የህወሓት የስለላ ድርጅት የስጋት እርምጃና ህዝብን የማሸበር ተግባር – በባህርዳር

በተከታታይ በአማራ አርበኞች ህዝባዊ ሃይል በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ግንባሮች ባደረገው የሽምቅ ውጊያ ክፋኛ የተደናገጠውና ከፍተኛ ጥቃትና ውርደትን የተከናነበው የህወሓት ዘረኛ ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ የነፃነት ትግሉ ከህዝብ ያለውን ድጋፍ እያየ እንዳቀረቀረ ማስታገሻ እንዲሆነው በማሰብ ህዝብን የማሸበሩን ሴራ ማንሰላሰሉን አላቆመም።
* በከፍተኛ ሁኔታ የሸቀጦችና የምግብ ፍጆታ ዋጋ እንዲንር ያደረገው ወያኔ ፤ነዳጂ አለ እየተባለ እንዲጠፉ ያደረገው ማስመሰል ዛሬም አዲስ ማሸማቀቂያና ማፈኛ ስልትን ይዞ መጥቷል።
* ከአመታት በፊት የከተማ ገፅታ ያበላሻል የተባለው መንደር እንዲፈርስ ሲወሰን ትክ ቦታ
ሳይሰጣቸው ነበር።አሁን ይሄን ሃሳብ ዳግም በማስፈፀም በዚህ ሰበብ ወጣቱን ማሰርና ማፈን አንድ የማስታገሻ ውጥረቱን ማርገቢያ መንገድ መስሎታል።
* እንዲህ ሆነ ባህርዳር ቀበሌ 13 ከኢሜግሬሽን ጀርባ አካባቢ ያለው የወያኔው የኢትዩጲያ መርብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ) ብሎ እራሱን የሚጠራው አፍኝ የስለላ ቡድን በተደጋጋሚ ባቀረበው የስጋት ሀሳብ “በባህርዳርና ጎንደር ያለው የወጣቶች አደረጃጀት እጂጉን ያስፈራል፤በየመንደሩ የሚሰባሰቡት ወጣቶች እጂግ የሚተዋወቁና
የነቁ ናቸው::በዚህም ምክንያት ተፈልጎ አስቸኳይ ዘመቻ እና ከተቻለ መዋቅሩን ጫፉ ከተገኘ ማፍረስ ካልተቻለ ውጥረቱን ማርገብ በዝምታ የሚገሰግሰውን ነበልባል ማፈን
አለብን” በማለት በቅርብ የተገኘ የህገወጥ መኖሪያ ቤት ምክንያት በመላ ከተማው ዳናውን ለመያዝ የተደረገ ሙከራ ሲጠኑ የነበሩ እየታደኑ ከ100 በላይ ወጣቶች ለእስር ዳረጉ፣ብዙወች ተደበደቡ ለአካል ጉዳት ተዳረጉ ፣ሁለት ወጣቶች በጥይት ተገደሉ።
* ከዚህ ላይ የፍራቻው ጥግ የደረሰው የስጋት እርምጃ ባለፈው ሰኞ በክልሉ ምክር ቤት ለዛሬ ሐሙስ ለመፍትሄ ሃሳብ የተቀጠሩት ነዋሪወች ሐሙስን ሲጠብቁ ማክሰኞ ዕለት
ደራሽ ጎርፉን ለቀቁት በዚህም ህገወጥ ናችሁ የተባሉ ቤቶችን ፈረሱ በዚህ አምባገነናዊ ተግባራቸውን አላከው በቦታው ያልነበሩ ወጣቶችን ሰብስበው ማስገባታቸውን የህወሓት ህዝብን የማሸበር ተግባር ለከት የሌለው እንደሆነ ያሳያል።
* የህወሓት የስለላ ድርጂት ከጠረፋማ ድንበሮች እስከ ማዕከላዊ ያለው ሰንሰለት እየተቆራረጠበት ይገኛል።ለዚህ የበሰበሰ ስርዓት ማገልገል የማይፈልጉና ቂም ቋጥረው የቆዩት ባገኙት አጋጣሚ ጥለው እየጠፉ ነው ።
* ለዚህም ማሳያው ላለፉት 3 ወራት ብቻ ብዙወች ወታደራዊና ሲቪል ሰላዩች ድራሻቸው አይታወቅም። አፈሳውና እስሩ በአጎራባች
አካባቢወች ሊቀጥል እንደሚችል ፍንጮች ወጥተዋል።
*በተለይ ወጣቶች እንቅስቃሴያችሁ በጥንቃቄ እንዲሆንና በስነልቦና ዝግጁ እንድትሆኑ ከወዲሁ እንመክራለን።

በጎንደር የወያኔ ቁልፍ የደህንነት አባል በነጻነት ኃይሎች ተረሸነ

በጎንደር ዙሪያ ደጎማ ከተማ የደህንነት አባል በሆነ ቢራራ ስመኝ በተባለ ግለሰብ ላይ መጋቢት 13 ቀን ከቀኑ 9:40 ላይ ልዩ ቦታው አይና ሽዋና በተባለ ቦታ ላይ ተገድሏል። የግለሰቡ ቀብርም ደጎማ አይና ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

የነጻነት ኃይሎች በወሰዱት ተከታታይ ጥቃቶች የተደናገጠው ወያኔ፤ ታጋዮችን አምጡ እያለ አርሶአደሮች መደብደብ እና ማሰር ይዛል፡፡ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይለሀል ይሄ ነው፡፡

የነፃነት ኃይሎች ወደ ጋይንት ከተማ በመግባት በወያኔ አማሪኛ ክፍል ብአዴን ጽ/ቤት እና ሹመት በተባለው አስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊ ላይ እርምጃ መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በተከታታይ በተካሄደው ዘመቻ በነፃነት ኃይሎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የለም።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከኢሕአዴግ ጋር በጋራ ለመደራደር ያደረጉት የመጀመሪያ ጥረት አልተሳካም

ሃያ አንድ አገር አቀፍ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከኢሕአዴግ ጋር በተናጠል ወይም በጋራ ለመደራደር ለመወሰን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ያደረጉት ስብሰባ ባለመሳካቱ፣ በተናጠል ውይይት የሚያደርጉት ዕድል እየሰፋ መምጣቱ ተጠቆመ፡፡

ዋናው ድርድር ከመጀመሩ በፊት ድርድሩ የሚመራባቸው ዝርዝር የሥነ ሥርዓት ደንብ ላይ ውይይት እያካሄዱ ያሉት 21 አገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ በዚሁ ጉዳይ ላይ አምስት ዙር ውይይት አድርገዋል፡፡ በመጪው መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚካሄደው ስድስተኛ ዙር ውይይት በደንቡ ላይ የሚደረገው ውይይት እንዲጠናቀቅ ባለፈው ሳምንት መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮችን ለመቋጨት ኢሕአዴግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተናጠል አልያም በቡድን ወይም በተወካይ አማካይነት መደራደር እንደሚፈልጉ ራሳቸው እንዲወስኑ ባቀረበው ሐሳብ መሠረት፣ 21 ፓርቲዎች መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ተገናኝተው ለመወሰን ተቀጣጥረው ነበር፡፡ ነገር ግን በዕለቱ የ12 ፓርቲዎች ተወካዮች ብቻ ናቸው የተገኙት፡፡

ኢሕአዴግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይ በተናጠል ወይም በቡድን ወይም በተወካዮች ለመደራደር እንዲወስኑ ሐሳብ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ በቡድን ሲደራደሩ የሚቀር የተለየ አጀንዳ ካለው አካል ጋር የተናጠል ድርድር ለማድረግም ፈቃደኝነቱን አሳይቷል፡፡ በዕለቱ የተገኙት ፓርቲዎች በአንድ ተወካይ ለመቅረብ ያላቸው ሐሳብ በዚሁ ስምምነት የተነሳ እንደተደናቀፈ ተገልጿል፡፡ ከተገኙት ፓርቲዎች መካከል ኢዴፓ፣ ሰማያዊና ኢራፓ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዕለቱ ካልተገኙ ፓርቲዎች መካከል መድረክ፣ መኢአድና ወለኔ ተካተዋል፡፡ ወለኔ የማንነት ጥያቄ የማያራምድ በመሆኑ በተወካይ ለመደራደር እንደማይችል መግለጹ ታውቋል፡፡

የኢዴፓ የጥናትና ምርምር ክፍል ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ፣ በመርህ ደረጃ ጠበብ ብሎ በተወካይ አማካይነት መደራደርን ኢዴፓ እንደሚደግፍ ገልጸዋል፡፡ 22 ፓርቲዎች ባደረጉት ስምምነት መሠረት በዕለቱ የተገኙት ፓርቲዎች በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ የሐሳብ ልውውጥ ቢያደርጉም፣ በአንድ ተወካይ ቡድን መደራደርን ተግባራዊ እንዳላደረጉም አክለዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ፓርቲዎቹ በተናጠል ከኢሕአዴግ ጋር የመደራደር ዕድላቸው እየሰፋ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን አሁንም ጠበብ ብለን በተወካዮች አማካይነት ለመደራደር ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥላለን፤›› ብለዋል፡፡

መድረክ በአምስኛው ዙር ውይይት ከኢሕአዴግ ጋር ለብቻው ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህ የተነሳ በሰኞው ስብሰባ አለመገኘቱ ብዙም የሚገርም አልሆነም ተብሏል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተናጠል ከሚደራደሩ ይልቅ በጋራ ቢደራደሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ያሳስባሉ፡፡ ስለጉዳዩ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ‹‹ኢሕአዴጎች በባህሪያቸው ትምክህተኞች ናቸው፡፡ ሁሉም ነገር የሚቻለው ሲፈቅዱና ፍላጎት ሲኖራቸው ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በቡድን ወይም በተወካይ መቅረብም ሆነ በተናጠል መደራደር ብዙ ልዩነት ያለው አይመስለኝም፤›› ብለዋል፡፡

ይሁንና መድረክ በተናጠል የመደራደር ሐሳብ ለማቅረብ የተገደደው በጋራ ለመሥራት የመረጣቸው የሰማያዊና የመኢአድ ፓርቲዎች የፀና አቋም ስለሌላቸው  እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

‹‹መድረክ በአቋሙና የፖለቲካ ምኅዳሩ እየፈጠረ ካለው ችግር አኳያ ለሰማያዊና ለመኢአድ ይቀርባል፡፡ ሌሎች ፓርቲዎች እንዲህ ዓይነት ጫና ደረሰብን ሲሉ አላይም፡፡ ስለዚህ ከሁለቱ ፓርቲዎች ጋር ሰፊ ጊዜ ወስደን ተነጋግረን ነበር፡፡ በኋላ ሐሳባቸውን ቀይረው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመሆን መረጡ፤›› ብለዋል፡፡

ከየካቲት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ የሰማያዊ ፓርቲ ሕጋዊ ፕሬዚዳንት መሆናቸው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፀደቀላቸው አቶ የሺዋስ አሰፋ ግን፣ የጋራ አጀንዳ እስካለ ድረስ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ቢሆን አብሮ ለመሥራት ሰማያዊ ዝግጁ እንደሆነ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹የጋራ አጀንዳዎቻችን አንድ እያደረጉን ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ፤›› ብለዋል፡፡

በሰኞው ስብሰባ ስምምነት ላይ ሳይደረስ መቅረቱ መነገሩ ትክክል እንዳልሆነም አመልክተዋል፡፡ ‹‹ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት አምስት ዙር ውይይቶች በተቃራኒ የሰኞው ስብሰባ የተቀናጀና ኃላፊነት ወስዶ የሚያስተባብር አካል ያልነበረው ነው፡፡ የተሻለ ቅንጅትና የማስተባበር ሥራ ቢሠራ የተለየ ለውጥ ሊኖር ይችላል፤›› ሲሉም አቶ የሺዋስ አክለዋል፡፡

ኢሕአዴግን በመወከል በፓርቲዎች ድርድር እየተሳተፉ የሚገኙትና የውይይቱ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በቡድን በቡድን ከኢሕአዴግ ጋር እንደራደር የሚል ጥያቄ ለገዢው ፓርቲ እንዳልቀረበ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ድርድሩ በጋራ ይሁን በተናጠል የሚወሰነው በሚቀርበው አጀንዳ እንደሆነ ነው የማምነው፡፡ ኢሕአዴግ ለተመሳሳይ አጀንዳ የተለያየ ድርድር አያደርግም፡፡ የተለየ አጀንዳ አለኝ ከሚል ማንኛውም ፓርቲ ጋር ለመደራደር ግን ዝግጁ ነን፡፡ ምርጫው ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተተወ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የተመዘዘዉ የወያኔ የበቀል በትር?

ሸንቁጥ አየለ

ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እየተነሳ ከ12 በላይ በሚሆኑ የኦሮሚያ ወረዳዎች ላይ የጥቃት እርምጃ ስለሚወስደዉ እና ወረዳዎቹን ስለሚወረዉ ህገወጥ ሀይል የጀርመን ድምጽ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል:: የጀርመን ድምጽ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣኖችን እያነጋገር ለመስማት የሚዘገንኑ ሀቆችን ሲያቀርብ ያደመጠ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በወያኔ በቀልተኛ እርምጃ መበሳጨቱም መገረሙም አይቀርም:: ይሄ ከሶማሌ ክልል የሚነሳዉ ወራሪ ሀይል በኦሮሚያ ክልል ያለዉን ማህበረሰብ የማፈናቀል: ወረዳዎችን የመዉረር ብሎም ወረዳዎቹን የሶማሌ ክልል ናቸዉ ብሎ የሶማሌ ክልል ባንዲራን በወረራቸዉ ወረዳዎች ላይ የማዉለብለብ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ተብራርቶ ቀርቧል::

ይሄዉ ህገወጥ ሀይል የኦሮሚያ ወረዳዎች የሶማሌ ወረዳዎች ናቸዉ የሚል መግለጫ እየሰጠ ኦሮሞዉን እያፈናቀለ ወረዳዎቹንም በቁጥጥሩ ስር እያደረገም እንደሆነ ያደመጠ ሁሉ ወያኔ በቀጣይነት ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርሳቸዉ በክልል ግዛት ጉዳይ ሊያጫርሳቸዉ በሰፊዉ እንዴት እንዳቀደ ግልጽ ይሆንለታል::የሚያሳዝነዉ ደግሞ የፌደራል መንግስቱ እና የሶማሌ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልል መንግስት አገላለጽ መሰረት ይሄ ከሶማሌ እየተነሳ ኦሮሞዉን እየፈጀ ስላለዉ ሀይል ሲጠየቁ ይሄ ሀይል ከመንግስት ቁጥጥር ዉጭ ነዉ እያሉ የፌዝ መልስ እየሰጡ ነዉ:: ሆኖም የኦሮሚያ ባለስልጣናት በመረጃ ለጀርመን ድምጽ እንዳቀረቡት ይሄ ከሶማሌ ክልል የሚነሳዉ ህገወጥ ሀይል የሰለጠነዉ እና የሚታዘዘዉ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ /ህዉሃት/ ነዉ::

የዚህ ሁሉ ዋና ማጠንጠኛዉ ግብ በቀል ነዉ::ኦሮሞው ለምን የዲሞክራሲያዊ መብቴ ይከበር የሚል ጥያቄ አነሳ የሚል ታሳቢ ነዉ::ወያኔ ስልጣን የያዘ አመታት ዉስጥ አንድ ሸዉራራ ታሳቢን አንግቦ ነበር ወደ ስልጣን የወጣዉ::ይሄዉም ኦሮሞዉን እያሞኘሁና እያስፈራራሁ ዘላለሜን እጋልበዋለሁ: አማራዉን ደግሞ በሌሎች ብሄሮች እያስቀጠቀጥሁና አከርካሪዉን ሰብሬ ለዘላለም እገዛዋለሁ የሚል ቀመርን ይዞ ነበር የተነሳዉ::

በወያኔ ቀመር መሰረት እነዚህን ሁለት ትልልቅ ብሄረሰቦች እርስ በእርስ ከፋፍለህ ግዛዉ ከተቆጣጠራቸዉ ሌላዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አስቸግሮም አያስቸግረዉም:: ሆኖም ወያኔ ያሰበዉ እና የቀመረዉ ስትራቴጅ ስህት መሆኑን ሀያ አምስት አመታት ሙሉ የኦሮሞ ህዝብ ወያኔን ተጋፍጦ ስለዲሞክራሲያዊ መብቱ እየሞገተዉ ይገኛል::በተለይም በመላዉ ኦሮሚያ ተነስቶ የነበረዉ የኦሮሞ ተቃዉሞ ወያኔን በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የበቀል በትሩን እንዲያነሳ አድርጎታል::አንዱ የበቀል በትሩም ኦሮሞዉን ከሶማሌ ክልል በሚነሳ ህገወጥ ሀይል ማስቀጥቀጥ ማፈናቀል እና ማስጨረስ ሆኖ ተከስቷል::

ወያኔ ምናልባትም የኦሮሞን ማህበረሰብ በአራቱም አቅጣጫ ከልዩ ልዩ የሀገሪቱ ማህበረሰቦች ጋር በማጋጨት እና በማስጨረስ የመጨረሻዉን የበቀል እርምጃ ሊወስድበትም እየተዘጋጀ ሊሆን ይችላል::

የኢትዮጵያን ህዝብ በአጠቃላይ ለመታደግ እና ለመፈወስ ኢትዮጵያዉያን የተቃዉሞ ሀይላት አንዱ የአንድነት ሀይል: ሌላዉ የብሄር ሀይል ተባብለዉ ለዬብቻ ሳይሮጡ ቁጭ ብለዉ በጥበብ እና በሰከነ መልክ ቢመክሩ ብቻ ለሁሉም የምትመች እና ሁሉም የሚስማማባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መፍጠር ይቻላሉ:: የኦሮሞ ተቃዉሞ ሀያላትም ከወንድሞቻቸዉ የአማራ ተቃዉሞ ሀይላት ጋር ያለባቸዉን የልዩነት መሰረት ለሁለቱም ማህበረሰብ በሚበጅ መልክ ፈትተዉ እንዲሁም መላዉ የኢትዮጵያን ህዝብ በሚጠቅም መልክ ኢትዮጵያን ለማዳን ከአንድነት ሀይሉም ጋር ተባብረዉ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መፍጠር ላይ ቢተጉ መልካም ይመስለኛል::

ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በደንብ ሊረዱት የሚገባዉ የዲሞክራሲያዊነት ምርጫ እና የመጻኢዉ ጊዜ ምልዓታዊ የማህበረሰብ ብልጽግና ሁሉ በራሳቸዉ እጅ ብቻ እንደሚገኝ ቢረዱት መልካም ነዉ::ከዚያ ዉጭ ድጋፍ ከዚያ ወይም ከዚህ የዉጭ ሀይል ወይም ከዚህኛዉ ወገን ለዚህኛዉ ማህበረሰብ ተብሎ የሚሰጥ ድጋፍ ሁሉ ሁሉንም ማህበረሰብ የማያድን ስለሚሆን የመጨረሻዉ ጉዞ ወደ ጥልቁ መርዛማ ባህር ነዉ::መፍትሄዉ ኢትዮጵያዉያን ብቻቸዉን ቁጭ ብለዉ የማንንም የዉጭ ሀይል እጅ ሳያስገቡ ይነጋገሩ: ይመካከሩ: መወቃቀስም ካስፈለገ ይወቃቀሱ: ሀይለኛ እና ፍጹም የአማራጭ ሀሳቦች ላይ ይከራከሩ::

በመጨረሻም ለሁሉ ወገን የሚበጀዉን የተሻለ አማካይ እና አካታች መስመር በመከተል አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመፍጠር በመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ህዝብ ላይ እየተፈጠረ ያለዉን ያለመረጋጋት እና የመከራ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቀረት ይስሩ:: ኢትዮጵያዉያን ከተባበሩ ወያኔን አንድም በድርድር ወይም በሀይል ከወንበሩ የማንሳት ስራም የሳምንታት ስራ ብቻ ይሆናል:: ሌላዉ ምርጫ ሁሉ የጨላማ ጉዞ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ አዙሪት ነዉ::

 16995957_1314634245271106_6741052944737895569_n

የፌዴራል ዓቃቢ ህግ በእነ ፕ/ር መረራ ጉዲና፣ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር መሃመድ ላይ የመሰረተው የመንግስት ግልበጣ የፈጠራ ክስ።

የፊዳራል ተብዪው ፍርድ ቤት በፕ/ር መረራ ጉዲና እና በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ጁሃር መሃመድ [በሉበት] ህገ-መንግስቱን በሃይል የመናድ ሲራና ተግባር ፈጽመዋል ሲል ክስ ከፈተባቸው።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ በፊትም በሌሉበት 2ግዜ የሞት ፍርድ እንደፈረደባቸው የሚታወቅ ሲሆን የአሁኑ የዓቃቢ ህግ 3ኛ ዙር ክስ ፕሮፌሰሩ ሁለት ግዜ ሞት ተፈርዶባቸው ግን እንዳልሞቱበትና ይባስም ብለው ለስርዓቱ ህልውና መናጋትና መናድ ሁነኛ ተግባር ፈጻሚ ሆነው በመገኘታቸው የጨነቀው ህወሃት ፕሮፌሰሩን ለ3ኛ ግዜ በሌሉበት 3ኛ የሞት ፍርድ ሊፈርድ ክስ እንደከፈተባቸው መረዳት ይቻላል።

እዚህጋ- የፕ/ር መረራ ጉዲና ጉዳይ ለየት ባለ ሁኔታ እንደተያዘና ፕሮፌሰሩን ለመጉዳት ህወሃቶች ምን ያህል ርቀው እንደሄዱ መረዳት እንችላለን።

በእርግጥ ፕ/ር መረራ ጉዲና ህገ-መንግስት ተብዪውን በሃይል ለመገልበጥ ተንቀሳቅሰዋልን? ብለን ብንጠይቅ የፕ/ሩን አካሄድ ለአመታት የምናውቅ ሰዎች የፈጠራው ክስ የህወሃቶች መሰሪና ፋሽስታዊ ባህሪና ተግባር መሆኑን እንረዳለን እንጂ የፕ/ሩን ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ የምናየውም ሆነ ያየነው ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ህዝብ ምስክር ነው።

%d bloggers like this: