እኔ ባለፍሬ ትልቅ ዛፍ ነኝ ሰዎች ድንጋይ በወረወረብኝ ቁጥር ፍሬ እሰጣቸዋለሁ፡፡

አቤል ብርሀኑ(የወይኗ ልጅ)

ምናልባት በዚህ ሰአት ያሰብከው አልሳካ ብሎ ይሆናል የጠበከው ሰው ቀርቶም ይሆናል ማን ያውቃል ያመንከው ከድቶህ ወይም በስደት አለም ትሆናለህ፡፡ አሰሪዎችህ ከአቅም በላይ እያንገላቱህ ወይም ሰዎች አቅምህን እየለኩት አትችልም ብለውክ ይሆናል፡፡ በዚህም ትላንት በሆነብህ ነገር ዛሬ እያዘንክ ወይም ህይወት መሮህ ሞትህን እየናፈክ ወይም ሰዎች እንዲህ አረጉኝ ብለህ በመጠጥ እራስህን እያደነዘዝክ ይሆናል፡፡ ለምን? ሰዎች ላረጉብህ ነገር ትጨነቃለህ?

ወዳጄ ይህንን እውነት እፅፍልሀለው፡፡ ሰዎች ሁሌም ትልቅና በፍሬ የተሞላ ዛፍ ሲያዩ መውጣት ስለማይችሉ ፍሬ ለማውረድ ድንጋይ ይወረውራሉ ዛፉም ፍሬ ይሰጣቸዋል እንጂ ወረወሩብኝ ብሎ አይደርቅም፡፡ አንተም እንደዚሁ ብልህ ዛፍ ሁን አንተ ውስጥህ ብዙ እምቅ ሀይል አለ ሰዎች ይህንን ሀይልህን ሲያዩ ደጋግመው ወደአንተ ድንጋይ ይወረውራሉ፡፡ አንተ አትሸነፍ በሀዘን በምሬት አትድረቅ ይልቅም ችሎታህን ፍሬህን መልሰህ ስጣቸው፡፡

ሁሌም የሰዎችን ጩኸት ድንጋይ ጥለህ ስለፍሬህ ስለስኬትህ አስብ ያለ ጥረትም ከስኬት ጫፍ አይደርስም፡፡ ስንደል ሲያቃጥሉት አከባቢን እሚያውደው ። የስው ልጅም በችግሮች ሲደበደብ ካልሆነ ጥሩ ጠረን አይወጣውም፡፡ ህይወትን የታገላት ነው የሚጥላት። ዓለምን እልህ የተጋባ ነው የሚያሽንፍት። ህይወት ሩጫ ናት። የስኬት ገበያ ሁሉ ውድድር አለው። መጀመረያ የጨሰ ነው ሆላ ብርሃን የሚወጣው።

መልካም ፍሬ የመስጠት ቀን!

ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፍሉ!

 

እናተ ሸክማችሁ የቀለለባችሁ …እንዳትጥሉት ! ! (አሌክስ አብርሃም)

እንዴት ናችሁ ጓዶች ?. . . እኔ ሰላም ነኝ ! ሆሳእና እንዴት ነበር ?. . . እሱማ እንዴት ይሆናል ያው ወደቀልባችሁ መለስ ብላችሁ ደግ ደጉን ስትለጥፉ አይቻለሁ ! እኔ የምላችሁ እንደው የሆሳእናን ነገር እያሰብኩ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝኮ ለምን አንጫዋወታትም ብየ አሰብኩ ! ይወራ አይደል . . .? ለነገሩ እንደው ለወጉ ነው እንጅ <<አይ>> ብትሉም ዝም አልልም:) ዳይ ወደጉዳያችን … ዛሬ ወደኢየሩሳሌም ግድም ነው የምንሄደው . . . .

እንግዲህ ኢየሩሳሌም ያልተነገረላትም ያልተነገረባትም ትንቢት የለም ! እንግዲህ ከትንቢቱ አንዱ ‹‹ንጉስሽ ይመጣል›› የሚል ነው ….መቸስ እነዛ ህዝቦች እግዚአብሔርን ያውቁታል ….በምድረበዳ አንዴ ተራራ ሲንጥ አንዴ ባህር ሲከፍል …ከደረቅ ድንጋይ ውሃ ሲያንዠቀዥቅ …ከሰማይ መና ሲያወርድ ያውቁታል ….እና አሁን ደግሞ ይመጣል የሚለውን ትንቢት እንቅ አድርገው ይዘው ግን ‹‹አመጣጡ እንዴት እንዴት ነው ?›› ብለው ሲየጠብቁ ነበር … ደግሞኮ በሮም ቅኝ ተገዝተው በስጋም በነፍስም ባርነት ውስጥ ሁነው ነው የሚጠብቁት ….

ቅኝ ገዥዎቻቸው በሚገርሙ ስልጡን ፈረሶች ላይ ጉብ ብለው …ሰረገላቸውን እያንካኩ እና ጦራቸውን እየሰበቁ ረግጠው ሲገዟቸው ነፃ አውጫቸው ከሮማ ወታደሮች ሽ ጊዜ በሚያስፈራ ግርማ በእሳት ሰረገላ ምድሩን እየገለባበጠው እንደሚመጣ አልተጠራጠሩም !

እና((( ንጉሱ መጣ )))….አዳኛቸው ወደኢየሩሳሌም መጣ ….ከዘላለም ባርነት የሚያወጣቸው ታዳጊያቸው ደረሰ ….እንዴት መጣ ?…ደመናውን ሰንጥቆ በሚያስፈራ ግርማ ተከሰተ …..? አልተከሰተም!! ….መሬትን ፈነቃቅሎ እንደገሞራ ሽቅብ ኢየሩሳሌምን አሸበራት ??…..በጭራሽ! …..እና እንዴት መጣ ?????…..((ሚስኪን ባለች ሁርጭላ ላይ ተቀምጦ መጣ በቃ !!)) እንዲህ አይነት ነገር ሲገጥመውኮ ነው ፈረንጅ ‹‹Are you kidding me ? ›› የሚለው …. እስካሁንም ጌታን ያክል ነገር እንዴት ሁርንጭላ ላይ ተቀምጦ መጣ ይባላል ብሎ የሚገረም አለም ላይ ነን ! ወደዛ ዝርዝር ሳንገባ አሁን በቀጥታ ወደአህያ ሁርንጭላዋ ጉዳይ እንሂድ ….መነሻየም እሱ ነው !!

ጓዶች …. ኢየሱስ በአህያ ሁርንጭላ ወደታላቋ ከተማ ከመግባቱ በፊት ምን እንደተፈጠረ ተመልከቱ ….ከተማዋ አቅራቢያ ደብረዘይት የሚባለው ተራራ ላይ ወደምትገኘው ቤተ ፋጌ ወደምትባል ስፍራ ሲደርሱ ኢየሱስ …ደቀመዛሙርቱን አዘዛቸው ‹‹በአቅራቢያችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ … እንደደረሳችሁም አንዲት አህያ ከነውርጭዋ ታስራ ታገኛላችሁ ፣ ፈታችሁም ወደኔ አምጧት …ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ ((ጌታ ይፈልጋቸዋል)) በሉት ወዲያው ይሰዳቸዋል !!

እናም ደቀመዛሙርቱ እንደተባሉት አደረጉ ! አሁን ለአህያዋ የሆነውን ተመልከቱ …አንድ የተናቀችውን አህያ ያውም ጌታ በአድራሻዋ ሰው ልኮ ፈለጋት ….ሁለት አህያም ሁና በዛ ላይ እስረኛ አህያ ነበረች በኢየሱስ ትዛዝ ተፈታች …ሶስት በሉ … ከእስራቷ እንዳትፈታ ዘብ የቆመ ማንም ሰው ለምን ትፈቷታላችሁ ቢል የጌታ ስም ወላ ጠባቂ ወላ አስሮ የሚያስቀምጥን ባለቤት ዝም ከነሚያስብል ክብሩ አብሮ ተላከ !! ‹‹ጌታ ይፈልገዋል›› የተባለን ነገር …በዚች ምድር ማንም መንገድ ዘግቶ ትእዛዙን የመከልከል አቅም ያለው የለም !! ከዚህ ሁሉ ነገር በላይ የሚደንቀው ግን አህያዋ ከነሁርጫዋ ከመጣች በኋላ ልብስ በላይዋ ላይ አስቀመጡባት ይላል ….

መቸም አህያን ማዘነጥ የሚያስብ ማንም የለም ….ጌታ በላይዋ ላይ ተቀመጠባት …. መቸም አህያ ምንም ነገር መሸከም ብርቋ አይደለም ….ድንጋይም ትሸከማለች ዱቄትም ትሸከማለች በህይዎት ዘመኗ ብዙ ነገር ትሸከማለች አህያ !…. ተሸክማም እየተዠለጠች ትነዳለች ….የዛን ቀን ግን …ጌታ በላይዋ ላይ ተቀመጠ ! ልክ ሲቀመጥባት ሲዠልጣት የኖረ ህዝብ ከፊቷ ግማሹ ልብሱን ግማሹ የዘንባባ ዝንጣፊ እያነጠፈ ‹‹ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ …በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው›› እያለ በከፍተኛ እልልታና ክብር ከአህያዋ ፊት እየተደፋ !! በፊት ክብር ገፎ እርቃን ያስቀረ ሳይቀር ዛሬ የራሱን ልብስ እያወለቀ የራሱን ክብር እየጣለ ማልበስና ማክበር ጀመረ ..ለምን ….. እስከዛሬ ለተሸከመችው ዱቄት ነው ?…ወይስ እስከዛሬ የቀጠቀጧት ፀፅቷቸው ?….ለሁሉም አይደለም !!በላይዋ ላይ ለተቀመጠው ክብር ሲሉ! ለጌታ ሲሉ! ((ለተሸከመችው ክብር)) !!

ጓዶች . . . በተለይ ክርስትና ገብቷችሁ የእግዚአብሔርን አደራ ተሸክማችሁ ሰው የሆናችሁ ጓዶች ….ወላ ሰባኪ ወላ ዘማሪ ወላ ፌስቡከር ወላ ሰፊው ህዝብ…. ክብራችሁ ኢየሱስ ነው ….አለም ያከበራችሁ በሰው ፊት ከፍ ከፍ ያላችሁት በእናተ ማንነት በእናተ ችሎታና ብቃት አይደለም …በተሸከማችሁት ክቡር ስም ነው !! ጭብጨባው ሲበዛ ልነጠፍ ልዘርጋ አፈር አይንካችሁ የሚል ሲበዛ በማንነትና ችሎታችሁ ወይም በምርጥ ወግ አዋቂነታችሁ …አልያም በምርጥ ዘራችሁ … ብትፈልጉ በጉልበትና ገንዘባችሁም የተከበራችሁ መስሏችሁ የተሸከማችሁትን ክብር አትጣሉ !! የጣላችሁት ቀን የሳቀችላችሁ አለም ዱላዋን ይዛ ነው የራሷን ኮተት አሸክማ በውርደት የምትነዳችሁ !! ከዛ አውጥታ ለጅብ ! እንደዛ ነው ዓለም አሰራሯ ! ሸክማችሁ ሸክም አይደለም ክብር ነው !!ቀለለን ብላችሁ እንዳትጥሉት !!

የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ፣ “ኢትዮጽያ” የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ ሥራ ያልተነገሩ፣ ግን መታወቅ ያለባቸው እውነታወች።

የቴዲ አፍሮ 5ኛ አልበም እነሆ ለህዝብ ሊደርስ የቀናት ጊዜያት ቀርተውታል።ቴዲ ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ደጋግሞ ያነሳል፣ ሕዝቦቿ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በአንድነት ለዳር ድንበሯና ለሉዐላዊነቷ የከፈሉትን ከፍተኛ መስዋዕትነትና የአርበኝነት ውሏቸውን ፣ የቋንቋና የባህል ውበቷን፣ የሃይማኖቶችና የትውፊቶች ባለፀጋነቷን ፣ .. ጥንታዊነቷንና የሰው ልጅ መገኛ ቀደምትቷን በልዩ ዜማ ይመሰክርላታል ይቀኝላታል ይዘፍንተላታል ኢትዮጵያን።

በኢትዮጵያ አልበም ውስጥ የተካቱት ዘፈኖች ሁሉ። በአማርኛ ቋንቋ የተዜሙ ናቸው። የሙዚቃ ቅንብሩን ሙሉ በሙሉ የሃገራችን ታዋቂ የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት ነው። በተለይም የሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጳውሎስ አብላጫውን ስራ ሰርቷል። አቤል የተወዳጆቹን የጎሳዬ ተስፋዬን፣ የፀዴንያ ገ/ማርቆስንና የበርካታ ታዋቂ ድምፃውያንን ስራዎች ያቀናበረ ነው። ዝነኛው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅም በቴዲ ኢትዮጵያ። አልበም ላይ አሻራውን ያሳረፈ ሲሆን እንዲሁም ተወዳጁ አቀናባሪ አማን ሌላው ተሳታፊ ባለሙያ ነው።

አልበሙ ለህዝብ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው በትንሳኤ።ሳምንት በሚውለው በዳግሚያ ትንሳኤ (ሚያዚያ 14 /15 ቀን 2009 ዓ/ም) ነው። የቴዲ ማኔጅመንት አባላትና አልበሙን ለማከፋፈል ውል የፈፀሙት አካላት “ኢትዮጵያ” የሚለውን ዘፈን (Track) ብቻ ለትንሳኤ ለሕዝብ ለማድረስ ፍላጎት አላቸው። በዚህም መሰረት ለትንሳኤ ዋዜማ ቅዳሜ ሚያዚያ 7 ቀን 2009 ዓ/ም ለህዝብ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

የሃገር ውስጥ የአልበም ሽያጩን በተመለከተ ከቴዲ ማኔጅመት ጋር ውል የፈፀሙት አካላት በውላቸው መሰረት በሃገር ውስጥ 3 የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ለመስራት የተስማሙትን ታሳቢ በማድረግ ለጊዜው 4 ከተሞች በዕቅድ ደረጃ ተይዘዋል። እነሱም በመዲናችን አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ደሴና ሃዋሳ ሲሆኑ ጊዜው ሲደርስ ከደሴና ከሃዋሳ አንዱ ከተማ ላይ የሙዚቃ ኮንሰርቱ ይካሄዳል።

የመጀመሪያው ኮንሰርት አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያ አዲስ አመት ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን ቀጣዩ በሳምንቱ ባህርዳር እንደሚደረግም ይጠበቃል። ቴዲ አፍሮ በዘንድሮው የማኀበረ ግሩያን ዘረ ኢትዮጵያ 25ኛ አመት ልዩ የክብር ሽልማት ተሸላሚ በመሆኑ ሽልማቱን ለመረከብ ከቤተሰቡና ከወዳጅ ጓደኞቹ ጋር በሜይ ወር መጨረሻ ወደ አሜሪካ ይሄዳል።በአሜሪካ
ቆይታውም ሲያትል ዋሺንግተን በሚካሄደው የዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው ፌስቲቫል ላይና በአንዳንድ የአሜሪካ ከተሞች በጉጉት ለሚጠብቁት አድናቂዎቹ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ አዲስ አመት ከመድረሱ አስቀድሞ ባሉትም ቅዳሜዎች በጥቂት የአውሮፓ ከተሞች አዲሱንና የማይሰለቹትን ቀደምት ስራዎቹን ለማቅረብም ዕቅድም አለ።

በመላው አለም የሚገኙ የቴዲ አድናቂዎች በጉጉት የሚጠብቁትን ይህን ታሪካዊ አልበም በተመሳሳይ ቀንና ሰዐት ለገበያ ለማቅረብ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፤ በተለይም ከአገር ውጭ ለሚኖረው የሙዚቃ አፍቃሪ አልበሙ በአገር ውስጥ ለገበያ በሚቀርብበት በዚያው ዕለት የአልበሙ ተቋዳሽ ይሆናል ማለት ነው። እስካሁን ድረስ አልበሙን በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአውስትራሊያ ለማከፋፈል ፍላጎት ካለቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እየተደረገና ከተወሰኑትም ጋርም ውል የተፈፀመ ነው።

በሃገር ውስጥ የማከፋፈሉንና የማሳተሙን ድርሻ የወሰዱት አካላት የአልበሙን ማስተር ከአርቲስቱ ተቀብለው ወደ ህትመትና ማባዛት ሂደት የገቡ ሲሆኑ ፣ የህትመቱን ሃላፊነት በመውሰድ በኩልም በሃገር ውስጥ በቅርብ ጊዜ በዱከም ኢንዱስትሪ ዞን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የድምፅና የምስል ኮምፓክት ዲስኮችንና ዲቪዲዎችን ለማተም የተቋቋመው ቆልያ ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች ድርሻ ይሆናል።

ቀደም ብሎ በተለቀቀው የአልበሙ ፖስተር ዙሪያ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡበት የከረሙ ሲሆን በተለይም በስዕላዊ ማስታወቂያው ላይ ጦርና ጋሻ ይዘው የሚታዩትን አርበኛ፤ የራስ ነሲቡ ዘአማኑኤል መደበኛ ያልሆነው ጦር አባል የነበሩ ተዋጊ አርበኛ ናቸው።አርበኛ ራስ ነሲቡ እ.ኤ.አ በሜይ 1936 ዓ/ም የኢትዮጵያን ልዑካንን በመምራት ወደ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ በመምጣት በሊግ ኦፍ ኔሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ ሲሆን፣ ህይወታቸው ያለፈውም በዚያው አመት በጥቅምት ወር በረዷማዋ የስዊዘርላንድ ከተማ ነው።

የዚህ መረጃ ምንጭ © አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ ነው። እኔም (ይድነቃቸው ከበደ) ይህ ጠቃሚ መረጃ ለተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አድናቂዎችና አክባሪዎች እንዲዳረስ። ይህን አድርጊያለሁ። ለድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ካለኝ አክብሮት ብቻ ።

አዎ ! ፍቅር ያሸንፋል !!!

ከቆሼ ሰፈር ልጆች የተፃፈ መልዕክት «ክፉ ነው ደሃ መሆን»

(ለቆሼ ሠፈር ልጆች) የችግሩ ጥግ ቆሻሻ ላይ የላስቲክ ቤት ያሰራሃል፡፡ መሠረት ስለሌለህ የሚያውቅህ የሚያስብልህ መንግስት አይኖርህም፡፡ ጥሩ መልበስ ንፁህ መብላት ያንተ የልብ መሻቶች አይሆኑም፡፡ አንገትህን ደፍተህ ነገን ትናፍቃለህ፡፡ ተፈጥሮ ፊቷን አዙራብህ ስትፍጨረጨር ሠዎች በፈጠሯቸው ተልካሻ ምክንያቶች ሕይወትህ ያልፉል፡፡ ቤትህ ተንዶ ማቅ ላይ ብትሆን እንኳን ጩኸትህን የሚሰማ አምቡላንስ እንጂ የሚያድን ወገን የለህም፡፡ ምክንያቱም አንተ ደሃ ነህ!
‹‹ኢስከን›› ( ትርፍራፊ) እየበላህ ያደክ ፤ የተማርክ ደሃ! ይሄ ነው የኔና የሠፈሬ ልጆች ኑሮ፡፡ ይሄም ኑሮ ሆኖ ይሄ ሁሉ ሃዘን ታዲያ ስለምን? … ዳሩ አንድ ቀን እንደ ሠው የምንታይበትና የምንኖርበት ቀን ይመጣል፡፡ ለሞቱት ነፍስ ይማርልን! … በጣር ላይ ላሉትሞ እግዚሔአብሔር ይሁናቸው፡፡ … ወይ ቆሼ ምግባችንም፤ ሞታችንም አንተው ትሆን! …›› በአሽናፊ እንዳለ
«ሼር እና ላይክ በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»

 Image may contain: 1 person, close-up

የኢትዮጵያዊቷ ሞደሊስት የዘር ሐርግ ፍለጋ ከአሜሪካ እሰከ ኦሞ ወንዝ የተደረገ የጉዞ ቅኝት

“እነዚህ ድንቅ ጎሳዎችን በስልጣኔ ሰም ከመጥፋታቸው በፊት መጎብኘቴ ትልቅ እድል ነው”ሞዲሊስት ፋጡማ ስይድ

እውቋ ሞደሊስት ፋጡማ ሰይድ የሁለት እህቶቿን በሶማሊያው የአርስ በርስ ጦርነት ካጣች በሁዋላ ከአስራ ሶስት አመቷ ጀምሮ በሰደት ያደገችበት የአሜሪካኑ የቦስተን ከተማን በተለይ ደግሞ ዛሬ ብዙዎች የሚያውቋት የኒዮርክ ከተማን “ቤቴ ነው “ብትለውም በውስጧ አንድ የጎደላት ነገር እንዳለ ከተረዳቸው ክረምረም ብላለች። እርሱም የማንነቷ ጥያቄ እና የዘር ሐረጓ ከየት እንደ ተመዘዘ ጠንቅቆ ማወቅን ነበር ።

ከኢትዮጵያዊ አባቷ እና ከሶማሊያዊ እናቷ በመጸነስ የዛሬ 29 አመት ወደዚህ አለም ብቅ ያለቸው ፋጡማን ብዙዎቹ ምእራባዊያን የፋሺን አዘጋጆች እና ስፓንሰሮች የሚያውቋት በ ጥቁር ፣እንቁ እና ሞደሊስትነቷ በኒዮርክ፣በፓሪስ፣በሎንዶን፣በሚላን ፣ በአቴንስ እና በመሰል መደረኮች ላይ ውብ ምስሎቿን እንጂ ከየተኛው ምድር እንደ በቀለች እራሷም ብትሆን ከልጅነት ምናቧ ውጪ በቅጡ የምታውቀው አትመሰልም ነበር።

ለዚህም ይመሰላል በቅርቡ ከምትኖርባት የኒዮርክ ከተማ በመነሳት የሰው ልጆች መገኛ ከሆነቸው ከምድረ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ የወላጅ አባቷ የዘር ሐርግ ከሚመዘዘባት እና በዘመናዊ ስለጣኔ ስም (ለሸንኮራ አገዳ ተክል ልማት እና ለግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀችት ሲባል) ከ200 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቀያቸው የመፈናቀል አደጋ ሊገጥማቸው ይችላል አሊያም የተፈጥሮአዊ የአኗኗር ኡደታቸው ሊቋራጥ ግድ ይላል ተብሎ የሚሰጋላቸው በጥንታዊ እና ማራኪ የአኗኗር ስልታቸው የበርካታ ጎብኘዎች እና የተመራማሪዎች ቀልብን የሚስቡት ከ 12 የሚበልጡ የተለያዩ ጎሳዎች የሚገኙበት ከኦሞ ወንዝ አቅራቢያ (ከደቡባዊው የአገሪቱ ክልል) ነበር የተጓዘችው።የፋጡማ የደቡብ ኢትዮጵያ ጉብኘት የዘር ሐረጓን ፍለጋ ብቻ ሳይሆን በስልጣኔ ሽፋን ከአይናቸን ሊጠፉ የሚችሉትን የኦሞ ወንዝ ያፈራቸው ኢትዮጵያዊያኖችን በግንባር እና በአይኗ ተገኘታ ለመቃኘት ሲባል “ከጊዜ ጋር የተደረገ እሸቅድምድም” መሆኑን አስረግጣ ተናግራለች።

ከዘመናችን እውቅ ሞዲሊስቶች መካከል አንዷ የሆነችው ፋጡማ የኢትዮጵያ ምድርን ስትረግጥ እነዚያ ብዙ ምእራባዊያን የምጣኔ ባለሙያዎች የመሬት ሽያጩ እርሷ ከከተመችበት ከኒዮርክ ከተማ እጅግ የናረባት የ አ/አ ከተማ እና ዘመናዊ ህንጻዎቿን ብዙም ሳትቃኝ በበነጋታው የዘር ሐርጓ ትስስርን ለመፈለግ ወደ ደቡባዊ ኢትዮጵያ ያደረገችው ጉዞን በተመለከተ በአለም ታዋቂ ሞደሊስቶች ፣የፋሺን ዲዛይነሮች ፣አደናቂዎች እና የመሳሰሉት ዙሪያ የሚያውጠነጥነው “ቮጎስ” የተባለ ታዋቂው መጽሄት ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 9/2016 እኤአ ሲዘግብ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ደም ሰላላት እውቋ ሞዲሊስት ፋጡማ ሲዘግብ ፋጡማ በኢትዮጵያ ቆይታዋ የልጅነት ጊዜዋን ባሳለፈችው አርብቶ አደሮች በሚበዙበት በጎረቤት ሶማሊያ (በእናቷ አገር) የነበረው ኑሮ በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ከሚኖሩ ጋር ተመሳስይነት እንዳለው ለመረዳት መቻሏን ተናግራለች።

እራሰቸውን በተለያዩ መንገዶች ከሚገልጹት ከሙርሲዎች (ከንፈራቸውን በትልቅ ሸክላ የሚወጥሩት) ፣ከዶርዚዎች (በሸማ ፣በ ፈትል ሰራ እና በድንቅ የጎጆ ቤት አሰራር የተካኑት)፣ ከ ከሮዎች (እራሳቸውን ነጭ አፈር በመቀባት የሚያሰወቡት) ጎሳዎች ጋር ለመገናኘት ከመቻሏ በተጨማሪ ወንድ ልጆች ለጉርምሳና ለመድረሳቸው መለኪያ/መፈተኛ የሆነው በርድፍ በቆሙ የቀንድ ከብቶች/ሰንጋዎች ጀርባ ላይ መዘለል ፣ ታዋቂው የምሽት ጭፈራን ( ኢቫንጋዲን) ከማየት በመለጠቅ በዶርዜዎች ቤት ተገኝታ በልጅነቷ ታደርገው የነበረው ለእናቶች ውሃ የመቀዳት ባህልን በተግባር ተወጥታለች ፣የሸማ ሰራ/ ጥጥ የመፍተል ስልጠናን ወስዳለች ፣ የማህበረሰቡን ከብቶችም ጠብቃላቸዋልች ።በስተመጨረሻም ከደሳሳ ነገር ግን በፍቅር ከተሞላው ጎጆዋቸው ተጋብዛ ቡና በጋራ ለመጠጣት በቅታለች። ዘውትር ቢቀርቧቸው እና ቢጎበኙ ከማይሰለቹት የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች እና ተፈጥሮ የደለቸው መልካ ምድሯ ጉብኝት መልስ በአ/ አ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቿ ጋር በዚያ በመከረኛው እና ትወልድ ገዳይ በሆነው በጫት እና ሺሻ(ሁካ) ዙሪያ እንደተገናኘች ፣ለማሰታውሻነት የተለያዩ ኢትዮጵያ ነክ አልባሳትን እና ጌጣ ጌጦችንም እንደገዛች የመትናገረው ፋጢማ የኢትዮጵያ ጉዞዋ ከአይምሮዋ የማይረሳ ትዝታ እንደጣለባት እና የምስራቅ አፈሪካ ቁርኝቷን ይበልጥ ያጠናከረላት መሆኑንም ሳትገልጽ አላለፈችም።
ፋጡማ በደቡብ ኢትዮጵያ(የኦሞ ወንዝን ብቸኛው ተገናቸው እና እስትንፋሳቸው ያድረጉ) ወገኖቻቸን ማየቷን በተመለከተ “በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ከምላቸው ክስተቶች መካከል ጉልሁ እና አንዱ ነው “ በማለት ከጉዞዋ መልስ በቲዊተር አካውንቷ ላይ ያሰፈረቸው ሲሆን የእነዚህ ዝርያቸው በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮአዎ ክስተቶች ሳቢያ በመመናመን እና በመጥፋት ላይ ያሉት ጎሳዎች የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይን በተመለከተ የተለያዩ የሰበአዊ መብት እና የአካባቢያዊ እንክብካቤ ተቶርቋሪዎችም ጭምር ስጋት ከመቼውም ጊዜ በላይ ሲያሰተጋባ ይሰማል። በተቃራኒው ደግሞ “ቱሪዝምን ጨምሮ በሁሉም መሰክ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ እሆናለሁ” የሚለው (ባለ ራእዩ) አገዛዝ ጩሀቱን እና ውግዘቱን በተመለከተ “ተቃውሞው ለዜጎች ዘላቂ መብት ከሚቆረቆሩ ወገኖች ሳይሆን ፈርንጆችን ለማሰደሰት ከሚዳክሩ ቡድኖች የመነጨ ወቅሳ ነው”በማለት ስጋታቸውን ያጥላላል። ታዲያ እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ የኦሞ ወንዝን መከታ ያድረጉት ቀደምት እና በአለማችን ላይ እጅግ ውብ የሆነ የአኗኗር ስልት ካላቸው ጎሳዎች የሚጠቀሱት ወገኖቻቸንን ባሕላቸውን፣ እኗኗራቸውን እና ቀያቸውን ሳይቀይሩ ህይወታቸው የሚሻሻልበትን መንገድ መቀየስ ወይስ በዘመናዊነት ምክንያት “ነበሩ”ሚለውን ብሄልን ማፋጠን? የሚሉ የሁለት የክርክር መድረኮች ተከፍተዋል።