የሕዝቡ ቁጣ እየጨመረ በመምጣቱ ለነፃነቱ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል

ጥር 17 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 6:15 ሲሆን በጦር ሄሊኮፕተር ልዬ ትግረኛ ተናጋሪዎችን ማለትም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መ/ቤት የጥበቃ ዋና መምሪያ አባሎች የሆኑ እና የዚህ ዋና ዳሪክተር መኮነን ወይም ወዲ ኮበል እየተባለ በሚጠራ የህወሓት ሰው የሚመራና ተጠሪነቱ ለደህንነቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታቸው አሰፋ ከሆነው ክፍል ውስጥ በእጀባና በረራ ደህንነት ውስጥ ልዩ ኩማንዶቹን በተጠቀሰው ቀን እና ሳዓት በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ እና ሮቢት ከተማ በማውረድ ፡ እነዚህ ኩማንዶዎች ሮቢት ከተማ ላይ በቀጥታ ወደ ሕዝብ በመተኮስ 3 ሰዎችን መትተዋል እንደዚሁ በቆቦ ከተማ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ጫካ የአግ7 አርበኞች አሉ በማለት ተዋጊ ሄሊኮፕተሩን ዝቅ አድርጎ ያበር ነበር ፡ በተጨማሪም በከተማው ማሀል ዝቅ በማለት በጩሆት ያስፈራራ ነበር ፡፡

ነገር ግን ይሄ አስነዋሪ የህወሓት ስራ ሕዝቡን እና አርበኞችን እጅግ አስቆጥቶ ለሊላ አመፅ ቀስቅሷል ፡ በመሆኑም በአሁኑ ሳዓት ጋብ ቢልም የህወሓት /ብአዴን ንብረት የሆኑ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ፡ በተለይም የሕዝብን ደም በመምጠጥ የሚታወቀው አብቁተ የተባለው መ/ቤት ሮቢት ከተማ ላይ ወድማል እንዲሁም የህወሓት ገዳይ ወታደሮች ያረፋባቸው ለጊዜያዊ መጠለያ የተጠቀማቸው መዘጋጃ ቤት ፡ ቀበሌ ጽ/ቤት ፡ ፍርድ ቤቶች ፡ የአስተዳደር ቤሮዎች እና የስርዓቱ የደህንነት አባላት ንብረቶችና መኖሪያ ቤቶች ተጠቅተዋል ፡ የሕዝቡ ቁጣ ይበልጥ እየጨመረ በመምጣቱ ለነፃነቱ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል ::

በተጨማሪም በቆቦ ወታደሮች እርስ በርስ የሚያደርጉት የተኩስ ልውውጥ አለመቆሙን መረጃዎች ደርሰውናል። የቆሰሉ ወታደሮች ወደ ህክምና ቦታዎች ተወስደዋል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአገር ሽማግሌዎችንና ጻጻሱን ይዘው ገብተዋል የሚል መረጃም ደርሶናል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ነን።

 

 

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: