ወያኔ ኢህአዴግ ለመለወጥ ዝግጁ አለመሆኑን ባወጣው መግለጫ ማረጋገጡ ተነገረ

ኢህአዴግ፣ ምንም ዓይነት የመለወጥ ተነሳሽነት እንደሌለው አረጋገጠ፡፡ ፓርቲው ቅዳሜ እና እሁድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ያካሔደ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይም ከዚህ ቀደም የተለመዱትን ቃላት ከመደጋገም ውጭ፣ የህዝቡን ጥያቄ የሚመልስ ተነሳሽነት አለመታየቱ ታውቋል፡፡ ሀገሪቱ በከባድ ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ሰዓት እንኳን ቆም ብሎ በማሰብ ፖለቲካዊ መፍትኤ መፈለግ ሲገባው፣ ጭራሽ የጠነዛ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳውን በመግለጫ መልክ ማውጣቱ እጅግ እንደሚያሳፍር የድርጅቱን መግለጫ የተከታተሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡

‹‹ዴሞክራሲያችን ገና ለጋ ነው፤ በሀገሪቱ የተከሰተው ግጭት እና ተቃውሞ የኪራይ ሰብሳቢዎች ሴራ ነው›› በሚሉ አሰልቺ ቃላት የተሞላው የገዥው ፓርቲ መግለጫ፣ ለህዝብ ጥያቄ እና ለሀገሪቱ ህልውና ደንታ የሌለው ሆኖ እንዳገኙት የሚናገሩት ታዛቢዎች፣ ፓርቲው ራሱን እያታለለ እንደሚገኝ ካወጣው መግለጫ መረዳታቸውን አክለው ተናግረዋል፡፡ አለበለዚያማ ሲሉ አስተያየታቸውን የቀጠሉት ታዛቢዎቹ፣ ‹‹… የሀገር ጉዳይ ቢያሳስበው እንዲህ ያለ መፍትኤ አልባ መግለጫ አያወጣም ነበር!›› ሲሉም አስተያየታቸውን ያጠናክራሉ፡፡


የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በአግባቡ ተመልሶ ሀገሪቱ ዳግም በሁለት እግሯ እንድትቆም ፖለቲካዊ መፍትኤ ማፈላለግ ሲገባ፣ በተቃራኒው ፓርቲው በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጎች ላይ ግድያ የፈጸሙ የጸጥታ አካላትን አመስግኗል፡፡ የንጹኃንን ህይወት በመቅጠፍ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱትን የጸጥታ አካላት፣ ‹‹ከፍተኛ እልቂት እንዳይከሰት ስላደረጋችሁ እናመሰግናለን፡፡›› ሲልም አሹፏል – ኢህአዴግ፡፡

የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ከሚቴ አባላት ቅዳሜ እና እሁድ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረጉት በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው ቢባልም፤ ያወጡት መግለጫ ግን ላለፉት በርካታ ዓመታት ህዝብን ያደነቆሩበት እና ምንም አዲስ ነገር ያልታከለበት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡

 

Advertisements

መቱ ከተማ ዉስጥ ሁከት ለመፍጠር በዝግጅት ላይ የነበሩ የህወሃት ደህንነቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮምያ ክልል ክልል መቱ ከተማ ዉስጥ ሁከት ለመፍጠር በዝግጅት ላይ የነበሩ የህወሃት ደህንነቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የትግራይ ተወላጅ እንደሆኑና በሆቴል ስራ ላይ እንደተሰማሩ የሚታወቁት እነዚሁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለው ቤታቸው እየተፈተሸ መሆኑ ታዉቋል።

እነዚሁ ደህነት ናቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት የትግራይ ተወላጆች ቤትና የንግድ ድርጅት ዉስጥ የጅ ቦምብ፣ለእስናይፐር ተኩስ (አልሞ ለመተኮስ) የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያዎች፣የኦነግ ሰንደቅ አላማ፣ወረቀት ለመበተን የሚያገለግሉ የህትመት መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ቢቢኤን የመቱ ከተማ ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማወቅ ችሏል::

ከፍተኛ የኦሮሚያ ጦር አዛዦች ከሃላፊነታቸው እየተነሱ ነው ተባለ

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ መከላከያ ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ ኦሮሞ የሆኑ የጦር አዛዦች ቀጥታ ሰራዊቱን ከሚያዙበት ምድቦች እየተነሱ ምንም ስራ በሌለባቸው ቦታዎች እየተመደቡ እንደሆነ ታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ኦሮሞ የሆኑ የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች ተቃውሞውን ይደግፋሉ የሚል ምልከታ በህወሃት የጦር አዛዦች መያዙን ለመረዳት ተችሏል። ታችኛው ላይ ያለው አብዛኛው ሰራዊት ከሌላ ብሄር የመጡ በመሆናቸው እነዚህ የኦሮሞ ከፍተኛ መኮንንኖች ኦሮሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ምክንያት አድርገው ታች ላይ ያለውን ሰራዊት በማንቀሳቀስ ህወሃት ላይ አደጋ እንዳያመጡና የተቃውሞው አካል እንዳይሆኑ በማለት ቀጥታ ሰራዊት ማዘዝ የማይችሉባቸው ቦታዎች ላይ እንዲመደቡ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ከሃላፊነታቸው ተነስተው በሹመት ስም ምንም ጦር ማዘዝ በማይችሉበት ቦታ በሆነው የደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ሃላፊ በማለት እንዲመደቡ ተደርገዋል።

በብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ምትክ የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ በመሆን ኮ/ል የማነ ገ/ሚካኤል የተባሉ የህወሃት የጦር አዛዥ ተመድበዋል። የ13ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ከድር አራርሳ ቀጥታ ጦሩን ከሚያዙበት ሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጎ በሹመት ስም ምንም ጦር ወደ ማይመሩበትየማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ሃላፊ በመሆን ተመድበዋል።

የ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ከፍያለው አምዴ እንዲሁ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የ21ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ዋኘው አማረ ከሃላፊነታቸው ተነስተው በመሃንዲስ ዋና መምሪያ ውስጥ እንዲቀመጡ ተደርጓል።

የአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ሃላፊ የሆኑት ብ/ጄነራል ሙላት ጀልዱ ከላፊነታቸው ተነስተው በመከላከያ የስነምግባር መከታተያ ዳይሬክተር በማድረግ ከሰራዊቱ ጋር ቀጥታ ከሚያገናኛቸው ስራዎች እንዲገለሉ ተደርጓል።

በርካታ የአማራና የኦሮሞ ከፍተኛ መኮንኖች በሰላም ማስከበር ሰበብ ከሰራዊቱ እንዲገለሉ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ መከላከያ ውስጥ ያሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰራዊቱ ተቃውሞውን እንዳይቀላቀል በህወሃት በኩል ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ሲሆን ለህዝብ ወገኝተኝነት ያሳያሉ የሚባሉ የጦር አዛዦችን ከሃላፊነታቸው በማንሳት ምንም ወደ ማይሰሩበት ቦታዎች በሹመት ስም እየተዛወሩ መሆኑ ታውቋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር ትራንስፖርት መቆሙ ተነገረ

ከሰሜን ሸዋ በሙከጡሪ ከተማ ተገንጥሎ ያሉት ቆላማወች ለሚ እና መርሃቤቴ ከተሞች ፣ በጎጃም ደጀን ሉማሜ ከተሞች ህዝባዊ አመፁ ሞቅታ እየደረሳቸው መሆኑ ተነገረ።

ከአ.አ በቅርብ ርቀት ከሱሉልታ እስከ ጉሃፅዩን ድረስ የአባይን ድልድይ ሳይሻገሩ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመፅ ና ቁጣ ወደ ጎጃምና ሰሜን ሸዋ እንዳይዛመት በመስጋት የወያኔ አጋዚ ጦር እየሰፈረ ይገኛል።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ መቆሙም የተነገረ ሲሆን
በህዝባዊ አመፁ በወያኔ የአጋዚ ወታደሮች የሀይል እርምጃ የተቆጣው ህዝብ በወሰደው እርምጃ በርካታ ተሽከርካሪወች ና ቤቶች መቃጠላቸውን ተከትሎ ከአባይ በረሃ ተሻግሮ ባሉት ከተሞች በርካታ ተሽከርካሪወች በመንገዱ ግራናቀኝ ተሰትረው ይገኛሉ።

ከትራንስፖርት መስተጓጎሉ ባሻገር ከግብር ጋር ተያይዞ በክረምቱ ህዝባዊ አድማ ሲደረግባቸው የነበሩ ከተሞች በመሆናቸው የኦሮሚያው ህዝባዊ አመፅ ሞቅታው ስለደረሳቸው ህዝቡ ለአመፅ እንዳይነሳ በከተሞቹ ካድሬወች ተሰግቷል።


በደጀን ከተማ በርካታ ተሽከርካሪወች የቆሙ ሲሆን ከጎንደር አ.አ እና ከጎጃም አዲስ አበባ የሚደረጉ ጉዞወች ተሰርዘዋል። በተለይ የህወሓት ንብረት የሆኑና ከሥርዓቱ ጋር የቅርብ ግንኙነት የጥቅም ተቋዳሾች ትልልቅ ልዩ አውቶብሶች የጉዞ ትኬታቸውን ለትናንት የተቆረጠ የመለሱ ሲሆን ዛሬ ጉዞ እንደማያደርጉ ገልፀው ትኬት ከመሸጥ ተቆጥበው ውለዋል።


ከመከጡሪ ከተማ በስተቀኝ ተገንጥሎ 50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ለሚ ከተማ እንዲሁም ከ100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው መርሀቤቴ አጠቃላይ ቆላው ዙሪያ ገባው በአብዛኛው በመከጡሪ ከተማ በነበረው ህዝባዊ አመፅ ተሳታፊ የነበረ ሲሆን ወደ ከተሞቹ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቆሞ ውሏል። ከተሞቹ እንደሌሎቹ የኦሮሚያ ከተሞች ጭር ብለው በወያኔ ወታደሮች ተወረው ውለዋል።


በተያያዘ መረጃ ከአባይ በረሃ ተሻግረው ባሉ ዙሪያው አካባቢ ባሉ ጥቃቅን መንደሮች የወያኔ ወታደሮች አፈሳ ሲያደርጉ እንደነበር ተሰምቷል።

የወያኔ ስርሀት የመጨረሻው ጫፍ ላይ የደረሰ ይመስላል ተባብረን እንግፋው

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ፡፡

ኤምባሲው ደረሰኝ ያለውን ዘገባ ጠቅሶ እንዳስታወቀው በግድያ እና ግጭቱ ተጠያቂዎችን ለመለየት ግልጽ ምርመራ መደረግ እንደሚገባው ሁኔታው ያመለክታል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ሰላማዊ ሰልፎችን የምትመለከተው እንደ ህጋዊ የሀሳብ እና የፖለቲካ ተሳትፎ መግለጫ እንደሆነ ኤምባሲው ዛሬ ያወጣው መግለጫ ያትታል፡፡

በቅርቡ በተካሄዱ በርከት ባሉ ሰልፎች ሰልፈኞች በሰላማዊ ሁኔታ ሀሳባቸውን መግለጻቸውን እና ይህን እንዲያደርጉም የጸጥታ ኃይሎች መታገሳቸውን በአድናቆት እንደሚመለከተው ኤምባሲው ገልጿል፡፡

ኤምባሲው ሁሉም ኢትዮጵያውያን አመለካከታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጻቸውን እንዲቀጥሉ አበረታቷል፡፡ ባለስልጣናትም ይህንኑ አንዲፈቅዱ ጠይቋል፡፡ በጥቅሉም «ኢትዮጵያዊያንን በሚጠቅም ጉዳይ ገንቢ፣ ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታች ብሔራዊ ተዋስዖ» መኖሩን እንደሚደግፍም በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

The United States sees peaceful demonstrations as a legitimate means of expression and political participation.  We note with appreciation a number of recent events during which demonstrators expressed themselves peacefully, and during which security forces exercised restraint in allowing them to do so.

We are saddened by reports that several recent protests ended in violence and deaths.  All such reports merit transparent investigation that allows those responsible for violence to be held accountable.

We encourage all Ethiopians to continue to express their views peacefully, and encourage Ethiopian authorities to permit peaceful expression of views.  More generally, we encourage constructive, peaceful, and inclusive national discourse on matters of importance to Ethiopian citizens.

%d bloggers like this: