በወልዲያ እና ዙሪያዋ ዳግም አመፁ አገረሸ

ህዝባዊ ንቅናቄው አድማሱን እያሰፋ ነው የወያኔ ህወሀት ስርሀት ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ መሆኑ እየተነገረ ነው።

ጥር 21 ቀን 2010 ዓ/ም ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ ተጀምራል ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን የገለፀ ሲሆን ህወሓትና የእሱ አገልጋዩ ብአዴን ባደረጉት መተናኮል ሕዝብ ተበሳጭቶ እርምጃ መውሰድ ጀምራል ፡

ቀደም ሲል ጨፍጫፊዎችን እነ ህወሓት ይቃወማል እርምጃ ይወስዳል የሚል የተሳሳተ ግምት ይዘን ብአዴንን ብንጠብቀውም ጭራሽ ገዳዩችን ደግፎ መግለጫ መስጠቱ ቁጣውን ቀስቅሶ ብአዴን ሕዝብን ለማፈን እና የህወሓትን መመሪያ ለማስፈፀም የሚጠቀምባቸው ተቃማት ላይ ጥቃት እየተፈፀመ ይገኛል ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ በሮቢት ከተማ ሕዝብን ለመሰብሰብ የሔደው የፊዲሪሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔው ያለው አባተ በሕዝብ ተዋርዶና ያሰበው ሳይሳካ ተባራል ፡፡ በአሁኑ ሳዓት የሕዝብ ቁጣ ጨምራል ቆቦ እና አካባቢው ነገሮች እየተቀያየሩ ይገኛሉ::

በመርሳ ወታደሮች ተሰብስበው በነበረበት ወቅት በተወረወረ ፈንጅ ፩፰ ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፩፮ ወታደሮች ህክምና አግኝተው ከሆስፒታል ሲወጡ፣ ሁለት ወታደሮች ግን በጽኑ ቆስለው ወልድያ ልዩ ክትትል በሚደረግበት ክፍል ውስጥ ተኝተዋል ተብላል።

Advertisements

የወያኔ ወታደሮች ባለመናበብ እርስ በርሱ በጥይት ተጨፋጨፈ

በጎጃም ጃዊ ወረዳ ጠረፋማ አካባቢወች እስከ ጎንደር ቋራ ድረስ ኩታ ገጠም በሆኑት ቦታወች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የወያኔ ሰራዊት የነፃነት ሃይሎችን እንቅስቃሴ በከበባ ለመግታት እና ትጥቅ ለመስፈታት ከብተሌ ከሚባል ስፍራ መስፈሩን መዘገቤ ይታወሳል።

በጃዊ ወረዳ ጠረፋማ አካባቢወች ከተንቀሳቀሰው ሃይል ውስጥ ልዩ ስሙ ” ቀዝቃዚት ” በሚባል አቅራቢያ ለአላጥሽ ብሄራዊ ፓርክ ኩታ ገጠም ስፍራ የነፃነት ሃይሎችን ዱካ ለማግኘት በንጋት 12 ሰዓት አካባቢ ቃኝ ወታደሮችን በተለያየ አቅጣጫ የተላኩ ሲሆን እነዚህ ቃኝ ወታደሮች ታጋዩቹ አሉበት ከተባለው ስፍራ ያደሩበትና የተንቀሳቀሱበት በሚል ዱካ በማፈላለግ ሳሉ ከኋቸው የመጣ የራሳቸው ወታደር በጥይት ጨፍጭፉቸዋል።

4ቱ ወዲያው ሲገደሉ በነበረው የእርስ በርስ የተኩስ ልውውጥ የቆሰሉም እንዳሉ ተነግሯል። በፈንድቃ ከተማ ወጣ ብሎ ባለው የኮማንድ ፖስቱ ማዘዣ አንድ አስከሬንና ቁስለኛ ወደ ከተማው እንዳይመጣ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ እንደተላለፈ ለመረጃው ቅርበት ካለቸው ሰወች ተረጋግጧል።

ይህ ከሆነ በኃላ የአጋዚ ጦር ትናንትና ዛሬ ወደ ስፍራው እንዲገባ ተደርጓል። በአካባቢው የሚገኙ አርሶአደሮችን እና በቀን ስራ በእርሻ ላይ የሚገኙትን ” ታጣቂወች ወዴት አሉ? ታውቃላችሁ ጠቁሙ ” እያሉ እያስጨነቁ እየደበደቧቸው እንደሆነም ተሰምቷል።


እስካሁን ግን የያዙት ታጣቂም ሆነ መሳሪያ የገፈፉት አርሶአደር አለመኖሩ ተረጋግጧል።
@እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ

በህወሐት የጦር መኮንንኖች የበላይ አዛዥነት የሚንቀሳቀሰው ሜቴክ ላላከናወነው ግንባታ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈጸመለት

በህወሃት የጦር መኮንንኖች የሚመራው የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ (ሜይቴክ) ላላከናወነው ግንባታ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈጸመለት።


በህወሃት የጦር ጄኔራሎች የበላይ አዛዥኘት ክፍያውን የወሰደው ሜቴክ ከ 3 አመት በፊት ግንባታውን አጠናቅቆ ለማስረከብ ውል ስለተፈረመበት ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ መሆኑ ከዋና ኤዲተሩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ሜቴክ ማዳበሪያ ፋብሪካውን ሰርቶ በማጠናቀቅ ማስረከብ የነበረበት በ 2006 አ’ም ቢሆንም አስከ አሁን ድረስ ሰርቶ ያጠናቀቀው ከግማሽ በታች (42 በመቶ ) ብቻ መሆኑን የኦዲት ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል’።


የዋናው ኤዲተር ሪፖርት አንዳመላከተው ሜቴክ ምንም አንኳን የአፈጻጻም ደረጃው ክፍያ ሊያስገኝለት የሚችለው 3.7 ቢሊዮን ብር ያህል ቢሆንም የተከፈለው 5.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን እና ላልተከናወነ ስራ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መከፈሉን አረጋግጧል።

ዋና ኦዲተሩ አያይዞ አንደገለጸው ሜቴክ በገባው ውል መሰረት ከ 3 አመት በፊት አጠናቅቆ ማስረከብ ያለበትን የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ በማንጓተቱ ምክንያት ኮርፖሬሽኑ ከባንክ ለተበደረው ብድር ወለድ ብቻ ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈሉን አስታውቀዋል።


በቀጣይም ሜቴክ በገባው ውል መሰረት ፕሮጀክቱ በተራዘመ ቁጥር የማዳበሪያ ፋብሪካው የሚያመነጨው ገቢ ስለማይኖር ለባንክ የሚከፈለው ወለድ በከፍተኛ መጠን ሊያድግ እንደሚችልና የፋብሪካው ዘላቂነት አደጋ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል አመላክተዋል።


በህወሐት የጦር መኮንንኖች የበላይ አዛዥነት የሚንቀሳቀሰው ሜቴክ በርካታ ፕሮጀክቶች ያለአቅሙ በመውሰድ በህዝብ ገንዘብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አያደረሰ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚገልጽ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ሰሜን ጎንደር አሁንም ፍጥጫው ቀጥሏል ! ኮሎኔል ደመቀ አሁንም ቀጠሮ አራዘሙበት

በግብርና ለሚተዳደረው ህዝባችን የእርሻ፣ የቡቃያ፣ የተስፋ ወቅት ነበር። የጎንደር አርሶ አደር ግን ለዛ አልታደለም። በድንበሩ፣ በባድማው፣ በርስቱ፣ በራስ መጠበቂያው በብረቱ በጠመንጃው፣ በቤተሰቡ፣ በህይወቱ መጡበት። ተው አለ በሰላም ጠየቀ መልሳቸው ግድያ ሆነ። እረዥሙ ትእግስት ተሟጠጠ።

እጅ ጠምዝዘን እንውሰድህ ያሉት ኮሎኔል ደመቀ የማን ልጅ እንደሆንኩ ላስታውሳቹህ ብሎ ችቦውን ለኮሰው። ወያኔ ፍርድ በማጓተት ጨለማ ቤት አስሮ አሁንም ለሐምሌ 5 ቀጥረውታል። ልብ በሉ ሐምሌ 5 2008 እጅ አልሰጥም ያለባት እለተ ቀኑ ናት! እናም በድርብ ማተብ የተሳሰሩት መሰል ጀግኖች እጅ አንሰጥም ብለው ዱር ቤቴ አሉ። አመት እየሞላቸው ነው።

የአመት ደሞዝ ማሳቸው ለሁለተኛ ተከታታይ አመት ጦም ሲያድር የስንቱ ቤተሰብ ህይወት እንደሚመሰቃቀል አስቡት። ኢትዮጵያ በባዶ እግር ከመሄድ ሳታወጣቸው፣ ሲታመሙ ሳታሳክማቸው፣ የትምህርት እድል ሳታመቻችላቸው፤ እሷን ከወደቀችበት አዘቅት ሊያነሷት እነሱ እየተነባበሩ አየወደቁላት ይገኛሉ። ወገናችን ይደርስልናል ብቻችንን አይደለንም ብለው ጀምረውታል። ስንቶቻችን አለሁላቹህ አልናቸው? ስንቱ ስንቅ ቋጠረላቸው? ስንቱስ አብሮ ለመውደቅ የመጨረሻዋን ውሳኔ ወሰነ?!

እናም ባለፈው ሳምንት በሰሜን ጎንደር ሁለት ግንባር ላይ የተነሳው ውጊያ አሁንም በመለስተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደቀጠለ ነው። የጎበዝ አለቆች አንፃራዊ ደህንነታቸውን የሚያስጠብቅ ቦታ ቢይዙም ወያኔ ግን ክረምቱ ሳይገፉ ህዝባዊ ትግሉን ለመቀልበስ ያለ የሌለ ሃይሉን አስጠግቷል። ፍጥጫው እንደቀጠለ ነው። ከታሪክ የማይማሩ ህሊናቸው በትእቢት የታወረ ነው እንጅ የማታ ማታ ህዝብ ያሸንፋል። እነሱም ደግመው ላይነሱ ይንኮታኮታሉ። አስናቀ አበበ

 

በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ቀውስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አለም አቀፍ ተቋማት ጠየቁ

በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ 11 ድርጅቶች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ በጋራ ያቀረቡትን ጥያቄ ከምክር ቤቱ እንዲያስገቡ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል።
ፍሪደም ሃውስ፣ ኢንተርናሽናል ሰርቪስ ፎር ሂውማን ራይትስ፣ ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ፣ ወርልድ ኦርጋናይዜሽን አጌይንስት ቶርቸር፣ እንዲሁም ኢንተርናሽናል ፊዴሬሽን ፎር ሂውማን ራይትስ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ምክር ቤት ጥያቄያቸውን ካቀረቡ ተቋማት መካክል ዋነኞቹ መሆናቸው ተመልክቷል።


እነዚሁ ድርጅቶች ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ሆኖ የሚገኘው የሽብርተኛ ወንጀል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው አዋጅ ለሰብዓዊ መብት መከበር ማነቆ ሆኖ መቀጠሉን በደብዳቤያቸው አብራርተዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለእስር ተዳርገው እንደሚገኙ ያወሱት አለም አቀፍ ድርጅቶች እነዚሁ ጉዳዮች በልዩ ጉባዔው ተነስተው ውይይት እንዲካሄድበት ጠይቀዋል።


በተለይ ከአንድ አመት በፊት በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ዕርምጃም በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲካሄድበት የተባበሩት መንግስታት ግፊቱን እንዲቀጥል 11ዱ ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ተፈጽሟል ያለውን ግድያና እስራት ለመመርመር ጥያቄን ቢያቀርብም መንግስት ጥያቄውን ሳይቀበል መቅረቱ ይታወሳል። በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው የነበሩ የምክር ቤቱ ሃላፊዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል በመጓዝ ቅኝትን ለማድረግ ለመንግስት ጥያቄን ቢያቀርቡም ፈቃድ ተከልክለዋል። ይኸው አለም አቀፍ አካል የኢትዮጵያ መንግስት ዳግም ለቀረበው የምርመራ ጥያቄ እስካሁን ድረስ ምላሽ እንዳልሰጠው ሲገልፅ ቆይቷል።


የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አካሄጀዋለሁ ባለው ምርመራ ከህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 669 ሰዎች መገደላቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፣ የመንግስት ባለስልጣናት ጥናቱ ከተጀመረበት ከሃምሌ ወር በፊት ከ100 በላይ ሰዎች ሞተው እንደነበር ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም።


ኮሚሽኑ በኦሮሚያ አማራና የደቡብ ክልሎች በአጠቃላይ 745 ሰዎች ሞተዋል ቢልም አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት ቁጥሩ ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ይገልጻሉ።
ቅሬታቸውን እያቀረቡ ያሉት እነዚሁ ድርጅቶች ግድያውና እስራቱ በገለልተኛ ቡድን ማጣራት እንዲካሄድበት እየጠየቁ ይገኛል።

%d bloggers like this: