በፒያሳ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ከመኖሪያ ቀያቸው ሊነሱ መሆኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚኖሩ 10ሺ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ከመኖሪያ ቀያቸው ሊነሱ መሆኑ ተገለጸ።


ከተቆረቆረ ረጅም ጊዜ እንደሆነ በሚነገርለት በዚሁ አካባቢ በርካታ በቅርስነት መፍረስ የሌለባቸው ህንጻዎች ያሉ ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና የታሪክ ምሁራን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
አካባቢውን በቀጣዮቹ ስድስት ወራቶች ሙሉ ለሙሉ ለማፍረስ ሃላፊነት የተሰጠው የአራዳ ክፍለ ከተማ፣ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጨምሮ 14 ቤቶች በቅርስነት በመታየታቸው እንደማይፈርሱ አስታውቋል።


ይሁንና የከተማ ነዋሪዎች አካባቢው ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ በመሆኑን ከ14 በላይ የሚሆኑ ይዞታዎች በቅርስነት መያዝ እንደሚኖርባቸው ጥያቄ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
በሰራተኛ ሰፈር በወረዳ 10 ቀበሌ 10 እና 13 ዙሪያ ያሉ 1ሺ 600 መኖሪያ ቤቶች በተያዘው አመት መጨረሻ ድረስ ሙሉ ለሙሉ እንደሚፈርሱና በድርጊቱ ወደ 10 ሺ አካባቢ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንደሚነሱ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ስር ያሉ ቤቶች እንዲሁም በተለያዩ አካላት ይዞታ ስር የነበሩ በርካታ የንግድ ተቋማት በመልሶ ማልማት ሂደቱ አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ እንደሚያደርግ ለመረዳት ተችሏል።
አካባቢውን የማፍረስ ሂደቱ እንደተጠናቀቀ የከተማዋ አስተዳደር ሰፊ ቦታውን በሊዝ ጨረታ ለአልሚዎች ለመሸጥ እቅድን የያዘ ሲሆን፣ ከመሬት ሽያጩ በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚሰበሰብ ተመልክቷል።
በክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ሃላፊ የሆኑት አቶ ዮሃንስ አድማሱ ነዋሪዎቹን ለማንሳት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል ሲሉ ለጋዜጣው አስረድተዋል።


ከ1ሺ በላይ በሚሆኑ የቀበሌ ቤት ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ተነሺ ነዋሪዎች አቅማቸው የሚፈቅድ ከሆነ የኮንዶሚኒየም ቤት በአማራጭነት እንደሚቀርብላቸውና አቅም የሌላቸው ደግሞ በተለያዩ አካባቢዎች በቀበሌ ቤት እንዲገቡ እንደሚደረግ የአራዳ ክፍለ ከተማ አስታውቋል።
በግል ይዞታ ስር ላሉ 260 አካባቢ ነዋሪዎች ደግሞ ምትክ ቦታና ካሳ እንደሚሰጣቸው አቶ ዮሃንስ ገልጸዋል። ይሁንና ሃላፊው ለግል ይዞታ ላላቸው ተነሺዎች የሚሰጣቸውን የመሬት እና የካሳ መጠን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማስፋፋት የያዘው እቅድ አለመሳካቱን ተከትሎ ከአልሚዎች ለሚቀርብለት የመሬት ጥያቄ ፊቱን በመዲናይቱ ማደረጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት አስረድተዋል።


አስተዳደሩ በተያዘው እና በቀጣዩ አመት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በርካታ ነዋሪዎችን በልማት ስም በማንሳት መሬትን ለባለሃብቶች በሊዝ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።
ይሁንና ከተያያዙ አካባቢዎች በመነሳት ላይ ያሉ ተነሺዎች መሰረተ ልማት ወዳደ አልተማላለት ቦታ እንዲሄዱ መደረጉን ሲቃወሙ ቆይተዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከግል ይዞታ የተነሱ ነዋሪዎች የሚሰጣቸው ምትክ ቦታና የካሳ ክፍያ በጣም አነስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ።

ሰሜን ኮሪያ የኢትዮጵያን እና የሌሎች አገራትን ባንክ ብርበራ (Hack) ማድረጓ ታወቀ

የሩሲያዉ የሳይበር ጥበቃዉ ተቋም ባወጣዉ ራፖርት ሰሜን ኮሪያ የአገራትን ባንኮች አገራቱ ሳያዉቁ እየበረበረች እንደሆነ አስታወቀ።

ይኸዉ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ተቋም ባወጣዉ ራፖርት ናይጄሪያ፤ ኢትዮጵያ፤ ጋቦን፤ ኢራቅ፤ ኬንያ እና ሌሎች 13 አገራትን ያካተተ ብርበራ ማድረጓን አያይዞ ገልጿል። የሳይበር ደህንነት ተቋሙ በ18 አገሮች ላይ ሰሜን ኮሪያ ሙከራ ማድረጓን ሲገልጽ በሁለት ኢንተርናሽናል ኤክስፐርቶች በተገኘዉ መረጃ መሠረት ምን አልባትም ይህንን በማጭበርበር የምታገኘዉን ገንዘብ ለኒዩክለር አላማ ልታዉለዉ እንደምትችል እምነት አሳድረዋል።

ባንኮችና የደህንነት ተቋማት አጥኝዎች ከዚህ በፊት አራት (4) የዚሁ አይነት ተመሳሳይ የሳይበር ሙከራዎች በባንግላዴሽ፤ ኢኳዶር፤ በፊሊፕን እና በቬትናም የፋይናንስ ተቋማት ላይ ሙከራ ተደርጎ እንደነበርም አስረድተዋል።

ካስፐርስኪ የተባለዉ የሩስያ የሳይበር ደህንነት ተቋም ላዛረስ በሚል መጠሪያ ተመሳሳይ የሆነ የኮስታሪካን፤ የኢትዮጵያን፤ የጋቦንን፤ የኢንዲያን፤ኢንዶኔዢያ፤ የኢራቅ፤ የማሊዢያ፤ የኬንያ፤ የናይጄሪያ የፖላንድ፤ የታይዋን እና ኡራጓይ የፋይናንስ ተቋማትን ብርበራ እንደተደረገም ደርሰዉበታል።

ካስፐርስኪ ብርበራ መደረጉን የሚያሳይ ዱካ ካገኘ በኋላ ባደረገዉ ክትትል ከሰሜን ኮሪያ ጋር ንክኪ ያለዉ ነገር ማግኘቱን ተከትሎ በግሩፕ ላዛረስ በሚል መጠሪያ እንድሚንቀሳቀስም የአለም አቀፉ የፕሬስ ትብብር ባለፈዉ ማክሰኞ ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።

እንደ ሪፖርቱ ገለፃ ከሆነ እነዚሁ የፋይናንስ ተቋማትን ሚበረብሩት ቡድኖች የመጀመሪያ ብርበራቸዉን የጀመሩት ፈረንሳይ ዉስጥ ባለ የኮምፒዩተር አገልግሎት መስጫ ሲሆን በሰሜን ኮርያ እና በታይዋንም ማድረጋቸዉ በቀላሉ ፈልጎ ለማግኘት እንዳልተቻለ እና በተለያየ ቦታ መደረጉ የችግሩ መነሻን ለማግኘት አስቸጋሪ እንዳደረገባቸዉ ኤክስፐርቶቹ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ላዛረስ የሚባለዉ ይኸዉ ግሩፕ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የዚህ አይነት ጥቃት የጀመረዉ በ2015 እ.ኤ.አ እንደሆነ ጥናትና ምርምር የሚያደርገዉ BAE systems, FireEye and Symantec. የሚባለዉ ተቋም አስረድቷል።

“በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት ጠባቂዎች ወደ እስረኞች ተኩሰዋል” – ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

ነሐሴ 28/2008 ዓ.ም. በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎና ለደረሰው ጉዳት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አባላት በሕግ እንዲጠየቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ የፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት አቅርቧል።

በአተት በሽታ ምክኒያት ምግብ ከውጭ አይገባም በሚለው የማረሚያ ቤቱ ውሳኔ የተበሳጩ የቀጠሮ እስረኞች ባስነሱት አድማ መነሻነት ከውጭ በገቡ እንደ ላይተር ባሉ አቀጣጣይ ነገሮች መነሻነት የተነሳ ቃጠሎ መሆኑን የሚጠቅሰው ሪፖርቱ ቃጠሎው ከደረሰ በኋላ አብዛኞቹ የቀጠሮ እስረኞች ከእሳቱ ራሳቸውን ለማዳን ሲሞክሩ ከውጭ በጥበቃ አባላት የተኩስ እሩምታ እንደተከፈተባቸና አስለቃሽ ጭስም ከውጭ ወደ ውስጥ እንደተኮሰ ተዘርዝሯል።

በተጨማሪም ለማምለጥ የሞከሩ ሁለት እስረኞች በጥይት ተመተው መገደላቸውን ሌሎች ስምንት እስረኞች ቆስለዋል ተብሏል።

ጽዮን ግርማ ሪፖርቱን በተመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰብዓዊ መብት ምርመራ ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አባዲን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

http://amharic.voanews.com/pp/3804210/ppt0.html

በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በብዛት አየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጫችን ገልፆ

ጎንደር የወያኔ ስርዓትን ጭንቅ ውስጥ እንደከተተችና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሰሜን ጎንደር በጠላት እጅ መውደቋን አመራሩን ዋና የችግሩ መንስኤ አድርጎ የቆጠረ ስብስባ በጎንደር ከተማ እየተደረገ እንዳለና የህውኃት ከፍተኛ መኮንኖች ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ አስተማማኝ መረጃዎች አሰታወቁ፡፡
በስብሰባው ሳሞራ የኑስን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ መኮንንኖች የተገኙበት ነው ተብሏል፡፡ ከተማዋም ከፍተኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በብዛት አየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጫችን ገልፆልናል፡፡
**
በሚያዚያ 21-28/2009 ዓ/ም በጎንደር ከተማ የሚከበረው የከተሞች ፎረም ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን በአሉንም አናከብርም የሚል ይዘት ያለው ፁሁፍ ወረቀት እንደተበተነ የተበተነውን ወረቀት ያዪ የአየን እማኞች ገልፀውልናል።
ለመሆኑ የከተሞች ፎረምና በዐል እነ መቀሌ ያክብሩት እንጂ ለ26 አመት ሆነ ተብሎ እንዳታድግ ለተደረገችው ጎንደር ከተማ ምኗ ነው፡፡ ጎንደር ላይ ባለፉት አመታት ምንስ ሰራን ብለው ሊያስጎበኙ ይሆን ለሚመጡት እንግዶች ነው ወይስ በዐሉ ጎንደርን ላለፉት 26 አመት እንዴት እንደገደሏት በተግባር ልምድ መቅሰሚያ ከተማ መሆኗን ሊያሳዯት፡፡ የወያኔ የለበጣ ስላቅ አያልቅም መቸም!

በጎንደር የወያኔ ቁልፍ የደህንነት አባል በነጻነት ኃይሎች ተረሸነ

በጎንደር ዙሪያ ደጎማ ከተማ የደህንነት አባል በሆነ ቢራራ ስመኝ በተባለ ግለሰብ ላይ መጋቢት 13 ቀን ከቀኑ 9:40 ላይ ልዩ ቦታው አይና ሽዋና በተባለ ቦታ ላይ ተገድሏል። የግለሰቡ ቀብርም ደጎማ አይና ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

የነጻነት ኃይሎች በወሰዱት ተከታታይ ጥቃቶች የተደናገጠው ወያኔ፤ ታጋዮችን አምጡ እያለ አርሶአደሮች መደብደብ እና ማሰር ይዛል፡፡ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይለሀል ይሄ ነው፡፡

የነፃነት ኃይሎች ወደ ጋይንት ከተማ በመግባት በወያኔ አማሪኛ ክፍል ብአዴን ጽ/ቤት እና ሹመት በተባለው አስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊ ላይ እርምጃ መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በተከታታይ በተካሄደው ዘመቻ በነፃነት ኃይሎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የለም።

%d bloggers like this: