የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ መግለጫ ማውጣቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ለአሜሪካ አምባሳደር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫ ሰራተኞቹ ከአዲስ አበባ ውጪ በምንም አይነት መንቀሳቀስ አደገኛ ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል ብሏል።
እናም በሀገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን የሚሰጡትን መረጃ በመከታተል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋልም ነው ያለው። በኤምባሲው መግለጫ መሰረት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ሰልፎችና ሕዝባዊ አመጾች ድንገት ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ቀውስ ሊባባስ እንደሚችል ነው ያስጠነቀቀው።

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫ መነሻ በማድረግም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ ማሳሰቢያ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአዲስ አበባ ከአሜሪካው አምባሳደር ማይክል ሬይነር ጋር በሀገሪቱ ባለው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተነግሯል።

አቶ ደመቀ አምባሳደሩን በጽሕፈት ቤታቸው ለማናገር የተገደዱት አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳይ በእጅጉ ያሳሰባት በመሆኑ ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በኩል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ ስብሰባ ላይ መሆኑ ይነገራል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለ3 ወራት ወይም ለ6 ወራት ሊደነገግ እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሀላፊነት ተነሱ

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሀላፊነት ተነሱ :: በቅርብም አምባሳደር ሁነው ይሾማሉ ተብለው ይጠበቃሉ። የትምህርት ሚንስትሩ አቶ ጥላየ ጌቴ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት የተሾሙ ሲሆን ደመቀ መኮንንን ደግሞ አለምነው መኮነን እንደሚተካው ተነግራል።

ዶ/ር ይናገር ደሴ የክልሉ ምክትል ፕሬዘዳንት በመሆን ተሹመዋል። አለምነው መኮነን በክልሉ ካቢኔም ሆነ በአማራ ህዝብ የማይወደዱ ሲሆን አዲስ አበባ ወደሚገኘው የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ ተመድበው ተሸኝተዋል።
ሌሎች ዝርዝር መረጃወችን እየተከታተልን እንገልጻለን።በተያያዘ ዜና፦
፨ ኮ/ል ደመቀ እና የወልቃይት ኮሚቴ አባላት ክስ እንዲቆረጥ የተወሰነ ሲሆን በቅርቡ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሰበር ዜና !! ጎንደር ዩኒቨርስቲ ቴድሮስ ካምፓስ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ ፡፡

ጎንደር ዩኒቨርስቲ ቴድሮስ ካምፓስ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ ፡፡
ዛሬ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 7:35 ሲሆን ተማሪዎች ህወሓት እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እና ግዲያ እንዲያቆም ቢጠይቁም ስርዓቱ አስነዋሪ ስራውን በመቀጠሉ እና በሰላማዊ መንገድ የቀረበውን ጥያቄ የህወሓት ወታደሮች በኃይል ለመጨፍለቅ በመሞከራቸው ጉዳዩ ወደ ግጭት አምርቶ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው ፡፡

የከተማው ሕዝብ ተማሪዎችን ከጨፍጫፊው ዘረኛ ህወሓት ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ፡ በሌሎች አካባቢዎች ያለውም የህብረተሰብ አካል ተቃውሞውን በመቀላቀል ላይ ይገኛል፡፡

 

የአብሮነትና አጋርነት ትስስር መገለጫ የስራ ማቆም አድማ ጥሪ ‘’

የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል እየፈፀመ የሚገኘው ህወሃት መራሹ ቡድን በህዝብ ተቃውሞ እየተናጠ በመምጣቱ እስከ ዛሬ ከሚፈፅመው የአጋአዚ ሃይልና የፌደራል ፓሊስ ታጣቂ ሀይል በተጨማሪም በዘር የተመረጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ ህዝብ አሰማርቶ ወደ ህዝብ እንዲተኩሱ በማድረግ ህዝቡን እያስገደለ ይገኛሉ ።
ይሄው ጨፍጫፊ ስርአት ቀን መሽቶ በነጋ ቁጥር በህዝብ እየተወገዘና ተቃውሞ እየገጠመው በመምጣቱ ከፍተኛ ስጋት ላይ መውደቁን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ከመከላከያ ሰራዊቱ የተቀነሱ ወታደሮችን ዳግም እያሰባሰበ እንደሚገኝ ይታወቃል ፡፡ በመሆኑም ይህ ዘረኛ የህወሓት ቡድን ከአሁን ቀደም በሰራው ስህተት የማይፀፀት ይበልጥ ለሌላ ጭፍጨፋና ግድያ እየተዘጋጀ እንደሆነ አሁን ግልፅ ነው ፡፡ በመሆኑም በቅርብ ቀን በሰሜን ወሎ ኃይማኖትን ባዋረደ እና ንፁሀንን በግፍ በአደባባይ በጠራራ ፀሀይ ጨፍጭፏል ፡ ገድሏል ፡ አሁንም እየገደለ ይገኛል ፡፡ በወልዲያ ፡ ቆቦ ፡ ሮቢት ፡ መርሳ ፡ ሀራ እና በሊሎች ከተሞች በግፍ የፈሰሰው የንፁሀን ደም እየተጣራ ይገኛል ፡፡
ዛሬ ጥር 21 ቀን 2010 ዓ/ም ወልዲያዎች ሰው እንዲህ እየተገደለ የምን ስራ ?፡ የምን የንግድ እንቅስቃሴ !
ያለ ነፃነት ምንም ነገር የለም በማለት የስራ ማቆም አድማ መትተው አደባባይ በመውጣት የነፃነት ጥሪ እያስተላለፉ ይገኛሉ ፡፡ በመሆኑም ጥር 23 እና ጥር 24 ቀን 2010 ዓ/ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ በሰሜን ጎንደር ፡ በደቡብ ጎንደር ፡ ባህርዳር እስከ ደጀን ፡ እንዲሁም ከደሴ እስከ ሰሜን ሽዋ ለሁለት ቀን የስራ ማቆም አድማ የተጠራ በመሆኑ ይህን አውቃቹሁ አጋርነታቹሁን እድትገልፁ ይሁን ፡፡
ድል ለሕዝብ !!!
ሕዝብ ያሸንፋል !!!
የሕዝባዊ እንቢተኝነት አስተባባሪ ፡፡

በወልዲያ እና ዙሪያዋ ዳግም አመፁ አገረሸ

ህዝባዊ ንቅናቄው አድማሱን እያሰፋ ነው የወያኔ ህወሀት ስርሀት ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ መሆኑ እየተነገረ ነው።

ጥር 21 ቀን 2010 ዓ/ም ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ ተጀምራል ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን የገለፀ ሲሆን ህወሓትና የእሱ አገልጋዩ ብአዴን ባደረጉት መተናኮል ሕዝብ ተበሳጭቶ እርምጃ መውሰድ ጀምራል ፡

ቀደም ሲል ጨፍጫፊዎችን እነ ህወሓት ይቃወማል እርምጃ ይወስዳል የሚል የተሳሳተ ግምት ይዘን ብአዴንን ብንጠብቀውም ጭራሽ ገዳዩችን ደግፎ መግለጫ መስጠቱ ቁጣውን ቀስቅሶ ብአዴን ሕዝብን ለማፈን እና የህወሓትን መመሪያ ለማስፈፀም የሚጠቀምባቸው ተቃማት ላይ ጥቃት እየተፈፀመ ይገኛል ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ በሮቢት ከተማ ሕዝብን ለመሰብሰብ የሔደው የፊዲሪሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔው ያለው አባተ በሕዝብ ተዋርዶና ያሰበው ሳይሳካ ተባራል ፡፡ በአሁኑ ሳዓት የሕዝብ ቁጣ ጨምራል ቆቦ እና አካባቢው ነገሮች እየተቀያየሩ ይገኛሉ::

በመርሳ ወታደሮች ተሰብስበው በነበረበት ወቅት በተወረወረ ፈንጅ ፩፰ ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፩፮ ወታደሮች ህክምና አግኝተው ከሆስፒታል ሲወጡ፣ ሁለት ወታደሮች ግን በጽኑ ቆስለው ወልድያ ልዩ ክትትል በሚደረግበት ክፍል ውስጥ ተኝተዋል ተብላል።