የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች በብአዴን አመራሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተነገረ

ነሀሴ 30 ቀን 2009 ዓ/ም ከቀኑ 11:35 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ አደዛ ኪዳነምህረት በተባለው ቀበሌ ከፌደራል ፣ ከክልልና ከዞን የተወጣጡ አመራሮች ሰሞኑን በተጀመረው “ቅማንት አማራ” እየተባለ ለመከፋፈል የህወሀትን ድብቅ ተልዕኮ ለማሳካት ሲንቀሳቀሱና እንዲሁም ጎንደርን ከሦስት ዞን በመክፈል ምዕራብ ዞን የተባለው እስከየት ድረስ እንደሆን ለማመላከት የገቡትን እነዚህ አመራሮች በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሱ የአርበኞች ግንቦት ታጋዬች መረጃ በመስጠቱ በተጠቀሰው ቦታ ደፈጣ በመያዝ ይጠቀሙበት በነበረው ኮብራ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ በመክፈት መኪናው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ስትሆን ለጊዜው ስሟ ያልተረጋገጠ ከፌዲራል ተወክላ የመጣች አመራር በመቁሶሏ ወደ ጎንደር ለህክምና ተወስዳለች ።

በተጨማሪም አንድ አጃቢ እና አንድ መካከለኛ አመራርም ቆስለው አይከል ከሚገኘው ክሊኒክ የህክና እርዳታ ቢደረግላቸውም ስላልተሻላቸው ዛሬ ጳጉሜ 01 ቀን 2009 ዓ/ም ወደ ጎንደር ሆስፒታል ተወስደዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እነዚህ ታጋዬች እዚህ ድረስ መጥተው ጥቃት ሲፈፅሙ የመንግስት ሚሊሻዎች እስከ ምርጫው ድረስ በተጠንቀቅ ( እስታንድ ባይ) እድትሆኑ ታዛቹሁ እያለ በቦታው አለመገኘታቹህ ከታጋዬች ጋር ምክር አላቹህ በማለት የሚኒሻ ኩማንደሩ ትጥቁን እዲፈታና ከኃላፊነት እዲወርድ ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ “ከቅማንት አማራ” በሚለው ጉዳይ ላይ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ የተጠየቁ በመተማ ወረዳ መተማ ዮሃንስ ከተማ ፣ የገንድውሃ ከተማ፣ በጭልጋ ወረዳ ፣ የነጋዴ ባህር ከተማ ከፍተኛ ተቋውሞ በማሰማትና የምርጫ ወረቀቶችን እና ቁሳቁሶችን በመቅደድ ተቋውማቸውን አሰምተዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን ውጥረቱ የጨመረ ሲሆን ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እየተከታተልን መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።

ድል የህዝብ ነው !

Advertisements

በኢትዮጵያ የመብት ጥሰት በከፍተኛ ሁናቴ ተባብሷል፤

በኢትዮጵያ የመብት ጥሰት በከፍተኛ ሁናቴ ተባብሷል፤ በሃገራችን በሚገኙ ‹ማረሚያ› ቤቶች እየደረሱ ያሉ ሰብኣዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በፖለቲካ እና የህሊና ‹ታራሚዎች› ላይ እየደረሰ ያለው ጥሰትን የመጨረሻ ደረጃ ማሳያ አይደለም፡፡ ምናልባትም ይህ ግፍ በህውሃት ዝቅተኛው ሊሆን ይችላል፡፡
በህውሃት እስር ቤት የሚደርስባቸው በደል፣ግፍ፣ስቃይ እና የመብት ጥሰት ሊሰማላቸው ያልቻለ ብዙዎች እንዳሉ ለመረዳት ነብይ መሆን አይጠይቅም ነገሩ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡
እንደ አጋጣሚ ሆኖ ታዋቂ ወይም ስራው/ዋ ከሚዲያ ጋር የተያያዘ ከሆነ፤ የሱ/ሷ ጉዳይ ለሚዲያ የመቅረቡ እድልም ሰፊ ነው፡፡ታዋቂና ለሚዲያ ቅርብ የሆነ ሰው የሚደርስባት ማንኛውም ኢ-ሰብኣዊ ድርጊት ለሚዲያ እንደሚደርስ እየታወቀ መብቶቿ በአደባባይ የተጣሱ፤ የሌሎች የፖለቲካ እና የህሊና ‹ታራሚዎች› አያያዝ ሁኔታ ከነሱ የባሰ እንደሚሆን ማስብ ተገቢ ነው።

በማንኛውም ሰው ላይ የደረሰ/እየደረሰ ያለ ማንኛውም አይነት የመብት ጥሰት ሁኔታውን መቀየር ባንችል፤ ቢያንስ መበደላቸውን እና መብታቸው እየተጣሰ እንደሆነ ካየን/ከሰማን በማንኛውም መልኩ ላልሰማ በማሰማት የበኩላችንን እንወጣ፡፡

ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ ምቹ፣ ሁሉም ዜጎቿ ካለምንም የጥላቻ ስሜት እርስ በርስ ተደጋግፈው ሰብኣዊና ቁሳዊ የሀገር ግንባታ ላይ ብቻ የሚያተኩርበት እና የበለጠ የምታኮራ ሀገር ሆና ማየት የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በዚህ አይነት የመብት ጥሰት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ሕልማችሁን እንድታጋሩ እና የሌሎችን ሕልም እንድትጋሩ መጣር ያስፈልጋል፡፡
ለዛም
ስለሚያገባን እንጦምራለን!!!
ከሰብኣዊ

 Zekarias Asaye

posted by Aseged Tamene

የሕግ ባለሙያ፣ ባለሀብትና አርቲስት የሆነው አበበ ባልቻ ተከስሶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዷል፡፡

የሰው ለሰዉ አስናቀ – 18ሺ ብር ከፈለ!

የሕግ ባለሙያ፣ ባለሀብትና አርቲስት የሆነው አበበ ባልቻ ተከስሶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዷል፡፡ አበበ ባልቻ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊሔድ የቻለው ባለፈው ሐሙስ ሌሊት ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ሸገር ሕንፃ ስር በሚገኘው ዩጎቪያ ክለብ በመዝናናት ላይ ነበር፡፡ በቦታው ለእረፍት ከኖርዌይ የመጣውና በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኖርዌያዊ የሆነው ሐሰን መሐመድና የወንድሙ እጮኛ እየተዝናኑ ነበር፡፡ ከሐሰን ጋር የነበረችው ሴትም አበበ አስናቀን ሆኖ በሚጫወትበት የሰው ለሰው ድራማ ታደንቀው ስለነበር ወደ እሱ በመሄድ አብራው ፎቶ ለመነሳት ትጠይቃለች፡፡ አበበም ፈቃደኛ በመሆን አብሯቸው ይነሳል፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መበሳጨት ይጀምራል፡፡ ከዚያም ወደ ሰዎቹ በመሄድ ከሐሰን ላይ ፎቶ ያነሳበትን አይፎን 5 ይቀበለውና መሬት ላይ በመጣል በእግሩ ይሰባብረዋል፡፡ ከልጁም ጋር ለመደባደብ መተናነቅ ሲጀምር የክለቡ ጠባቂዎች ይገላግሏቸዋል፡፡
ሞባይሉ የተሰበረበት ሐሰን አበበን እንዲሁ ሊለቀው ስላልፈለገ ወደ ሕግ ሊወስደው ሲጥር እሱ ባልጠበቀው ሁኔታ ጠባቂዎቹ አበበን ከቤቱ ያወጡታል፡፡ የአበበን መውጣት ያወቀው ሐሰን ግን ከአበበ ጋር አብሮ ይዝናና የነበረውን አርቲስት ሰለሞን ቦጋለን በመያዝ “አንተ ስለሆንክ ያስመለጥከኝ አንተን ወደ ሕግ እወስድሃለሁ” በማለት ይዞት አቅራቢያው ወደሚገኝ ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ይሄዳሉ፡፡ ጣቢያ ደርሰውም ጉዳዩን ያስረዳሉ፡፡ ስለ ሁኔታ የተጠየቀው ሰለሞንም ድርጊቱ መፈፀሙንና በማግስቱ አበበን እንደሚያቀርበው ተናግሮ የአበበንም ስልክ ለፖሊሶች በመስጠት ይለቀቃል፡፡
በማግስቱም ከሳሾች በንብረት ማጉደል ክስ መስርተው ለአበበ በወኪሉ አማካኝነት መጥሪያ በመስጠት ይመለሳሉ፡፡ አበበም ፖሊስ ጣቢያ በመቅረብ ሁኔታ መፈፀሙን እንደማያስታወስ ግን ምናልባት በትከሻው ገፍቶት ወድቆ ሊሆን እንደሚችል ይናገራል፡፡ አቃቤ ሕግና ፖሊስም እነ አበበ ጉዳዩን በሰላም እንዲፈቱት በማግባባታቸው አበበ ለሰበረው ሞባይል 18 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እንዲከፍል በመወሰኑ ተያይዘው ወደ ቢሮው በመሄድ ቼክ ፈርሞ ለሐሰን በመስጠቱና ይቅርታ በመጠየቁ ችግሩ ሊፈታ ችሏል፡፡ (የዚህ ወሬ ምንጭ ኢትዮጲካ ሊንክ የተሰኘው የአዲስ አበባ ሬዲዮ ነው)

 
from . Nigus Kifle
 
posted by Aseged Tamene
 

የኢትዮጵያ እና ሴንትራል አፍሪካ ጨዋታ ቀጥታ ስርጭት ( ኢትዮጵያ 2 – ሴንትራል አፍሪካ 1) ኢትዮጵያ አሸነፈች!!

ኢ.ኤም.ኤፍ – በዛሬው እለት ለአለም ዋንጫ  የማጣሪያ  ጨዋታ እያደረገ ይገኛል። ጥቁር አንበሶቹ  የኢትዮጵያ ቡድን ተጫዋቾች የተለመደውን አረንጓዴ እና ቢጫ መስመር ያለውን ማልያ አድርጎ ነው የገባው። አራቱም ዳኞች ከአልጄርያ የመጡ ናቸው። ጨዋታው ሲጀመር የድምጽ ማጫወቻው ባለመስራቱ የሁለቱም አገር የህዝብ መዝሙር አልተዘመረም። በስቴዲየሙ የሚገኙት ጥቂት የሴንትራል አፍሪካ ቲፎዞዎች ያለሙዚቃ መዝሙራቸውን ጀምረዋል። የኛ በዝምታ ታልፏል። ጨዋታው በገለልተኛ አገር – በኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ቡድን ይህንን ጨዋታ ካሸነፈ ወይም እኩል ከወጣ ከአስሩ አሸናፊዎች አንዱ በመሆን፤ በሚደረገው እጣ መሰረት ከደረሳቸው አገር ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ያደርጋሉ። በደርሶ መልሶ ጨዋታ ካሸነፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ለአለም ዋንጫ ታልፋለች ማለት ነው። ይህንን ጨዋታ በቀጥታ እየተከታተልን እናስተላልፍላችኋለን። አሁን ጨዋታው ከተጀመረ 15 ደቂቃ ተቆጥሯል። ኳስ በብዛት በመሃል አካባቢ ናት። ታዋቂዎቹ አስራት፣  አዳነ፣ ሳላዲን፣ ኡመድ እና  ሽመልስ ወደፊት እያጠቁ በመጫወት ላይ ናቸው።

በረኛው ጀማል ጣሰው ባለፈው ሁለት ቢጫ ካርድ በማየቱ  እዚህ ጨዋታ ላይ መሳተፍ አልቻለም። በመሆኑም ሲሳይ ባንጫ በረኛ ሆኖ ጨዋታው ቀጥሏል። የሴንትራል አፍሪካ አሰልጣኝ ከጨዋታው በፊት እንደተናገሩት፤ “እኛ የኢትዮጵያን ቡድን እናከብራለን። ሆኖም እኛ ያጣነው እድል ነው እንጂ፤ በጨዋታ እንበልጣለን” ብለው ነበር። በርግጥም አሁን እንደምናየው ከሆነ፤ አልፎ አልፎ ሲያጠቁ ይታያል። 25ኛው ደቂቃ ላይ ሽመልስ ያለቀላት ኳስ ስቷል። ከሶስት ደቂቃ በኋላ ደግሞ ሴንትራል አፍሪካ  ያለቀለት ኳስ ስቷል። ከአምስት ደቂቃ በኋላ ደግሞ ሴንትራል አፍሪካ ሌላ እድል አግኝቶ፤ በኬታ አማካኝነት የመጀመሪያ ግብ ኢትዮጵያ ላይ ተቆጥሯል። ጥሩ ዜና አይደለም። ጨዋታው ከተጀመረ 30 ደቂቃ ተቆጥሯል።

32ኛው ደቂቃ ላይ ሴንትራል አፍሪካ እንደገና አጥቅቶ የሚገርም ሙከራ አድርጎ አዳናት። ልትገባ ያለቀላትን ኳስ ነው በእግሩ ጨርፎ አድኗታል። የኢትዮጵያ ቡድን ጨዋታ ብዙም የሚያመረቃ ሙከራ እያደረገ አይደለም። አጭር ቅብብል እያደረጉ ለማለፍ እየሞከሩ ነው ሆኖም  ቶሎ ቶሎ እየከሸፈባቸው ነው። በሌላ በኩል ደቡብ አፍሪካ እና ቦትስዋና በሚያደርጉት ጨዋታ 0 -0 ናቸው።

አሁን36ኛው ደቂቃ ላይ… ደቡብ አፍሪካ 1 ጎል አግብታለች። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ… ደቡብ አፍሪካ አሸንፋ፤ ኢትዮጵያ ከተሸነፈች፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጉዳይ ኮንጎ ላይ ያበቃለታል ማለት ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ በጨዋታም ቢሆን በልጠውናል። ቢሆንም ተስፋ ሳንቆርጥ እስከመጨረሻው እንቀጥላለን። የመጀመሪያው 45 ደቂቃ አብቅቶ እረፍት ወጥተዋል። ሴንትራል አፍሪካ 1- ኢትዮጵያ ዜሮ። በሌላ በኩል የደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ግብ አስቆጥሯል። ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለናንተ መናገር አያስፈልግም።

ከእረፍት በኋላ እንደገና ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን። ከ እረፍት በኋላ ተጠናክረው ካልገቡ በዚህ አይነት ሁኔታ የማሸነፍ እድላችን የመነመነ ነው።

አሁን እረፍት ወጥተው እያለ፤ አንዳንድ ነገሮች ለማለት አሰብን። ግን ምን ሊባል ይቻላል? ብዙም ጥሩ ጨዋታ አላየንም። አጭር ቅብብል ነው የሚያደርጉት፤ እሱንም ወዲያው እየተነጠቁ እድላቸውን ሲያጡ አይተናል። ቢያንስ ረዥም ኳስ በመጫወት የሚታወቀው ዳዊት እስጢፋኖስ አልገባም። ሌላኛው አጥቂ ጌታነህ ከበደም አልገባም። እንግዲህ ይሄ ሁሉ የአሰልጣኙ ውሳኔው ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም። ያለውን ነገር እንዳለ ተቀብለን፤ ጸሎት ጨምረንበት የሚቀጥለውን ጨዋታ እንከታተላለን።

ለማንኛውም አብራችሁን ቆዩ።

ከእረፍት  ተመልሰዋል። ኡመድ በበሃይሉ አሰፋ (ቱሳ) ተቀይሯል። ከ እረፍት በኋላ 2ኛው ደቂቃ ላይ ሳላዲን ሰይድ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሯል። ቢያንስ በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን እናልፍ ይሆናል። የኢትዮጵያ ተስፋ እንደገና ጨምሯል።

ከእረፍት በኋላ አሁንም ሴንትራል አፍሪካ  አልፎ አልፎ  ሲያጠቁ እያየን ነው።

ዘጠነኛው ደቂቃ ላይ ሳላዲን ሌላ ሙከራ አድርጎ ነበር። አሁን ከመጀመሪያው ይልቅ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምረዋል። ሆኖም የሚያደርጉት አጭር ቅብብል ስለሆነ ኳስ እንደገና ስለሚነጠቁ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ጨዋታ እየተጫወቱ ናቸው። ጨዋታው ከተጀመረ 15 ደቂቃ ተቆጥሯል። ልክ አስራምስተኛው ደቂቃ ላይ ምንያህል ተሾመ ወሳኝ የሆነች በጣም አሪፍ ጎል አግብቷል። አሁን ኢትዮጵያ 2 – ሴንትራል አፍሪካ 1 ሆነዋል። የሚገርም ነው – ምንያህል ተሾመ የኢትዮጵያን ቡድን እንደገና ክሶታል። ባለፈው ሁለት ቢጫ በማየቱ እና ተመልሶ በመግባቱ ምክንያት ኢትዮጵያ አንድ ጨዋታ ሶስት ነጥብ የተቀሰ ባት መሆኑ ይታወሳል። እናም አሁን ሁለተኛ እና ወሳኟን ጎል በማስቆጠር የኢትዮጵያን ቡድን ክሷል።

አሁን ጨዋታው ሞቅ ማለት ጀምሯል። 2-1 ጨዋታው ከተጠናቀቀ ከምድቡ በ13 ነጥብ አንደኛ ሆነን በማለፍ፤ ከአስሩ የምድብ አሸናፊዎች አንዱ እንሆናለን። ከዚያም በእጣ ከሚደርሳቸው ቡድን ጋር በደርሶ መልስ የሚያደርጉት ጨዋታ ወሳኝ ይሆናል ማለት ነው።

ጨዋታው ከተጀመረ 23ኛ ደቂቃ ሆኗል። ሴንትራል አፍሪካ መልሰው ማጥቃት ስለጀመሩ ሁኔታው የሚያሰጋ እና የሚያጓጓ ሆኗል። የኢትዮጵያ ቡድን ቢያንስ ይሄንን ውጤት ይዞ ቢጨርስ፤ የማለፍ እድሉ የተረጋገጠ ይሆናል።

አሁን ጥሩ ጨዋታ እየተጫወቱ ናቸው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተረጋግቶ በቄንጥ እየተጫወተ ነው። ቄንጡ ቀርቶ ግን ጠንክረው ማጥቃቱን ቢቀጥሉ ደግሞ የበለጠ ጥሩ ይሆናል። ስቴዲየሙባዶ ነው ለማለት ይቻላል። ሆኖም ጥቂት ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ማልያ አድርገው ሲጨፍሩ ይታያሉ።

አሁን የኢትዮጵያ ቡድን ኳሱን ተቆጣጥረው መጫወት ጀምረዋል። አሁን ገና መጫወት ጀመሩ። ባለፈው 15 ደቂቃ ውስጥ ያለቀላቸው ሁለት ግቦች ‘ኦፍ ሳይት’ ሆነውባቸዋል። ጨዋታው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃዎች ቀርተዋል። እነሱ በጨዋታ፤ እኛ በጸሎት ጭምር ጨዋታውን እየተከታተልን እንገኛለን።

ሴንትራል አፍሪካዎች ሲያጠቁ፤ ሲሳይ ባንጫ ላይ ጉዳት ስላደረሱበት በመውደቁ፤ ጨዋታው ለአንድ ደቂቃ ያህል ተቋርጦ ነበር።  አሁን ጨዋታው ከተጀመረ በኋላ ደግሞ ሽመልስ ተጎድቶ ወጥቷል። ብርሃኑ ቦጋለ (ፋቲጋ) ሊገባ እያሟሟቀ ነው። ብርሃኑ ፋቲጋ በፈጣን ሩጫ እና አክርሮ በመምታት የሚታወቅ ተጫዋች ነው።

ሲሳይ ባንጫ ለኢትዮጵያ ቡድን ባለውለታ እየሆነ ነው። በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የሚገርሙ ኳሶችን አድኗል።

ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂቅ ደቂቃዎች ቀርተው፤ የማዕዘን ምት ባገኘንበት ሁኔታ ላይ እያለን… ረብሻ ቢጤ ተነስቶ ነበር። ኢትዮጵያውያኑ የማዕዘን ቅጣት ምቱን እየተቀባበሉ ጊዜ ለማባከን እየሞከሩ ናቸው። ሴንትራል አፍሪካዎች ተናደው የኢትዮጵያ ቡድን ተጫዋቾችን ሲጎነትሏውቸው ይታያል። ሴንትራል የሴንትራል አፍሪካው 15 ቁጥር ቢጫይቷል።

በመጨረሻም ጨዋታው ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ ቡድን ከአስሩ ቡድኖች አንዱ መሆኑ ተረጋገጠ። ኢትዮጵያ 2-1 አሸነፈች። በ13 ነጥብ ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ተሸጋግረናል። ደስ ብሎናል ደስ ይበላቹህ!!

በየቦታው ጨዋታው ካለቀ በኋላ ጭፈራው እና ሆታው ቀጥሏል። እናመሰግናለን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን።

source. EMF

posted by Aseged Tamene

)የአንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ በአዳማ/ናዝሬትና የአዳማው ድራማ( video)

የአዳማው ድራማ
==========
በህገ መንግስቱ መሰረት ለአዳማ አስተዳደር አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግና መስተዳድሩ ይህንኑ በማወቅ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ በደብዳቤ ካሳወቀና መስተዳድሩም የሰልፉ ቀን ይቀየርልኝ በማለት ባቀረበው ምክንያት የተነሳ አንድነት ሰልፉን ለፊታችን እሁድ ማዞሩን አስታውቆ ቅስቀሳ ይጀምራል፡፡

ድራማ 1
——–
በራሪ ወረቀቶች መበተን እንደተጀመሩ ፖሊስ አባላቶችን ጣብያ በመውሰድ መበተን አትችሉም አለ፡፡ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አሳውቀናል፣ ይህ ወረቀት ለሰላማዊ ሰልፍ የተዘጋጀ በመሆኑ ልትከለክሉን አትችሉም ፡፡ የሚል ምላሽ ተሰጠው፡፡ለሰዓታት በጣብያ እንዲቆዮ የተደረጉ አባላት በጭቅጭቅ ከጣብያው እንዲወጡ ተደረጉ፡፡

ድራማ 2
————
ከአዲስ አበባ ለቅስቀሳ የወጣ መኪና ሞንታርቦ ተጭኖለት ወደ ስራ ሊሰማራ ሲል ፖሊስ መኪናውን በማስቆም መቀስቀስ አትችሉም አለ፡፡ምክንያቱ የተፈቀደው ለሰልፍ እንጂ ለቅስቀሳ አይደለም የሚል ነው፡፡የአንድነት ልጆች ፖሊስ ቢፈልግ ማሰር እንደሚችል በመጥቀስ ከመቀስቀስ ወደ ኋላ እንደማይሉ አስረግጠው በመናገራቸው ጭንቅ ያለው ፖሊስ ‹‹ሂዱና የቱሪዝም ኮሚሽንን አነጋግሩ››ይላል፡፡
ዛሬ ማለዳ ወደ አዳማ ቱሪዝም ቢሮ የሄዱ አባላት አስገራሚ መልስ ተሰጥቷቸዋል፡፡ባለስልጣኑ ‹‹በመኪና መቀስቀስና ፖሰተር መለጠፍ ትችላላችሁ ነገር ግን በራሪ ወረቀት መበተን አትችሉም ምክንያቱም ወረቀቱ ኦህዴድን የሚሳደብ ነው››በማለት ፖሊስ ዙሪያ ጥምጥም ሲዞር የዋለበትን እቅጩን ተናግረዋል፡፡ኦህዴድን ትሳደባለች የተባለችው በኦሮምኛና በአማርኛ የተዘጋጀችው በራሪ ወረቀት በአሁኑ ሰዓት በአዳማ ነዋሪ እጅ እየገባች ነው፡፡

source: finotenesanet

posted by Aseged Tamene

%d bloggers like this: