በዶ/ር አቢይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳ ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቶላቸው እንደነበር ተናገሩ

በዶ/ር አቢይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳ ላይ የወጣው የእስር ትእዛዝ ጠ/ምኒስትሩ ቃለ መሀላ ከመፈጸማቸው አምስት ቀናት በፊት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ህወሃት በጄኔራል ሳሞራ የኑስ ግንባር ቀደም መሪነት እነ አቶ ለማንና ዶ/ር አቢይን በወታደራዊ ኋይል አስገድዶ ዝም ለማሰኘት ሞክሮ እንደከሸፈበት ከዚህ በፊት ገልጸናል (የመጨረሻ የኢህአዴግን ሊቀመንበር ለመምረጥ በሚራኮቱበት ደረጃና እነ አባይ ጸሃዬ ሃይላንድ ውሃ እየተወራወሩ ልዳባደብ ብለው የተፍጨረጨሩበት ወቅት ማለት ነው)

ይህን ወታደራዊ አፈናቸው እንደከሸፋባቸው ሌላ ዙር የእስር ትእዛዝ በእነ ዶ/ር አቢይና አቶ ለማ ላይ መውጣቱ ለእኔ ባያስገርምም ይህን ክስተት ጠ/ምኒስትሩ ዛሬ ይፋ ማድረጋቸውና ብሎም ይህንን ትእዛዝ አስተላላፊዎችን ምንም ሳያደርጉ ባሉበት ስራና ኋላፊነት መተዋቸው (ለጊዜውም ቢሆን ) የገረመኝ ጉዳይ ሆኗል፡፡

እነሱ ለእስር ሲያዘጋጁት ዶ/ሩ ግን ወደ ቤተ መንግስት -ይህ በዘመነ ወያኔ እማይታሰብ ግን የሆነ የአምላክ ስራ እንጂ እነ ዶ/ር አቢይ ጥንካሬና እስማርትነት ብቻውን በቂ ሆኖ ይህን ውጤት አያሳየንም፡፡

ብቻ የዚህ ሁሉ ልዩ ክስተት መጨረሻውን ለማየት ናፍቄያለሁ- ምን ይወጣው ይሆን ያስብላል!!

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment