በእስር ቤት ለወራት ታስረው የሚገኙ የነጻነት ታጋዮች ለችግር ታድርገዋል

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉና የእስረኞችን ሁኔታ የሚከታተሉ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ለመብታቸው በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ገብተው ሲታገሉ የነበሩ፣ በግላቸው በአገሪቱ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲያጋልጡ እንዲሁም በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማርተው ለአገራቸው የሚችሉትን መስዋትነት በመክፈል ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ከሚደርስባቸው ስቃይ በተጨማሪ፣ መሰረታዊ የሚባሉትን ልብስ እና ጫማዎችን ለመቀየር አልቻሉም።
ከአማራ እና ኦሮምያ አካባቢ የመጡ እስረኞች በተለዬ ለከፍተኛ ስቃይ መደረጋቸውን የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ተብሎ ሊፈረጅ የሚችል ነው ይላሉ። ከሰሜን ጎንደር የመጡ እስረኞች አብዛኞቹ እየታመሙ እየወደቁ ነው የሚሉት ታዛቢዎች፣ አቶ አንጋው ተገኝ በደረሰበት ድብደባ መስማት እንደተሳነው ፣ አባይ ዘውዱም በልብና በጉበት በሽታ እየተሰቃየ መሆኑን ገልጸዋል።
ቅያሬ ልብስ አጥተው የሚቸገሩ በርካታ እስረኞች እንዳሉ የሚገለጹት እነዚሁ ወገኖች፣ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሰዎቹን በህይወት እያሉ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የአርበኖች ግንቦት 7 አባላት የትግል ጥሪ ወረቀቶችን በተኑ።

በትናትናው ዕለት በተቀናጀ መንገድ በአንድ ቀን በተለያዩ ቦታዎችች ተመሳሳይ መልዕልክት ያላቸው በራሪ ወረቀቶች ተበተኑ፤ ጥቂቶችም በግድግዳዎችና ፓሎች ላይ ተለጠፉ።
በሐዋሳ መናኸርያ አካባቢ፣ዩኒቨርስቲ ዋናው ግብ ፊት ለፊት፣ አግሪ ግብ ፊት ለፊት አከባቢ ፣ T T C አካባቢ ፤ በወላይታ ዞን ወላይታ ከተማ አጀፊ አካባቢ፣መናሐርያ አካባቢ ዙርያውን ፣ልጋባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አካባቢ፣ መርካቶ ገበያ አካባቢ ፤ በጋሞ ጎፋ ዞን አርባምንጭ ከተማ ጋሞ አደባባይ አካባቢ ፣ኦሮምያ ባንክ አካባቢ፣ኩልፎ ት/ቤት አካባቢ መንገድ ላይ 03 ባዩሽ ምግብ በት አከባቢ 03 ጤና ጣቢያ አካባቢ መስጅድ አከባቢ ፣ የትራፊክ ፖሎች ላይ ፣ እድገት ቀበሌ ጽህፈት ቤት ግንብ አጥር ላይ ፤ስሆን በኮንሶ ደግሞ መሐል አደባባይ አከባቢ ፣ ገበያ ሰፈር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አካባቢ በላመራ የተሰማሩ ትራፊኮች ላይ በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማ አየር መዳ አከባቢ ፣መነሐርያ አከባቢ ፣ሾላ ሰፈር ፣ ተኮላ ት/ ቤት አከባቢ ስሆን በተጨማሪ በራር ወረቀቶች ደግሞ በወያኔው ጠቅላይ ምንስቴር ኃ/ማሪያም ደሰላኝ የትውልድ አከባቢ በሆነው አረካም ተበትኗል ተግባራዊ ስራም ለሊቱን ተሰርቷል ተግባራዊ ስራውን የሰሩ አባሎቻችንን ለጊዜው ከቦታው ዞር እንዲሉ ተደርጓል።

በቅማንትና አማራ ስም ህዝብ ለማፋጀት አዲስ እቅድ ወጣ!

የሰሜን ጎንደርን ህዝብ በቅማንት እና አማራ የማይገቡ ወረዳና ቀበሌዎችን በማካለል የውሸት ሪፈረደምን ተግባራዊ በማድረግ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲያደርጉ እና እነሱም ጣልቃ በመግባት የሚፈልጉትን በግላጭ ለመግደልና ለማሰቃየት እኩይ ተግባሩን በቀላሉ ለማሳለጥ የሚያስችሉ ካድሬዎቹን አሰልጥኖ ስራ አስጀምሯል፡፡ ወያኔ የሚያደርገውን ደም አፋሳሽ አዲስና ተጨማሪ ክለላ ህዝቡ ሆን ተብሎ እንደተቀነባበረ ሊያውቅና እንደበፊት ቀደሙ በከፍተኛ ብልሃት እንዲያልፉት የሚፈጠረውን ችግር እንዲያመክን መልእክቱ በአስቸኳይ ለሁሉም እንዲዳረስ ይሁን።
ይህንን መሰሉን መሰሪ የወያኔ መርዛማ እቅድ ለማሳካት ዛሬ የሰሜን ጎንደር ዞን የፀጥታ አመራሮች ሁሉም ደባርቅ ነበሩ። የፀጥታ አመራሮች፣ የፖሊስና የልዩኃይል ኃላፊዎች አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።
ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ወያኔ የወልቃይት ጥያቄ በተለይ ጎልቶ ሲመጣበት በፍቅርና በአንድነት የሚኖረውን የጎንደርን ሕዝብ እርስ በእርስ ለማፋጀት የቅማንትና የአማራ በሚል ትልቅ አደጋ ማድረሱ ይታወቃል። ይህን መሰሪ ተግባር የጎንደር ህዝብ አንከፋፈልም በማለት ጠንካራ ምላሽ ቢሰጥም ወያኔ በዚህ መርዛማ ተግባሩ ሊቀጥል መወሰኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። በቅርቡ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. የወያኔ ኢምባሲ ለሰበሰቧቸው ካድሬወች ጎንደር ያለውን ከባድ ህዝባዊ ትግል ለማክሸፍ የአማራና የቅማንት አጀንዳን ዳግም እንደሚቀሰቅሱት መረጃው ደርሶን አጋልጠናል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

16114034_379724762420032_2191638666481950464_n

ወሎ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መሃከል ግጭት ተፈጥሮዋል፡፡

wollo university

ግጭቱ ዛሬ ጥዋት እሁድ 14/05/2009 ዓ/ም የጀመረ ሲሆን የፌደራል ፖሊስ ወደ ግቢው ገብቶ ግጭቱ ለመቆጣጠር ቢሞክርም እስካሁን ሊረጋጋው ኣልቻለም። በግጭቱ በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸው እየተገለፀ ነው።
ወሎ ዩኒቨሲቲ ደሴ ግቢ በኦሮሞ እና በትግራይ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት በመፈጠሩ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ኦሮሞ ተማሪዎች መጎዳታቸው እየተነገረ ነው። ግጭቱን ለማብረድ በአሁኑ ስአት ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፖሊስ ወደ ግቢው በመግባት ላይ ይገኛል፡፡
ዛሬ በወሎ ዩኒቨርስቲ በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መካከል የተቀሰቀሰዉ ግጭት መንስኤ ቋንቋ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን። ጠቡን የጀመሩት በቡድን የነበሩ የትግራይ ተማሪዎች ሁለት የኦሮሞ ተማሪዎችን በኦሮሞኛ ለምን ታወራላችሁ በሚል ሲሆን በእነዚህ ተማሪዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ይሄን ተከትሎ የኦሮሞ ተማሪዎች በመሰባሰብ የአፃፋ እርምጃ ለመዉሰድ የሞከሩ ሲሆን ከሁለቱም ብሄር ቁጥራቸው ያልታወቀ ተማሪዎች ከከባድ እስከ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፀቡን የጀመሩት በቡድን የነበሩ የትግራይ ተማሪዎች አስቀድመዉ የተዘጋጁ እንደሚመስሉ የሚያሳዩ ምልክቶች እንደታዩባቸውና ለዚህም የተለያዩ ብረቶችና ስለታማ ነገሮች ከኪሳቸዉ ለማዉጣት ይሞክሩ እንደነበር ታውቋል። ይሄንን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ግቢዉን ተቆጣጥሯል።

 

የ24ተኝ ክ/ጦር መዳከምና የህርዳታ ጩኸት!

ከተመሰረተበት ወቅት አንስቶ ከተመረጡ አራት ማዘዦ ጣቢያዋች በመወርወር የህውሀትን ጸረ-ሽብር ሀይል በመደገፍና ለግንባር ሰራዊት ደጀን በመሆን በመተካካት..በመከላከል..በማጥቃት እና የአካባቢ ጥበቃዋችን በማድረግ የሚሊሻ እንዲሁም የልዩ ሀይልን ከማገዝ በላይ ከላይ የወረዱ ትእዛዛትን በማከናወን ይታወቃል::
በሰሜኑ በኩል ሊፈጠሩ ይችላሉ ከሚባሉ የጦር ትኩሳቶች የተነሳ 24ትኛ ክፍለ ጦርን ለማደራጀት ከፍተኛ የሆነ የሰውና የገንዘብ መጠን ከመከላከያው በጀት በወጥ መልኩ ፈሰስ እየተደረገለት ይገኛል::
ከህዳር 2009 ዓ/ም መጀመሪያ አንስቶ የ 24ትኝ ክ/ጦር የመናጋት አደጋን ምክንያት በማድረግ የክፍለ ጦሩ አዛዦች እና የወታደራዊ ደህንነቱ ከመከላከያ ሚኒስቴር አምራሮች ጋር በብርቱ መክረዋል::
በሰራውቱ ላይ የደረሰው ያለመተማመንና የብሄር ልዩነት ያስከተለው አደጋ እንዳለ ሆኖ የወታደሮች ደሞዝ በወቅቱ ያለመከፈልና ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ አልባሳት መሰል ጥቅማ ጥቅሞችን በተመረኮዘ ከደሞዝ ላይ የሚቆረጡ አግባብነት የሌላቸው የገንዘብ መጠኖች እንዲሁም የወታደራዊ ቅጣቶች እርምጃዋችና የዲሲፕሊን ህጎች ለክ/ጦሩ መዳከም በዋነኛንት ለውይይት ቢቀርቡም ባሉበት እንዲቀጥሉ ተወስኗል::
የክፍለ ጦሩ አባላት ከ2006 ዓ/ም መካከለኛው ግዜ አንስቶ ከጦሩ በመኮብለል በመክዳትና በተደጋጋሚ በተከስቱ የማጥቅትና የመከላከል እገዛ ጦርነቶች ላይ በመመታታቸው በመማረክና በተለያዩ ምክንያቶች የተመናመኑ ሲሆን ክፍተቶችን ለመተካት በተደጋጋሚ የተወሰዱ እርምጃዋች ያልተሳኩና ተመሳሳይ ግድፈቶች እንዳጋጠሙት ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የሰሜኑ እዝ በተደጋጋሚ የ24ተኛ ክ/ጦርን ጩኸት በማስተጋባቱ ምክንያት በመከላከያ ሚኒስትር የወታደራዊ ስምሪት አዛዦች ትእዛዝ ከታህሳስ 2/2009 አንስቶ ከተለያዩ እዞች የተዉጣጡ ውታደሮችን ወደ ምድብ የክ/ጦሩ ቀጠናዋች ተጉዋጉዘዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ በስምሪት ላይ የነበሩ 34 የ24ተኛ ክ/ጦር አባላቶች የገቡበት በመጥፋታቸው ምክንያት አጣብቂኙ ተባብሶ ቀጥሏል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
( ጉድሽ ወያኔ )

%d bloggers like this: