የዚካ ቫይረስ በሽታ የአለማችን አዲስ ስጋት

alladdis.net's photo.

ሰላም ውድ የገፃችን ተከታታዮች ዛሬ የአለማችንን ትኩረት ስለሳበው አዲሱ በሽታ እናወራለን እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡
የዚካ ቫይረስ በሽታ
ዚካ ቫይረስ የፍላቪቫይረስ ዝርያ ሲሆን ከደንጉ፣ ቢጫ ወባና ከምዕራብ ናይል ቫይረስ በሽታዎች ጋር የሚመሳሰል ባህሪአለው፡፡ ይህ ቫይረስ ዚካ ፌቨር ወይም የዚካ በሽታ ለተባለ በወባ ትንኝ ለሚተላለፍ በሽታ መነሻ ነው፡፡ የዚካ ቫይረስ በአሁኑ ጊዜ የአለምን ትኩረት እየሳበ የመጣ በሽታ ሊሆን ችሏል የዚህም ምክንያት ጥናት አድራጊዎች በሽታው አዲስ ከተወለደ ህፃን የጤና ችግርና ከአእምሮ ችግሮች ጋር የተያያዘ ሆነው ስላገኙት ነው፡፡
✔የዚካ ቫይረስ ስርጭት
ዚካ ቫይረስ በመጀመሪ የተገኝው በ1947 ዓ.ም በኢንቴቤ ኡጋንዳ ውስጥ በሚገኝ በዚካ ጫካ ረኸሰስ በሚባል የዝንጀሮ ዝርያ ደም ውስጥ ነው፡፡ ይህ ቫይረስ በሰውና በወባ ትንኝ ውስጥ በኡጋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ናይጀሪያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ማሌዢያ ተገኝቷል፡፡
በ2007 በጣም ከፍተኛ የሆነ የዚካ ቫይረስ ኢንፌክሽን ያፕ በተባለ ደሴት የተከሰተ ሲሆን 75% የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል በወረርሽኙ ተጠቅቶ ነበር፡፡
የዚካ ቫይረስ እስከ ሜይ 2015 ድረስ በምዕራብ ንፍቀ ክበብ ስርጭቱ አልተከሰተም ነበር የብራዚል ህብረተሰብ ጤና ባለስልጣን ወረርሽኙ በሰሜን ምስራቅ ብራዚል መከሰቱን እስካረጋገጠበት ድረስ፡፡
በአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት በብራዚል የመጀመሪያው የበሽታው ስርጭት የታየ ሲሆን ዚካ ቫይረስ በ21 ሀገሮች እና በአሜሪካ ግዛቶች ተሰራጭቷል፡፡
✔የዚካ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች
የዚካ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በወባ ትንኝ ንክሻ ይተላለፋል፡፡ ቫይረሱ ኤደስ() በምትባል የወባ ትንኝ ዝርያ ውስት ይገኛል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዚካ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በደም ልገሳ፣ ከእናት ወደ ልጅ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ይተላለፋል ነገር ግን ይህ መተላለፊያ መንገድ የመከሰት ዕድሉ በጣም ጥቂት ነው፡፡ በአንድ አጋጣሚ ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ተገኝቷል፡፡
በቫይረሱ ተይዘን ምልክት እስከምናሳይበት ያለው የጊዜ ቆይታ በውል የመታወቅ ባይሆንም ከ 3-12 ቀናት እንደሆነ ይገመታል፡፡
✔የበሽታው ምልክቶች
ከ 20-25% በዚካ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ብቻ የበሽታውን ምልክት ያሳያሉ፡፡ በብዙ በሽተኞች ላይ የሚታዩ የዚካ በሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦
• ትኩሳት
• ሽፍታ
• የመገጣጠሚያ ህመም
• የአይን መቅላት
• የጡንቻ ህመም ናቸው፡፡
የዚካ ኢንፌክሽንን የከፋ የሚያደርገው ሁለት ከአእምሮ ጋር የሚያያይዙት ጉዳዩች ስላሉ ነው፡፡
• በህክምና ቋንቋ ማይክሮሴፋሊ ይባላል የዚህ ቃል ትርጉም የሆነ ችግር ኖሮበት የሚወለድ ህፃን ለማለት ሲሆን የሚወለደው ህፃን ጭንቅላት እጅግ በጣም ያነሰ እና አእምሮ ዕድገቱን ሳይጨርስ ይወለዳል፡፡ ይህ ችግረ የሚያጋጥመው የህፃኑ እናት በመጀመሪያው ትራይሚኒስቴር ወቅት በዚካ በሽታ የተያዘች እንደሆነ ነው፡፡
• ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ጉሊያን ባሪ ሲንድረም ()ይባላል፤ ይህ ችግር አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ሲሆን የራሳችን የበሽታ መከላከያ ስርዓት የራሳችንን ነርቭ ሴሎች በማጥፋት/በመግደል የጡንቻ መልፈስፈስ ሲያስከትል አልፎ አልፎ ደግሞ ልምሻ ወይም ፓራሊሲስ ያስከትላል፡፡
የዚካ በሽታ ምርመራ
ለዚካ ኢንፌክሽን የሚያገለግል በብዛት በአለማችን ላይ የምንጠቀምበት ምርመራ የለም በአብዛኛው ሰዎች ላይ ምርመራው መሠረት ያደረገው ምልክቶችን በማየትና የስርጭት ቦታውን በማወቅ ነው፡፡ በላቦራቶሪ ውስጥ ከሚደረጉ ምርመራዎች መካከል ፒ.ሲ.አር(PCR)፣ ሴሮሎጂካል ምርመራዎች()፣ ኒኩሊክ አሲድ አምፕሊፊኬሽን ምርመራዎች() ይጠቀሳሉ፡፡
✔የዚካ ቫይረስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መንገድ
• የወባ ትንኝን መቆጣጠር እና ማጥፋት
በግቢ ውስጥና በአካባቢያችን የተከማቸ ውሃ ዌም ኩሬ ካለ ማስወገድ
• በወባ ትንኝ እንዳንነከስ ራሳችንን መከላከል
የበሽታው ስርጭት ባለባቸው ቦታዎች የሚገኙ ከሆነ በወባ እንዳይነከሱ የግል ጥንቃቄን ማድረግ አጎበር መጠቀም፣ በሽታው ወደተከሰተበት ቦታዎች አለመሄድ፡፡
• ስለ ዚካ ቫይረስና ወባ ለማህበረሰቡ ማሳወቅ
ህብረተሰቡ ስለ ዚካ ቫይረስ እና መከላከያ መንገዶቹ ማሰወቅና እራሳቸውን ከበሽታው እንዲከላከሉ ማድረግ፡፡
አንብበዉ ሲጨርሱ ሼር እና ላይክ ያድረጉት ወገኖቻችን እንዲያነቡት ሼር በማድረግ የ ዚካ ቫይረስን አስቀድመን እንከላከል !!!
መልካም ጤንነት እንመኛለን ለሁሉም

Advertisements

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ስህተት የ 5 ልጆች እናት ህይወት አለፈ

ዘውዲቱ ሆስፒታል የመህፀን እጢ እንዳለባቸው የተነገራቸው የ 5 ልጆች እናት እጢው ወደ ካንሰር እንዳይለወጥ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና እንዲደረጉ ይታዘዛሉ ። ለዚህም ቀዶ ጥገና ሆስፒታሉ መሳሪያ ስለሌለው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የምርመራ ውጤታቸውን አባሪ በማድረግ ይልካቸዋል። የተጠቀስው ሆስፒታል እደደረሱም እናት ለህክምና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ክፍያ ሰለተጠየቁ «ያለአባት የሚያሳድጓቸው የ 5 ልጆች እናትና የቤተሰብ ሃላፊ መሆናቸውን ጭምር በመግለጽ ሆስፒታሉ ከሞት እንዲታደጋቸው ይማፀናሉ ። የሆስፒታሉ አስተዳደር እናት ከቀበሌ ደብዳቤ ካመጡ በነጻ ህክምና የሚያገኙበትን መላምታ እንደሚያመቻቹላቸው ቃል በመግባት ያሰናብቷቸዋል። የጤና ጉዳይ ነውና እናት የተባለውን ሁሉ አሞልተው ዳግም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በማቅናት ለነጻው ህክምና ተራ ያሲዛሉ ። ከወራት ቆይታ በኃላ እናት የቴሌፎን ጥሪ ከሆስፒታል ይደርሳቸዋል « ተራዎ ስለደረሰ መጥትው ነጻ ህክምናውን ይውሰዱ የሚል» ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቁሙ የገባ ታካሚ እንደዋዛ በሬሳ ሳጥን ታሽጎ በአስከሬን በር የሚወጣበት ፤ የመኪና ግጨትን ጨምሮ በተለያያ ድንገተኛ አደጋዎች እግርጥሎት ወደ ሆስፒታሉ ያቀና «ዘመድ አዝማድ የሌለው የኔ ቢጤ » የሰውነት ክፍሉ ተበልቷ ለሃብታሞች ጫራታ የሚቀርብበት ፡ በአጠቃላይ ሆስፒታሉ ወደ ሰው ቄራነት የተለወጠ ፤ የህክምና መሳሪያን ጨምሮ በ መደሃኒትና በባለሙያ እጠረት ያለበት መሆኑን ቀደም ብለው የተረዱ እናት ሁኔታው ደስ ስላላቸው « እሱ እንደፈጠረኝ እሱ ይግደለኝ » ብለው ምንም አይነት የህመም እንደማይሰማቸው ገልጸው የቀዶ ጥገና ሃሳባቸውን መለወጣቸውን ለሆስፒታሉ ያስረዳሉ። የኚህን እናት ሙሉ መረጃ የያዙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዶ/ሮች በተደጋጋሚ ስልክ በመደውል እጢው ቀላል እንደሆነና በዛው ልክ ቀዶ ጥገና እንደሚያደርጉላቸው ያግባቦቸዋል።

እናት ያለአባት የቀሩ ልጆቼን ላሳድግ ኽረ ! ጉድ ታደርጉኛላችሁ ! ቢሉ ማን ሊሰማ ። በዶ/ክተሮች ተማጽኖ ሆስፒታል የገቡት እናት ግን የፈሩት አልቀረላቸውም። ዕለቱ ማክሰኞ ረፋዱ ላይ ነው ። ከሶስት ቀን በፊት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አልጋ ተይዞላቸው የቀዶጥገና ቀናቸውን የሚጠብቁት የ 5 ልጆች እናት ስጋታቸው ጨምሯል። እናት ፍረሃት ፍረሃት እንዳልቸው ለገኙት ሁሉ ቢገልጹም ደሃ ታሞ በማይድንባት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም እንደሆነ የሚነገርለትን የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ባዶ ህንጻና ነጫጭ ገዋን በለበሱ የጤና ባለሙያዎች በተማረኩ ወገኖች አበረታችነት እናት በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8 ሰዓት ልጆቻቸውን ተሰናብተው ወትሮም ወደ አላመኑበት ቀዶ ጥገና ክፍል ገቡ ። ልጆቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ቤተሰብ ቀዶ ጥገና ክፍል በሩ ላይ በጭንቀት ተውጦ ፈጣሪውን ይማፀናል ። የቀዶ ጥገና ክፍሉ መግቢያ ላይ ዶ/ሮቹ ቀዶ ጠገናውን መጀመራቸውን የሚያመላክተው ቀይ መብራት በርቷል ።ሶስት ሰዓት ይፈጃል ይተባለለት ቀዶ ጥገና ሳይጥናቀቅ ከቀዶ ጥገና ክፍሉ አንድ በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ የህክምና ባለሙያ እይተቻኮለ ወጣ ፤ በጭንቀት ተመስጥው በር ላይ ለታደሙት ቤተሰቦች በተርበተበተ አንደበት « ሴትየዎ ብዙ ደም ስለፈሰሳቸው ደም ስለሚያስፈልግ ፈልጋችሁ አምጡ » የሚል ትዕዛዝ ቢጤ አስተላልፎ እየተቻኮለ ወደ መጣበት ክፍል ተመለስ ።ሁሉም ቤተሰብ በየአቅጣጫው ደም ፍለጋ ከተማ ውስጥ ያሉትን ሆስፒታሎች ማካለል ጀመር ወትሮስ ምክንያት እንጂ ችግሩ የደም አልነበረም ። የናታቸው ህይወት አደጋ ውስጥ መውደቅ የተነገራቸው ልጆች እሪታቸውን አቀለጡት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህንጻ እንደዚህ አይነት ጩህቶችን በየግዜው መስተናገድ የተለመደ ቢሆንም የልጆቹ ጩኽት ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነበር ፤ በአካባቢ የነበረውን ሁሉ ደረት በማስደቃት የሆስፒታሉን ድባብ ለወጠው ።በሁኔታው የተደናገጡት ዶ/ር ተብዬዎች ከአካባቢው ተሰወሩ ችግሩ ወደ ተፈጠረበት የቀዶ ትገና ክፍል የመጡ የሆስፒታሉ ህላፊዎች በቀዶ ጥገና ወቅት በደም ስር ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረና ሴትየዋ የማይተርፉ መሆናቸውን ቢረዱም የዜጎች ህይወት በተደጋጋሚ በቀዶ ጥገና ስህተት መጥፋት የተለመደ ነውና በአካባቢ የነበረውን ቤተሰብ ከማስተዛዘን ውጭ ዴታም አልነበራቸውም ፤ በተለይ ልጆቻቸውን ለማረጋጋት በእድሜ የገፋውን ልጅ ቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ይዘውት በመግባት ከማደነዘዣ የነቁትን እናት እንዲያይ ፈቀዱለታል ።
የአባት ፍቀር እንደተራበ እናቱን ለማየት ወደ ቀዶ ጠገና ክፍል የዘለቀው ልጅ ከእናቱ አንደበት « ብርድ ብርድ አለኝ ፤ ተጫወቱብኝ የሚለውን ቃል ከመስማት ባሻገር »እናት ጤና እያሉ ይለግሱት የነበረውን የእናትነት ፍቅር ዳግም መስማት አለታደለም ። የማህጸን እጢ አለባቸው ተብለው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተለምነው የገቡት እናት ይህይወት ፍጻሜ በቀዶ ጠገና ስህተት ሁሉም ነገር አበቃ ። በዛው ቅጽፈት የቀዶ ጠገና ክፍሉ ዘግናኝ የደውል ድምጽ አቃጨለ ተጠያቂነትና የህግ የበላይነት በሌለበት ሃገር ተተኪ የሌላት የ 5 ልጆች እናት ላትመለስ እስከ ወዲያኛው አሸለበች ። በፖለቲካ አመመለካከታቸው አያሌ የሃገሪቷን እውቅ ዶክተሮች ከሃገር እንዲሰደዱ ያደረገው « የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት » በጤና ፖሊሲው የፖለቲካ ቱሩፋት ለማግበስበስ ያለ በቂ ባለሙያ ፤ የህክምና መሳሪያና መደሃኒት በየክልሉ ለይስሙላ ባስገነባቸው ባዶ ህንጻዎች ውስጥ ህይወታቸው እንደዋዛ ያጡትን ዜጎቻችንን ቤት ይቁጠው። june , 2/2015
Ethiopian Hagere Jed Bewadi

Ethiopian Hagere Jed Bewadi's photo.Ethiopian Hagere Jed Bewadi's photo.
posted by Aseged Tamene

ኢትዮጵያ ለወሲብ ንግድና ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር መነሻ አገር ሆናለች ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ

የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው የ2014 ሪፖርት ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣ ለወሲብ ንግድና ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መነሻ፤ በተወሰነ ደረጃም መዳረሻ አገር ናት ብሎአል።

አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና የገበያ ማዕከል ከአፍሪካ ቀዳሚው የወሲብ ንግድ ቤቶች መገኛ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣ ዕድሜያቸው እስከ 8 ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ ቤቶች በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርተዋል ይላል።

ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ከኢትዮጵያ ውጪም በተለይ በጂቡቲ፣ደቡብ ሱዳን እና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ በቤት ሠራተኝነት እና በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰሩ እንደሚገደዱ፣ ኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶች ደግሞ ጂቡቲ ውስጥ በሱቅ ሰራተኝነት፣ በተላላኪነት፣ በቤት ሰራተኝነት፣ በስርቆት እና በጎዳና ላይ ልመና ለግዳጅ ሥራ ተዳርገዋል ብሎአል።

በርካታ ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሲሰደዱ ጂቡቲ፣ ግብጽ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን ወይም የመንን እንደመሸጋገሪያ ይጠቀማሉ የሚለው ሪፖርቱ፣አንዳንዶቹ ሊሄዱ ካሰቡበት አገር ሳይደርሱ እንደመሸጋገሪያነት ባረፉበት አገር ተይዘው ለብዝበዛ፣ለእስራት፣ለግዳጅ ስራ እና ለመታገት ይዳረጋሉ ብሎአል።

በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በቤት ሰራተኝነት የተሰማሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች አካላዊ እና ወሲባዊ ጥቃት፣ ደሞዝ ክልከላ፣ እንቅልፍ መነፈግ፣ የፓስፖርት መያዝ፣ በቤት ውስጥ መታገት እና ግድያን ጨምሮ አስከፊ ጥቃቶች እንደሚደርስባቸው፣ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያውያን ሴቶች ስራ ፍለጋ ከአገር ከወጡ በኋላ፣ በወሲብ ንግድ ቤቶች፣ በማዕድን ማውጫ ቦታዎች፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ ነዳጅ ዘይት ማውጫ አካባቢዎች ለወሲብ ንግድ ብዝበዛ ይዳረጋሉ ብሎአል።

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀን እስከ 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውን በሕጋዊ መንገድ ከአገር እንደሚወጡ ቢገልጽም፣ ይህ ቁጥር ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ30 እስከ 40 በመቶ ብቻ የሚወክል ብሎአል። ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች በሕገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወይንም ስደት እንደሚዳረጉ ጠቅሷል።

መንግስት በአስቀጣሪ ኤጀንሲዎች ላይ ክልከላ ቢጥልም ክልከላውን ተከትሎ በሱዳን በኩል የሚደረግ ሕገወጥ የሰራተኞች ፍልሰት መጨመሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ጠቁሟል። እ.ኤ.አ. ከሕዳር 2013 ጀምሮ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከ163 ሺ 000 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከአገሩ ያስወጣ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከ94 ሺ 000 የሚበልጡት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ ወንዶች፤ ከ8 ሺ 000 የሚልቁት ደግሞ በእረኝነት እና በቤት ሰራተኝነት የተቀጠሩ ሕጻናት ናቸው ብሎአል።

መንግሥት ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስወገድ የተቀመጡትን ዝቅተኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባያሟላም፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል የሚለው ሪፖርቱ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 106 ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የፈጸሙ ወንጀለኞች ሕግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ ያደረገ ሲሆን፤ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበርም ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች መጠለያ እና የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አድርጓል ሲል አትቷል።

መንግስት የሕገወጥ ዝውውር ሰለባ የሆኑትን ጨምሮ ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከሌሎችም አገራት የተባረሩ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የማመቻቸት ስራ ቢሰራም፣ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ሳያደርግ የውጭ አገር ድርጅቶች ይወጡት በማለት ሃላፊነቱን ለእነሱ መተውን ገልጿል።

መንግስት ውጭ አገር በሚገኙ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች የሰራተኛ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አታሼዎችን አለመመደቡ፤በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሚሰጡ የዜጎች ደህንነት አገልግሎቶች ላይም ማሻሻያ አለማድረጉም ተጠቅሷል፡፡

መንግስት የሕጻናት የወሲብ ንግድን እና ሌሎች በአገር ውስጥ የሚፈጸሙ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎችን በሕግ ማስከበር፣ ከለላ በመስጠት እና በመከላከል በኩል በቂ ሥራ አልተሰራም በሚል ስቴት ዲፓርመንት ትችት አቅርቧል።

source: http://www.state.gov/j/tip/rls/tiprpt/countries/2014/226721.htm

posted by Aseged Tamene

በአገር ላይ የሚመጣ አደጋን አቅልሎ የማየት ያልሰለጠነ አስተሳሰብ፤

ታዳጊ አገሮችን በሙሉ የሚያመሳስላቸው አንድ ግርም የሚለኝ ነገር ከገደል አፋፍ ቆሞ ገደሉን መናቅ፣ ከአደጋ ጫፍ ቆሞ አደጋን ማቃለል፤ ከዚያም ከገደሉ ወድቆ መሰበር፣ በአደጋው ተጠራርጎ መወሰድ። ይህ ሐሳብ በርግጥ ፍንትው ብሎ የታየኝ የማሌዢያ አውሮፕላን በዩክሬይን ሰማይ ላይ በሚሳኤል በጋየበት ጊዜ ነበር። ሁላችሁም እንደምታስታውሱት የሰው አካል ቁርጥራጭ ከሰማይ ይዘንብ እንደነበር እማኞች ሲናገሩ መልክተናል።

ታላላቆቹ የዜና አውታሮች ራሺያ ላይ አተኩረው ነገሩን በዚያ ፈፀሙት አንጂ «አውሮፕላኑ በጦርነት ሰማይ ላይ ለምን ሄደ?» የሚለውን የሚያነሱ ሰዎችም ተደምጠዋል። ብዙ አየር መንገዶች አቅጣጫቸውን ቀይረው በሌላ መስመር መሔድ ከጀመሩ ቆይተው ነበር። የሳንቲም ስባሪ ለማትረፍ አንድም በማሌዢያኛ «አቦ አታካብዱ» ብለው ሳይሆን አይቀርም በዚያ በታዳጊ አገር አስተሳሰብ መንገዳቸው ሳይቀይሩ ቀሩ።

«የእባብ ጉድጓድ በጅል ክንድ ይለካል» እንደሚባለው የዩክሬይን አየር በማሌዢያ አውሮፕላን ክንድ ሲለካ ጅልም እጁ አይተርፍ፣ አውሮፕላኑም አልተረፈ። ተመሳሳይ ነገር እነሆ ሊከሰት ነው። ኢትዮጵያ በበኩሏ 200 ነርሶች ወደ ኢቦላ ዞን (Ebola ZOne) ልትልክ ጀብደኛ ውሳኔ ወስናለች። የማሌዢያ ውሳኔ።

ኢቦላ ምዕራብ አፍሪካን ምን እያደረገ ነው? ከበሽተኛው በሚወጣ ፈሳሽ በሚተላለፈው በዚህ በሽታ የአገራች ኢኮኖሚ እንዴት እንዴት እየሆነ ነው? የዚያ አገር ዜጋ የሆኑ በማለው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች እንዴት እየታዩ ነው? ምን ዓይነት ችግር እየገጠማቸው ነው? አይበለውና በሽታው አገራችን ቢገባ ዘመዶቹን በማስታመም የሚታወቅ የአገራችን ሰው እንዴት ባለ አደጋ ላይ ይወድቃል? የትኛው ሆስፒታል በርግጥ ብቁ ነው? መቸም በፌዴራል ፖሊስ ዱላ አታስቆሙት ነገር። «የሕዳር በሽታን» በአገራችን በ21ኛው ክ/ዘመን ልታመጡብን ካልሆነ በእውነቱ ምን ሌላ ምክንያት ይኖራችኋል? በዓለም ላይ በሕክምና አያያዛቸው ጥራት የተመሰገነላቸው ብዙ አገሮች አሉ። ኢቦላን በረዓድ እያዩት ነው። ሕዝቡ ገና ስሙን ሲሰማ ሽብር ይይዘዋል። አንድ ሰው ቴክሳስ ግዛት በበሽታው በመሞቱ መላው አሜሪካ ከሥሩ ነው የተነቃነቀው። በርግጥ እነርሱ ፈሪዎች ስለሆኑ እኛ ጀግንነት ይዞን ይሆን? የሚመጣውን ጉድ ስለሚረዱት ነው።

ይህንን ያልሰለጠነ አስተሳብ እንዴት ማስለቀቅ ይቻል ይሆን? አለመሰልጠን ወንጀል አይደለም ነገር ግን አገር ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ እያወቁ ለጋ ወጣቶችን ወደ እሳት መላክ ግን ሌላ ዓላማ እንዳለው ነው የሚረዳኝ። ምናልባት በበሽታው የሚገኝ ትርፍ እንዳለ እንጃ። ፈጣሪ ሕዝቡን ይታደገዋል። ለእናንተ ግን እንጃ!!!

ኤፍሬም እሸቴ

posted by Aseged Tamene

የሸዋ አማራና ኦሮሞዎች እያለቁብት ያለው የተበከለ ሃይቅ የመንግስት እጅ አለመት ተባለ

የወያኔ ድብቅ ሴራ ሲጋለጥ የሸዋ አማራና ኦሮሞዎች እያለቁብት ያለው የተበከለ ሃይቅ የመንግስት እጅ አለመት ተባለ ቪዲዮ ይመልከቱና አሳቦን ያካፍሉ

እጂግ ብዙ ቤተሰብ የሞተበት ይህ ሃይቅ በተበከሉ ኬሚካሎች የተበረዘ ከመሆኑ የተነሳ ለመጠጥና ለተለያዩ ነገሮች የሚጠቀሙት የአካባቢው ማህበረሰቦች የቤት እንሻቶች በከፍተኛ ሁኔታ እያለቁ ነው።  የአካባቢው ነዋሪዎች  በተደጋጋሚ ለመንግስት ችግራችንን ብናስረዳም ምንም መፍሄ ኣልሰጡንም በዚህም ተስፋ ቆርጠናል በለዋል ሌላ ለመጠጥ የሚጠቀሙበት ወሃም ስለሌለ እየጠጢ መሞትን ምርጫቸው እንደኦነ በምሬት ተናግረዋል።

posted by Aseged Tamene

%d bloggers like this: