የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች በብአዴን አመራሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተነገረ

ነሀሴ 30 ቀን 2009 ዓ/ም ከቀኑ 11:35 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ አደዛ ኪዳነምህረት በተባለው ቀበሌ ከፌደራል ፣ ከክልልና ከዞን የተወጣጡ አመራሮች ሰሞኑን በተጀመረው “ቅማንት አማራ” እየተባለ ለመከፋፈል የህወሀትን ድብቅ ተልዕኮ ለማሳካት ሲንቀሳቀሱና እንዲሁም ጎንደርን ከሦስት ዞን በመክፈል ምዕራብ ዞን የተባለው እስከየት ድረስ እንደሆን ለማመላከት የገቡትን እነዚህ አመራሮች በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሱ የአርበኞች ግንቦት ታጋዬች መረጃ በመስጠቱ በተጠቀሰው ቦታ ደፈጣ በመያዝ ይጠቀሙበት በነበረው ኮብራ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ በመክፈት መኪናው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ስትሆን ለጊዜው ስሟ ያልተረጋገጠ ከፌዲራል ተወክላ የመጣች አመራር በመቁሶሏ ወደ ጎንደር ለህክምና ተወስዳለች ።

በተጨማሪም አንድ አጃቢ እና አንድ መካከለኛ አመራርም ቆስለው አይከል ከሚገኘው ክሊኒክ የህክና እርዳታ ቢደረግላቸውም ስላልተሻላቸው ዛሬ ጳጉሜ 01 ቀን 2009 ዓ/ም ወደ ጎንደር ሆስፒታል ተወስደዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እነዚህ ታጋዬች እዚህ ድረስ መጥተው ጥቃት ሲፈፅሙ የመንግስት ሚሊሻዎች እስከ ምርጫው ድረስ በተጠንቀቅ ( እስታንድ ባይ) እድትሆኑ ታዛቹሁ እያለ በቦታው አለመገኘታቹህ ከታጋዬች ጋር ምክር አላቹህ በማለት የሚኒሻ ኩማንደሩ ትጥቁን እዲፈታና ከኃላፊነት እዲወርድ ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ “ከቅማንት አማራ” በሚለው ጉዳይ ላይ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ የተጠየቁ በመተማ ወረዳ መተማ ዮሃንስ ከተማ ፣ የገንድውሃ ከተማ፣ በጭልጋ ወረዳ ፣ የነጋዴ ባህር ከተማ ከፍተኛ ተቋውሞ በማሰማትና የምርጫ ወረቀቶችን እና ቁሳቁሶችን በመቅደድ ተቋውማቸውን አሰምተዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን ውጥረቱ የጨመረ ሲሆን ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እየተከታተልን መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።

ድል የህዝብ ነው !

Advertisements

የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ በቋራ ወረዳ አላጥሽ ደን ላይ በህወኃት ሰራዊት ላይ ጠቃት ፈፀመ

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬችን “ለመደምሰስ” በሚል ዘመቻ ወጥቶ የነበረ 2 ሻምበል የወያኔ ጦር በ6 ኦራል የሄደው ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ ሲሆን በዚህ የተበሳጩ የህወኃት ጄኔራሎች በልዩ ትዕዛዝ ነባር የተባሉ የጦር አባላትን በ3 ኦራል በመጫን ሰኔ 21 ቀን 2009ዓ/ ም ወደ ቋራ ወረዳ አላጥሽ በርሃ የላከ ሲሆን ገና ወርደው መንቀሳቀስ ሳይጀምሩ ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል። በመሆኑም የህወኃት ጄኔራሎች እነሱንና ቤተሰባቻቸውን በሞቀ እና በተንደላቀቀ ኑሮ እየኖሩ፣ልጆቻቸውን በሰሜን አሚሪካና በአውሮፓ እያስተማሩና እያኖሩ፣እነሱ ጮማ እየቆረጡ፣በዊስኮ እየተራጩ የድሀ ልጆችን ወደ ጦርነት በመላክ እያስጨረሱ ይገኛሉ።

በመሆኑም አሁን እየተካሄደ ያለው ትግል ህወኃት ሰፌውን ህዝብ በባርነት ለማኖርና ለመግዛት ሲሆን በእኛ በኩል ደግሞ ሰፌው ህዝባችን ከዚህ ዘረኛ ስርዓት ነፃ ለማውጣት የሚደረግ ትግል ነው በመሆኑም ለዚህ ዓላማ ለሌለው ህዝባችንን በባርነት ለመግዛት ለሚሻው ወያኔ መጠቀሚያ ከመሆን የህዝብ ነፃነት ከሚታገሉት ታጋዬች ጎን በመሰለፍ የዚህን ግፈኛ ስርዓት ግብዓተ መሬት እናፋጥን ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሬያችንን እናስተላልፋለን። በአሁኑ ሰዐት ወያኔ ወደ ቦታው ወታደሮችን በመላክ ላይ ሲሆን አካባቢው ህብረተሰብ ከታጋዬች ጎን በመሰለፍ እየተፋለመ ይገኛል ዝርዝር ጉዳዩ እንደደረሰን የምንገልፅ መሆኑን እንገልፃለን።

አርበኞች ግንቦት ሰባት የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ በሰሜን ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ ላይ በህወኃት ሰራዊት ላይ ጥቃት ፈፀመ

ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2009ዓ/ ም ንጋት ላይ ሰሞኑን በዘመቻ ወያኔ የአግ7 ታጋዬችን “እደመስስ አለሁ” በማለት እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን በተጨማሬም ህዝቡን ትጥቅ ለማስፈታት በሙሉ ኃይሉ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ገና ከጅምሩ ጥቃት ደረሰበት በዚህ ውጊያ በታላቅ ድፍረት እና ጀግንነት ቡድኑን የመራው አርበኛ አደራጀው የእሱ ቡድን በመጀመሪያ የገባውን አንድ የወያኔ ቲም ከ10 አባላት 7 ሙት 3 ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።

ከዚያም በርካታ ኃይሉን ይዞ ወደ እንቃሽ የገባው የጠላት ጦር ከታጋዬች እና ከህዝቡ ጋር ከፍተኛ የሆነ ውጊያ ውስጥ የገባ ሲሆን የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት እየሞከርን ነው በርካታ አሙቡላንሶች ቁስለኛ ጭነው ወደ ጎንደር ሆስፒታል እየገቡ ሲሆን ወያኔ የስልኩን ኔት ወርክ ዘግቶታል። ሁኔታውን እየተከታተልን እንገልፃለን። ሕዝቡ መሣሪያዬን ከምሰጥ እዋጋለሁ በማለት ከታጋዬች ጋር በመቀላቀል እየተዋጋ ነዉ።

መላዉ የኢትዬጵያ ሕዝብ በያለበት ይሄን የአዉሬ ቡድን በመወለጋት ተብብሩን ያሳይ እኛ ጀምረነዋል ለመጨረስ ሁሉም በያለበት እንዲታገል ጥሪያችን እናስቸላልፋለን።

የህወኃት ደህንነት መኖሪያ ቤት እስከነ ሙሉ ንብረቱ ተቃጠለ።

ጎንደር ዞን በደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ጎርጎራ ክፍል ቀበሌ 01 የህወኃት ደህንነት መኖሪያ ቤት እስከነ ሙሉ ንብረቱ ተቃጠለ።

ይህ ደህንነት ስሙ ግርማይ ገብረመስቀል ሲሆን ህወኃት በነጋዴ ሽፋን በደህንነት መስመር ካስገባቸው ቀንደኛውና ዋናው ነው።

ይህ ሰው ራሱ ብቻ ሳይሆን 3 ልጆቹን በዚህ የደህንነት ስራ በማስገባት ሁሉም ተሽከርካሪ በስማቸው ተገዝቶላቸው በሽፌር ሽፋን በርካታዎችን ንፁሃን ዜጎች ከህወኃት
መከላከያና ከብሄራዊ ደህንነት መረጃ ጋር በመሆን ከሀምሌ 5 ቀን 2009 ዓ•ም ጀምሮ ግርማይና የመጀመሪያው ልጅ የመከላከያ ሬንጄር በመልበስ ቅርፃቸውን በመለዋወጥ አብረው
ያፍናሉ፣ ያሳፍናሉ፣ ይገድላሉ፣ ያስገድላሉ፣ የተያዙ ንፁሃን ዜጎችን ወደ ተመረጡ የማሰቃያ ቦታዎች ወደ ትግራይ እና ወደ ማዐከላዊ ጭነው በመውሰድ ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች
ናቸው።

አሁንም በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። ይህ ደህንነት በነጋዴ ሽፋን ስለሚሰራ ከደንቢያ፣ ከአለፋ፣ ከደልጊ ጤፍ፣ ቅቤ፣ ማር፣ የርድ ከብቶችን፣ ደሮና እንቁላል ሳይቀር ያለምንም ከልካይ እና ፍተሻ ሳይደረግበት ተፈላጊውን ግብር ሳይከፍል እንደፈለገ ወደ ትግራይ ያጉዛል። በቅርብ ንብረትነቱ የህወኃት ኢፈርት ንብረት የሆነው መስፍን እንጅነሪግ ጤፍ ለመግዛት ጨረታ ሲያወጣ ዋና አቅራቢ በመሆን ይዘርፍ ነበር።


በመሆኑም በህብረተሰቡ ጥቆማ በዚህ ደህንነት ላይ በትናንትናው ቀን የተጠቀሰው ጥቃት ተፈፅሞበታል። ጥቃቱን የፈጸሙ የአማራ ጀግኖች በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል።

በደቡብ ጎንደር ያለው ውጥረት ቀጥላል ተባለ

በጎንደር የደጋ መልዛ፡ የመቀጠዋ፡ የዙ ሀሙሲት ፡የደብር አባጃሌ፡ የክልቢ፡ ወጣቶች ከተማውን ከበውታል የወያኔ መከላከያ እብናት አሁንም ስላለ ከእነርሱ ጋር ለመግጠም ተዘጋጅተዋል በተለይ ደብር አባጃሌ ቀበሌ ከባድ ውጥረት እንዳለ ይነገራል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት ልዩ ኮማንዶ በደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ የመሸገውን የወያኔን ጦር ማጥቃቱንና በጥቃቱም የክልሉ የፀረ፡ሽብር ግብረሀይል የዘመቻ መምሪያ ሀላፊን ሙሉ ኮማንደር አወቀን መግደሉን ተናግረን ነበር። ውጥረቱ የቀጠለ ሲሆን ያካባቢው ወጣቶች ባጠቃላይ ከዚሁ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ጎን መቆማቸው ተነግራል።

%d bloggers like this: