የሚታገሉትን የማያቁ የአማራ ነን ባዮች የከሸፈ ስልት

ለሀያ አምስት አመት ተንሰራፍቶ ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ የሚገኘው ትግራይን ለመገንጠል አላማ አድርጎ የተነሳ ግን የሚታገለው በማጣቱ የሀገሪቱ መራሒ መንግስት በመሆን በሀገሪቱን ዜጎች የፈለገውን በማሰር፣ ኣሰቃቂ ድብደባ በመፈጸም እና በመግደል እስከወዲያኛው ትውልድ ድረስ ተከፍሎ የማያልቅ ብድር በሀገሪቱ ስም በመበደር የሕወሓት ባለስልጣናት በየግል ካዝናቸው በስበብ አስባቡ ዘርፈው አከማችተውታል።

ግፍ የመረረው ህዝባችን በእልህ እና በቁጭት መሳሪያ አንግቦ ለነጻነት የትጥቅ ትግል ከሕወሓት ወታደር ጋር በሚያደርግበት ስአት ህዝቡን በሞራል እና በገንዘብ አይዞህ እንደማለት የነጻነት ትግል በሚያካሒዱ የፖለቲካ ድርጂቶች እና መሪዎቻቸው አልፎም በንቁ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች ላይ ያነጣጠረ መንቻካ ዘመቻ ለበርካታ ሳምንት ማህበራዊ ሚዲያውን ለመበጥበጥ የነጻነት የትግል አቅጣጫውን እንዲስት ሆን ተብሎ ደጎስ ያለ ድጎማ ከህወኃት በሚያገኙ ጥቀመኞች ጥቃት ሲሰነዘር መቆየቱ ብዙዎችን አሳዝኗል፣አበሳጭቷል።

ስለሆነም በተለይ በአማራ እና በኦሮሞ መብት ተሟጋች ነን በሚሉ ኢትዮጵያዊነት ባህልን ያቆሸሸ እና ታሪኩን ያሳደፈ ምግባር የታየ ሲሆን የአግ፯ ደጋፊ ነን የሚሉ ጥቂት ሰዎችም ለተሰነዘረባቸው አላስፈላጊ ዘመቻ ምላሽ ለመስጠት በእልህ ውስጥ በመግባት ያደረጉት ምልልስ ተገቢ አልነበረም።

ለሀገር እና ለወገን መብት ውድ ህይዎታቸውን ለመገበር በርሃ የገቡ ጄግኖቻችን ሞራል በተራ ስድብ የሚፈታ የመሰላቸው ሽባ የወያኔ ቅጥረኞች ከዚህ ስራቼው እንዲታቀቡ አስቀድመን እንመክራለን። ማንኛውም ኃይል እና ጉልበታችን ወያኔ ላይ ለማሳረፍ በአዲሱ የፈረንጆች አመት ዳር እስከዳር መያያዝ አለብን።
ድል ለነጻነት ታጋዮች

14956437_220660495029930_1633004519583544399_n

የአርበኞች ግንቦት 7 ክ/ጦር ዛሬ ቁልፍ ቁልፍ የተባሉ ሁለት መደበኛ የዉጊያ መስመሮችን ሰብሮ በመዝለቅ ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው

ወሃት ወያኔ በመላዉ ሐገራችን ኢትዮጵያ ላይ የደነገገዉ የአስቸክዋይ ግዜ አዋጅ በሰሜን ጎንደር ፈጽሞ ሊሰራ አለመቻሉን ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎች እያመላከቱ ይገኛሉ ዛሬ ለሶስተኛ እለት ቀጥሎ የዋለዉ የሰሜን ጎንደሩ ዉጊያ የህወሃታዊያንን ጉልበት በእጅጉ አዳክሞታል።
በቃብትያ ሁመራና አጎራባች ቀበሌዎች የህወሃት ኮማንድ ፖስት በመደምሰሱ ተጨማሪ ሐይል ሲያሰባብስብ የነበረዉ የትግራይ ነጻ አዉጩዉ ቡድን ሰርከሌት በተባለዉ ስፍራ ወታደራዊ ማዘዣና ቁልፍ የአደባይ ተራራማ ቀጠናዎችን ለአርበኖች ግንቦት 7 ሰራዊት አስረክቦ እንዲፈረጥጥ ተገዷል።
በአርበኞች ግንቦት 7 የሰላምና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሐላፊነት የተወሰደበት ጥቃት ተባብሶ በመቀጠል አንድ ዘመናዊ መሳሪያዎችን የታጠቀ የአርበኞች ግንቦት 7 ክ/ጦር ዛሬ ቁልፍ ቁልፍ የተባሉ ሁለት መደበኛ የዉጊያ መስመሮችን ሰብሮ በመዝለቅ ወደ ፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝ የ24ተኛ ክ/ጦር ምንጭ ያሳወቀ ሲሆን።
በተያያዘ መረጃ ዛሬ ከኤርትራ የጸጥታ ሐላፊዎች የወጣዉ መረጃ እንደጠቆመዉ በኤርትራ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የተገናጣይ ቡድኖቹ ለምስራቅ አፍሪካ ዘላቂ ሰላም ሲባል ወደ አንድነት እንዲመጡ ወይም ከትግሉ ምእራፍ እራሳቸዉን እንዲያወጡ በተለዩ አካሎች መጠየቃቸዉንና አብዛኞቹ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር የተዋሃዱ ሲሆን ጥቂቶቹ በኤርትራ ምድር ነቅልዉ ተበትነዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

ኮንሶ በአሁኑ ሰአት የጦር አውድማ ሆናለች!

ወያኔ የኮንሶ ነዋሪዎችን ከነቤታቸው በእሳት አቃጥሎ እየገደላቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ኮንሶ ውስጥ የሚሰሩ የመንግሥት ሰራተኞች ለ5 ወራት ደመወዛቸው አልተከፈላቸውም፡፡ ህዝቡ ካለፈው መጋቢት 2008 ዓ.ም. በወታደሮች እየተገደለ፣ እየታሰረና እየተፈናቀለ ነው፡፡ ከዚህ በደል ያመለጠ ቀየየውን ለቆ ወደ አጎራባች ኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች እና ሌሎች አካባቢዎች እየተሰደደ ነው፡፡

ህዝቡ ይህ ሁሉ በደል እየደረሰበት ያለው ”ካለን የህዝብ ብዛት እና የቦታ ስፋት አንፃር ከልዩ ወረዳነት ወደ ዞን አስተዳደር በማደግ ራሳችንን እናስተዳድር” ብለው ሰዎቹ ፅፈው በሰጧቸው ሕገ-መንግሥት መሰረት ጥያቄ ሲያቀርቡ፤ ይብሱኑ ወደ ወረዳ አስተዳደር አሳነሳቸው፡፡ ይሄንን የአገዛዙን የኃይል ርምጃ በመቃወም ሰላማዊ ሰለፍ አደረጉ፡፡ ከዚያም በወታደሮች ግድያ፣ እስር፣ ስቃይና ስደት ዕጣ ፈንታቸው ሆነ፡፡ እነሆ ሰሞኑን ደግሞ የመብት ጥያቄውን አስተባብረዋል፣ ደግፈዋል፣…ተብለው በአገዛዙ የተጠረጠሩ፣ ከመጋቢቱ ግድያ፣ እስርና ስቃይ የተረፉትን ”መንግሥት” በያዝነው መስከረም 2009 ዓ.ም. ከነ መኖሪያ ቤታቸው ጋር አብሮ እያቃጠለ ሲሆን፤ ለማምለጥ የሞከሩት ደግሞ በወታደሮች ጥይት እየተገደሉ ነው፡፡

የሠራዊቱ ቁጥር እየተጨመረ ነው እስካሁን ከ2000 በላይ መከላከያ ከ1500 በላይ የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ከ100 በላይ የሠገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ፖሊስ የፌዴራል መከላከያ ምክትል አዛዥ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ አቶ ፊስሃ ጋረደው የሚመሩ ናቸው እስካሁን ድረስ ቃጠሎ ቀጥሏል የሞቱት ሰዎች ከ150 በላይ ሲሆን የቆሰሉ 200 በላይ በዛሬው ዕለት ብቻ የተቃጠሉ ቤቶች ከ159 በላይ ሲሆኑ ከ15,000 በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ ፤ ከ50 በላይ ሰዎች ታስረዋል ፡፡ የአንድ ባለሀብት ንብረት የሆነው አይሱዙ መኪና በልዩ ኃይል መንገድ ላይ እየሄደ እያለ ጎማ በጥይት ተመትቶ ግለሰቡ አቶ አዲሱ ሙሉ እና የወንድሙ ልጅ ከወንድሙ ጋር አሳስረው ክፉኛ ተደብድበው በህይወት አፋፍ ላይ ናቸው ፡፡ ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው ተከልክለዋል ፡፡ እስካሁን ተፈናቃዮችም ሆነ የታሰሩ ሰዎች የሚጠይቅ የመንግሥትም ሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሉም ፡፡

ይህ ግፍ ምናልባት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ታርክ በኢህአዴግ መንግሥት የጠፋ ብሔር ሆኖ ኮንሶን ሊያስመዘግብ ይችል ይሆናል ፡፡

14355142_877873255646464_8782711721462134178_n 14349126_636354039863263_1654501838_n

ሐሃይለማርያም ደሳለኝና ቴድሮስ አድሀኖም የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስገድደውን አዲሱ ስምምነት ከሀገራት ቀድመው መፈረማቸው ታውቋል።

ሐሃይለማርያም ደሳለኝና ቴድሮስ አድሀኖም የሚባሉ የወያኔ ተላላኪዎች በአሁኑ ወቅት ቤልጅየም ብራሰልስ የሚገኙ ሲሆን በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ስደተኞችን በሀገራቸው ለመገደብና ተቀባይነት ያላገኙትን ወደ መጡበት ለመመለስ ለሚያስችለው ስምምነት ከ62ቢሊዮን ዩሮ በላይ በጀት መመደቡን ተከትሎ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን ወደ እናት ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስገድደውን አዲሱ ስምምነት ከሀገራት ቀድመው መፈረማቸው ታውቋል።

እነዚህ ጨቋኝ የዜጎችን ደም የሚጠጡ አምባገነኖች እንደዚህ አይነቱን በሰበብ አስባቡ ከፈረንጅ የሚወረወርላቸውን ዳርጎት ለአገዛዙ እኩይ ምግባርና የጭቆና ቀምበር ለመጠቀም ከሀገራት ሁሉ ተሽቀዳድመው ፈራሚ መሆናቸው ታውቋል።

ስምምነቱን ሀይለማርያም ደሳለኝና የአውሮፓ ህብረት ኮምሽነር ጃን ክላውድ ጃንከር ማክሰኞ ዕለት በብራስልስ ተፈራርመዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ህብረት ከተለያዩ የአፍሪቃ አፋኝ መንግስታት ጋር የተናጠል ስምምነት በማድረግ ስደተኞችን ላለመቀበል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በርካታ የስብዓዊ መብት ድርጅቶች እያወገዙት ይገኛሉ።

ስምምነቱ ከዚህ ቀደም የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪቃ አህጉር ጋር በጋር ችግሮች ዙሪያ ለመስራት ያደረገው ስምምነት አካል መሆኑም ታውቋል።

ትግራይ ክልል እራሳችሁን ጠብቁበት ተብሎ ጠብመንጃ ይሰጣል።

914e2-tplf_failing

መቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር በነበርኩበት ወቅት ጏደኛየ እና እኔ ቤት ተከራይተን የምንኖረው ከሁለት ጎረቤት አከራዮች ነበር። እናም አንድ ቀን የጏደኛየ አከራዮች ሰርግ ተጠርተው ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ይወስናሉ። ሰዎቹ በእድሜ ገፋ ያሉ ስለሆነ ትንንሽ ልጆች የሏቸውም ነበርና ወደ አዲስ አበባ ሲሆዱ ቤት የሚጠብቅላቸው ሰው ያጣሉ። ከዚያም ይህ ሰውየ ታጣፊ ክላሹን አውጥቶ ጏደኛየን እንካ ይሄን ይዘህ ቤቴን ጠብቅልኝ አለውና ሰጠው። ልጅም ክላሹን ተቀብሎ ግን እንዲህ ብሎ ጠየቀው” ጠብመንጃ መያዝ እንዴት ተፈቀደልህ አለው” ሰውየውም “እኛ እኮ እራሳችሁን ጠብቁበት ተብለን ጠብመንጃ ይሰጠናል” አለው። ልብ በሉ ይህ ሰውየ የቀበሌ ሊቀመንበር ወይም የመንግስት ስራ አስኪያጅ አይደለም የመንግስት ሰራተኛ እንጅ።

ኤርምያስ ለገሰ በመጽሀፉም እንደጻፈው የወያኔ አባላት የነበሩ 10ሺህ ትግሬዎች ከሰራዊቱ ተሰናብተው የአዲስ አበባ ነዋሪ እንዲሆኑ ሲደረጉ ከነሙሉ ትጥቃቸው ነው። ስለዚህ ትግሬ የታጠቀው ትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባና በየሚኖርበት የአገሪቱ ክፍል ውስጥ ነው።

አማራ ክልል እንኳን የመንግስት ሰራተኛው አርሶ አደሩ ጠብመንጃ መያዝ አይፈቀድለትም። Gashaw AlemyeAgegne

%d bloggers like this: