የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት “አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት አድማ መጀመራቸውን ተሰማ

ፖሊሶቹ አድማውን የሚያደርጉት ቢሮአቸው ውስጥ ያለ ስራ በመቀመጥ መሆኑን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። የአድማው መነሻ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንደማይሰጣቸው መታወቁን ተከትሎ ነው። የከተማው አስተዳደር የልዩ ሃይል እና የፖሊስ አባላት መሬት እንደሚሰጣቸው ከገለጸ በሁዋላ፣ ረዳት ኮሚሽነር ደስዬ ደጀኔ ለከተማ አስተዳደሩ ትዕዛዝ በመስጠት ቦታ እንዳናገኝ አስከልክሎናል በሚል አድማ መጀመራቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

አድማውን የሚያስተባብሩ አካላት “ እኛ መሬት ለማግኘት ስንል ግደሉ ስንባል መግደል?” አለብን ወይ በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ “ መሬት ለማግኘት ስንል ህዝብን አንጨፈጭፈም” የሚል አቋም በመያዛቸው ከአዛዦች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ችግሩን በሽምግልና ለመፍታት በሚል የተወሰኑ ሰዎች እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

የክልሉ ፖሊሶች ከዚህ ቀደም የህወሃት የበላይነት ይብቃ በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር መዘጋቡ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ የመጀመሪያው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደታወጀ፣ የክልሉን ፖሊስ እንደገና የማደራጀት ስራ ተሰርቷል። የህወሃትን የበላይነት ይቃወማሉ የተባሉ የፖሊስ አዛዦች ከስራ እንዲባረሩ ወይም እንዲታሰሩ ተደርጓል።

Advertisements

የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ መግለጫ ማውጣቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ለአሜሪካ አምባሳደር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫ ሰራተኞቹ ከአዲስ አበባ ውጪ በምንም አይነት መንቀሳቀስ አደገኛ ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል ብሏል።
እናም በሀገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን የሚሰጡትን መረጃ በመከታተል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋልም ነው ያለው። በኤምባሲው መግለጫ መሰረት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ሰልፎችና ሕዝባዊ አመጾች ድንገት ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ቀውስ ሊባባስ እንደሚችል ነው ያስጠነቀቀው።

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫ መነሻ በማድረግም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ ማሳሰቢያ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአዲስ አበባ ከአሜሪካው አምባሳደር ማይክል ሬይነር ጋር በሀገሪቱ ባለው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተነግሯል።

አቶ ደመቀ አምባሳደሩን በጽሕፈት ቤታቸው ለማናገር የተገደዱት አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳይ በእጅጉ ያሳሰባት በመሆኑ ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በኩል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ ስብሰባ ላይ መሆኑ ይነገራል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለ3 ወራት ወይም ለ6 ወራት ሊደነገግ እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል።

በወልዲያ እና ዙሪያዋ ዳግም አመፁ አገረሸ

ህዝባዊ ንቅናቄው አድማሱን እያሰፋ ነው የወያኔ ህወሀት ስርሀት ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ መሆኑ እየተነገረ ነው።

ጥር 21 ቀን 2010 ዓ/ም ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ ተጀምራል ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን የገለፀ ሲሆን ህወሓትና የእሱ አገልጋዩ ብአዴን ባደረጉት መተናኮል ሕዝብ ተበሳጭቶ እርምጃ መውሰድ ጀምራል ፡

ቀደም ሲል ጨፍጫፊዎችን እነ ህወሓት ይቃወማል እርምጃ ይወስዳል የሚል የተሳሳተ ግምት ይዘን ብአዴንን ብንጠብቀውም ጭራሽ ገዳዩችን ደግፎ መግለጫ መስጠቱ ቁጣውን ቀስቅሶ ብአዴን ሕዝብን ለማፈን እና የህወሓትን መመሪያ ለማስፈፀም የሚጠቀምባቸው ተቃማት ላይ ጥቃት እየተፈፀመ ይገኛል ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ በሮቢት ከተማ ሕዝብን ለመሰብሰብ የሔደው የፊዲሪሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔው ያለው አባተ በሕዝብ ተዋርዶና ያሰበው ሳይሳካ ተባራል ፡፡ በአሁኑ ሳዓት የሕዝብ ቁጣ ጨምራል ቆቦ እና አካባቢው ነገሮች እየተቀያየሩ ይገኛሉ::

በመርሳ ወታደሮች ተሰብስበው በነበረበት ወቅት በተወረወረ ፈንጅ ፩፰ ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፩፮ ወታደሮች ህክምና አግኝተው ከሆስፒታል ሲወጡ፣ ሁለት ወታደሮች ግን በጽኑ ቆስለው ወልድያ ልዩ ክትትል በሚደረግበት ክፍል ውስጥ ተኝተዋል ተብላል።

የህወሓት ኤፈርት የሆኑ ንብረቶች በህዝቡ እርምጃ ተወሰደባቸው ተባለ

ጥር16 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 4:45 ሲሆን ጨለማን ተገን አድርገው እና በህወሓት ታጣቄዎች ታጅበው ከደቡብ ጎንደር ጋይንትና ከሰሜን ወሎ ወረዳዎች በሁለት ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች እስከነ ተሳቢያቸው የተጫነ ለህወሓት ችፑድ ፋብሪካ ግብአት የሚሆን የጥሪ ዕቃ ጭነት መረጃው በደረሳቸው አርበኞች ሰሜን ወሎ ሮቢት ከተማ ላይ በደፈጣ በመጠበቅ ጭነቱን ሙሉ በሙሉ ጥሪ ዕቃዎችን ከተሽከርካሪዎች በማውረድ አቃጥለውታል፡፡

በወቅቱ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ሹፊሮችና ባለቤቶች ቀደም ሲል ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው እና መረጃም ያልነበራቸው መሆኑን ግንዛቤ በመውሰድ እና ሊሎችንም ሊያስተምሩ ይችላሉ በሚል ስምምነት አንደኛው ተሽከርካሪ ወደ ወልዲያ ሲመለስ አንደኛው ደግሞ ወደ ደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ተመልሷል ፡፡ ይህ እርምጃ የተወሰደው አርበኞች እኛ ጠባችን ንፁሀንን ዜጎች ከሚጨፈጭፍ ፡ የአገሪቱን አንድነት ከሚበታትን ዘረኛ ከሆነው ከህወሓት ጋር እንጄ ከሊላ ጋር ከማንም ጋር አይደለም፡፡ ስለሆነም ህወሓት እርስ በርስ ለማጋጨት እና በማሀከላችን መጠራጠርን ለመፍጠር ህዝባዊ እንቢተኝነት ሲነሳበት በነዚህ ቦታዎች ለሰራዊቱ እና ለህወሓት ፋብሪካዎች አገልግሎት የሚውሉ ጥሪ ዕቃዎች እና የጦር መሳሪያዎችን በሲቪል እና በነዚህ አመፅ በተነሳባቸው ከተሞች ነዋሪዎች በሆኑ ተሽከርካሪዎች ይጠቀማል ፡፡

ማምሻውን በቆቡ የሚገኙ የህወሀት የእርሻ ኢንዱስትሪዎች በእሳት መጋየታቸው ተገለጸ። የዘለቀ እርሻ ሜካናይዜሽን ወይም የወልዲያ አትክልትና ፍራፍሬ፡ የራያ ፍሬ በእነአዜብ መስፍን የሚመራ፡ የእርሻ ማሳዎች ወድመዋል። የእህል መጋዘኖች እህሉ ለህዝብ ከተከፋፈለ በኋላ መጋዘኑ ተቃጥሏል። ተጨማሪ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በእሳት እንዲወድሙ ተደርገዋል። ክ15 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው ታውቋል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ማምሻውን መግባታቸው እየተነገረ ነው።

ስለሆነም ይህን አውቃቸዋለሁ በአሁኑ ሳዓት ወደ ትግራይ የሚወስድ መንገዶች በሙሉ ዝግ መሆናቸውን አውቃቸዋለሁ ማንኛውንም ሸቀጥ ይሁን ዕቃዎች ጭናቹሁ በምትመጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ኝርምጃ የሚወሰድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን ፡፡ ይህን ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ኃላፊነቱ የራሱ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

የትግራይን ህዝብ ለመካስ አዲሱ አመራር ቆርጦ ተነስቷልስ ሲሉ ጅሉ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

የትግራይን ህዝብ ለመካስ አዲሱ አመራር ቆርጦ ተነስቷል። በኢትዮጵያ በክልሎች መካከል ሰፊ የልማትና የእድገት ልዩነት ፖለቲካዊ ቀውስ በፈጠረበት በዚህን ወቅት የአቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ ቀውሱን ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

የ2016 የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መረጃ እንደሚያመለክተው ከህዝብ ብዛትና ከቆዳ ስፋት አንጻር በትግራይ ክልል የተሰራው የአስፋልት መንገድ ከሌሎች ክልሎች በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ነው። በሆስፒታል ተጠቃሚነት የትግራይ ክልል በቀዳሚ ስፍራ ላይ ይገኛል።

በትግራይ አንድ ሆስፒታል ለ285ሺህ ሰው አገልግሎት ሲሰጥ ፦

በአማራ ክልል አንድ ሆስፒታል ከ1ሚሊየን በላይ ለሆነ ህዝብ የሚዳረስ ነው።

በኦሮሚያ 1 ሆስፒታል ለ900ሺህ ሰው አገልግሎት ይሰጣል።

6 ሚሊየን ህዝብ ባላት በትግራይ በሶስት ከተሞች ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ሲገነቡ ከ5 እጥፍ በላይ የህዝብ ብዛት ባለው የኦሮሚያ ክልል በሁለት ከተሞች ብቻ እንዳለ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከ66 በላይ ኩባንያዎች ያሉት የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ድርጅት ኤፈርት በትግራይ ክልል ከ100ሺህ በላይ የስራ እድል ፈጥሯል። ንጽጽሩ ብዙ ነው። በየዘርፉ የሚታየው ልዩነት ግልጽ ነው። በዩኒቨርስቲ ብዛትና ጥራት፣ በኤሌክትሪክ አቅርቦትና በኢንዱስትሪ ግንባታ በትግራይና በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች መካከል ያለው ልዩነት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ዋነኛ ማጠንጠኛ ሆኖ ዘልቋል።

የእድገትና የልማት ልዩነቱን ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጭምር በመረጃ አስደግፈው በማሳየት ላይ ሲሆኑ ወደ አንድ አካባቢ ያደላው ተጠቃሚነት ኢትዮጵያን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንዳይከታት ስጋቱ ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው።
መቀሌ ላይ እየተካሄደ ባለው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሀት 7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የህወሀቱ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ህዝብ ከከፈለው መስዋዕትነት አንጻር ያገኘው በጣም ኢምንት ነው።

የትግራይ ህዝብ አሁንም በከፈለው ዋጋ መጠን ውለታ ይቅርና ከሩብ በላይ ህዝብ አሁንም በመራራው ድህነት ስር የሚኖር ህዝብ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው ከማንም በላይ ውድ ዋጋ የከፈለው ይህ ህዝብ የሚካስበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።
ሳይበላ በልቷል እየተባለ የውሸት ሪፖርት የሚቀርብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጌታቸው አዲሱ አመራር የትግራይን ህዝብ ለመካስ ተዘጋጅቷል ማለታቸውን ከምንጮች መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

አምባገነኑ የደርግ ስርዓት ያንበረከከው የትግራይ ህዝብ በዚህ ዘመን የቀበሌ አመራሮችን እንዲፈራ ተደርጓልም ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው አዲሱ አመራር ይሄን ህዝብ ከዚህ ችግር ለማላቀቅ ቆርጦ ተነስቷል ብለዋል ቃል አቀባዩ። ኢሳት ያነጋገራቸው የፖለቲካ ምሁራን በኢትዮጵያ የተዛባ የእድገት ልዩነት እንዲፈጠር በማድረግ ሀገሪቱን ለከፍተኛ አደጋ የዳረገው ህወሃት የትግራይን ህዝብ ይበልጥ ተጠቃሚ አድርጎ መነሳቱ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ያባብሰዋል ብለዋል።

%d bloggers like this: