በኢአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ የስራ አስፈጻሚ አባል ያልሆኑ መገኘት አነጋጋሪ ነው ተባለ

ባሁን ሰሃት የወያኔ ኢአደግ ስርሀትን ለማስቀጠል ስራ አስፈጻሚዉ ስብሰባ ላይ መጠመዳቸው ይታወቃል።
ይህ ስራ አስፈጻሚ  ነባር የሆኑትን ባሁን ሰሃት ግን ከስራ አስፈጻሚነት የተነሱት የህወሀት ባለስልጣኖችና ሌሎችም መገኘት የህወሀትን ጭንቀትና የቀድሞው ተሰሚነቱን ማጣቱ አስቆጭቶት ያንን ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑ ተነግራል።
ህወሀት ከገባበት አጣብቂኝ ያወጡኛል ያላቸውን በስብሰባው ላይ መገኘት የማይገባቸው እንደ በረከትና አባይ ፀዐዬ የመሳሰሉትን አስቀምጦ ውጥረት በተሞላው መልኩ ጭቅጭቁ ተጣጡፋል የተለመደው ማስፈራርያ በኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ይሰነዘራል ።

ህወሓቶች የመጣው ይምጣ እያሉ ያስፈራራሉ። ኦህዴድን በተደጋጋሚ ይከሳሉ። ብአዴንንም አልፎ አልፎ ያነሳሉ። በህወሃቶች ዘንድ ኦሮሚያ ውስጥ ያለውን ምስቅልቅል ሁኔታ ኦህዴድን ተጠያቂ እያደረጉ ተናግረዋል። አባይ ጸሃዬ እና ደብረጺዮን በዋናነት ኦህዴድ ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል።

አቶ በረከት ስምዖን አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አያስፈልግም መጀመሪያ መከላከያ አገሪቱን ያረጋጋና ከዛ ብኋላ ይመረጣል እያለ ነው። በእሱ ስሌት መሰረት ወታደሩ እዛም እዛም የሚታዩትን ተቃውሞዎች ደብዛቸውን ካጠፋ ብኋላ ለምን ብሎ የሚጠይቅ ማንም ስለሌለ የዛንጊዜ የፈለግነው ጠቅላይ ሚኒስተር መሰየም እንችላለን ከሚል ነው፡፡

በረከት ዶ/ር አቢይ ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን የለበትም የሚል አቋም ይዞ በስብሰባው እና ከስብሰባው በኋላ ባለው የእረፍት ጊዜ ሌሎችን ሎቢ ሲያደርግ ተስተውሏል። የተወሰኑ የህወሃት አባላት ደብረጺዮን ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁን እያሉ ነው። ይህ የማይሆን ከሆነ ምክትሉ ከኛ ይሁን በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል። ጌታቸው አሰፋ አሁን ደብረጺዮንን ጠቅላይ ሚኒስተር ማድረግ አሁን ካለው የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ፈጽሞ መሆን የሌለበት ነው በማለት አቋሙን ገልጿል። በህወሃት መካከል ቀጣይ ማን ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ ሙሉ በሙሉ አንድ አይነት አቋም እንደሌለ ታይቷል::

እስካሁን ያለውን የሃገሪቱ ሁኔታም እየገመገሙ ነው፡፡ በረከተ በስብሰባው ላይ ዋና ተዋናይ ሆኗል።ስብሰባው እንደቀጠለ ነው።

 

የአርበኞች ግንቦት 7 አባላቶች በተጠኑ ሥፍራዎች ላይ 800 በራሪ የአርበኞች ግንቦት ሠባት የትግል ጥሪ ወረቀቶች ተበተኑ!

በደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ አሥተዳደር ዛሬ ህዳር 29 ቀን እለተ አርብ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላቶች በተጠኑ ሥፍራዎች ላይ 800 በራሪ የአርበኞች ግንቦት ሠባት የትግል ጥሪ ወረቀቶች ተበተኑ::

በከተማው ማለትም አሥመራ በር ቀቀዋ በዴሴ ከተማ መግቢያ እና መውጫ በሆነችው ቢሻናቆ በሃይቅ በገባያ ማእከል በመሣናዶ እና በኮሌጅ ትምህርት ቤት መግቢያ እና መውጫ እንድሁም በመከነ እየሡሥ ባለው መግቢያ እና መውጫ በሮች የተበተኑት በራሪ ወረቀቶች በከለርድ የተዘጋጁ እና የተቆራረጡ በመሆናቸው ህብረተሠቡ በቀላሉ በኪሡ ይዞ እንድያሠራጮቸው ታሥበው የተዘጋጁ ከመሆኑ በተጨማሪ በሃይቅ ከተማ ትልቅ ገባያ በሚውልበት አርብ ገበያ ላይም ተበትኖል::

በዚህም ገባያ ከሀይቅ ከተማ አዋሣኝ ወረዳዎች የገጠሩም ሆነ የከተማው ህብረተሠብ ነጋዴው ተማሪን ይሁን አርሶ አደሩ ቀሥቃሽ በራሪ ፅሁፎቹን በእጃቸው እንዲገባ ለማድረግ ታቅዶ የተበተነ ሲሆን በተለያዩ ግርግዳ እና የመብራት ፖሎቹም ላይ ተለጥፈዋል በሶስት አቅጣጫ ለወረቀት ብተና በህብኡ የተደራጁ አባላት በተባለው ሥፍራ እና ጊዜ የበራሪ ፅሁፎቹን ለመበተን የወጡ አባሎቻችን በሠላም ወደ አሉበት ሥፍራ ተመልሠዋል፡፡

በቀጣይም በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ በህወህት ሆድ አደር አፋኝ እና አሥገዳይ ግለሠቦች ላይ እርምጃ እንደምንወሥድ እንገልፃለን። አርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጵያ እዝ፡፡

የደህንነት አላፊው ጌታቸው አሰፋ አሜሪካንን ማስጠንቀቁ አነጋጋሪ ሆንዋል

የደህንነት(የሰቆቃ) መስሪያ ቤት ዳይሬክተር፡ ገዳይ አስገዳይ፡ ገራፊ፡ አስገራፊ፡ የለየለት ጨካኝ። መልኩ ቀይ፡ ልቡ ጥቁር፡ ባህሪው ልስልስ፡ ተግባሩ እርኩስ፡ ድምጹ የማይሰማ፡ የጭካኔው ወሰን በኢትዮጵያ ምድር ጫፍ እስከጫፍ የደረሰ ፍጹም አረመኔ ሰው ነው። በቴሌቪዥን መስኮት ታይቶ አይታወቅም። የአደባባይ ሰው አይደለም። መድረክ፡ ስብሰባ ላይ አይታይም። ቢኖር እንኳን በፎቶና በቪዲዮ ራዳር ውስጥ እንዳይገባ ይደረጋል። እናቶቻችን ‘ቀትረ ቀላል፡ ጥላቢስ፡’ የሚሉት ዓይነት ሰው ነው የሰቆቃና ቶርቸር ዳይሬክተር ጄነራል
ጌታቸው አሰፋ።

ማዕከላዊን ረገጠው ህይወታቸው ሳያልፍ የወጡ እድለኛ ታሳሪዎች በአንድ ቃል እንደሚናገሩት ሰቆቃ፡ ግርፋት፡ ግድያ፡ የሚፈጸሙት ትግርኛ በሚናገሩ ሰዎች ነው። የእነዚህ ሰዎች አለቃ፡ መሪ ደግሞ ይህ ሰው ነው ጌታቸው አሰፋ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 15 ዓመታት በተፈጸሙት ፖለቲካዊ ሰቆቃዎች፡ ግድያዎች፡ እስሮች፡ውስጥ ይህ ሰው ዋናው ተዋናይ ነው። ይህ ሰው የስንቱን የኢትዮጵያ ልጅ የቀን ብርሃን አጨልሟል፡፡ የስንቱን ወጣት ተስፋ ቀጥፏል፡፡ አያሌ ህጻናትን ያለአባት፡ ያለእናት አስቀርቷል። ስንቱን ቤተሰብ በትኗል።

ይህ ሰው ማዕከላዊ ሌሊቱን ሲገርፍ ሲያስገርፍ፡ ያድራል፡ ሲደክመው ዋሽንግተን ዲሲ መጥቶ ውስኪውን ይጎነጫል። የኢትዮጵያን ወጣት ዘቅዝቆ፡ በርበሬ እያጠነ፡ በሽንት የተነከረ ጨርቅ እያጎረሰ ወፌ ላላ እየሰቀለ፡ ብልት እያኮላሸ ሲያሰቃይ ይቆይና ለእረፍት ጣሊያን ሲሲሊያ የባህር ዳርቻ በረር ብሎ ይንፈላሰሳል።

ድንቁርናው አይጣል ነው። በዊኪሊክስ እንደተጋለጠው ከሆነ ይህ ሰው አሜሪካንን አስፈራርቷል። ያማማቶ ለተባሉ የአሜሪካ አምባሳደር ”አሜሪካ የእኛን ተቃዋሚዎች መርዳት የማታቆም ከሆነ እኛም ለአሜሪካን ተቃዋሚዎች ድጋፍ እናደርጋለን” ማለቱን ዊክሊክስ አስነብቦናል።

ህወሀት የአድዋን ስረወ መንግስት በሰየመበት በሰሞንኛው መድረክ ይህን ሰው ዳግም ከፍ ያለ ቦታ ሰጥቶታል። መልዕክቱ ግልጽ ነው። ለውጥ የለም። የነበረው ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ቀጥቅጠን፡ ረግጠን እያኮላሸን፡ በኤሊክትሪክ ሽቦ ጡት እየተለተልን በጉልበትና በሃይል እንቀጥላለን የሚል መልዕክት መሆኑ ይገባናል። ህወሀት ተውሳኩን አስወግጄ መጣሁ፡ ታድሼ፡ ተወልውዬ በአዲስ መንፈስ ለለውጥ ተነሳሁ ያለው ይህን የዲያቢሎስ ቁራጭ፡ የሳጥናኤል ወንድም፡ ክፉና ነውረኛ ሰው ከስልጣን ማማ ላይ አስቀምጦ ነው።

ይህ ሰው በሰው ልጅ ላይ በፈጸመው ወንጀል፡ በዘር ማጥፋት፡ ወደር በሌለው የሰቆቃ ተግባሩ እጁ ወደ ኋላ ተጠርንፎ በፍትህ አደባባይ ቅጣቱን ማግኘት የሚገባው ሰው ነበር። ደግሞም አይቀርም። ይዘገይ እንደሁ እንጂ ፍትህ ይመጣል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ፡፡

ኤምባሲው ደረሰኝ ያለውን ዘገባ ጠቅሶ እንዳስታወቀው በግድያ እና ግጭቱ ተጠያቂዎችን ለመለየት ግልጽ ምርመራ መደረግ እንደሚገባው ሁኔታው ያመለክታል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ሰላማዊ ሰልፎችን የምትመለከተው እንደ ህጋዊ የሀሳብ እና የፖለቲካ ተሳትፎ መግለጫ እንደሆነ ኤምባሲው ዛሬ ያወጣው መግለጫ ያትታል፡፡

በቅርቡ በተካሄዱ በርከት ባሉ ሰልፎች ሰልፈኞች በሰላማዊ ሁኔታ ሀሳባቸውን መግለጻቸውን እና ይህን እንዲያደርጉም የጸጥታ ኃይሎች መታገሳቸውን በአድናቆት እንደሚመለከተው ኤምባሲው ገልጿል፡፡

ኤምባሲው ሁሉም ኢትዮጵያውያን አመለካከታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጻቸውን እንዲቀጥሉ አበረታቷል፡፡ ባለስልጣናትም ይህንኑ አንዲፈቅዱ ጠይቋል፡፡ በጥቅሉም «ኢትዮጵያዊያንን በሚጠቅም ጉዳይ ገንቢ፣ ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታች ብሔራዊ ተዋስዖ» መኖሩን እንደሚደግፍም በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

The United States sees peaceful demonstrations as a legitimate means of expression and political participation.  We note with appreciation a number of recent events during which demonstrators expressed themselves peacefully, and during which security forces exercised restraint in allowing them to do so.

We are saddened by reports that several recent protests ended in violence and deaths.  All such reports merit transparent investigation that allows those responsible for violence to be held accountable.

We encourage all Ethiopians to continue to express their views peacefully, and encourage Ethiopian authorities to permit peaceful expression of views.  More generally, we encourage constructive, peaceful, and inclusive national discourse on matters of importance to Ethiopian citizens.

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች በብአዴን አመራሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተነገረ

ነሀሴ 30 ቀን 2009 ዓ/ም ከቀኑ 11:35 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ አደዛ ኪዳነምህረት በተባለው ቀበሌ ከፌደራል ፣ ከክልልና ከዞን የተወጣጡ አመራሮች ሰሞኑን በተጀመረው “ቅማንት አማራ” እየተባለ ለመከፋፈል የህወሀትን ድብቅ ተልዕኮ ለማሳካት ሲንቀሳቀሱና እንዲሁም ጎንደርን ከሦስት ዞን በመክፈል ምዕራብ ዞን የተባለው እስከየት ድረስ እንደሆን ለማመላከት የገቡትን እነዚህ አመራሮች በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሱ የአርበኞች ግንቦት ታጋዬች መረጃ በመስጠቱ በተጠቀሰው ቦታ ደፈጣ በመያዝ ይጠቀሙበት በነበረው ኮብራ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ በመክፈት መኪናው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ስትሆን ለጊዜው ስሟ ያልተረጋገጠ ከፌዲራል ተወክላ የመጣች አመራር በመቁሶሏ ወደ ጎንደር ለህክምና ተወስዳለች ።

በተጨማሪም አንድ አጃቢ እና አንድ መካከለኛ አመራርም ቆስለው አይከል ከሚገኘው ክሊኒክ የህክና እርዳታ ቢደረግላቸውም ስላልተሻላቸው ዛሬ ጳጉሜ 01 ቀን 2009 ዓ/ም ወደ ጎንደር ሆስፒታል ተወስደዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እነዚህ ታጋዬች እዚህ ድረስ መጥተው ጥቃት ሲፈፅሙ የመንግስት ሚሊሻዎች እስከ ምርጫው ድረስ በተጠንቀቅ ( እስታንድ ባይ) እድትሆኑ ታዛቹሁ እያለ በቦታው አለመገኘታቹህ ከታጋዬች ጋር ምክር አላቹህ በማለት የሚኒሻ ኩማንደሩ ትጥቁን እዲፈታና ከኃላፊነት እዲወርድ ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ “ከቅማንት አማራ” በሚለው ጉዳይ ላይ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ የተጠየቁ በመተማ ወረዳ መተማ ዮሃንስ ከተማ ፣ የገንድውሃ ከተማ፣ በጭልጋ ወረዳ ፣ የነጋዴ ባህር ከተማ ከፍተኛ ተቋውሞ በማሰማትና የምርጫ ወረቀቶችን እና ቁሳቁሶችን በመቅደድ ተቋውማቸውን አሰምተዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን ውጥረቱ የጨመረ ሲሆን ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እየተከታተልን መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።

ድል የህዝብ ነው !