የኢትዮጵያ ብ/ቡድን አሰልጣኝ ዮሀንስ ሰሀሌ አሰልጣኝ ሆነው እንዲቀጠሩ ቀጭን ትእዛዝ የሰጡት ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ናቸው።
April 8, 2016 Leave a comment
የኢትዮጵያ ብ/ቡድን አሰልጣኝ ዮሀንስ ሰሀሌ ቡድኑን ከመረከባቸው በፊት በደደቢት አሰልጣኝ ሆነው እንዲቀጠሩ ቀጭን ትእዛዝ የሰጡት ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ናቸው። የብ/ቡድኑ ስፖንሰር ዋልያ ቢራ ነው። በካምፓኒው ማርኬቲንግ ክፍል የምትሰራ ሴት የዮሀንስ የፍቅር ጓደኛ ናት። በዝች ሴት በኩል ሁሴን አብዱልቀኒና ዳዊት የተባሉ የስፖርት ጋዜጠኞች ገንዘብ እየተዛቀ ይሰጣቸዋል። በራዲዮ “ሽንፈቱ ምንም ማለት አይደለም።ዮሀንስ መቀጠል አለበት” እያሉ ሲያላዝኑ የታዩበትና አሁንም ድረስ ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩበት ሚስጥሩ የሚሸጎጥላቸው ገንዘብ ነው። በነገራችን ላይ ዮሀንስ የአሜሪካ ኦሎምፒክ ቡድን አሰለጠንኩ የሚሉት ነጭ ውሸት ነው። ዮሀንስ ልጆች በወለዱላትና አሜሪካ በምትኖረው የቀድሞ የትዳር ጓደኛቸው ክስ ተመስርቶባቸዋል። የልጅ ማሳደጊያ በየወሩ መስጠት እየተገባቸው ይህን ባለማድረጋቸው ነው ክሱ። በየጊዜው እዳው እየተጠራቀመ ስለሆነ አሜሪካ የመመለስ ሀሳብ እንደሌላቸው የሚያውቋቸው ይናገራሉ።