አሜሪካንን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አመድነት እቀይራታለሁ ሲል የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ተናገረ

በዚህ በሰሜን ኮረያ መሪ ዛቻ መላው የአለም ሀያላን አገሮች ከመደንበራቸውም በላይ የጦር ሃይላቸውን በዝግጅት ላይ አድርገዋል፡፡ የሩሲያና የአሜሪካ ነገር ድራማማ ቢመስልም ሩሲያ ሳትቀር የኒውክለር ሃረር የተሸከሙ ሚሳኤሎቿን ወደ ሰሜን ኮሪያ ድንበር አእያስጠጋች ነው፣አውስትራሊያ፣ኒውዘርላንድ ፣ካናዳና ጃፖን ጨምሮ ለሰሜን ኮሪያ የማስጠንቀቂያ መልክት አስተላልፈዋል፡፡ቻይና የሰሜን ኮሪያን አቋም ደግፋ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ቆማለች፡፡ #ኪምጆንግ_ዩን የአሜሪካን የጦር መርከብ የጫነች ጀልባን በአንድ ምት አሰምጣታለሁ እያለ እየዛተ ነው፡፡

ይህ ሰው እንደሚለው ከሆነ ሰሜን ኮሪያ የአለማችን ሀያላን አገር ነች ስለዚህ የምን አሜሪካን ነው አሜሪካንንማ በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አመድነት እቀይራታለሁ እያለ ነው፡፡ እስኪ የሚሆነውን ነገር አብረን እንከታተል፡፡

ይሄ ሰው አሜሪካን እያስፈራራ ነው ምን ትሉታላችሁ ?

አሜሪካ በፀጥታው ም/ቤት አንስታ ትላልቆቹን ሃገራት የተንጫጩበት አሳብ ምን ይሆን ?

አሜሪካ ሰሞኑን አንድ የሚገርም ሀሳብ በፀጥታው ም/ቤት አንስታ ትላልቆቹን ሃገራት ሳይቀር አንጫጭታለች፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው የሰባዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፀሙ መንግስታት ያሉባቸው ሀገራት ወደፊት የግጭት ቀጣና (crisis potential) ሊሆኑ ስለሚችሉ እና ለአለም ሰላም ስጋት ሲለሚሆኑ፤ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በተመለከተ በፀጥታው ምክር ቤት በቋሚነት አጀንዳ ሆነው ለውይይት እንዲቀርቡ ም/ቤቱን ጠይቃለች፡፡

ምንም እንኳን ለም/ቤቱ አዲስ ሀሳብ ቢሆንም፤ ጉዳዩ ከምርም ለቀጣይ የአለማችን ሰላም ጠቃሚ ነው፡፡

ከአሁን ቀደም ሆነ በአሁኑ ስዓት ግጭት እና አለመረጋጋት ውስጥ ያሉ ሀገሮች የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፀምባቸው ናቸው፡፡

ይህን ሀሳብ አባል ሀገሮች፤ በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መገንባት ነው በማለት ተቃውመውታል፡፡

መቸስ ከሰብዓዊነት ይልቅ አሜሪካ የግል ጥቅሟን ተመርኩዛ ሀገሮችን መጥቀምም መጉዳት ተክናበታለች፤ የሀገሮችም ስጋት ከዚያ የመነጨ ይመስላል፡፡

ይህ ጉዳይ የምር ከሆነ የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች እኛ ልንሆን እንላለን፡፡ አሜሪካ ሆይ በርች፤ የአሜሪካ መስራች አባቶች በህገመንግሥቱ ያሰፈሩትን የአሜሪካ እሴቶች ተገቢ ነው ቃላችን፡፡


ነጻነት ሚዲያ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ እጁን በሚያስገባ በሩስያም ሆነ በማንኛውም የውጭ አገር መንግሥት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስጠነቀቁ።

“የምርጫ ሂደታችንን ክብር የሚነካ አንዳች ነገር ሲፈጸም፣ እርምጃ መውሰዳችን የግድ መሆኑ፣ የሚያጠያይቅ አይመስለኝም” ብለዋል የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ።

“በእርግጥም እናደርገዋለን” በማለት ሃሳባቸውን አጠናክረዋል፣ ሚስተር ኦባማ ዛሬ ጧት ኤንፒአር ለተባለው ራዲዮ በሰጡት ቃል።

አንዳንዶቹ እርምጃዎቻችን ግልፅና ሕዝብ የሚያውቃቸው ወይም የሚሰማቸው፣ ሌሎቹ ደግሞ በተቃራኒ የሚወሰዱ እንደሚሆኑ ነው ፕሬዚዳንቱ ያስገነዘቡት።

የሩስያ የኢንተርኔት ሰርጎ ገቦች፣ በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት፣ ከዲሞክራቲክ ፓርቲው ኮምፒተሮች ውስጥ፣ ስለ ሂለሪ ክሊንተን የምርጫ ዘመቻ አሳፋሪ የሆኑ ኢሜሎችን ይፋ እንዳደረጉ፣ ሲ አይ ኤ ድምዳሜ ላይ እንደደረሰ ማስታወቁ ይታወሳል።

ይህ ድርጊት ከሩስያው ፕሬዚደንት ከቭላዲሚር ፑቲን እውቅና ውጪ እንደማይሆን፣ የኋይት ሀውስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያምናሉ።

ሞስኮ ግን፣ ክሱን፣ አስቂኝና የማይረባ ትለዋለች።

Image result for obama putin

ቱርክ በ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ ትችላለች ተባለ

ቱርክ ለአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመደራደር የተገባላት ቃል ተግባራዊ አለመደረጉን ተከትሎ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ እንደምትችል አሳስባለች።
ባለፈው አመት የሶሪያ ስደተኞች ቱርክን በመጠቀም ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ሲገቡ የነበረ ሲሆን፣ ህብረቱ ቱርክ ሰደተኞቹን በሃገሩ እንድታቆይ የጥቅማ-ጥቅም ቃል ገብቶ እንደነበር ይታወሳል።
ቱርክ የሃገሯ ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ አውሮፓ እንዲገቡና ሃገሪቱ የአውሮፓ ህብረት አባል እንድትሆነ ቃል ከተገባላቸው አገሮች አንዷ እንደሆነ ይታወሳል።
ይሁንና የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ቱርክ የህብረቱ አባል እንድትሆን በቀረበ የውይይት ሰነድ ላይ ጉዳዩ እንዲዘገይ ውሳኔን እንዳስተላለፉ ቢቢሲ ዘግቧል።
በድርጊቱ ቅሬታ ያደረባቸው የቱርኩ ፕሬዚደንት ታይፕ ኤርዶጋን ሃገራቸው በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የሶሪያና የሌሎች ሃገራት ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ እንደምትችል አሳስበዋል።
“የገባችሁትን ቃል የማትጠብቁ ከሆነ ድንበራችንን ክፍት እንደምናደርግ መግለጽ እንወዳለን” ሲሉ ፕሬዚደንት ኤርዶጋን ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል።
ይሁንና በርካታ የአውሮፓ አባል ሃገራት ቱርክ እያቀረበች ያለው የማስፈራሪያ በጎ ጎን አይኖረውም ሲሉ ምላሽን የሰጡ ሲሆን፣ ቱርክ በህብረቱ አቋም ቅሬታ እንዳደረባት ገልጻለች።
ሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ስደተኞችን አስጠልላ እንደምትገኝ ታውቋል።
ቱርክ በሃገሯ ያሉ ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንዲገቡ የምታደርግ ከሆነ ባለፈው አመት የታየው የስደተኞች ፍልሰት ዳግም ሊቀሰቀስ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
ባለፈው አመት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ስደተኞች በቱርክ በኩል ወደ አውሮፓ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የስደተኞቹ ሁኔታ በአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ መነጋገሪያ ሆኖ ይገኛል።
የአውሮፓ ህብረት ቱርክ ስደተኞቹን በሃገሯ እንድታቆይ የገባውን ቃል ተከትሎ ቁጥር መቀነስ ያሳየ ሲሆን፣ ግሪክ በርካታ ስደተኞች ወደ ቱርክ እንዲመለሱ ማድረጓ የሚታወስ ነው።
በቱርክና በህብረቱ ማካከል የተፈጠረው አዲስ አለመግባባት የስደተኞች ፍልሰት ዳግም እንዲከሰት ያደርጋል ተብሎ ስጋት ማሳደሩንም የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው።

ትራምፕ 3ኛው የዓለም ጦርነት የሚጀመረው በሄላሪ ነው አሉ

   – የምርጫ ውጤትን እቅጩን የሚገምቱት ፕሮፌሰር፣ ትራምፕ ያሸንፋል ብለዋል
– ሪፐብሊካኑ ኮሊን ፖል ድምጻቸውን የሚሰጡት ለዲሞክራቷ ሄላሪ እንደሆነ አስታውቀዋል

የሳምንታት ጊዜ በቀረው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካኑን ወክለው የሚወዳደሩት አነጋጋሪው ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ፣ 3ኛው የዓለም ጦርነት የሚጀመረው ተፎካካሪያቸው ሄላሪ ክሊንተን ይዛው በተነሳቺው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሳቢያ ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡
ሄላሪ ክሊንተን በሶርያ ጉዳይ ላይ የያዘቺው እቅድ በአሜሪካና በሩስያ መካከል የከፋ ግጭት የሚያስከትልና ለሶስተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ሊሆን አንደሚችል ትራምፕ ባለፈው ማክሰኞ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ማስጠንቀቃቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
የሄላሪን ዕቅድ በመደገፍ በምርጫው ድምጻችንን የምንሰጣት ከሆነ፣ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት መጀመሩ አይቀሬ ነው ያሉት ትራምፕ፤ ሄላሪ ስታብጠለጥለው ከከረመቺው ከሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመደራደር ያላት ብቃት እንደሚያጠራጥራቸው በመግለጽ፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ታበላሸዋለች ብለዋል፡፡
ያልተለመዱ ክስተቶች የተስተናገዱበት የዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ እየተጧጧፈ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ በደረሰበት በአሁኑ ወቅት፣ ሪፐብሊካኑ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሊን ፖል ዲሞክራቷን ሄላሪን እንደሚመርጡ ማስታወቃቸውን የዘገበው ደግሞ ስካይ ኒውስ ነው፡፡ ሊዲሞክራቷ ዕጩ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ በይፋ የሚናገሩ ስመጥር ሪፐብሊካኖች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ ኮሊን ፖልም ሄላሪ እንደ አገር መሪ ያላትን የካበተ ልምድና ክህሎት በማድነቅ ድምጻቸውን ለእሷ እንደሚሰጡ ባለፈው ማክሰኞ ማስታወቃቸውን ገልጧል፡፡
በተያያዘ ዜና ምንም እንኳን በርካታ ቅድመ ትንበያዎች በቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራቷ ሄላሪ በለስ እንደሚቀናት እያመላከቱ ቢሆንም፣ የአሜሪካን ምርጫ ውጤት በመተንበይ የሚታወቁት የፖለቲካ ተንታኙ ፕሮፌሰር ሄልሙት ኖርፖዝ ግን፣ በስተመጨረሻ ድል የትራምፕ ትሆናለች ሲሉ መተንበያቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
ላለፉት 100 ያህል አመታት በአሜሪካ ከተከናወኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዎች ከአንዱ በቀር የሁሉንም ውጤት በትክክል የገመቱት የኒውዮርኩ ሰኒ ስቶኒ ብሩክ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፕሮፌሰር ሄልሙት ኖርፖዝ፣ በቀጣዩ ምርጫ ትራምፕ እንደሚያሸንፉ በይፋ ተንብየዋል፡፡
ፕሮፌሰር ኖርፖዝ የፈጠሩትና ያለፈውንና የወደፊቱን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሚያመላክተው የትንበያ ቀመር፣ እ.ኤ.አ ከ1912 አንስቶ በተደረጉት የአገሪቱ ምርጫዎች ላይ ያቀረበው ትንበያ ከአንዱ በስተቀር በሁሉም ስኬታማ እንደነበር የጠቆመው ዘገባው፣ ቀመራቸውን ተጠቅመው የሰጡት ትንበያ ያልያዘላቸው እ.ኤ.አ በ2000 በተካሄደው ምርጫ ብቻ እንደነበርም አስታውሷል፡፡

%d bloggers like this: