የወልቃይት ማንነት ጥያቄ ያነሱ 12 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ተከሰሱ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በክሱ ላይ የሽብር ቡድን አመራር መባላቸውን ጠበቆች ተቃውመዋል ተከሳሾቹ ከጎቤ መልኬና ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር በመገናኘት ወልቃይት ውስጥ የሚገኙትን የመንግስት ደጋፊዎችና የትግራይ ተወላጆችን የሰፈራ ቦታ በመለየት ጥቃት ለመፈፀም ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄን ያነሱ 12ቱ ግለሰቦች ‹‹የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከዞን እስከ ክልል ከዚያም አልፎ እስከ ፌዴሬሽን ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

አሁን ግን ጥያቄያቸው ተግልብጦ በሽብር ወንጀል ተከሰዋል። ተከሳሾቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል በመሆን በመደራጀትና የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል፥ የአካባቢው ነዋሪ ላይም ከባድ ስጋት ፈጥረዋል›› በሚል ተወንጅለዋል፡፡

ተከሳሾቹ ከጎቤ መልኬና ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር በመገናኘት ወልቃይት ውስጥ የሚገኙትን የመንግስት ደጋፊዎችና የትግራይ ተወላጆችን የሰፈራ ቦታ በመለየት ጥቃት ለመፈፀም ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስም ቀርቦባቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ በተለይ ከኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር በመገናኘት የወልቃይት አማራ የማንነት ጥያቄን ለመመለስ የመንግስት ደጋፊዎች ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ተልዕኮ ወስደዋል በሚልም ተፈርጀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአርማጭሆና ወልቃይት ከሚገኙ የግንቦት ሰባት ታጣቂዎች፣ እንዲሁም በክሱ የግንቦት 7 አመራር ነበር ከተባለው ጎቤ መልኬ ከሚመራቸው 80 ያህል ታጣዊዎች ጋር ጫካ ገብተዋል ይላል በሕወሀት ኣአቃቤ ሕግ የቀረበባቸው የክስ ሰነድ። ወልቃይት ውስጥ በነበረ የመንግስት ጦር ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የትግራይ ተወላጆችና ባለሀብቶች የሰፈራ መኖሪያ ካምፖች ላይ ጥቃት አድርሰዋልም ነው የተባሉት፡፡

ከተከሳሾቹ መካከል አብዛኛዎቹ ወልቃይት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆኑ መኖሪያቸው ሰ/ጎንደር ጠገዴ ወረዳ የሆኑ ሁለት ተከሳሾች ‹‹እኛንም የወልቃይት ጥያቄ ይመለከተናል›› ብለው አብረው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጠበቃ የደንበኛቸው ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ሁኔታ በዚህ ክስ ‹‹የሽብር ቡድን አመራር›› ተብለው መጠቀሳቸው የኮሎኔሉን በህግ ፊት ንፁህ ሆኖ የመታየት መብት የነፈገ መሆኑን በመግለፅ ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡ በሌሎች ክሶች ላይም ኮሎኔሉ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጠቀሱ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ አቤቱታቸውን በክስ መቃወሚያ ማቅረብ እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

Advertisements

በደቡብ ጎንደር ያለው ውጥረት ቀጥላል ተባለ

በጎንደር የደጋ መልዛ፡ የመቀጠዋ፡ የዙ ሀሙሲት ፡የደብር አባጃሌ፡ የክልቢ፡ ወጣቶች ከተማውን ከበውታል የወያኔ መከላከያ እብናት አሁንም ስላለ ከእነርሱ ጋር ለመግጠም ተዘጋጅተዋል በተለይ ደብር አባጃሌ ቀበሌ ከባድ ውጥረት እንዳለ ይነገራል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት ልዩ ኮማንዶ በደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ የመሸገውን የወያኔን ጦር ማጥቃቱንና በጥቃቱም የክልሉ የፀረ፡ሽብር ግብረሀይል የዘመቻ መምሪያ ሀላፊን ሙሉ ኮማንደር አወቀን መግደሉን ተናግረን ነበር። ውጥረቱ የቀጠለ ሲሆን ያካባቢው ወጣቶች ባጠቃላይ ከዚሁ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ጎን መቆማቸው ተነግራል።

ሰበር ዜና በሁመራና አርማጭሆ የተደረገው የእርቅ ሙከራ ከሸፈ!

ሸማግሌዎች የተባሉት ብዛት 16 ሲሆኑ አብራሃጅራ ላይ አሰማራዉ መኮነን የተባለ የወያኔ ተላላኪ፣ አብደራፊ ላይ ዋኘዉ አቡሃይ፣ ፋሲል አሻግሬ፣ አድምጠዉ ታደሰ
ሲሆኑ ዳንሻ ላይ የወያኔ አሽከር የሆነ በገዘብ ትግሬ ነኝ የሚል ካህሳይ ሐብቱ ከ1986 ጀምሮ የወልቃይትና የጠገዴ ተወላጆች በገዘብ እየተገዛ ካሰገደለ በኋላ ወያኔ የቀጠሩት
ነው። እሱ እና ሌላው ሹምየ የተባሉት በሃገሬው ህዝብ ተከዜ ወዲህ ቤት እዳትሰሩ ተብለዉ የተወገዙ በመሆኑ ትግራይ ሄደው ቤት የሰሩ ናቸዉ። የጎንደርን ሕዝብ ወክለው
በምንም መልኩ ከትግሬወች ጋር ሊነጋገሩ አይችሉም። ይልቅ የአርማጭሆ ህዝብ ለምትገሏቸው ወንድሞቻችን ሃላፊነት ውሰዱ፣ የአሰራቹሃቸውን ወገኖቻችንን ኮለኔል
ደመቀን ከነ ወልቃይት ኮሚቴወች በሙሉ ፍቱ፣ መሬታችንን ልቀቁ፣ ማንነታችንን አክብሩ ብለው እቅጩን ነግረዋቸዋል።
ሁመራ ላይ በተደረገው የእርቅ ድራማ ደግሞ የተገኙት በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ ወልቃይቴወች አልተገኙም። የስብሰባው መሪ የሆነው የወያኔ ሹም ህዝቡ
ከወልቃይቴወችና ጠገድቸወች ጋር የማለሳለስ ስራ እንድትሰሩ ሲላቸው በአንድ ወላጁ ግማሽ ወልቃይቴ የሆነ ወጣት መንግስት የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ እሮሮ መስማት
ሲገባቹህ የእናንተ አፈና ነው ይህን ችግር ያመጣው ብሎ በድፍረት ተናግሯል።
በአጠቃላይ ወያኔ በእርቅ ስም የህዝቡን ትግል ለመቀልበስ የሞከረው ሙከራ ከሽፏል። የጎንደር ህዝብ ወልቃይት ላይ ከ1972 ጀምሮ ከዛ ቆላማው ወገራ ከ1974 ጀምሮ
ዳባት ላይ ደግሞ ከ1977 ጀምሮ አብዛኛው የጎንደር ቦታ ላይ እስከ 1983 ከወያኔ ጋር እጅግ ዘግናኝ ጦርነት ሲያደርግ ኖሯል። አሁን ደግሞ ፀረ ወያኔ ትግሉ ስልቱን እየቀያየረ
ጎንደር ላይ ሳይቋረጥ ከሃምሌ 5 2008 ከጀመረ ድፍን አንድ አመት ሞላው።

በጎንደር ከተማ ትናንት የተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ዝርዝር ደርሶናል

ትናንት ለሊት 10:20 ሲሆን ኮሎኔል አጠና ተፈራ በተባለው የወያኔ አመራር ላይ በጎንደር ከተማ በቀበሌ 18 በሚገኘው መኖሪያ ቤት በቦንብ ተጠቅቷል። ይህ ሰው ለህወሓት አገልጋይ በመሆን እስከ ኮኔሪል ማዐረግ የደረሰ ከዚያም በ20008 ዓ/ም በነበረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ ጎንደር ተመድቦ በርካቶችን የገደለ ትዕዛዝ በመስጠት ያስገደለ በሐምሌ 05/2008 በነበረዉ እንቅስቃሴ ሲሳይ ታከለ እና ሰጠኝ ባብል የተባሉትን ባላሃብቶች የገደለውን አለቃ ይህንስ የተባለውን የህወሃት የደህንነት አባል ከቤቱ በመደበቅ ይህን በደም የተጨማለቀ ወንጀለኛ ከ3 ቀን በሃላ አጅቦ አክሱም አድርሶ ተመልሳል ።

ይህ ሰው በአሁኑ ጊዜ የማራኪ ክፍለከተማ ምክትል አስተዳዳሪ እና የአስተዳደርና ፀጥታ ኅላፊ በመሆን ተሹሞ በርካቶችን ይገድላል ያሰቃያል ለዚህ ሰው እና ለመሰሎቹ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከዕኩይ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ብቦንብ ሊጠቃ ችላል ።

የወያኔን ፀረ-ህዝብ ኃይል እንበትነዋለን፡፡

የጎበዝ አለቆች ለወያኔ በማደር መንገድ በመምራትና በመጠቆም የተባበሩት ላይ እርምጃ ተወሰደባቸው

ከጎንደር ከተማብዙም ባራቀ ስፍራ ላይ በምትገኘው የገደብጌው ከተማ ውጊያው ማክሰኞ ሌሊት እስከ እሮብ ንጋት ነበር። ወደ ገደብጌ ሁለት ተልዕኮወችን ይዘው ነበር የገቡት። አንደኛው ደሳለኝ አስላከ የተባለ ዋና የወያኔ ጠቋሚና መንገድ መሪ ሰው ነበር። በወገን ላይ እየጠቆመ ለጠላት አሳልፎ በመስጠት ያሳሰረና ያስገደለ ነው። ከድርጊቱ እንዲታቀብ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ በተደሃጋሚ አልቀበልም ያለው ሰውየው ለስብሰባ ወደ ባህር ዳር ሄዶ ነበር። እናም ሲመለስ ተጠብቆ እርምጃ ተወሰደበት። ደሳለኝ አስላከ እርምጃ ተወስዶበታል። ቀብሩ ተፈፅሟል።

ሁለተኛው ተልዕኮ ከተማው የሰፈረው የወያኔ ሃይል ላይ ጥቃት መፈፀም ነበር፡፡ ሁለቱም ተልዕኮወች በድል ተጠናቀዋል። የወያኔ ሚሊሻና ልዩ ሀይሎች ጀግኖቹን ለመክበብ ሲሞክሩ ቅድመ ዝግጅት ያደረጉት የጎበዝ አለቆች ከፍተኛ የሆነ ጉዳት በወያኔ ቅጥረኞች ላይ አድርሰዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው ሌሊት ስለሆነ የወያኔ ቅጥረኛ ሟቾችን በትክክል ለማወቅ ባይቻልም ከባድ ምት ደርሶባቸዋል። የጎበዝ አለቆች ለወያኔ በማደር ህዝቡን የሚበድሉ አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ በድጋሜ ከባድ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።
የጎቤ መስዋዕትነት በከንቱ አይቀርም!

%d bloggers like this: