በእስር ላይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድረሱልን እያሉ ነው

ቦረና አበራ፣ ወየቻ ታምሩ፣ ወሰኑ ገረመው፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ፣ ገዳ ገመቹ፣ እዮብ ሙሊሳ እና ሳሎ ነጋሳ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን በሚከታተሉበት ወቅት ለእስር ተዳርገዋል።

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ምክንያት በነበረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ አራት ወራት ከታሰሩ በኋላ “ወንጀሉ በተፈፀመበት አካባቢ ይዳኙ” ተብሎ ሚያዝያ 28/2008 ወደ ዲላ ከተማ ተዛውረዋል። ሀምሌ 7/2008 ዓም ወደ ሀዋሳ ተዛውረው በእስር ላይ ይገኛሉ።

የካቲት 7/2010 በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ቦረና አበራ በነፃ ሲሰናበት፣ ቀሪዎቹ እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል። ተከላከሉ ከተባሉት 6 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ሳሎ ነጋሳ (4ኛ አመት ተማሪ የነበረ) ብቻ “እከላከላለሁ” ሲል ወየቻ ታምሩ (የ3ኛ አመት ተማሪ)፣ ወሰኑ ገረመው (3ኛ አመት)፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ (3ኛ አመት)፣ ገዳ ገመቹ (3ኛ አመት) “አንከላከልም” ብለዋል።

ተከሳሾቹ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው የታሰሩ በመሆናቸው ችግር ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። “የሚረዳን የለም፣ ሚዲያም እያስታወሰን አይደለም” ሲሉም ገልፀዋል።በጌታቸው ሺፈራው

 

የአቶ በረከት መልቀቂያ ዜናና የሕወሐት ሴረኝነት

 

ይልቃል ጌትነት

አሁን ባለንበት ሁኔታ ሕወሐት/ኢሕአዴግ ከባድ ችግር ውስጥ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ ያለበትን የውስጣዊ ችግር የእድገት ደረጃ በጥሞና ለመረዳት እያንዳንዱን ክንዋኔ በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ የውስጣዊ ድርጅት ሽኩቻውን በአጠቃላይ ሀገራዊ ፖለቲካ ፋይዳው ጋር ሚዛን በመስራት ለእውነት የተጠጋ ትንተና ላይ ለመድረስ ሁለቱን ማለትም የድርጅት ውስጣዊ ሽኩቻውንና ሀገራዊ ፋይዳውን ሚዛን ላይ አስቀምጦ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ሕወሐት እጅግ ሚስጥራዊ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሀገሪቱን የመምራት ኃላፊነትም በእነሱ ትክሻ ላይ መውደቁን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ሀገራዊ ምስቅልቅል ውስጥ የአቶ በረከትን መልቀቂያ ይፋ ማድረግ ለምን አስፈለገ? ለዚህ ጥያቄ ለእውነት የቀረበ መልስ ለማግኘት ሁለት መላምቶችን ማቅረብ ይቻላል፡፡


አቶ በረከት የድርጅቱ ጭንቅላት እንደሆኑ ይታመናል፡፡ አቶ አባዱላ የይስሙላ ፓርላማም ቢሆን በዓለም አቀፍ ግኝኙነት ደረጃ ሲታይ የነበሩበት ቦታ ትልቅ ገፅታ ነው፡፡ የእነዚህ ባለስልጣኖቸ መልቀቅ ሕወሐት/ኢሕአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሞና ሁሉንም ነገር መቆጣጠር አቅቶት ባለስልጣኖቹ ተስፋ በመቁረጥና በመደናገጥ ሀገራዊ ኃላፊነት መውሰድ የማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው በግላቸው እየወሰኑ ነው ማለት ነው፡፡በመሆኑም እነዚህ ትልልቅ ባለስልጣኖች በእንድ ጊዜ ስልጣን መልቀቃቸው ከፍተኛ ችግር መኖሩንና ለሀገራዊ የፖለቲካ ለውጥ መቃረባችንን መገመት ይቻላል፡፡


ሌላው በአሁኑ ሰዓት ኦህዴድ ከሕወሐት የበላይነት በብዙ መልኩ የማፈንገጥ አዝማሚያና በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር አጀንዳ መጋራትና የአላማ መደበላለቅ አለ ብሎ ሕወሐት ያምናል፡፡ የአባዱላ ገመዳ መልቀቅና ለመልቀቁ የሰጠው ምክንያት የኦሮሞን ህዝብ ለማነሳሳትና አባዱላ የህዝባዊ እንቅስቃሴው ቀጥተኛ ያልሆነ መሪ /informal leader/ ለመሆን በኦሮሞ ፖለቲከኞች የተቀነባበረ ነው በሚል ሕወሐት ይህንን የድርጅት ሽኩቻ ሚዛን ለማስጠበቅ የአቶ አባዱላን መልቀቅ በህዝብ ዘንድ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያው ያገኘውን የዜና ሽፋን ለመበረዝና በአባዱላ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን የፖለቲካ ትኩሳት ዝቅ አድርጎ ማሳየት ስለነበረበት አቶ በረከት በተመሳሳይ ሁኔታ ከስራ እንዲለቁና የዜና ሽፋኑን እንዲቆጣጠረው አድርገዋል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡

ይህንን ግምት የሚያጠናክረው ሕወሐት እጅግ ሚስጥራዊ ድርጅት መሆኑ፣አቶ በረከት ይሰሩበት የነበረው ቦታ ከህዝብ ገፅታ የራቀ በመሆኑ ዜናውን በአሁኑ ደረጃ ይፋ ሳያደርጉ በዝግታ መልቀቅ የሚችሉበት እድል ሰፊ በመሆኑ፣አቶ በረከትም በድርጅቱ ውስጥ ያላቸው ቦታ ከፍተኛና ሴራን ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸው፣በድርጅትም ሆነ በሀገራዊ ፖለቲካ የእሳቸው መልቀቅ ዜና ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸው ድርጊቱ ታስቦና ታቅዶ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ በፖለቲካ ስራ ውስጥ አንድ ከባድ አደጋ ሲያጋጥም ያንን ዜና ለመሸፈንና አቅጣጫ ለማስቀየር አዳዳዲስ ዜናዎች ፈጥሮ አቅጣጫ ማስቀየርና ችግሩን ለመፍታት ትንፋሽ የማግኛ ዘዴ አድርጎ መጠቀም የተለመደ ተግባር ነው፡፡


ለማጠቃለል አሁን ያለው እውነታ በተራ ቁጥር 1 ተገለፀው ከሆነ ሀገራችን በፈጣን የለውጥ ማዕበል ላይ ስለሆነች ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በጥንቃቄና በአስቸኳይ ከባድ ሀገራዊ ስራዎች መስራት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ያለው እውነታ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለፀው ከሆነ የውስጥ የድርጅት ሽኩቻ ለትግሉ ከፍተኛ አስተዋፆ ቢኖረውም ጊዜ የሚሰጥና በተረጋጋ ሁኔታ አስቦ ትግሉን ለመምራት የሚቻልበትን ዕድል ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች በወያኔ ሀይል ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ተነገረ

በደቡብ ጎንደር የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች ባሳለፍነው ሳምንት ነበር በወያኔ ሀይል ላይ ጥቃት ማድረሳቸው የተነገረው።  ከለሊቱ 6:00 እስከ 8:00 በቆየው የተኩስ ልውውጥ የወያኔ ፀረ ሽምቆች ሀይሎች እግሬ አውጭኝ በማለት መሸሻቸው የተነገረ ሲሆን

ለማምለጥ በሚሞክሩበት ጊዜም ወደገደል የገቡና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑንም ተነግራል።

በወቅቱ ይህን የወያኔን ፀረ ሽምቅ በዋና አዛዥነት እና በምክትል አዛዥነት ሲመሩት የነበሩ ዋና አዛዥ ማሩ ዋለ እና ምክትሉ ጌትነት ወንድዬ መሽገውበት እና ማዘዣ ጣቢያ አድርገው ይጠቀሙበት የነበረው ሁለት ትልልቅ ክፍሎች ከነ ሙሉ ንብረታቸው እና ዕቃቸው በቦምብ በእሳት መጋየታቸውም ተነግራል።

እነዚህ አዛዦች ሆድ አደር በመሆን ለህወሓት አገልጋይ ሆነው የአካባቢውን ህብረተሰብ መኖሪያቤት ፡ አዝመራ ሲያቃጥሉ እና የህዝቡን የቤት እንሰሳ ሲያርድና ሲዘርፉ የነበሩ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።

ይህ ዘመቻ ከአሁን በኃላ ለሆዳቸው በማደር በማንኛውም መልኩ ለህወሓት አገልጋይ በመሆን እየሰሩ በሚገኙ ሁሉ እርምጃውና ጥቃቱ የሚቀጥል መሆኑን ባካባቢው የተንቀሳቀሱ ያሉት የአርበኞች ግንቦት 7 ዓይሎች መናገራቸውም ተነግራል።
ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ
ሞት ለዘረኛው የወያኔ ቡድን

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ በሀገሪቱ አለመረጋጋት መኖሩ ታወቀ፡፡

እንደ መረጃዎች ገለጻ፣ በተለይ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለው የህዝብ ቁጣ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ሰኞ እና ማክሰኞ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተካሔዱትን ህዝባዊ የስራ ማቆም አድማ እና ተቃውሞዎችን ተከትሎ የተፈጠረው ድባብ አሁንም ድረስ መኖሩን መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በሁለቱም ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች አሁንም መረጋጋት አለመኖሩን የጠቆሙት ማስረጃዎች፣ በዚህም የተነሳ መደበኛው የእለት እንቅስቃሴ መቋረጡን አመላክተዋል፡፡

በባህርዳር የተካሔደውን ከቤት ያለ መውጣት አድማ ተከትሎ ወጣቶችን በገፍ ሲያስር የቆየው አገዛዙ፣ ዛሬም በከተማዋ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በከተማዋ ያለው ድባብ ውጥረት የነገሰበት መሆኑን የሚገልጹት የዓይን እማኞች፣ የመንግስት ወታደሮችም በተለያዩ የከተማዋ መግብያ እና መውጫዎች መሰማራታቸውንም እማኞቹ ጠቁመዋል፡፡ እንዲሁም በዚያው በአማራ ክልል በደብረ ታቦር እና ደብረ ብርሃን ያለው ድባብ ከወትሮዉ የተለየ እና ተቃውሞ ያረገዘ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ሁለቱ ከተሞች ሰኞ ዕለት የስራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በማግስቱ ማክሰኞ አድማውን ቀጥላ ውላለች፡፡ በወልድያ ከተማም የህዝብ ተቃውሞ መቀስቀሱን መረጃዎች እየጠቆሙ ናቸው፡፡

በተያያዘ የተቃውሞ ዜና፤ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ መብቱን እየጠየቀ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ሰኞ ዕለት ተቃውሞዋን በስራ ማቆም አድማ የገለጸችው አምቦ፣ ትላንትም በአድማዋ ቀጥላ መዋሏን መዘገባችን ይታወቃል፡፡ ዛሬም ቢሆን በከተማዋ መደበኛው እለታዊ እንቅስቃሴ አለመከናወኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በወሊሶ ከተማም እንዲሁ ተመሳሳይ የተቃውሞ ድባብ መስፈኑን የጠቆሙት መረጃዎች፣ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ያለው ሁኔታ አለመረጋጋት እንደሚስተዋልበት መረጃዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ልዩ ኮማንዶ በደቡብ ጎንደር ጥቃት አደረሰ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ልዩ ኮማንዶ በደቡብ ጎንደር ጥቃት አደረስኩ ማለት ተነገረ፤፤

አርበኞች ግንቦት ሰባት ልዩ ኮማንዶ በደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ አርበኛ ታጋይ አረጋን ለመያዝ ማዘዣ ጣቢያውን እብናት ከተማ አድርጎ የነበረውን የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ሰኔ 11 ለ 12 ል ከሌሊቱ 7 ፤30 ሲሆንጥቃት እንደፈፀሙ ተገልፃል፤፤

በጥቃቱም የክልሉ የፀረ-ሽብር ግብረሀይል የዘመቻ መምሪያ ሀላፊን ሙሉ ኮማንደር አወቀ የተገደለ ሲሆን ሌሎች ሁለት ከፍተኛ አመራሮች ቆስለው ለህክምና ወደ ባህርዳር ተወስደዋል::

ሌላው ተራ ወታደር ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን የከፍተኛ አመራሩ የኮማንደር አወቀ መገደል በክልለሉ ባለስልጣናት ከፍተኛ ድንጋጠን ሲፈጥር አስከሬኑ በአሁኑ ሰዓት በብዙ መኪና ታጅቦ ወደ ባህር ዳር እንደገባ  ተነግራል፤፤