በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ጉባዬና ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በስኬት ተጠናቀቀ

Aseged Tamene

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ጉባዬና ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በስኬት ተጠናቀቀ::

በዛሬው ህዝባዊ ጉባዬ የአገራዊው ንቅናቄ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታና ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በእንግድነት የተገኙ ሲሆን የጉባዬው አዘጋጅ የዴሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ይበልጣል የመግቢያ ንግር አድርገዋል።

በማስከተልም አቶ ሌንጮ ለታ ስለ አገራዊው ንቅናቄ ምስረታ ገለፃ አድርገዋል ።
አቶ ሌንጮ በተለይ ከጠቀሷቸው ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ስለሆነ ነው እንጂ እንዲህ ተርቦ ተቸግሮና በድህነት ተሰቃይቶ ዝም ብሎ አይቀመጥም ነበር ብለዋል ። ሲቀጥሉም ወያኔን ማስወገድ የምንችለው እኛ ተቀራርበን ስንመካከር ነው ። ስለዚህ የተስማማንባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ልዮነታችንን ለመፍታትና ወደቀጣይ ስራ ለመጋዝ በቀርጠኝነት መነጋገር ይገባናል ብለዋል።

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው ወደ አገራዊ ንቅናቄውን የመሰረቱበትን ምክንያት ሲያስረዱ ሁለት በሆኑ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መጀመርያ ተስማማን እነሱም

፩ኛ አንድነታ የተጠበቀ ነፃነትና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን በመቀበል።
፪ኛ ልዮነታችንን በግልፅነት በመነጋገር ለመፍታት የሚሉት ናቸው ብለዋል።
ህነዚህ ለህብረታችን መሰረት ናቸው ያል ሲሆን ሌሎች ልዩነታችንን ሁሉ በመነጋገር እንፈታዋለን ብለዋል በተጨማሪም ወደፊት ከኦብነግ፣ከትፕዴም፣ከየአማራ አይል ንቅናቄ ጋር ተነጋግረር ወደ አንድነት እንመጣለን ብለዋል በዚህም ወያኔ ህወሀት ሊያፈርሳት ያሰባትን ሀገራችንን እንደማትፈርስ እናረጋግጥለታለን ብለዋል።

በመጨረሻም የገቢ ማሰባሰብ ስነስርሀት ተካይዶ አንድ መቶ አምሳ ሺ የኖርዌይ ገንዘብ ከተሰበሰበ በኃላ ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የለቱ ጉባዬ ተጠናቋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ችንፋዝ ሲላሪ ከተማ የተሳካ ግዳጅ ፈፅመው በርካታ አስረኞችን ማስፈታታቸው ታወቀ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ግንቦት 28 ቀን 2009ዓ/ም ምሽት 5:00 ሲሆን ወደ ሲላሪ ከተማ በመግባት በከተማው ያለውን ልዩ እስር ቤት በማጥቃት በስቃይ ላይ የነበሩ በርካታ አስረኞችን በማውጣት ወደ ነፃነት ኃይሎች እንዲቀላቀሉ አድርገዋል፡፡

በዘመቻው 3 የወያኔ ወታደሮች ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው አመራር ሲሰጥ የነበረው አዛዥ ተገድሏል።

በድምሩ 1 በመግደል 3 በማቁሰል እሰሮኞችን የማስወጣቱ ስራም በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። በወቅቱ በተካሄደው ውጊያ የወያኔ አመራሮች ቦታቸውን ጥለው የሸሹ ሲሆን በአካባቢው የወያኔ የካብኔ አባላትም ወጥተው ጥቃቱን መከላከል ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

የእስር ቤት ጠባቂዎችም ከ20 ደቂቃ መታኮስ በሁዋላ ቦታዉን ጥለው ሊሸሹ ችለዋል። በውጊያው 1 የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋይ ቀላል የመቁሰል አደጋ ከማጋጠሙ ውጪ ሌላ የደረሰ ጉዳት አለመኖሪንም ለማወቅ ችለናል ።

ታስረው ይሰቃዩ የነበሩ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ከአርበኞች ጋር እንደሚገኙ ታውቋል

አርበኞች ግንቦት7 በወያኔ ደህንነቶች ላይ የሚያደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ ነው

አርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄው በላከው መግለጫ በደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ልዩ ስሙ ጎርጎራ ክፍል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ግንቦት21 ቀን 2009 ዓም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በአንድ የህወሃት የደህንነት አባል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።
በደንቢያ ወረዳ የህወሃት ሰላይ በመሆን በአካባቢው ህዝብ ላይ ለሚደርሰው ግድያ ፣ አፈናና እስር ዋና ተጠያቂ ነው ባለው አብርሃ ተበጀ መኖሪያ ቤት እና ድርጅት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።ጥቃቱ ለህወሃት በመሰለል በህዝቡ ላይ ግፍ እንዲደርስ ለሚያደርጉት ማስተማሪያ ይሆን ዘንድ የተፈጸመ ነው ሲል የጥቃቱን ምክንያት አስቀምጧል።
በተመሳሳይ ዜናም ግንቦት19 ቀን 2009 ዓም ምሽት 6 ሰአት ላይ በዚሁ ወረዳ ከንች ውሃ በተባለው ቦታ ላይ አንድ የህወሃት አባል ንብረት የሆነ የሩሎ ማሽን ጥቃት ተፈጽሞበት መቃጠሉን ገልጿል።


ጥቃቱ የተፈጸመው በህዝቡ ጥቆማ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ፣ ጥቃቱን በፈጸሙት ታጋዮች ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ተናግሯል። አርበኞች ግንቦት7 ወሰድኩት ባለው እርምጃ ላይ ገዢው ፓርቲ መግለጫ አልሰጠም።
በዚህ ወረዳ ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊት አባላት የጦር መሳሪያቸውን ሽጠው በመጥፋታቸው ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።


ምን ያክል ወታደሮች እንደጠፉ ለማወቅ ባይቻልም፣ ወታደሮች ህዝቡ የጠፉ ወታደሮች ያሉበትን ቦታ እንዲጠቁሙ ሲያስፈራሩ ሰንብተዋል። ወታደሮች የጠፉት ባለፈው ቅዳሜ ነው።

የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል በወያኔ ኃይል ላይ ጥቃት መፈፀሙን ቀጥላል ተባለ

አገር ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ለትንሳኤ ሬዲዮ በላከው መልእክት ግንቦት 04 ቀን 2009ዓ/ም ምሽት 2፡00 ሰዓት ላይ የህውሐት የደህንነት አባል በሆነው ወርቁ ካሳሁን በተባለው የምዕራብ አርማጭሆ አብርሀጅራ ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ ላይ በወሰደው እርምጃ ግለሰቡ ወዲያውኑ መገደሉን አስታውቋል።

እርምጃው የተወሰደበት ይህ ግለሰብ ሀምሌ 05 ቀን 2008ዓ/ም በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ንፁሃንን ያስገደለ፤ ታፍነው አድራሻቸው እንዲጠፉ ያስደረገ እና በቅርብም የአካባቢው ተወላጅ የሆኑቱን እያሳደነ በርካታ ባላሃብቶችን ያፈናቀለ የሥርዓቱ ደህንነት አባል ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ወጣቶችን ከትውልድ አገራቸው እንዲባረሩ አድርጓል። ለአብነት ያህልም ሁነኛው አበበ ፣ አየልኝ፣ በፈቃዱ የተባሉትን መጥቀስ ይቻላል ብሏል መልእክቱ ።

እርምጃው ከመወሰዱ በፊት ይህ ሰው ከድርጊቱ እዲታቀብ በተደጋጋሚ ቢነገረውም ጭራሽ የአካባቢውን ህብረተሰብ በመናቅ እና የሎሌነት ጭካኔ እርምጃውን አጠናክሮ በመቀጠል ሲንቀሳቀስ በትናንትናው ዕለት ምሽት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደበትና እንዲወገድ እንደተደረገ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና አርበኛ ነጋ አዲሱ የተባለ የነጻነት ታጋይ ግንቦት 04 ቀን 2009ዓ/ም ከቀኑ 11፡20 ላይ በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ የህወሓት የሚሊሺያ ኮማንደር የሆነውን ማሩ ነጋሽ የተባለውን እና አብረውት የነበሩ 2 ሌሎች የሚሊሽያ አባላትን በድምሩ 3 ሰዎች ገድሎ 2ቱን ካቆሰለ በኋላ የጀግንነት ተግባር ፈጽሞ መሰዋቱን ከግንባሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

አርበኛ ነጋ አዲሱ ለቆመለት ዓላማ አረአያነት ያለው የጀግንነት ተግባር ፈጽሞ በማለፉ አብረውት የሚንቀሳቀሱ የትግል ጓዶቹ መኩራታቸውን የገለጸው መረጃ፥ የእርሱን የጀግንነት ቀንድል በመከተል ይዞት የተነሳውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ እሰከ መጨረሻው የደማቸው ጠብታ እንደሚታገሉ ማረጋገጣቸውንና የህዝብ ጠላት የሆነውን የህወሃት አገዛዝ ሥልጣን ዕድሜ በማሳጠር ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነበት ማህበረሰብ በመገንባት ዘለዓለማዊ ህይወት እንደሚያወርሱት ቃል መግባታቸውን ያትታል።

አርበኞች ግንቦት7 ፣ መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓም የሱዳን ታርጋ ያለው መኪና ላይ ጥቃት አደረሰ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈጸሙን የሚገልጸው አርበኞች ግንቦት7 ፣ መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓም ከሱዳን ተነስቶ ወደ ጎንደር በማቅናት ላይ የነበረ የሱዳን ታርጋ ያለው መኪና ላይ በፈጸመው ጥቃት የመኪናውን ከፊል አካል ማቃጠሉን ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ካለበት አካባቢ ነው። እንዲሁም ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓም አምባጊዮርጊስ አካባቢ የአገዛዙ ሰላይ ነበር ባለው እንዳልከው ንጉሴ በተባለ ግለሰብ ላይ እርምጃ እንደወሰደበት ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መረጃ አስታውቋል።

ንቅናቄው ሁለገብ የትግል ስልቱን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገልጾ፣ የህዝባዊ ጥሪ ወረቀቶች ከሰሜን አልፈው በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች በትኗል።

ኢሳት ወረቀቶች መበተናቸውን ከስፍራው ከሚገኙ ወኪሎቹ ለማረጋገጥ ችሎአል። የወረቀቶችን መበተን ተከትሎ በርካታ ዜጎች፣ ታፍሰው ምርምራ እየተካሄደባቸው ነው።

የኢህአዴግ ፓርላማ በቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ለአዋጁ መራዘም የሰጡት ምክንያት በክልል ድንበሮች አካባቢ ተቃውሞች መኖራቸውና ያልተያዙ አመራሮች አሉ የሚል ነው። ምንም እንኳ ገዢው ፓርቲ በይፋ የሚደረጉ ተቃውሞችን ለማፈን ቢችልም፣ በስውር የሚደረጉ ተቃውሞዎች ግን አሁንም እንደቀጠሉ ነው።

%d bloggers like this: