ከ89 ሺ የሚበልጡት ኢትዮጵያዊያን ከሳውዲ አረቢያ ተይዘው ሀገር ቤት መመለሳቸው ተሠማ፡፡

ባህር አቋርጠውና ድንበር ሰብረው በህገ-ወጥ መንገድ ሳውዲ አረቢያ ከገቡት መሀከል በአንድ አመት ብቻ ከ89 ሺ የሚበልጡት ኢትዮጵያዊያን ተይዘው ሀገር ቤት መመለሳቸው ተሠማ፡፡

ከ2 ሺ 897 የሚልቁት ደግሞ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወርና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በሳውዲ አረቢያ እሥር ቤቶች እየማቀቁ ነው ተብሏል፡፡

ሸገር ወሬውን የሰማው የጀርመን ሬዲዮ ድምፅ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙትን የኢትዮጵያን ኤምባሲ የዲያስፖራ እና የቆንስላ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑትን አቶ ፋይሰል አልዩን ጠይቆ ካዘጋጀው ወሬ ነው፡፡

ሳውዲ አረቢያ በባሕርና በየብስ በተለያዩ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ድንበሬን ተላልፈው ገብተዋል ብላ ከምታባርራቸው የዓለም ዜጎች መሀከል ኢትዮጵያዊያን ቀዳሚዎቹን ቁጥር መያዛቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ከጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም እስከ መስረም 2009 ዓ.ም ድረስ በነበረው አንድ ዓመት ብቻ ከሳውዲ አረቢያ የተባረሩና ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከ89 ሺ በላይ ነው ተብሏል፡፡

በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች አማካይነት ባሕር አቋርጠውና ድንበር ሰብረው ሳውዲ አረቢያ ከገቡ በኋላ ተይዘው የተመለሱት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በአማካይ በየሣምንቱ 246 ነውም ተብሏል፡፡

ከሳውዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሚቀርብለት ጥያቄ መሠረት ኢትዮጵያኖቹን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ሪያድ ያለው ኤምባሲ ለሚመለሱት ሰዎች የሚሆን ከ2 ሺ 500 ጊዜያዊ ሰነድ በላይ በየሣምንቱ እያዘጋጀ ነው ሲሉም አቶ ፋይሰል ለወሬ ምንጩ ተናግረዋል፡፡

ከሪያድ በተጨማሪ ጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንፅላ ጽ/ቤትም ተመሣሣይ ቁጥር ያለውን ጊዚያዊ ሰነድ እያዘጋጀ ተመላሾቹ ሀገር ቤት እንዲገቡ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ሀገር አቀፍ ግብረ-ሃይል ከሦስት ዓመታት በፊት ቢመሰረትም ህገ-ወጥ ጉዞዎቹ ዛሬም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተደረጉ መሆኑን ይነገራል፡፡

በአርበኞች ግንቦት7 እና በአገዛዙ ጦር መካከል ከባድ ጦርነት ተካሄደ

ከሌሊቱ 9 ሰአት ላይ በረሃ ውስጥ ጉዞ እያደረጉ ባለበት ወቅት፣ የአገዛዙ ወታደሮች ድንገት መንገድ ላይ ከጠበቁዋቸው በሁዋላ፣ ለ4 ተከታታይ ሰአት ውጊያ አድርገው ከበባውን ሰበርው ወጠተዋል። በዚህም ጦርነት ላይ በኢሳት በተደጋጋሚ እየቀረበ መግለጫ በመስጠት የሚታወቀው አርበኛ ሰጠኝ አራጋው መሰዋቱን ታጋዮች ገልጸዋል።
አርበኛው ሰጠኝ አራጋው፣ አርበኞች ግንባርን ከመሰረቱት መካከል አንዱ ነው የሚሉት ጓዶቹ፣ አገዛዙ ምህረት አድርገንልሃል በሚል እንዲገባ ተደርጎ በ1999 ዓም 45 አመታት ተፈርዶበታል። 10 አመታትን በእስር ካሳለፈ በሁዋላ የጎንደር ማረሚያቤትን አቃጥሎና አንድ ፖሊስ ገድሎ መሳሪያውን ይዞ ወጥቷል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አርበኞች ግንቦት7ትን ሲመራ ከቆየ በሁዋላ ትናንት በአጋጣሚ በተደረገ ውጊያ ተሰውተል። ጓዶቹ እንደሚሉት ከእነሱ መካከል የተሰዋው አርበኛ ሰጠኝ ብቻ ነው። በአገዛዙ ወታደሮች ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ጓዶቹ ገልጸዋል
ከወያኔ ሞት ብቻ ነበር የሚጠብቀው እንደጠበቀውም ተሰዋ ሲሎ ጓዶቹ ተናግረዋል። “ ትግላችን ወደ ሁዋላ አይልም፣ እየተተካካን እንቀጥላለን” በማለት በአርበኛ ሰጠኝ መሰዋት ትግላቸው እንደማይቆም ገልጸዋል።
በአርማጭሆ ኪሻ ቀበሌ የተወለደው ታጋይ ሰጠኝ በሰሜን ጎንደር የሚደረጉ ትግሎችን ሲያስተባብርና እንደ ቃል አቀባይ በመሆን መግለጫ ይሰጥ ነበር።

15181707_1137531262981768_4033955364324500917_n

በትግራይ ምድር በሚገኙ ዩኒቨርሲቲወች በአማራና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈፀመባቸው ነው!

በአዲ ግራት ዩኒበርስቲ ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ መብራት የለም፤ ይህንን የጨለማ አጋጣሚ ተገን በማድረግ በእራት ሰአት ጊዜ የትግራይ ተማሪወች በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ ወደ አማራና ኦሮሚያ ልጆች መመገቢያ ሳህንና ወንበር በተደጋጋሚ እየወረወሩብን እና እየደበደቡን ይገኛሉ፤ በዚህ ያልተመለሱት የህወኃት ተከታዮች ከፕሬዘዳንት እስከ ተማሪ ህብረት ያሉት የትግራይ ተወላጆች የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ በአማራ ተማሪወች ላይ እስከ መባረር የደረሱ፣ ፒሲ የተቀሙ፣ የታሰሩና የደረሱበት ያልታወቀ ተማሪወች አሉ። በተለይ የአማራን ተወላጆች ትኩረት አድርገው የሚረብሸን አማራ ነዉ ከየት ነዉ የመጣህ እየተባልን ስለምንዋከብ በጣም እየተቸገርን ነዉ በማለት ከዩኒቨርሲቲው ሰለቫ የሆኑ ተማሪወች ብሶታቸውን ለህዝብ እንድንገልፅ ጠይቃዋል።

ሁለት የአማራ ተወላጅ ተማሪወችም የትግሬ ጥላቻ አለባችሁ ተብለው አማራውን ታነሳሳላችሁ በሚል ሰበብ ተከሰው የነበሩ ሲሆን በምርመራ ጊዜም ከየት መጣህ ክልል ዞን ወረዳ ከየት ነው? መለስን ትወደዋለህ ? አይናፍቅህም ? በማለት የነገር ፍለጋ ጥያቄ ሲጠይቁዋቸዉ ተማሪወቹም (አንወደዉም, አይናፍቀንም) ብለዉ በድፍረት እንደመለሱና ከዚህ መልስ በሁዋላ ተማሪወቹ ከዩኒበርስቲዉ እንደተሰናበቱ ታውቆአል። (ስማቸውን ለጊዜው ለመግለፅ አልተፈለገም)
በዚሁ ዩኒቨርስቲና በሌሎችም በትግራይ ምድር የሚገኙ የትምህርት ተቁሞች የሚማሩ የአማራ ተወላጆች በሚደርስባቸው የተለያዩ ጥቃቶች ትምህርታቸውን በተገቢው ሁኔታ መከታተል እንዳልቻሉና የማቁአረጥና የመባረር እድላቸው ሰፊ እንደሚሆን ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል።

በየዩኒቨርሲቲወቹ በተፈጠረው የብሄር አደረጃጀትም ህውኃት በብአዴን በኩል የአማራ ተማሪወችን ለብቻ በማደራጀት የአማራው ህዝብ እያነሳው ያለውን የመብት ጥያቄ ተማሪወቻችን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማድረግ የማይሳካ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑንም ባለጉዳዮቹ ገልፀዋል። በተለይም በአማራና ሱዳን ደንበር ያለውን የመሬት ሁኔታ፣ የወልቃይት የማንነን ጥያቄ ህዝቡ ያነሳውን ተቀዋውሞ በማወያየት ቢዲዮና ድምፅ እሪከርድ በማድረግ ለህወኃት ሪፖርት እንደሚደረግና ተማሪወቹን ለከፋ ችግር ለመዳረግ እየተሰራ እንደሆነም አክለው አረጋግጠዋል።
መረጃውን ያቀበሉት ተማሪወች በትግራይ ምድር በሚገኙ ዩኒቨርስቲወች የምንገኝ የአማራ ተወላጅ ተማሪወች ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪወች ጋር የጋራ አጋርነት በመፍጠር በሚገባ ተደራጅተን ከሚደርስብን ጥቃት ራሳችን ከመከላከል አልፈን ህዝባችን እያካግሄደ ያለውን የማንነት ትግል አጠናክረን መደገፍ አለብን ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። በየዩኒቨርስቲው የተመሰረተው የብአዴን የተማሪወች ፅ/ቤትም የህወኃት የስለላ መዋቅር መሆኑን አውቀን በንቃት ማክሸፍ ይገባል ብለዋል።

14012564_10205198112430990_355381106_o

በምስጢር የተያዘው የአራት ኪሎ ተኩስ ልውውጥ እና የአዲስ አበባው ፍተሻ

በከፍተኛ ምስጢር የተያዘው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳብያ በአዲስ አበባ በተለይ ደግሞ በአራት ኪሎ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጅምሮ ከፍተኛ የሰራዊት ክምችት ይታያል።

ከትላንት ማምሻ የጀመረው ፍተሻ አሁንም እንደቀተለ ሲሆን የአጋዚ ሰራዊት አላፊ አግዳሚውን በማሸበር እና በመፈተሽ ላይ እንደሚገኝ የአይን ምስክሮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። የአይን ምስክሮች እንደሚሉት መሃል አዲስ አበባ- የገዢው ፓርቲ መቀመጫ ኣራት ኪሎ አካባቢ ውጥረቱ የከፋ ይመስላል። በአካባቢው ይሰማ የነበረው የተኩስ ልውውጥ በዚያው በቤተ-መንግስት እንደሆነም ይነገራል። የከባድ መሳርያው ጩኸት እንደተሰማ በከፊል አዲስ አበባ መብራት እንዲጠፋ ተደርጎ እነድነበርም ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች ተናግረዋል።

አለም አቀፍ እና የግል መገናኛ ብዙሃን በተከለከሉበት በአሁኑ ሰዓት በጨለማ እየተደረገ ያለውን ሁሉ ለማጣራት ቢቸግረም – አንደኛ በኢሃዲግ ድጅቶች መካከል ሁለተኛ ደግሞ በሕወሃት ከፍተኛ አመራር እና መካከለኛ ካድሬዎች መሃል የከረረ አለመግባባት እንዳለ እየተሰማ ነው። የዚህ የጥቅም እና የሃሳብ ልዩነት እየሰፋ መጥቶ ወደ ከፍተኛ ፍልሚያ ሊያመራ እንደሚችል የሚገምቱም ጥቂቶች አይደሉም።

በሃገሪቱ ያሉ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እስካሁን ድረስ እንዳይከፈቱ ትእዛዝ ተሰጥቷል። የትምህርት ቤቶችን የልብ ትርታ ለማዳመጥ በመምህራን የተጀመረው ስብሰባ ውጤት ገዥው ፓርቲ እንደጠበቀው አልሆነም። የመምህራኑ ቁጣ እንዲህ ከበረታ የተማሪዎቹ የከፋ እንደሚሆን በመገንዘባቸው ትምህርት በቶችን የመክፈቱ አደጋ ስጋት ውስጥ ከትቷቸዋል።

በፊታችን የሚከበሩ ሁለት በዓላት (የመስቀል እና የእሬቻ በዓላት) አከባበርም ገዥውን ፓርቲ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

አገዛዙ በአካባቢ እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ላይም እምነት በማጣቱ የአጋዚ ሰራዊቱ እና ታማኝ ደህንነት አባላት ብቻ ናቸው ፍተሻውን እና ግድያውን እያካሄዱ ያሉት።

በኤርትራ ጠረፍ (ባድመ) ላይ ተሰማርቶ የነበረው የህወሃት ሃይል አካባቢውን ለቅቆ ወደ አዲስ አበባ እና ጎንደር እንዲዘምት ተደርጓል።

የሕዝብን ውጫዊ አካል ሊፈትሹ ይችላሉ – የሸፈተ ልቡን ግን ለመፈተሽ አይቻላቸውም። ወከባው ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ አይፈታውም።

14495381_727547754050198_1341726531349737107_n

ይህ መልዕክታችን ለነጻነታችሁ ለምትዋደቁት የአገራችን ድንቅ ልጆች በሙሉ ባላችሁበት ይድረስ:- ከአርበኞች ግንቦት 7

ውድ የአገራችን ጀግኖች

ለነጻነታችሁ የምታደርጉት ተጋድሎ ወደር የማይገኝለት መሆኑን ስንነግራችሁ በኩራት ነው። ይህን ተጋድሎአችሁን በጠመንጃ ሃይል ለማፈን የወያኔ አገዛዝ የሚወስደው ፋሽስታዊ እርምጃ አልበቃ ብሎት፣ አሁን ደግሞ የስነ ልቦና ዘመቻ ከፍቶባችኋል። አባቶቻችሁን ፣ እናቶቻችሁን፣ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን በየመድረኩ እየጠራ እናንተን እንዲያወግዙ እየስገደደ ነው። አድሎአዊነትና ኢፍትሃዊነት አንገሽግሾአችሁ ያቀጣጠላችሁትን የነጻነት ትግል ለማራከስ፣ ታሪካችሁን ለማቆሸሽ ላይና ታች እያለ ነው። የእናንተ ታሪክ ግን እንደ ገዳዮቻችን ታሪክ የሚቆሽሽ አይደለም። ማንም ምን ቢል የእናንተ ስራ ወደር የማይገኝለት ዘለላም ለትውልድ ሲተላለፍ የሚኖር ነው። የእናንተ ትግል ለራሱ ክብርና ነጻነት የሚቆጭ የሰው ልጅ ሁሉ ሊያደርገው የሚገባ እውነተኛ ትግል ነው። ለዚህ ነው የህይወት መስዋትነት ቢከፈልበት የሚያንስበት እንጅ ከቶውንም የሚበዛበት የማይሆነው ።

በዚህ ወሳኝ የታሪክ ወቅት ለራሳችሁ፤ ለወገናችሁና ለአገራችሁ ስትሉ ከጨካኝ ሥርዓት ጋር ግብግብ ገጥማችሁ በምትከፍሉት መስዋዕትነት የአሁኑ ብቻ ሳይሆን የሚመጣውም ትውልድ እንደሚኮሩባችሁ አትጠራጠሩ። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የጭቆና ዘመኑን ለማራዘም ዛሬ በወላጆቻችሁ ላይ የፈለገውን ጫና ቢፈጥር እናቶቻችሁና አባቶቻቸሁ ለምን ወለድኩት፣ ለምን ወለድኳት ሳይሆን እንኳንም ወለድኩት እንኳንም ወለድኳት ብለው ገድላችሁን የሚዘክሩበትና በናንተ ጀግኖች ልጆቻቸው መስዋዕትነት የሚኮሩበት ወቅት ሩቅ አይሆንም ።

ውድ ያገራችን ልጆች

የእስከዛሬው የሰው ልጆች ታሪክ እንደሚመሰክረው በምድር ላይ ለነጻነት የሚደረግን ትግል ያክል ክቡር ዋጋ የሚያወጣ ነገር የለም። ዛሬ ነጻነታቸውን ያገኙ አገሮች፡ አሁን የሚሳሱለትን ነጻነት ለማግኘት ከፍተኛ የህይወት መስዋትነት ከፍለዋል፤ ዛሬም በተለያዩ የአለም ክፍሎች የህይወት መስዋትነት የሚከፍሉ ጀግኖች አሉ። እናንተም ከእነዚህ ጀግኖች አንዱ ሆናችኋልና ድስ ሊላችሁና ልትኮሩ ይገባል። በአረሜኔው የአጋዚ ጦር በየአደባባዩ የሚፈሰው የእናንተ ደም ኢትዮጵያ አገራችሁንና ላለፉት 25 አመታት በዘረኞች የባርነት ቀንበር ሥር እየማቀቀ የሚገኘውን ወገናችሁን አርነት የሚያወጣ መሆኑን ፍጹም አትጠራጠሩ። ። እናት አገራችን ኢትዮጵያ እናንተን በብዙ ምጥ ወልዳለችና ፣ እናንተም በነጻነት መልሳችሁ ልትወልዷት ደማችሁን እያፈሰሳችሁላት እንደሆነ ሁሌም አትዘንጉት ።

ውድ ያገራችን ልጆች

እየከፈላችሁት ያለው የህይወት መስዋዕትነትና እየፈሰሰ ያለው ደማችሁ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የገዥዎቻችን መሣሪያ በመሆን ደማችሁን እያፈሰሱ ያሉትን ሳይቀር ነጻ ያወጣቸዋል። ደማችሁ ከገዳዮቻችሁ ደም በላይ ወፍራም ነውና ፤ ሞታችሁ ከገዳዮች ህይወት በላይ ዋጋ አለው። ለነጻነት ሲባል በምትከፍሉት መስዋዕትነት እናንተ በህይወት ባትኖሩም ህያው ናችሁ፣ እነሱ ግን በህይወት እየኖሩ በቁም የሞቱ ናቸው። ደማችሁን እያፈሰሳችሁ ያላችሁ ሁሉ፣ እስካሁን ለፈጸማችሁትም ሆነ ለወደፊት ለምትፈጸሙት ገድል እጅግ ከፍተኛ ክብር ይገባችሁዋል። በአገራችን ነጻነት እውን እስኪሆን የጥይቱንም የፕሮፓጋንዳውንም ናዳ ተቋቁማችሁ ትግላችሁን ዳር እንደምታደርሱ ኢትዮጵያ ታምናለች።
እናንተን እንዲገድሉ ከታዘዙት ወታደሮች መካከል አንዳንዶች የአለቆቻቸውን ትእዛዙ በመጣስ ከእናንተ ጎን ቆመዋል።

የመግደያ መሳሪያቸውን እየጣሉ የእናንተን ፈልገ ተከትለዋል። ኢትዮጵያ በእነዚህ ወታደሮች ድርጊት ኮርታለች። ለወደፊቱም ብዙ ወታደሮች እንደሚቀላቀሉዋችሁ ልንነግራችሁ እንወዳለን። አሸናፊነትን እየተቀናጃችሁ በሄዳችሁ ቁጥር የዳር ተመልካቾችና ተሸናፊዎች ወደ እናንተ ይመጣሉ።

ምን ጊዜም ከናንተ ጋር የሆነው ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 አፈሙዛቸውን ማስታገስ ተስኖአቸው በናንተ የነጻነት ቀንድሎች ላይ የጭካኔ እጃቸውን ለሚሠነዝሩት የወያኔ ጀሌዎች እና አዛዦቻቸው መምከርም ማስጠንቀቅም የሚፈልገው ነገር አለ ።

ጀግኖቻችን በዚህ የለጋ እድሜያቸው ደማቸውን የሚያፈሱት እናንተንም ነጻ ለማውጣት ነው። እናንተ የእነሱን ደም ማፍሰሳችሁን በቀጠላችሁ ቁጥር፣ ህይወታችሁንም ሞታችሁንም እያራከሳችሁት ትሄዳለችሁ። እስካሁን ያረከሳችሁት ይበቃል፤ ከዚህ በሁዋላ ግን በእርኩሰት ላይ እርኩሰት አትጨምሩ። ልብ በሉ! ህዝብን ያሸነፈ ሃይልና ጉልበት በየትኛውም ዘመን ኖሮ አያውቅም ! ወደፊትም አይኖርም ! በህዝብና የአገር ሃብት ዘረፋ ልባቸው ያበጠው አልቆቻችሁ ይህንን ሃቅ መረዳት ተስኖአቸው እናንተን በገዛ ወገኖቻችሁ ላይ አዝምተዋችኋል።

እናንተ ግን ከህዝብ አብራክ የወጣችሁ ያገሪቱ መከላኪያ ሠራዊት ፤ የፖሊስና የደህንነት አባላት እንጂ ለጥቂት ባለሥልጣናት የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ በወገኖቻችሁ ላይ ጭፍጨፋ ለማካሄድ የተቀጠራችሁ የባዕድ ቅጥረኞች /mercenaries / አይደላችሁም። ስለዚህ በእብሪትና በጥጋብ ተወጥሮ በገዛ ወገናችሁ ላይ ያዘመታችሁን የህወሃት ጦር አዛዦች ትዕዛዝ አትቀበሉ። የአገር ዳር ድንበር ከውጭ ወረራ ለመከላከል እንጂ ፍትህ የሚጠይቀውን ወገኔን ለመግደል አልተቀጠርኩም በላቸው! የተሸከምከው ጠመጃና የታጠከው ጥይት የገዛ ወንድሞችህን ለመግደል እንዳልሆነ ንገራቸው። እምቢ ካሉ ለአንተና ለልጆችህ ነጻነት ጭምር ከሚታገሉ የአገርህ ልጆች ጎን ለመሰለፍ ህዝቡን ተቀላቀል! የህዝብ አለኝታነትህንና ወገናዊነትህን በተግባር አረጋግጥ ! ይህ ሳይሆን ከቀረ ነገ የአሸናፊነቱ ደወል ሲደወል ዛሬ ደማቸውን በምታፈሳቸው እምቡጦች ጫማ ስር ትወድቃለህ ። ስለዚህ ወቅቱ ሳይዘገይ ሚናህን ለይና ከህዝብ ጎን ቁም! የህዝብ ጥሪ ተቀብለህ ከህዝብ ጎን ከቆምክ ፣ ህዝብ ከጎንህ ይቆማል።

የአገሬ ልጅ ሆይ የጠመንጃህን አፈሙዝ በገዢዎቻችን ላይ አዙር! ካልሆነልህ ደግሞ መሳሪያህን ጥለህ ራሳህን ከገዳዮች ጎሬ ለይ!

ህዝብ አንቅሮ የተፋውን የህወሃት አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም በወገን ላይ ጦርነት ያወጃችሁ የሥርዓቱ ቅምጥሎችም አፈሙዙን ሰከን አድርጋችሁ በጊዜ ከነጻነት ሃይሎች ጎን እንድትሰለፉ ካልሆነም የግድያ ትእዛዝ ከመስጠት ራሳችሁን እንድታርቁና አርበኞች ግንቦት 7 ወገናዊ ጥሪ ያቀርብላችኋል። ህዝባችን ለነጻነቱ የሚከፍለው መስዋዕትነት እንዲራዘም የሚደረግ ማንኛውም ሃላፊነት የጎደለው እርምጃ ይዋል ይደር እንጂ በህግም በታሪክም የሚያስጠይቅ መሆኑን ለአፍታም አትዘንጉ!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

 
%d bloggers like this: