በደብረ ዘይት የሚገኘው የአየር ኃይል ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሆነ ምንጮች ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያውያን ፓይለቶች አታበሩም ተብለው ግራንድ ከተደረጉ በኋላ ከምስራቅ አውሮፓ የመጡ ቅጥረኞች ብቻ እንዲያበሩ መወሰኑን ተከትሎ 40 የሚሆኑ አብራሪዎች የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፤ መልቀቂያ ያስቡት አብራሪዎች ግዳጃቸው እስከሚቀጥለው ሐምሌ ወር ድረስ ብቻ እንደሚሆንም ታውቋል፡፡
የአገልግሎት ጊዜያቸው ገና በመሆኑ ምክንያት መልቀቅ የማይችሉት አብራሪዎች ሥራቸውን ጥለው እየጠፉ እንደሆነ የሚናገሩት የመረጃ ምንጮች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አራት የዐማራና ሰባት የኦሮሞ ተወላጅ አብራሪዎች ሲጠፉ ተይዘው ታስረዋል ተብሏል፡፡ ከታሰሩት አብራሪዎች መካከል አንድ የዐማራ ተወላጅ አብራሪ የደረሰበት እንደማይታወቅና ከጎንደር የሔዱ ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሊያገኙት እንዳልቻሉ ነው የተነገረው፡፡
ሌላው ለውጥረቱ መንስኤ ነው የተባለው በከፍተኛ ጀነራሎቹና በታችኛው እርከን ላይ ባሉት መካከል ልዩነት መፈጠሩ ነው ያሉት ምንጮች ወታደራዊ እዝና ተዋረድ መተግበር ካቆመ እንደሰነባበተ ገልጸዋል፡፡ ለአየር ኃይል አባላት በየትውልድ ቦታቸው የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ተፈቅዶላቸው የነበረውን አፈጻጸም ላይ ችግር መኖርም ሌላው የውጥረቱ መንስኤ ነው ብለዋል፡፡ የአየር ኃይል እማኞች እንደሚሉት በአየር ኃይል ግቢ ውስጥ የተፈጠረው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ የተለየ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከ89 ሺ የሚበልጡት ኢትዮጵያዊያን ከሳውዲ አረቢያ ተይዘው ሀገር ቤት መመለሳቸው ተሠማ፡፡

ባህር አቋርጠውና ድንበር ሰብረው በህገ-ወጥ መንገድ ሳውዲ አረቢያ ከገቡት መሀከል በአንድ አመት ብቻ ከ89 ሺ የሚበልጡት ኢትዮጵያዊያን ተይዘው ሀገር ቤት መመለሳቸው ተሠማ፡፡

ከ2 ሺ 897 የሚልቁት ደግሞ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወርና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በሳውዲ አረቢያ እሥር ቤቶች እየማቀቁ ነው ተብሏል፡፡

ሸገር ወሬውን የሰማው የጀርመን ሬዲዮ ድምፅ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙትን የኢትዮጵያን ኤምባሲ የዲያስፖራ እና የቆንስላ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑትን አቶ ፋይሰል አልዩን ጠይቆ ካዘጋጀው ወሬ ነው፡፡

ሳውዲ አረቢያ በባሕርና በየብስ በተለያዩ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ድንበሬን ተላልፈው ገብተዋል ብላ ከምታባርራቸው የዓለም ዜጎች መሀከል ኢትዮጵያዊያን ቀዳሚዎቹን ቁጥር መያዛቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ከጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም እስከ መስረም 2009 ዓ.ም ድረስ በነበረው አንድ ዓመት ብቻ ከሳውዲ አረቢያ የተባረሩና ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከ89 ሺ በላይ ነው ተብሏል፡፡

በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች አማካይነት ባሕር አቋርጠውና ድንበር ሰብረው ሳውዲ አረቢያ ከገቡ በኋላ ተይዘው የተመለሱት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በአማካይ በየሣምንቱ 246 ነውም ተብሏል፡፡

ከሳውዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሚቀርብለት ጥያቄ መሠረት ኢትዮጵያኖቹን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ሪያድ ያለው ኤምባሲ ለሚመለሱት ሰዎች የሚሆን ከ2 ሺ 500 ጊዜያዊ ሰነድ በላይ በየሣምንቱ እያዘጋጀ ነው ሲሉም አቶ ፋይሰል ለወሬ ምንጩ ተናግረዋል፡፡

ከሪያድ በተጨማሪ ጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንፅላ ጽ/ቤትም ተመሣሣይ ቁጥር ያለውን ጊዚያዊ ሰነድ እያዘጋጀ ተመላሾቹ ሀገር ቤት እንዲገቡ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ሀገር አቀፍ ግብረ-ሃይል ከሦስት ዓመታት በፊት ቢመሰረትም ህገ-ወጥ ጉዞዎቹ ዛሬም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተደረጉ መሆኑን ይነገራል፡፡

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወታደሮች በሰሜን ጎንደር የወያኔ ፖሊስ ጣብያ ላይ ጥቃት አደረሱ ተባለ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች  በሰሜን ከጎንደር 50 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኝ ከተማ ዘልቀው በመግባት የከተማውን ፖሊስ ፅ/ቤት ማጥቃታቸው ተነገረ::

በጥቃቱም ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን በከተማው በፀጥታ ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙት የመከላከያ ፤ የፀረ ሽምቅ የሚሊሻ እና የመደበኛ ፖሊስ ላይ ለ45 ደቂቃ የቆየ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ተሰምታል::

ከወያኔ በኩል 3 ሰዎች ተመትተው 2 ወዲያውኑ ሲሞቱ አንደኛው ሆስፒታል ገብቶ የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም መትረፍ ባለመቻሉ ዛሬ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል ተብላል ::

በውጊያው ወቅት በርካታ የፀጥታ ሀይሎች በመሮጥ ራሳቸውን ሲደብቁ ታይተዋል :: በዚህ ድርጊታቸው የተበሳጨው የዞኑ ኮማድ ፖስት በ12/07/09 ስብሰባ በመጥራት የከተማውን ፖሊስ አዛዥ ፤ በወቅቱ የፀረ ሽምቅ ጋንታ አመራር እና የመከላከያ የቲም አመራር የነበሩትን ከስራ በማገድ ያሰራቸው ሲሆን ሌሎች አመራሮችም በከተማው ከፍተኛ ተኩስ ሲደረግ ከቤትና ከካምፕ ወጥተው ማገዝ ሲገባቸው ይህን ባለማድረጋቸው ከሀላፊነት ታግደዋል ::

ይህን ዘመቻ ያደረጉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ግዳጃቸውን ጨርሰው ወደ ቦታቸው በሰላም መመለሳቸው ተነግራል ፡፡

የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትላቸው ከሃገር ኮበለሉ

የበርካታ ሚሊዮን ብር ብክነት ሪፖርት የቀረበባቸው የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከሃገር መኮብለላቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ሁለቱ ባለስልጣናት ከሃገር የኮበለሉት ስራቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ መሆኑንም መረዳት ተችሏል።
ባሳለፍነው ታህሳስ ወር የ16 ሚሊዮን 863 ሺ 33 ብር ከደምብ ውጭ ህገወጥ የመድሃኒት ግዢ ፈጽመዋል በሚል በፓርላማ ሪፖርት የቀረበባቸው ዋናው ዳይሬክተር አቶ መስቀሌ ሌራ እና ምክትላቸው ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ በቦሌ በኩል በህጋዊ መንገድ ከሃገር መውጣታቸው ታውቋል።
በአለም አቀፍ ድርጅቶችና የውጭ መንግስታት ድጋፍ የሚደረግለት የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ከተመሰረተ እኤአ ከ2007 ጀምሮ ከፍተኛ ምዝበራ ሲካሄድበት መቆየቱም ተመልክቷል። በታህሳስ ወር 2009 ለፓርላማ በቀረበ በጠቅላይ ኦዲተር ሪፖርት በህገወጥ አሰራር ወደ 17 ሚሊዮን ብር በማውጣት የተወነጀሉት ሁለቱ የስራ ሃላፊዎች፣ ለጤና ተቋማት መሰራጨት የነበረባቸው የ569 ሚሊዮን 833ሺ 919 ብር ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎች ሳይሰራጩ በመገኘታቸውም ተጠያቂ መሆናቸውን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ከለጋሾች የተገኘ ወደ መቶ ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ብር በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማባከን ስማቸው የተነሳው የኤጀንሲው ሃላፊዎች ወዲያውኑ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁ ቢሆንም፣ ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ ሃገር ጥለው መጥፋታቸው ተመልክቷል።
ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መስቀሌ ሌራ እና ምክትላቸው ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ ከሃገር ህጋዊ በሆነ መንገድ የወጡት ተባባሪዎቻቸው በሆኑት የመንግስት ባለስልጣናት ድጋፍ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ብክነት የዳረጉት የልማት ባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ ባህረም በተመሳሳይ ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ በህጋዊ መንገድ ከሃገር መውጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ከደህንነት ሚንስትር አፈትልኮ የወጣ መረጃ

የህዝብን ትኩረት ለመሳብ ወይንም ለማስቀየር በባለሥልጣኖች ላይ ትችት ማቅረብ በተለይ በውጩ አለም ያሉትን የተቃወሚ ኋይሎችን በሚያወጧቸው መረጃዎች ላይ ጥልቅ ጥናት ተካሂዶበታል።የነአባይ ጻሃየ ካብኒና በአባይ ወልዱ የሚመራው የተለያዩ አስተያየት ሰንዝረዋል፡አባይ ጻሃየ
የህወሃት ባለሥልጣናት በተለያዩ ሚዲያዎች አስመሳይ ነገሮችን ለህዝብ ተስፋ ሰጭ መርህዎችን በመስጥት የመጣብን ጫና በንደዚህ አይነት ካልሆነ ልንቋቋመው አንችልም ፡በማለት ተናግሯል።አንዱ ወገን ያቀረበ ሲሆን በሊላኛው አባይ ወልዱ ጠቅላይ ሚንስትሩን ኋይለማሪያም ደሳልኝ ለምን ከስልጣን አናወርዳቸውም፡በምትኩ ቴዎድሮስ አድኖምን ማሰቀመጥ አለብን መለስ ዜናዊ ይሂን ቦታ መያዝ ያለበት ደኩትሩ ነው ብሎ ነበር ።በማለት ሲናገር ፡ሊሎች በፈንታቸው አንድኛ ለአለም ጤና(WHO)ቦታ ከተሰጠው ለእኛ ትልቅ ድጋፍ አለን ። ይሂማ ካደርግን በውጩ አለም የድፕሎማሲያችን መርህ ይበላሻል፡በባለፈው ከአሜሪካ በኩል የአንድ ብሔር ስብስብ ነው ተብለን ተፈርጀናል ስለዚህ ሊላ እናስቀምጥ ብንል ከሊላ ብሔር እንደ ደሣለኝ ኋይለማሪያም ታዛዥ ለሥራቱ ታማኝ አይገኝም በዛው መቀጠል አለበት ብለዋል ።ይልቁንስ ይህ ሥልጣን ከእጃችን እንዳይወጣ ማድረግ ያለብን ከፍተኛ በጅት መድበን የአርበኞች ግንቦት ሰባትን መዋቅር ለማዳከም መስራት አለብን ሊላውን እንተወው ኋይል ያለውና ተፅኖ ፈጣሪው ይህ ድርጅት ነው ትኩርውታችን ውደ ዚህ መስራት አለብን በማለት ስብስባውን ባጭሩ ቋጽተውታል።
ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ።
ሞት ለባንዳ ወያኔ
ይሂን ሚስጥር ላካፈሉና ለተባበሩኝ ውድ ታጋዮች
ለውስጥ አርበኛ ታጋዮች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ
ካርበኞች መንደር አሞራው ምንአለ ባሻ

%d bloggers like this: