አዲስ አበባ በዛሬው ለት በአጋዚያውያን እንዲህ ተወራ ነበር

በዛሬው የከተራ ዝግጅት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ አጋዚዎች እንዲ ሲፈነጩበት ሰንብተዋል የሚገርመው የከተማዋን ነዋሪዎችንና የጥምቀት ባህልን ለማክበር የወጡ ምህመናንን እንዲ በፓትሮል ተጭነው ሲያሸብሩ መዋላቸው ብቻ ሳይሆን የአይኑ ከለር ያላማራቸውንም የለዮ መፈተሻቸው ነው

በብዛት በበአሉ ላይ የተገኙት የመከላከያ እና የፓሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ መሳሪያ እና ዱላ የያዙት ናቸው እውነት ለመናገር በአሉ ሀይማኖታዊ ለዛውን አጥቶ የመንግስት በአል ነው የሚመስለው።
ሳጠቃልለው ወያኔዎች በጣም ስጋትላይ ናቸው ምን ያህል እንደሚቆዩ አይታወቅም እንጂ አይሉ ከእጃቸው ከወጣ ቆይታል እኛም ፈርተን ነበር ነው ያለው ጠ አይለማርያም ደሳለኝ
መጨረሻው የደረሰ ደግሞ እንዳበደ ውሻ ያገኘውን መናከስ ያምረዋል

በትግራይ ምድር በሚገኙ ዩኒቨርሲቲወች በአማራና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈፀመባቸው ነው!

በአዲ ግራት ዩኒበርስቲ ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ መብራት የለም፤ ይህንን የጨለማ አጋጣሚ ተገን በማድረግ በእራት ሰአት ጊዜ የትግራይ ተማሪወች በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ ወደ አማራና ኦሮሚያ ልጆች መመገቢያ ሳህንና ወንበር በተደጋጋሚ እየወረወሩብን እና እየደበደቡን ይገኛሉ፤ በዚህ ያልተመለሱት የህወኃት ተከታዮች ከፕሬዘዳንት እስከ ተማሪ ህብረት ያሉት የትግራይ ተወላጆች የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ በአማራ ተማሪወች ላይ እስከ መባረር የደረሱ፣ ፒሲ የተቀሙ፣ የታሰሩና የደረሱበት ያልታወቀ ተማሪወች አሉ። በተለይ የአማራን ተወላጆች ትኩረት አድርገው የሚረብሸን አማራ ነዉ ከየት ነዉ የመጣህ እየተባልን ስለምንዋከብ በጣም እየተቸገርን ነዉ በማለት ከዩኒቨርሲቲው ሰለቫ የሆኑ ተማሪወች ብሶታቸውን ለህዝብ እንድንገልፅ ጠይቃዋል።

ሁለት የአማራ ተወላጅ ተማሪወችም የትግሬ ጥላቻ አለባችሁ ተብለው አማራውን ታነሳሳላችሁ በሚል ሰበብ ተከሰው የነበሩ ሲሆን በምርመራ ጊዜም ከየት መጣህ ክልል ዞን ወረዳ ከየት ነው? መለስን ትወደዋለህ ? አይናፍቅህም ? በማለት የነገር ፍለጋ ጥያቄ ሲጠይቁዋቸዉ ተማሪወቹም (አንወደዉም, አይናፍቀንም) ብለዉ በድፍረት እንደመለሱና ከዚህ መልስ በሁዋላ ተማሪወቹ ከዩኒበርስቲዉ እንደተሰናበቱ ታውቆአል። (ስማቸውን ለጊዜው ለመግለፅ አልተፈለገም)
በዚሁ ዩኒቨርስቲና በሌሎችም በትግራይ ምድር የሚገኙ የትምህርት ተቁሞች የሚማሩ የአማራ ተወላጆች በሚደርስባቸው የተለያዩ ጥቃቶች ትምህርታቸውን በተገቢው ሁኔታ መከታተል እንዳልቻሉና የማቁአረጥና የመባረር እድላቸው ሰፊ እንደሚሆን ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል።

በየዩኒቨርሲቲወቹ በተፈጠረው የብሄር አደረጃጀትም ህውኃት በብአዴን በኩል የአማራ ተማሪወችን ለብቻ በማደራጀት የአማራው ህዝብ እያነሳው ያለውን የመብት ጥያቄ ተማሪወቻችን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማድረግ የማይሳካ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑንም ባለጉዳዮቹ ገልፀዋል። በተለይም በአማራና ሱዳን ደንበር ያለውን የመሬት ሁኔታ፣ የወልቃይት የማንነን ጥያቄ ህዝቡ ያነሳውን ተቀዋውሞ በማወያየት ቢዲዮና ድምፅ እሪከርድ በማድረግ ለህወኃት ሪፖርት እንደሚደረግና ተማሪወቹን ለከፋ ችግር ለመዳረግ እየተሰራ እንደሆነም አክለው አረጋግጠዋል።
መረጃውን ያቀበሉት ተማሪወች በትግራይ ምድር በሚገኙ ዩኒቨርስቲወች የምንገኝ የአማራ ተወላጅ ተማሪወች ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪወች ጋር የጋራ አጋርነት በመፍጠር በሚገባ ተደራጅተን ከሚደርስብን ጥቃት ራሳችን ከመከላከል አልፈን ህዝባችን እያካግሄደ ያለውን የማንነት ትግል አጠናክረን መደገፍ አለብን ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። በየዩኒቨርስቲው የተመሰረተው የብአዴን የተማሪወች ፅ/ቤትም የህወኃት የስለላ መዋቅር መሆኑን አውቀን በንቃት ማክሸፍ ይገባል ብለዋል።

14012564_10205198112430990_355381106_o

በምስጢር የተያዘው የአራት ኪሎ ተኩስ ልውውጥ እና የአዲስ አበባው ፍተሻ

በከፍተኛ ምስጢር የተያዘው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳብያ በአዲስ አበባ በተለይ ደግሞ በአራት ኪሎ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጅምሮ ከፍተኛ የሰራዊት ክምችት ይታያል።

ከትላንት ማምሻ የጀመረው ፍተሻ አሁንም እንደቀተለ ሲሆን የአጋዚ ሰራዊት አላፊ አግዳሚውን በማሸበር እና በመፈተሽ ላይ እንደሚገኝ የአይን ምስክሮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። የአይን ምስክሮች እንደሚሉት መሃል አዲስ አበባ- የገዢው ፓርቲ መቀመጫ ኣራት ኪሎ አካባቢ ውጥረቱ የከፋ ይመስላል። በአካባቢው ይሰማ የነበረው የተኩስ ልውውጥ በዚያው በቤተ-መንግስት እንደሆነም ይነገራል። የከባድ መሳርያው ጩኸት እንደተሰማ በከፊል አዲስ አበባ መብራት እንዲጠፋ ተደርጎ እነድነበርም ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች ተናግረዋል።

አለም አቀፍ እና የግል መገናኛ ብዙሃን በተከለከሉበት በአሁኑ ሰዓት በጨለማ እየተደረገ ያለውን ሁሉ ለማጣራት ቢቸግረም – አንደኛ በኢሃዲግ ድጅቶች መካከል ሁለተኛ ደግሞ በሕወሃት ከፍተኛ አመራር እና መካከለኛ ካድሬዎች መሃል የከረረ አለመግባባት እንዳለ እየተሰማ ነው። የዚህ የጥቅም እና የሃሳብ ልዩነት እየሰፋ መጥቶ ወደ ከፍተኛ ፍልሚያ ሊያመራ እንደሚችል የሚገምቱም ጥቂቶች አይደሉም።

በሃገሪቱ ያሉ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እስካሁን ድረስ እንዳይከፈቱ ትእዛዝ ተሰጥቷል። የትምህርት ቤቶችን የልብ ትርታ ለማዳመጥ በመምህራን የተጀመረው ስብሰባ ውጤት ገዥው ፓርቲ እንደጠበቀው አልሆነም። የመምህራኑ ቁጣ እንዲህ ከበረታ የተማሪዎቹ የከፋ እንደሚሆን በመገንዘባቸው ትምህርት በቶችን የመክፈቱ አደጋ ስጋት ውስጥ ከትቷቸዋል።

በፊታችን የሚከበሩ ሁለት በዓላት (የመስቀል እና የእሬቻ በዓላት) አከባበርም ገዥውን ፓርቲ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

አገዛዙ በአካባቢ እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ላይም እምነት በማጣቱ የአጋዚ ሰራዊቱ እና ታማኝ ደህንነት አባላት ብቻ ናቸው ፍተሻውን እና ግድያውን እያካሄዱ ያሉት።

በኤርትራ ጠረፍ (ባድመ) ላይ ተሰማርቶ የነበረው የህወሃት ሃይል አካባቢውን ለቅቆ ወደ አዲስ አበባ እና ጎንደር እንዲዘምት ተደርጓል።

የሕዝብን ውጫዊ አካል ሊፈትሹ ይችላሉ – የሸፈተ ልቡን ግን ለመፈተሽ አይቻላቸውም። ወከባው ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ አይፈታውም።

14495381_727547754050198_1341726531349737107_n

ሰበር ዜና ዶክተሮች በሀብታሙ አያሌዉ ጉዳይ የመጨረሻ ዉሳኔ አሳለፉ ፡፡

የካዲስኮ ሆስፒታል የቦርድ አባላት ከትላንት በስቲያ ቀደም ሲል በጀነራል ሰርጂኑ በዶክተር አብርሃም አስናቀ ተፈርሞ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተላከዉን የህክምና ማስረጃ አፀደቁ፡፡

በተያያዘ የሆስፒታሉ ዶክተሮች “ከበሽታዉ መወሳሰብ አንፃር ለከፋ አደጋ ከመጋለጡ በፊት በሀገር ዉስጥ ወደ እማይገኘዉ ኮሎ ሬክታል ሴንተር በመሄድ አስቸኳይ ቀዶ ህክምና እንዲደረግለት ወስነን ሳለ ህመምተኛዉን በሆስፒታላችን ማቆየት አንችልም” በማለት በትላንትናዉ እለት እንዲወጣ ትእዛዝ ሰጥተዉ ነበረ፡ ይሁን እንጂ ሀብታሙን ባለበት ሁኔታ ወደ መኖርያ ቤቱ ማስገባት የ4አመት ህፃን ልጁን ማሳቀቅ ስለሚሆን እና የግድ የህክምና ደጋፍ ስለሚያስፈልገዉ ተጨነቅን፡፡ ሌላ ሆስፒታል እንዳንሄድ የጠየቅናቸዉ ሁሉ “ምንም መርዳት የማንችለዉን ህመምተኛ ያዉም ቦርድ ዉሳኔ ሰጥቶበት ልናስተኛዉ አንችልም አሉን፡፡” ትላንት በጣም ታሞብን ስለነበረ ሆስፒታሉን ተማፅነን አደርን፡፡ ያም ቢሆን ዶክተሮቹ ለትላንትናዉ ሌሊት ሀላፊነት አንወስድም ብለዉ ተማፅኖአችን ለማደር ብቻ ነበረ፡፡ ዛሬ ግን እንድንወጣ ስለተገደድን የግለሰብ ቤት ተከራይተን ፍቃደኛ በሆኑ የግል ሀኪሞች ስቃይ ማስታገሻ እንዲሰጠዉ እያደረግን ነዉ፡፡ ያ ሀገር የማይበቃዉ የህዝብ ልጅ እንዲህ ሆኖ ማየት በጅጉ ያማል፡፡ ቀጣዩን ተከታትዬ አሳውቃለሁ…

የጣይቱ ልጅ's photo.

ሰበር ዜና ሳውዲ አረቢያ ከመካ ወደ ሪያድ ይጓዝ የነበረ አንደ የህዝብ ማመላሻ አውቶብስ ተገልብጦ ኢትዮጵያውያን ሞቱ !

እሁድ ጁላይ 2 2016 ቀትር ላይ በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ በቅዱስነቷ ከምትታወቀው መካ የፀሎት ሰረዓታቸውን አድርሰው ወደ ሪያድ ከተማ ይመለሱ የነበሩ ምዕመናኖችን አሳፍሮ የነበረ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ በኢትዮጵያውያን ላይ የሞት እና ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የሆስፒታል ምንጮች ገለጹ። የረመዳንን ጾም መጨረሻ ምክንያት በማድረግ መካ ፀሎታቸውን አድረሰው የመለሱ የነበሩ ምዕመናኖችን አስፍሮ አደጋ የደረሰበት አውቶብስ ውስጥ ነዋሪነታቸው ሪያድ ከተማ የሚኖሩ እንደነበረ የሚገልጹት ምንጮች በአደጋው ከሞቱት እና ከቆሰሉት ውስጥ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጸዋል። ከመካ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት እንደተጓዘ ቀጢፍ የሚባል በረሃማ አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት ተገልብጦ ከተቃጠለው የህዝብ ማመላለሽ አውቶብስ ውስጥ ሾፌሩን ጨምሮ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ተሳፋሪ ሲሞት እስካሁን ክፉኛ የተጎዱ እና የሞቱ ኢትዮጵያውያን አስከሬን በተለምዶ ጣይፍ የሚባል ከተማ የሚገኝ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል;። የከተማው አውቶብሱ ከተገለበጠ በኃላ መቃጠሉ አደጋውን የከፋ እንዳደርገው የሚናገሩት የሆስፒታሉ ምንጮች በአደጋው የሞቱትን ምመዕናን አስከሬን ማንነት እስካሁን መለየት እንዳልተቻለና የአስከሬኑ በልዩ የህክምና ምርመራ ተለይቶ እስኪታወቅ አስከሬን ማረፊያ ፊርጅ ውስጥ እንደሚቆይ አክለው ገልፀዋል። የአደጋው መንስኤ እና የአውቶብሱ ቃጠሎ መነሻ ምን እንደሆነ እስካሁን በውል ባይታወቅም በአሁኑ ወቅት የሳውዲ አረቢያ የአየር ሙቀት መጠን ከ 45 ዲግሪ ሲንትግሬድ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይነገራል ። በአደጋው ስለሞቱት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በየትኛውም የዜና አውታር የተሰጠ መረጃ ባይኖረም በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንሳል ጄኔራል ጽ/ቤት በመደወል በአደጋው ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ እስካሁን አልተሳካም ።

ኢትዮጵያ ሃገሬ ጅዳ በዋዲ

 

%d bloggers like this: