ኦብነግ ከሶማሊ ልዩ ሃይልና ከመከላከያ ጋር መዋጋቱ ተዘገበ

ኦጋዴን ኒውስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሁለት ቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊት በሚደገፈው የሶማሊ ልዩ ሃይልና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት መካከል በደጋሃቡር አውራጃ፣ በብርቆት ወረዳ ልዩ ስሙ ሊዲለይ በሚባል ስፍራ ላይ በተደረገ ውጊያ 3 አዛዦችን ጨምሮ 17 ወታደሮች መገደላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።

21 ቁስለኛ ወታደሮች ደግሞ በአየር ወደ ጅግጅጋ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን እማኞች እንደገለጹለት የዜና ድርጅቱ አስታውቋል። የኦብነግ ወታደሮች በኮሌራ በሽታ ለተጠቁት የአካባቢው ሰዎች መድሃኒት በማከፋፈል ላይ እያሉ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የዘገበ ሲሆን፣ በኦብነግ በኩል የደረሰ ጉዳት የለም ተብሎአል። ይህንኑ ተከትሎ የአገዛዙ ወታደሮች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑም ተዘግቧል።

ጥቃቱን በተመለከተ በክልሉ መንግስት በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም።

በደቡብ ኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የአርበኖች ግንቦት 7 አባላት የትግል ጥሪ ወረቀቶችን በተኑ።

በትናትናው ዕለት በተቀናጀ መንገድ በአንድ ቀን በተለያዩ ቦታዎችች ተመሳሳይ መልዕልክት ያላቸው በራሪ ወረቀቶች ተበተኑ፤ ጥቂቶችም በግድግዳዎችና ፓሎች ላይ ተለጠፉ።
በሐዋሳ መናኸርያ አካባቢ፣ዩኒቨርስቲ ዋናው ግብ ፊት ለፊት፣ አግሪ ግብ ፊት ለፊት አከባቢ ፣ T T C አካባቢ ፤ በወላይታ ዞን ወላይታ ከተማ አጀፊ አካባቢ፣መናሐርያ አካባቢ ዙርያውን ፣ልጋባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አካባቢ፣ መርካቶ ገበያ አካባቢ ፤ በጋሞ ጎፋ ዞን አርባምንጭ ከተማ ጋሞ አደባባይ አካባቢ ፣ኦሮምያ ባንክ አካባቢ፣ኩልፎ ት/ቤት አካባቢ መንገድ ላይ 03 ባዩሽ ምግብ በት አከባቢ 03 ጤና ጣቢያ አካባቢ መስጅድ አከባቢ ፣ የትራፊክ ፖሎች ላይ ፣ እድገት ቀበሌ ጽህፈት ቤት ግንብ አጥር ላይ ፤ስሆን በኮንሶ ደግሞ መሐል አደባባይ አከባቢ ፣ ገበያ ሰፈር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አካባቢ በላመራ የተሰማሩ ትራፊኮች ላይ በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማ አየር መዳ አከባቢ ፣መነሐርያ አከባቢ ፣ሾላ ሰፈር ፣ ተኮላ ት/ ቤት አከባቢ ስሆን በተጨማሪ በራር ወረቀቶች ደግሞ በወያኔው ጠቅላይ ምንስቴር ኃ/ማሪያም ደሰላኝ የትውልድ አከባቢ በሆነው አረካም ተበትኗል ተግባራዊ ስራም ለሊቱን ተሰርቷል ተግባራዊ ስራውን የሰሩ አባሎቻችንን ለጊዜው ከቦታው ዞር እንዲሉ ተደርጓል።

ሰሜን ኮሪያ የኢትዮጵያን እና የሌሎች አገራትን ባንክ ብርበራ (Hack) ማድረጓ ታወቀ

የሩሲያዉ የሳይበር ጥበቃዉ ተቋም ባወጣዉ ራፖርት ሰሜን ኮሪያ የአገራትን ባንኮች አገራቱ ሳያዉቁ እየበረበረች እንደሆነ አስታወቀ።

ይኸዉ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ተቋም ባወጣዉ ራፖርት ናይጄሪያ፤ ኢትዮጵያ፤ ጋቦን፤ ኢራቅ፤ ኬንያ እና ሌሎች 13 አገራትን ያካተተ ብርበራ ማድረጓን አያይዞ ገልጿል። የሳይበር ደህንነት ተቋሙ በ18 አገሮች ላይ ሰሜን ኮሪያ ሙከራ ማድረጓን ሲገልጽ በሁለት ኢንተርናሽናል ኤክስፐርቶች በተገኘዉ መረጃ መሠረት ምን አልባትም ይህንን በማጭበርበር የምታገኘዉን ገንዘብ ለኒዩክለር አላማ ልታዉለዉ እንደምትችል እምነት አሳድረዋል።

ባንኮችና የደህንነት ተቋማት አጥኝዎች ከዚህ በፊት አራት (4) የዚሁ አይነት ተመሳሳይ የሳይበር ሙከራዎች በባንግላዴሽ፤ ኢኳዶር፤ በፊሊፕን እና በቬትናም የፋይናንስ ተቋማት ላይ ሙከራ ተደርጎ እንደነበርም አስረድተዋል።

ካስፐርስኪ የተባለዉ የሩስያ የሳይበር ደህንነት ተቋም ላዛረስ በሚል መጠሪያ ተመሳሳይ የሆነ የኮስታሪካን፤ የኢትዮጵያን፤ የጋቦንን፤ የኢንዲያን፤ኢንዶኔዢያ፤ የኢራቅ፤ የማሊዢያ፤ የኬንያ፤ የናይጄሪያ የፖላንድ፤ የታይዋን እና ኡራጓይ የፋይናንስ ተቋማትን ብርበራ እንደተደረገም ደርሰዉበታል።

ካስፐርስኪ ብርበራ መደረጉን የሚያሳይ ዱካ ካገኘ በኋላ ባደረገዉ ክትትል ከሰሜን ኮሪያ ጋር ንክኪ ያለዉ ነገር ማግኘቱን ተከትሎ በግሩፕ ላዛረስ በሚል መጠሪያ እንድሚንቀሳቀስም የአለም አቀፉ የፕሬስ ትብብር ባለፈዉ ማክሰኞ ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።

እንደ ሪፖርቱ ገለፃ ከሆነ እነዚሁ የፋይናንስ ተቋማትን ሚበረብሩት ቡድኖች የመጀመሪያ ብርበራቸዉን የጀመሩት ፈረንሳይ ዉስጥ ባለ የኮምፒዩተር አገልግሎት መስጫ ሲሆን በሰሜን ኮርያ እና በታይዋንም ማድረጋቸዉ በቀላሉ ፈልጎ ለማግኘት እንዳልተቻለ እና በተለያየ ቦታ መደረጉ የችግሩ መነሻን ለማግኘት አስቸጋሪ እንዳደረገባቸዉ ኤክስፐርቶቹ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ላዛረስ የሚባለዉ ይኸዉ ግሩፕ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የዚህ አይነት ጥቃት የጀመረዉ በ2015 እ.ኤ.አ እንደሆነ ጥናትና ምርምር የሚያደርገዉ BAE systems, FireEye and Symantec. የሚባለዉ ተቋም አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮች ከሰሜን ኮሪያ መንግስት ጋር ንኪኪ ላላቸው ዘራፊዎች መጋለጣቸው ተዘገበ

በጎንደር ከተማ ትናንት የተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ዝርዝር ደርሶናል

ትናንት ለሊት 10:20 ሲሆን ኮሎኔል አጠና ተፈራ በተባለው የወያኔ አመራር ላይ በጎንደር ከተማ በቀበሌ 18 በሚገኘው መኖሪያ ቤት በቦንብ ተጠቅቷል። ይህ ሰው ለህወሓት አገልጋይ በመሆን እስከ ኮኔሪል ማዐረግ የደረሰ ከዚያም በ20008 ዓ/ም በነበረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ ጎንደር ተመድቦ በርካቶችን የገደለ ትዕዛዝ በመስጠት ያስገደለ በሐምሌ 05/2008 በነበረዉ እንቅስቃሴ ሲሳይ ታከለ እና ሰጠኝ ባብል የተባሉትን ባላሃብቶች የገደለውን አለቃ ይህንስ የተባለውን የህወሃት የደህንነት አባል ከቤቱ በመደበቅ ይህን በደም የተጨማለቀ ወንጀለኛ ከ3 ቀን በሃላ አጅቦ አክሱም አድርሶ ተመልሳል ።

ይህ ሰው በአሁኑ ጊዜ የማራኪ ክፍለከተማ ምክትል አስተዳዳሪ እና የአስተዳደርና ፀጥታ ኅላፊ በመሆን ተሹሞ በርካቶችን ይገድላል ያሰቃያል ለዚህ ሰው እና ለመሰሎቹ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከዕኩይ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ብቦንብ ሊጠቃ ችላል ።

የወያኔን ፀረ-ህዝብ ኃይል እንበትነዋለን፡፡

%d bloggers like this: