በዳባት ወረዳ በአጅሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በክትባት ሰበብ አስደንጋጭ ፍጅት በህፃናት ላይ የደረሰ ነው ተባለ

ዛሬ በዳባት ወረዳ በአጅሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በክትባት ሰበብ 4 ህፃናት ሲሞቱ 8 ደግሞ በከፍተኛ ህመም ላይ ናቸው። ይህ የመኪና መንገድ የሌለው አካባቢ የሚሩረት ወገኖች በሄሊኮፍተር እርዳታ ካልደረሰላቸው ብዙ ህፃናት የሞት አደጋ ላይ ናቸው። ዳባት ከተማ ውስጥም በተመሳሳይ መንስኤ 1ህፃን ቅዳሜ ሞቷል።
የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከየካቲት 16/2009 ዓ.ም ጀምሮ በመላ አገሪቱ ስለሚሰጥ ህጻናትን ያስከትቡ በሚል በይፋ የተጀመረው ዘመቻ ህፃናት እየጨረሰ ነውና ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።
ህዝቡ በዚህ አስደንጋጭ ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ወንጀል ቁጣውን እየገለፀ ነው። ከአሁን በሁዋላ አናስከትብም ብሏል። የአካባቢው የወያኔ መንግስት የካቢኔ አመራርና የጤና ሰራተኞች ደንግጠዋል። ይህ ወንጀል በቀጥታ ከወያኔ የበላይ አመራር መጥቶ በአፋኙ የኮማንድ ፖስት ተግባራዊ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ይህ አካባቢ የወያኔ የጭቆና አገዛዝ በቃኝ በማለቱ ላለፉት 6 ወራት የጦር ቀጠና እንደሆነ በተከታታይ ስንዘግብ መቆየታችን ይታወቃል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

14369897_632974823553373_2956361535740993228_n

የዶክተር መረራ ጉዲና ቤተሰቦች ስንቅ ከማቀበል በዘለለ ለማነጋገር እንደማይችሉ ተነገረ

ዶክተር መረራ ጉዲና ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር በመገናኘት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሶስት ወር የሞላቸው ሲሆን ጤንነታቸው አለመታወኩን
ጠበቃቸው ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማሪያም ገለፁ።
የደንበኛቸውን የጤንነትና የምርመራ ሁኔታ የተጠየቁት ዶክተር ያዕቆብ “በሳምንት ለሁለት ቀናት (ረቡዕ እና ዓርብ) ለ30 ደቂቃዎች እኔና ሌላኛው ጠበቃቸው አቶ ወንድሙ ኢብሳ እንድናነጋግራቸው በተፈቀደልን መሰረት እየጎበኘናቸው ነው። ጤንነታቸው በተመለከተ ደህና መሆናቸውን ነግረውናል” ሲሉ የዶክተር መረራ ጤንነት በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዶክተር መረራ በቁጥጥር ስር ውለው በቀድሞ ማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን ላለፉት ሶሰት ወራት ለሶስት ጊዜ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም እስካሁን የክስ ቻርጅ አለመነበቡን የገለጹት የህግ ባለሙያው “በተለይ በሶስተኛው ቀጠሯቸው የክስ ቻርጁ መነበብ እንዳለበት ለፍርድ ቤቱ ብናቀርብም አቃቢ ህግ የሰውና የሰነድ ማስጃዎችን አሰባስቤ አልጨረስኩም በማለቱ ዳኛው ለአራተኛ ጊዜ በደንበኛዬ ላይ ቀጠሮ ሰጥተዋል” ሲሉ ገልጸዋል።
የዶክተር መረራ ጉዲና ቤተሰቦች ስንቅ ከማቀበል በዘለለ ለማነጋገር ያልተፈቀደላቸው መሆኑን የገለጹት ዶክተር ያዕቆብ ደንበኛቸው የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተናግረዋል። ዶክተር ያዕቆብ አክለውም “ዶክተር መረራ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ሰሞን ከእኛ ጋር የምንገናኘው እጃቸውን በካቴና ታሰረው ነበር። ሆኖም ይህ ድርጊት ተገቢ አለመሆኑን በመገናኛ ብዙሃን ከገለጽኩ በኋላ እጃቸውን በካቴና ሳይታሰሩ ነው የምናገኛቸው” ብለዋል።

16266251_1248266475267774_2596220851978438808_n

በጋይንት ለውጊያ የሄደው የወያኔ ጦር ተደመሰሰ

16486916_400669860285745_3212805512513841110_o

ምስራቅ በለሳና ጋይንት ላይ  ለውጊያ የሄደው የወያኔ ጦር 10 ተገድሎ 20 ቆስሎ ሽንፈቱን በመከናነቡ ተበትኖ ቀርቶል ::

በዛም አካባቢ የነፃነት ሀይሎች ድል ቀንቶቸዋል በሌላ የድል ዜና ደግሞ በምስራቅ በለሳ 400 የሚጠጋ የአጋዚ ጦር ተልኮ ከነፃነት ታጋዮች ጋር ቢገጥምም እጅ የማይሰጡ ጀግኖች ይሄን ቅጥረኛ የሆነ ሰራዊት በመፋለም በቁስለኛና በምርኮኛ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ::

በነበረው ትግል ወቅት በነፃነት ሀይሎች ላይ የተወሰነ ጉዳት ቢደርስም አልንበረከክም በማለት የስርአቱ ሎሌ የሆነ ቅጥረኛ ሰራዊት በዚህ የውጊያ ወቅት የተጎዱ በጎንደር ሆስፒታል በዛሬው እለት ህክምና እያገኙ መሆናቸውን በአካባቢው የሚገኙ ታማኝ ምንጮች ገልጠውልኛል ::

በተመሳሳይ ለቃላቸው ታማኝ በመሆን እስከድል ደጃፍ ነፃነታቸውን እስኪያገኙና ድረስ ወደ ሆላ እንደማይሉና ድል በእጃቸው እስኪገባ ድረስ ወደ ሆላ እንደማይሉ በጥብቅ አሳስበዋል

በበለሳ ግንባር በከፋኝ ሃይሎችና በወያኔ መካከል ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው

16114034_379724762420032_2191638666481950464_n

ከጎንደር በደረሰን መረጃ መሰረት ብዛት ያላቸው የወያኔ ወታደር የጫኑ መኪኖች ወደ በለሳ ግንባር እየሄዱ ስለሆነ መረጃው ለህዝባችን በቶሎ ይድረስ።

ላለፉት ሶስት ቀናት በበለሳ ግንባር በከፋኝ ሃይሎችና በወያኔ መካከል ከባድ ውጊያ እየተደረገ ሰንብቷል። የከፋኝ ሃይሎች የተቀናጀ ትግል ለማድረግ በለሳ ውስጥ ለማድረግ አቅደውት የነበረው ጉባኤ ወያኔ መረጃ ስለደረሰው ለጊዜው ሳይከናወን ቀርቷል። ይሁንና ይህን መረጃ ያወጣው እከሌ የሚባል የጎበዝ አለቃ ነው በማለት ሃላፊነት በጎደለው መልኩ በአንዳንድ ሃይሎች መራገቡ በእንጭጩ መታረም ካልቻለ በትግል ላይ ያሉትን መከፋፈል ብሎም ለአደጋ ማጋለጥ ነው።

በተጨማሪም በማህበራዊ ሚዲያ መረጃ የምትለቁ እጅግ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በትህትና ልለምናቹህ። እባካቹህ የጎበዝ አለቆችን ስምና የትግል ቦታወች አትጥቀሱ። ምስላቸውንም አታሳዩ። በስልክ እየደወላቹህም ዝርዝር ጉዳይ አታውሩ። ወያኔ ከፍተኛ የሆነ የስልክ ጠለፋ እያደረገ ለመሆኑ ተደጋጋሚ ሪፖርት አውጥተናል።
ድል ለጀግኖቻችን!
ህዝብ ያሸንፋል®!
ሙሉነህ ዮሃንስ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ6 አየር ሃይል አባላት ላይ የእስራት ቅጣት አስተላለፈ

የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ስድስት የአየር ሃይል አባላት ላይ ከሶስት እስከ 10 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት አስተላለፈ።
ከሳሽ አቃቤ ህግ በሰኔ 2007 አም ተከሳሾቹ የአየር ሃይልን በመክዳት ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ እንደተያዙ በክሱ አመልክቶ እንደነበር ይታወሳል።
የቀድሞው የአየር ሃይል አባላት ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል የማፍረስ አላማ ይዘው በሽብር ድርጅት ውስጥ አባላት በመሆንና በሽብር ድርጊት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው የሚል ክስን አቅርቦ እንደነበርም በወቅቱ መዘገባችን አይዘነጋም።
ይሁኑ የክስ ሁኔታ ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ በስድስቱ ተከሳሾች ላይ ከሶስት አመት እስከ 10 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ማስተላለፉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ መ/አ ብሩክ አጥናዬ፣ መ/አ ዳኔኢል ግርማ፣ መ/አ ጋዘኸኝ ድረስ እንዲሁም አቶ ተስፋዬ እሸቴ እና አቶ ሰይፉ ግርማ ስድስቱ ተከሳሾች ናቸው።
ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያሉት መቶ አለቀ ተከሳሾች በ10 አመት አምስተኛና ስድስተኛ ተከሳሾች ደግሞ በሶስት አመት ከስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ታውቋል።
ከተከሳሾቹ መካከል መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤና ስደተኛ ተከሳሽ ሰይፉ ግርማ በሃምሌ ወር በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት አደጋ እጃቸው አለበት ተብሎ ተደራራቢ ክስ ከተመሰረተባቸው በርካታ እስረኞች ጋር እንደሚገኙበትም ለመረዳት ተችሏል።
የፍርድ ውሳኔው ሰኞ በተላለፈበት ወቅት አንደኛ ተከሳሽ ከግንቦት ወር 2008 አም ጀምሮ በጨለማ ክፍል እንዲቆዩ መደረጋቸውንና ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተገናኝተው እንደማያውቁ ለችሎት አስረድተዋል።
ከእነዚህም በተጨማሪ በምርመራ ወቅት ከባድ ድብደባ ሲፈጸምባቸው መቆየቱንና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጸምባቸው እንደነበር አቤቱታቸውን አሰምተዋል።

15542125_1875786285986970_8207959935562296567_n

%d bloggers like this: