላቸው ወገኖች ገንዘባቸውን ከሀገር ለማስወጣት እየተጣጣሩ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር እስከ 30 ብር ሲመነዘር የቆየ ሲሆን በገበያው ውስጥ ያለው መጠን በጣም እየቀነሰ በመምጣቱ ለማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል ተብሏል። በዚህ ምክንያት በውጭ አገር ገንዘብ ለዘመዶቻቸው ወይም ለአንዳንድ ሥራዎች የሚልኩ ኢትዮጵያውያንን እየቀረቡ ውደ አገር ውስጥ ሊልኩ ያቀዱትን ገንዘብ በውጭ አገር በዶላር ከሰጡ በሰላሳ ብር ሂስብ አገር ውስጥ ለሚፈልጉት ሰው ሊሰጥላቸው እንደሚችል በመንገር ልዋጩን የሚያካሂዱና የድላላ ስራ የሚሰሩ ግለስቦች ቁጥር እየበረከተ መጥቷል ተብሏል።

cropped-15354184_682255945273072_1620739714_o.jpg

በጎንደር አንድ የገዢው ፓርቲ ንብረት የሆነ ተሳቢ የጭነት መኪና በቦንብ ተመታ

ኢሳት ዜና :- ዛሬ ረቡዕ ከንጋቱ 11 ሰዓት ላይ ከጎንደር ወደ መቀሌ እቃ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማው በ10 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ ወለቃ በምትባለዋ መለስተኛ መንደር ላይ ሲደርስ በቦንብ በመመታቱ መኪናው እስከነጭነቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተያይዞ ወድሟል።
ምንጮች እንደገለጹት ተሽከርካሪው ሌሊት ጎንደር ላይ እቃዎችን በመጫን ወደ መቀሌ ጉዞ በማድረግ ላይ ነበር። አስቀድሞ መረጃ የደረሳቸው ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ተዘጋጅተው ሲጠብቁ እንደነበርና እነዚህ ሃይሎች ጥቃቱን እንደፈጸሙት የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ጥቃቱ እንደተፈጸመ የእሳት አደጋ መኪና የደረሰ ቢሆንም፣ ቃጠሎውን መቆጣጠር ሳይችል ቀርቷል። የአጋዚ ወታደሮች አካባቢውን በመቆጣጠራቸው መኪናውን ምን እንደጫነ ለማወቅ ሳይችሉ መቅረታቸውንም ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በጎንደር እና ትግራይ መካከል በደባርቅ በኩል የሚደረገው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መንገዱ አደጋኛ በመሆኑ እንዲቋረጥ ተደርጓል። በሁመራ በኩል የሚደረገው ጉዞ እንዳማራጭ ጥቅም ላይ እየዋለ ባለበት ወቅት፣ የአሁኑ ጥቃት ይህንንም መንገድ ለተሽከርካሪ ዝግ ያደርገዋል የሚል ግምት አሳድሯል። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች የሚፈጽሙት የደፈጣ ጥቃት መጨመር አገዛዙ በአካባቢው ያለውን ወታደራዊ ሃይሉን እንዲጨምር አስገድዶታል።
በወለቃ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እስካሁን ድረስ ሃላፊነቱን የወሰደ ሃይል የለም።

15354184_682255945273072_1620739714_o

 

%d bloggers like this: