በጎንደር የወያኔ ቁልፍ የደህንነት አባል በነጻነት ኃይሎች ተረሸነ

በጎንደር ዙሪያ ደጎማ ከተማ የደህንነት አባል በሆነ ቢራራ ስመኝ በተባለ ግለሰብ ላይ መጋቢት 13 ቀን ከቀኑ 9:40 ላይ ልዩ ቦታው አይና ሽዋና በተባለ ቦታ ላይ ተገድሏል። የግለሰቡ ቀብርም ደጎማ አይና ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

የነጻነት ኃይሎች በወሰዱት ተከታታይ ጥቃቶች የተደናገጠው ወያኔ፤ ታጋዮችን አምጡ እያለ አርሶአደሮች መደብደብ እና ማሰር ይዛል፡፡ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይለሀል ይሄ ነው፡፡

የነፃነት ኃይሎች ወደ ጋይንት ከተማ በመግባት በወያኔ አማሪኛ ክፍል ብአዴን ጽ/ቤት እና ሹመት በተባለው አስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊ ላይ እርምጃ መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በተከታታይ በተካሄደው ዘመቻ በነፃነት ኃይሎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የለም።

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ ስፍራዎች ማክሰኞ ምሽት ጥቃት ፈጸሙ።

ከአይን ምስክሮችና ከንቅናቄው ምንጮች ለመረዳት እንደተቻለው በጭልጋ፣ ደንቢያና በጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በተመሳሳይ ቀንና በተቀራራቢ ሰዓት በመንግስት ሃይሎችና ተቋማት ላይ ጥቃት ተፈጽሟል።
በትግል ላይ እያሉ መስዋዕትነት በከፈሉት ሻለቃ መሳፍን ጥጋቡ ወይንም ገብርዬ እንዲሁም በታጋይ ጎቤ መልኬ እና በአበራ ጎባው ስም የተሰየሙት ወታደራዊ ዘመቻዎች፣ ማክሰኞ መጋቢት 5 ፥ 2009 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን መግደልና መቁሰል ጭምር ማስከተላቸውንም ለመረዳት ተችሏል።
ዘመቻ “ዋዋ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚሁ ጥቃት ከጎንደር 80 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ በሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በተሰነዘረ ድንገተኛ ጥቃት 3 ወታደሮች ሲገደሉ፣ 15 መቁሰላቸው ተመልክቷል። በአምስቱ ላይ የደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ጎንደር ሬፈራል ሆስፒታል ሲወስዱ፣ ቀላል ጉዳት የደርሰባቸው 7 ወታደሮች በመተማ ገንዳ ውሃ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን የተገኘው ዜና ያስረዳል።
በቅርቡ በትግል ሜዳ ላይ እያሉ የተሰውትን ጎቤ መልኬን ለማስታወስም በስማቸው መጠሪያ “ዋዋ” የተሰየመው ዘመቻ ተሳታፊ የሆኑት የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊዎች ጥቃቱን ፈጽመው ወደ ነበሩበት መመለሳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በመከላከያ ሰራዊት በኩል በቡድን መሳሪያ የተደገፈ የአጻፋ ምላሽ መሰጠቱም ተመልክቷል። በመትረየና ላውንቸር የተደገፈውን የአጸፋ ምላሽ ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱንና የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡም ተመልክቷል።
በዚሁ በጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ በተመሳሳይ ቀን ዘመቻ ገብርዬ በሚል በተሰየመው ወታደራዊ ዘመቻ በቆላ ድባ ከተማ በሚገኝ የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በተከፈተ ዘመቻ የአስተዳደር ጽ/ቤቱ በከፊል ሲወድም፣ የአስተዳዳሪው መኪና መቃጠሉንም የመጣው ዜና ያስረዳል። በተመሳሳይ ጯሂት ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በካምፕነት በሚጠቀሙበት ቁጥር 2 በተባለው ጽ/ቤት ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በወታደሮቹ ላይ የቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአብራጅራ ከተማ አብራጅ ጽ/ቤት በሰፈሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ እንዲሁም በቸንከር ቀበሌ የከተማዋ ኮማንድ ፖስት ማዘዣ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። በጥቃቱ የቸንከር ቀበሌ ኮማንድ ፖስት ማዘዣ ጣቢያ ሲወድም፣ አንድ የኮማንድ ፖስቱ አባል መጎዳቱንና አንድ መጋዘን መቃጠሉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች መሳሪያ አንስተው በትግል ላይ ከነበሩት አንዱ በነበረውና መስዋዕትነት በከፈለው በአበራ ጎባው ስም በተመሳሳይ ቀን በጎንደር ዙሪያ የአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎች ጥቃት መፈጸማቸውም ተመልክቷል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊዎች ማክሰኞ መጋቢት 5 ፥ 2009 እኩለ ሌሊት አካባቢ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በደጋማ ከተማ በወህኒ ቤት እንዲሁም ኮማንድ ፖስቱ በሚጠቀምባቸው ቢሮዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል። እንዲሁም የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል በሆኑት በአቶ ደሴ ዘገየ መኖሪያ ቤት ላይም ተመሳሳይ ጥቃት መከተሉንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

የህወአት ተላላኪው ብአዴን ከ1000 በላይ አመራሮችን ከሀላፊነት አገደ

ከመጋቢት 1 እስከ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ የነበረው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 1,091 በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የነበሩ አመራሮችን ከኃላፊነት በማገድ ተጠናቀቀ፡፡

ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኰንን በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ ክልሉ ካሉት አመራሮች መካከል 1091 የሚሆኑትን በብልሹ አሠራር፣ በአቅም ውስንነትና በሌሎች ጉድለቶች ተገምግመው ከኃላፊነት እንዲነሱ ተደርጓል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለጻ እነዚህ ግለሰቦች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ እንደሠሩት ጥፋት ታይቶ በሕግ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡

ከኃላፊነት የመታደግ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረ፣ የአዊ ዞን የቀድሞ አስተዳዳሪና በኋላም የአማራ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ባዘዘው ጫኔ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ድርጅቱ በክልሉ ውስጥ በተለይም ከባህር ዳር ከተማ ማደግ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የቤት ችግር ለመፍታት፣ የተለያዩ አሠራሮችን ለማስፈን መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መጠናቀቅ ማግሥት የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ከመጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡ በዚህ ጉባዔም ለክልሉ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ አዳዲስ አዋጆች እንደሚፀድቁ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ተከትሎ የአዲሳባ ሴቶች ስጋት ላይ መውደቃቸው ተነገረ :p

ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ… ”ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን እኛ ያለንበት የእድገት ደረጃ ላይ በነበሩ ግዜ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት የሴቶቻቸውን ጸጉር እየቆረጡ ኤክስፖርት ለማድረግ ተገደው ነበር…” ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መናገራቸውን ተከትሎ… አንዳንድ በአዲሳባ የሚኖሩ ሴቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄንን ያሉት ነገ ከነገ ወዲያ የእኛንም ጸጉር አጭደው ገበያ ለማውጣት ፈልገው ነው በማለት እያናፈሱ ያለው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን የሴቶች ወጣቶች እና ህጻናት ሚኒስቴር ገለጸ!

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አያይዞ እንደገለጸው… ባመዛኙ የከተማዋ ሴቶች በግዢ ጸጉር እያጌጡ እንደሚወጡ የደህንነት እና መረጃ ጸረ ሽብር ግብረ ሃይል ቀድም ሲል መረጃው ያለው በመሆኑ መንግስታችን የከተማዋን ሴቶች ጸጉር አጨዳ በመሰማራት አላስፈላጊ ወጪ እንደማያወጣ ገልጸው… ‘መንግስት ጸጉራችንን ቆርጦ ኤክስፖርት ሊያደርግ አስቧል’ በሚል ውዥንብር ውስጥ የገቡ ሰላማዊ የከተማ ሴቶች ወሬው መሰረት የለሽ መሆኑን ተረድተው ሰላማዊ እና ህጋዊ መሽቀርቀራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል። …

የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱም፤ መንግስት ጸጉሬን ይወስድው ይሆናል በሚል ያልተጨበጥ ስጋት ዝረክርክ ብለው በሚወጡ ሴቶች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል!!!

የሚታገሉትን የማያቁ የአማራ ነን ባዮች የከሸፈ ስልት

ለሀያ አምስት አመት ተንሰራፍቶ ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ የሚገኘው ትግራይን ለመገንጠል አላማ አድርጎ የተነሳ ግን የሚታገለው በማጣቱ የሀገሪቱ መራሒ መንግስት በመሆን በሀገሪቱን ዜጎች የፈለገውን በማሰር፣ ኣሰቃቂ ድብደባ በመፈጸም እና በመግደል እስከወዲያኛው ትውልድ ድረስ ተከፍሎ የማያልቅ ብድር በሀገሪቱ ስም በመበደር የሕወሓት ባለስልጣናት በየግል ካዝናቸው በስበብ አስባቡ ዘርፈው አከማችተውታል።

ግፍ የመረረው ህዝባችን በእልህ እና በቁጭት መሳሪያ አንግቦ ለነጻነት የትጥቅ ትግል ከሕወሓት ወታደር ጋር በሚያደርግበት ስአት ህዝቡን በሞራል እና በገንዘብ አይዞህ እንደማለት የነጻነት ትግል በሚያካሒዱ የፖለቲካ ድርጂቶች እና መሪዎቻቸው አልፎም በንቁ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች ላይ ያነጣጠረ መንቻካ ዘመቻ ለበርካታ ሳምንት ማህበራዊ ሚዲያውን ለመበጥበጥ የነጻነት የትግል አቅጣጫውን እንዲስት ሆን ተብሎ ደጎስ ያለ ድጎማ ከህወኃት በሚያገኙ ጥቀመኞች ጥቃት ሲሰነዘር መቆየቱ ብዙዎችን አሳዝኗል፣አበሳጭቷል።

ስለሆነም በተለይ በአማራ እና በኦሮሞ መብት ተሟጋች ነን በሚሉ ኢትዮጵያዊነት ባህልን ያቆሸሸ እና ታሪኩን ያሳደፈ ምግባር የታየ ሲሆን የአግ፯ ደጋፊ ነን የሚሉ ጥቂት ሰዎችም ለተሰነዘረባቸው አላስፈላጊ ዘመቻ ምላሽ ለመስጠት በእልህ ውስጥ በመግባት ያደረጉት ምልልስ ተገቢ አልነበረም።

ለሀገር እና ለወገን መብት ውድ ህይዎታቸውን ለመገበር በርሃ የገቡ ጄግኖቻችን ሞራል በተራ ስድብ የሚፈታ የመሰላቸው ሽባ የወያኔ ቅጥረኞች ከዚህ ስራቼው እንዲታቀቡ አስቀድመን እንመክራለን። ማንኛውም ኃይል እና ጉልበታችን ወያኔ ላይ ለማሳረፍ በአዲሱ የፈረንጆች አመት ዳር እስከዳር መያያዝ አለብን።
ድል ለነጻነት ታጋዮች

14956437_220660495029930_1633004519583544399_n

%d bloggers like this: