በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ኢጣሊያ ገቡ

የኢጣሊያ ባህር ኃይል ዳግም በሺ የሚቆጠሩ የጀልባ ላይ ስደተኞችን ማዳኑን አስታወቀ። እንደ ባህር ኃይሉ ከሆነ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከ3000 በላይ ስደተኞችን ከኢጣሊያ የባህር ጠረፍ ተቀብሏል። ከሰሜን አፍሪቃ በኩል እንደመጡ የተነገረዉ አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ ሲሲሊያ መወሰዳቸውም ተነግሯል።

እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ አብዛኞቹ ስደተኞች ከሶሪያ እና ግብፅ ናቸው። ካለፈው ግማሽ ዓመት አንስቶ የኢጣሊያ የባህር ኃይል በርካታ ስደተኞችን መታደግ ግድ ሆኖበታል። የኢጣሊያ መንግሥት ገና በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች በሰሜን አፍሪቃ በኩል አድርገው ወደ አውሮጳ ለመግባት ዝግጁ እንደሆኑ ይገምታል። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አንጄሊኖ አልፋኖ ኢጣሊያ ብቻዋን የስደተኞቹን ጎርፍ መቋቋም ስለማትችል ሌሎች የአውሮጳ ሀገራት እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

ባለፉት ግዝያት አፍሪቃውያን ስደተኞች በሰሜን አፍሪቃ ወደምትገኘው የስጳኝ ወሽመጣዊ ግዛት ሜሊላ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባትን አጥር ጥሰው በብዛት መግባታቸው ይታወቃል። የሜሊላ ፕሬዚደንት ኽዋን ኾዜ ኢምብሮዳ ለአንድ የስጳኛውያኑ ራድዮ፤ ወደ ሜሊላ ለመግባት ከሞከሩት 1000 ስደተኞች መካከል ወደ 400 የሚጠጉ እንደ ቀናቸዉም ተናግረዉ ነበር። ካለፉት አምሥት ወራት ወዲህ ወደ ስጳኛውያኑ ወሽመጣዊ ግዛቶች ሜሊላ እና ሴውታ የገባው ስደተኛ ቁጥር በጉልህ ከፍ ብሎዋል። ጥቅምት የኤርትራ ስደተኞች ያሳፈረች አንዲት ጀልባ ላምፔዱዛ አጠገብ ሰጥማ ከሰወስት መቶ በላይ ስደተኞች ካለቁ ወዲሕ ኢጣሊያ ባሕር ሐይል የባሕር ጠረፎቹን በጥብቅ እየተቆጣጠረ መሆኑ ይታወቃል። ስደተኞቹን ለማዳን ሲል ባለፈው ጥቅምት ወር የተቋቋመው

« ማሬ ኖስትሩም » ወይም ሲተረጎም ባህራችን የተሰኘው ቡድን በየወሩ ዘጠኝ ሚልዮን ዩሮ ወይም በየቀኑ 300,000 ዩሮ እንደሚያወጣ የኢጣልያ መገናኛ ብዙኃን አስታውቀዋል። በዚሁ የማዳን ተግባር በየሳምንቱ በአማካይ አምስት የጦር መርከቦች እና 900 ሰዎች ተሳታፊ ይሆናሉ። የመሀል ቀኝ ዘመም « ፎርሳ ኢጣልያ » እና ፀረ ፍልሰቱ «ሰሜናዊ ሊግ » ፓርቲዎች የውዱን የሰው አድን ተግባር ወጪ የሚሸፍኑት የኢጣልያ ቀረጥ ከፋይ ዜጎች ናቸው በሚል ምክንያት ስደተኞችን ከመስመጥ አደጋ የማዳኑ ተግባር አሁኑኑ እንዲቆም ጠይቀዉ እንደነበር ተዘግቦአል። ኢጣልያ እና ሌሎች ስድስት በሜድትሬንያን ባህር አካባቢ የሚገኙ ሀገራት የአውሮጳ ህብረት በተለይ ስደተኞቹ ለሚገቡባቸው ሀገራት የሚሰጠውን ርዳታ ከፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። የአውሮጳውያኑ 2014 ዓም ከገባ ወዲህ ኢጣልያ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ወደ 22,000 የሚጠጋ ሲሆን፣ አምና በዚሁ ጊዜ ከገቡት ስደተኞች በ10 እጥፍ ጨምሮዋል።

posted by Aseged Tamene

ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤

ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤ ባልና ሚስቱ ራሳቸውን ያጥፉ ወይም ይገዳደሉ አልታወቀም። ይሄ ሁሉ ሲካሄድ የ5 አመት ልጃቸው ወደ ጎረቤት አምልጣ ተርፋለች። ሙሉ ዜናው እነሆ!


NEW MARKET, Md. (WUSA9) — The Frederick County Sheriff’s Office have identified the three people, including an infant, who died after a shooting Wednesday night.

Officials say they are 40-year-old Benyam Asefa, 42-year-old Barbara Giomarelli, and 3-month-old Samuel Asefa. Authorities say that Giomarelli is an Italian citizen and Asefa is an American citizen. Both were scientists and had been working on medical research. According to the LinkedIn profiles, Barbara was a PhDresearcher at University of Maryland and had spent time at the Institute of Marine and Environmental Technology. Benyam, aslo known as Ben was a clinical immunologist who was a contractor supporting research at the National Institute of Allergy and Infectious Diseases and a graduate of McGill University.

The incident happened before 8:50 p.m. in the 6800 block of Woods Court in New Market, Md., officials say.

A five-year-old girl ran to a neighbor’s house and told the neighbors, who called police, according to officials. The girl and neighbor told deputies that the family members may be injured and in need of assistance.

When deputies entered the home they found a 40-year-old male, a 42-year-old woman and a boy less than 1 year old dead inside the home, say officials. Officials tell us that their injuries were consistent with gunshot wounds and that a handgun was found at the scene but that the wounds will have to be confirmed by autopsies.

Officials say the girl was checked by EMS and was not harmed. The girl is now in child protective custody. She hid in the home when the incident occurred.

Police say they are investigating the incident as a murder-suicide confined to one family in one home.

Authorities say the family recently moved from Howard County and bought the house in New Market.

The three family members will be transported to the Medical Examiner’s Office in Baltimore for autopsies.

Source: wusa9.com

posted by Aseged Tamene

የተዘጋው የአሜሪካ መንግስትና የአሜሪካ ምስቅልቅል

የተዘጋው የአሜሪካ  መንግስትና የአሜሪካ ምስቅልቅል

ከ3 ሚሊዮን በላይ ሰራተኞች ክፍያቸውን አያገኙም
800 ሺህ ሰራተኞች ያለ ምንም ካሳ ከስራ ይሰናበታሉ
የአገልግሎት፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ክፉኛ ይጎዳሉ
የሩብ አመቱ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በ0.3 በመቶ ሊቀንስ ይችላል

ባለፈው ማክሰኞ ማለዳ በይፋ የተዘጋው የአሜሪካ መንግስት፣ መቼ እንደሚከፈት እርግጡን መናገር እንደማይቻልና የአገሪቱ ኮንግረስ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ማካሄጃ ገንዘብ የሚገኝበትን መላ ፈልጎ እስኪያገኝና የጋራ መግባባት ላይ እስኪደርስ ድረስ፣ መንግስት እንደተዘጋ መቆየቱ ግድ እንደሚሆን የዋሽንግተን ፖስቱ ዘጋቢ ብራድ ፕላመር ይናገራል፡፡
የአገሪቱ መንግስት መዘጋቱ በይፋ ከተገለጸበት ቅጽበት አንስቶ ጉዳዩ አለምአቀፍ መነጋገሪያ ሆኗል። የመንግስት መዘጋት በዜጎችና በአጠቃላዩ የአገሪቱ እንቅስቃሴ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ያሳድር ይሆን የሚለው ጉዳይ የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡
የአሜሪካ መንግስት መዘጋቱን ተከትሎ በቀዳሚነት የተደመጠው ተያያዥ ዜና፣ ፓንዳ ካም የተሰኘው የአገሪቱ ብሄራዊ መካነ እንስሳት መዘጋቱ ነበር፡፡ ይሄን የሰሙም ታዲያ፣ ነገሩ የእንስሳቱን ኑሮ ከማመሳቀል አልፎ፣ ይሄን ያህል የከፋና ዜጎችን የሚጎዳ መስሎ አልታያቸውም ነበር፡፡ የዋሽንግተን ፖስት ዘጋቢው ብራድ ፕላመር ግን ጉዳዩ ከዚህም የባሰ የከፋ ተጽዕኖ ያሳድራል ባይ ነው፡፡ እሱ እንደሚለው የተዘጋው መንግስት ፈጥኖ ካልተከፈተ ገና ብዙ ቀውስ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ብራድ ፕላመር ነገርየው የሚያሳድራቸውን ከፉ ተጽዕኖዎች በዝርዝር ዳሷቸዋል፡፡
ጉዳዩ በአፋጣኝ የሚያሳድረው ትልቁ ተጽዕኖ፣ የአገሪቱን ሰራተኞች ሰለባ እንደሚያደርግ ነው ዘጋቢው የሚናገረው፡፡ እሱ እንደሚለው፣ የአገሪቱ ኮንግረስ አፋጣኝ መፍትሄ ካልፈለገና መንግስት እንደተዘጋ የሚቆይ ከሆነ፣ ከ 2 ሚሊዮን በላይ የአገሪቱ የፌዴራል ሰራተኞች የሚገባቸውን ክፍያ በወቅቱ አያገኙም፡፡ 800 ሺህ ያህሉ ደግሞ ምናልባትም የሰሩበት ገንዘብ ሳይከፈላቸው ያለምንም ካሳ ባዶ እጃቸውን ወደቤታቸው ሊሸኙ ይችላሉ፡፡
የኢኮኖሚክስ ባለሙያው ማርክ ዛንዲ እንደሚሉት፣ በርካታ ሰራተኞች ከስራ መሰናበታቸው በአገሪቱ የመጨረሻ ሩብ አመት አጠቃላይ የምርት እድገት ላይ 0.3 በመቶ ቅናሽ ይፈጥራል፡፡ ከአገሪቱ ሰራተኞች አብዛኞች የሚገኙባት ሜሪላንድም፣ በየቀኑ በገቢና በሽያጭ ታክስ መልኩ ትሰበስብ የነበረውን 5 ሚሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ ታጣለች፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፡፡ የአገሪቱ ተቋራጮችም እንቅስቃሴያቸው መገታቱን ተከትሎ ሰራተኞቻቸውን በገፍ ይቀንሳሉ፡፡ ይህም ተጨማሪ ቀውስ መፍጠሩ አይቀሬ ነው ተብሏል፡፡
የአገሪቱ የነባር ሰራተኞች ጉዳይ ባለስልጣናት፣ ነገሩ ክፉኛ አሳስቧቸው ለኮንግረሱ ስጋታቸውን እንደገለጹ ተነግሯል፡፡ ባለስልጣናቱ መንግስት ከሁለት ሳምንታት በላይ እንደተዘጋ የሚቆይ ከሆነ፣ ለአካል ጉዳተኞች ወይም ለጡረተኞች የሚሰጡት ቤሳቤስቲን ሳንቲም እንደማይኖራቸው አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ደግሞ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ 3 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን የቀድሞ ሰራተኞችን ተጠቂ ያደርጋል፡፡
ባለስልጣናቱ ከኮንግረሱ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ አብዛኞቹ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ህይወታቸውን የሚመሩት ከመንግስት በሚያገኙት ድጎማ በመሆኑና ቀድመው እንዲዘጋጁ መረጃ ስላልተሰጣቸው ጉዳታቸው የከፋ እንደሚሆን አሳስበዋል፡፡
የአገሪቱ የጤናና የሰብዓዊ አገልግሎቶች ዲፓርትመንትም ጉዳዩ መላ እንዲበጅለት አበክሮ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ዲፓርትመንቱ እንደሚለው፣ የበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል የተባለው ድርጅት አመታዊውን የወቅታዊ ኢንፍሉዌንዛ ፕሮግራም ስራውን ለመስራት ሲዘጋጅ በተከሰተው የመንግስት መዘጋት ሳቢያ ስራውን ለማከናወን ተቸግሯል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ድርጅቱ ለተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር በሚል ለመንግስትና አጋር አካላት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማቆም እንደሚገደድ አሳውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በወረርሽኝ ፍተሻ፣ ቤተ-ሙከራ ድጋፍና በሃያ አራት ሰዓት የድንገተኛ ህመም ህክምና አገልግሎት ዘርፎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎትም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ገልጧል፡፡
የአሜሪካ መንግስት መዘጋት ከሚያሳድራቸው የከፉ ተጽዕኖዎች መካከል የሚመደበው ሌላው ነገር ደግሞ፣ የአገሪቱ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አብዛኛዎቹን የምግብ ዋስትና ስራዎች ሊያቋርጥ መገደዱ ነው፡፡ ስራቸውን ለማቋረጥ ይገደዳሉ ተብለው የተጠቀሱት ሌሎች ተቆጣጣሪ አካላትም አሉ፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ የአየር ብክለትና የጸረ ተባይ መድሃኒቶች አጠቃቀም ቁጥጥሩን፣ የስራ ዲፓርትመንትም የክፍያና የስራ ሰዓታት ወይም የሰራተኞች ደህንነት ህጎችን በአግባቡ ተግባራዊ የማድረግ ስራውን ማቋረጣቸው አይቀሬ ነው እየተባለ ነው፡፡ እነዚህና ሌሎች መሰል ተቆጣጣሪ አካላት ስራ በፈቱበት ሁኔታ፣ የአገሪቱ እንቅስቃሴ ጤናማ ይሆናል ብሎ ማሰብ አይቻልም ይላል- የዋሽንግተን ፖስቱ ዘጋቢ፡፡
የአገሪቱ የግብርና ዲፓርትመንትም መንግስት ተዘግቶ በሚቆይባቸው ጊዜያት ሴቶች፣ ጨቅላዎችና ህጻናት ጤናማ ምግብ እንዲያገኙ የሚያደርገውን የገንዘብ፣ የመረጃና የጤና ክብካቤ አገልግሎት ድጋፍ ፕሮግራሙን ሙሉ ለሙሉ ያቋርጣል፡፡ በአገሪቱ የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 9 ሚሊዮን እንደሚደርስም ዘገባው ያሳያል፡፡ ከፌደራል ድጋፍ የሚደረግላቸው ፕሮግራሞችም ቢሆኑ ከአንድ ሳምንት የዘለለ እድሜ ሊቆዩ እንደማይችሉ ተነግሯል፡፡
ለአነስተኛ የንግድ ተቋማት የሚደረገው የፋይናንስ ድጋፍና አቅርቦት ሌላው የችግሩ ሰለባ እንደሚሆን የተቀሰው ዘገባው፣ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባለፉት አራት አመታት ከ 193 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አነስተኛ የንግድ ተቋማት 106 ቢሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ በብድር መልክ መስጠቱን ያስታውሳል፡፡ የሰሞኑ ክስተት ግን ይሄን የገንዘብ አቅርቦት ፈተና ላይ ይጥለዋል እየተባለ ነው፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተሰራ ጥናት፣ አመታዊ ገቢያቸው ከ5 ሚሊዮን ዶላር በታች ከሆነ መሰል የአገሪቱ ተቋማት 41 በመቶ የሚሆኑት ሁኔታው ከሶስት ወራት በላይ የሚቀጥል ከሆነ ሰራተኞቻቸውን ለመቀነስ እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡
ሌላው ከአሜሪካ መንግስት መዘጋት ጋር ተያይዞ ተጎጂ ከሚሆኑ ዘርፎች መካከል እንደሆነ በዘገባው የተጠቀሰው የአገሪቱ የቱሪስት ንግድ ዘርፍ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአገሪቱ ብሄራዊ ፓርኮች አገልግሎት ታዋቂዎቹን ዮስማይት፣ ግራንድ ካንዮን፣ አልካትራዝና የኒዮርኩን የነጻነት ሃውልት ጨምሮ ከ400 በላይ ብሄራዊ ፓርኮችን፣ ሙዚየሞችንና የቱሪስት መዳረሻዎችን ለመዝጋት እንደተገደደ ተነግሯል፡፡ ቱሪስቶችም ወደመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡ በቱሪዝሙ ዘርፍ የሚፈጠረው ቀውስ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያደርስ የገለጸው ዘገባው፣ እ.ኤ.አ በ1995 በተከሰተው ተመሳሳይ የአገሪቱ መንግስት መዘጋት 7 ሚሊዮን ያህል ጎብኝዎች ወደመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን ያስታውሳል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ኮንግረስ ምርምር አገልግሎት መረጃ እንደሚያሳየው፣ ክስተቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውና አየርመንገዶች በየቀኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ያሳጣቸዋል፡፡
በዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ላይ እንደተጠቀሰው፣ በአገሪቱ አነስተኛ ገቢ ላላቸው 1 ሚሊዮን ያህል ህጻናትና ቤተሰቦቻቸው የትምህርት፣ የጤና፣ የምግብና የሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡ 1ሺህ ስድስት መቶ ያህል ፕሮግራሞች አሉ፡፡ እነዚህ ፕሮግራሞችም ታዲያ የመንግስትን መዘጋት ተከትሎ ቀስበቀስ ራሳቸውን መዝጋታቸው አይቀሬ ነው ተብሏል፡፡ ለነገሩ አሁንም ተጀምሯል፡፡ በኒዮርክ ካውንቲ መሰል አገልግሎት የሚያገኙ 864 ያህል የቅድመ አጸደ ህጻናት ተማሪዎች ትናንት ትምህርታቸውን አቋርጠዋል፡፡
ከመንግስት መዘጋት ጋር ተያይዞ ስጋት ውስጥ ከወደቁ ነገሮች መካከል ሌላው ደግሞ፣ የማህበራዊ ደህንነት አገልግሎት ነው፡፡ የአገሪቱ የማህበራዊ ደህንነት አስተዳደር ከአካል ጉዳተኞች የሚቀርቡ የድጋፍና ጥቅማጥቅም ጥያቄዎችን ተቀብሎ በአግባቡ የሚያስተናግድ በቂ ሰራተኛ ሊኖረው አይችልም ተብሏል፡፡ የቀድሞ ሰራተኞች የሚያቀርቧቸውን አቤቱታዎች ተቀብሎ የሚያስተናግደው ቦርድ የሚዘጋ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ይህም ከአካል ጉዳተኝነት ድጋፍና ጥቅማጥቅሞች ጋር በተያያዘ አቤቱታ ያቀረቡ የቀድሞ ሰራተኞች ውሳኔ ለማግኘት፣ የመንግስት ወቅታዊ ጉዳይ እልባት እስኪያገኝ እንዲጠብቁ ግድ ይላቸዋል፡፡
የአሜሪካ ብሄራዊ የጤና ኢንስቲቲዩትም ነገሩ መላ ይባል እያለ ነው፡፡ የተዘጋው ነገር አንዳች መፍትሄ ካላገኘ፣ የራሱን እርምጃ እንደሚወስድ ተቋሙ በይፋ ተናግሯል፡፡ መንግስት በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ በህክምና ምርምር ማዕከሉ አገልግሎት ሲሰጣቸው የነበሩ ታካሚዎችን ሳያጋግሙ ከአልጋ ለማስወረድ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል፡፡ የካንሰር ታማሚ የሆኑ ህጻናትን ጨምሮ፣ በየሳምንቱ በአማካይ 200 ታካሚዎችን ያለ ጊዜያቸው ሳያገግሙ እንደሚያሰናብት በመግለጽ፡፡
ለአገሪቱ መንግስት መዘጋት አንዳች መላ ካልተዘየደለት የሚደርሰው ምስቅልቅል መልከ ብዙ እንደሚሆን የሚናገረው የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ፣ ብሄራዊ የጤና ኢንስቲቲዩት ለህክምና ሙከራዎች አዳዲስ ታማሚዎችን መቀበል ሊያቆም እንደሚችል ይጠቁማል፡፡ የመሬት አስተዳደር ቢሮም በህዝብ ቦታዎች ላይ የነዳጅ ዘይት ፍለጋ ለሚያከናውኑ ኩባንያዎች ፍቃድ መስጠቱን ሊያቋርጥ እንደሚችል፣ ልዕለ ሃያሏን አሜሪካ፣ ኢኮኖሚዋንና ህዝቦቿን፣ አልፎ ተርፎም ተስፋ አድርገው የተጠጓትን ስደተኞች ክፉኛ የሚጎዱ ብዙ፣ እጅግ ብዙ ነገሮች ሊሆኑ እንደሚችሉም ያትታል፡፡

addis admas

posted by Aseged Tamene

ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ! ጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል

dola-indidis

የየሱስ ክርስቶስ ክስ፣ ፍርድና ሞት ተገቢው የሕግ አሠራር የተከተለ አይደለም፤ ጉዳዩም እንደገና መታየት አለበት በማለት ኬኒያዊው ጠበቃ ዶላ ኢንዲዲስ ሔግ ለሚገኘው ዓለምአቀፉ ፍርድቤት ክስ ማሰማቱን ጀሩሳሌም ፖስት ኬኒያ የሚታተመውን ናይሮቢያን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የቀድሞ የኬኒያ ፍርድቤት አፈቀላጤ የነበረው ይኸው ጠበቃ በወቅቱ የሮም ቄሣር የነበረውን ጢባሪዮስ ቄሣር፣ ጲላጦስን፣ የአይሁድ መሪዎችን፣ ንጉሥ ሔሮድስን፣ የአሁኑን የጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል፡፡

“ማስረጃው በመጽሐፍቅዱስ ላይ ይገኛል፤ ይህንን ደግሞ ማንም ሊክድ አይችልም” የሚለው ጠበቃ የሱስ በወቅቱ ተገቢውን ፍርድ እንዳላገኘ ጉዳዩም በትክክል በፍርድ ሒደት ውስጥ እንዳላላፈ ጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ ሁለት ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁን ያሉት የጣሊያንና የእስራኤል መንግሥታት በዚያን ጊዜ (በስቅለት) የነበረውን የሮም ህግጋትን አሁንም በሕጋቸው ውስጥ በተግባር እየተረጎሙ ስለሆነ ተጠያቂ ናቸው ብሏል፡፡

ክሱን የማቀርበው የየሱስ ወዳጅ (ጓደኛ) በመሆን ነው ያለው ጠበቃ አስቀድሞ ለኬኒያ ከፍተኛ ፍርድቤት ተመሳሳይ ክስ አቅርቦ ውድቅ በመደረጉ ጉዳዩን ወደ ለዓለምአቀፉ ፍ/ቤት መውሰዱ ተጠቁሟል፡፡

በወቅቱ ተገቢው ምርመራና የፍርድ አሠራር እንዳልተፈጸመ የተናገረው ጠበቃ በቦታው የነበረ “ተፍተውበታል፣ በበትርና በጡጫና በጥፊ መትተውታል፣ አሠቃይተውታል በመጨረሻም ላይ ሞት እንደሚገባው ፈርደውበታል” የሚለው ጠበቃ ኢንዲዲስ የሱስ እንዲናገር እንኳን ዕድል እንዳልተሰጠው ተናግሯል፡፡

ስለ ጉዳዩ እንደሚያውቁ የተጠየቁ አንድ የዓለምአቀፉ ፍ/ቤት ኃላፊ ሲመልሱ “ፍርድቤቱ ይህንን ክስ የማየት ሥልጣን የለውም፤ ፍ/ቤቱ የሚመለከተው በመንግሥታት መካከል የሚከሰት ክርክርና ክስ ነው፤ ይህንን ክስ ለመመልከት በጽንሰሃሳብ ደረጃ እንኳን የማይቻል ነው” በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡

ጠበቃ ኢንዲዲስ ግን ተገቢና ትክክለኛ ክስ እንዳቀረበ በእርሱ የሕይወት ዘመንም ፍትህ ተፈጽሞ ለማየት እንደሚበቃ ያለውን ተስፋ ተናግሯል፡፡

በጌትሰማኒ የመጨረሻውን ጸሎት ኢየሱስ ካደረገ በኋላ የሮም ወታደሮችና የካህናት አለቆች መጥተው በያዙት ጊዜ በሁኔታው ህገወጥነት የተናደደው አንደኛው ደቀመዝሙር (ጴጥሮስ) በሰይፉ የአንዱን አገልጋይ ጆሮ ቆርጦ ነበር፡፡ የጴጥሮስን ድርጊት የተቃወመው የሱስ ሲመልስ አስፈላጊ ከሆነ “12 ሌጊዮን (ከ60ሺህ – 90ሺህ) መላዕክት” በቅጽበት በማዘዝ ራሱን መከላከል ይችል እንደነበር መናገሩን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል፡፡ (ማቲዎስ፡26፤53)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

posted by Aseged Tamene

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ቁጥር በ7 ሚሊዮን መቀነሱን አምናለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ቁጥር በ7 ሚሊዮን መቀነሱን ቀደም ብላ በ2002 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያኗ በይፋ አምናለች፡፡ “ኤጲስ ቆጶስ ጠባቂ ነውና ይጠብቅ ተብሏል። እንደ ተባለው መንጋው ተጠብቋል ወይስ አልተጠበቀም? መንጋው አልተጠበቀም የሚለው መልስ እንደሚጎላ ግልጽ ነው። ይህንንም የሚያሳየው ያለፈው ዓመት የሕዝብ ቈጠራ ነው። መንጋው በትክክል ከተጠበቀ 7,000,000 (ሰባት ሚሊዮን) ያህል ሕዝበ ክርስቲያን ለምን ቀነሰ? ይህን ያህል መንጋ በመናፍቃን ተሰርቋል ወይም ወደ ሌላ ሃይማኖት ተወስዷል ማለት ነው።” (የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 17ኛ ዓመት የፓትርያርክነት በዓለ ሲመት 2002 ገጽ 34)።

ቤተክርስቲያን እንዲህ ስትል በአንድ ወገን መንጋው አለመጠበቁንና በዚህ ምክንያት መሰረቁን አምናለች፡፡ በሌላ በኩል ግን ሌሎች ሰረቁኝ ወሰዱብኝ ከማለት ባለፈ ምክንያቱን በሚገባ ያጤነችው አይመስልም፡፡ ሌሎች በውጪ አግኝተው ከወሰዷቸው በላይ እንደማኅበረ ቅዱሳን ያለ የወንድሞች ከሳሽና አክራሪ ቡድን እኔን አልመሰላችሁምና መናፍቃን ሆናችኋል በሚል በህገ ወጥ መንገድ ያሳደዳቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ምናልባት ለቁጥሩ መቀነስ የማቅ እጅም እንዳለበት መታመን አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ለወንድሞች ከሳሽ ለማቅ ይህ እንደሃይማኖተኝነት የሚቆጠር ትልቅ ገድል ነው፡፡ ማኅበሩ በዚህ ድርጊቱ ከማፈር ይልቅ “ቤተክርስቲያንን ከመናፍቃን እየጠብቅኩ ነው፡፡ እኔ ባልኖር ይህች ቤተክርስቲያን ትጠፋ ነበር” እያለ በመለፈፉ ብዙዎች ማቅን እንደቤተክርስቲያን ጠበቃ ያዩታል፡፡ ቢያስተውሉት ግን ይህ ቤተክርስቲያንን ሰው አልባ እያደረገበት ያለ የማቅ አጋንንታዊ ስራ ነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ 7 ሚሊዮን ምእመናን የጎደሉት ማቅ እኔ እየጠበኳት ነው እያለ አሳዳጅነቱን እንደ ገድል በሚያወራበት ዘመን ላይ መሆኑ ነው፡፡
ታዲያ በማቅ ዘመን ቤተ ክርስቲያን አተረፈች? ወይስ ከሰረች? ሌላው ቢቀር እንኳን 7 ሚሊየን አማኞቿን ያጣችው ማቅ ለቤተክርስቲያን ዘብ ቆሜያለሁ እያለ በሚፎክርበት ዘመን መሆኑ ማቅ ቤተክርስቲያንን እያፈረሰ ለመሆኑ አንዱ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ማቅ የቤተክርስቲያን ያልሆኑ ትምህርቶችን እያቀረበና ወንጌል እንዳይሰበክ እየተቃወመ ቤተክርስቲያንን የያዘበት ዘዴ ለጊዜው እንጂ ሰውን የሚያሳርፍና በቤተክርስቲያኑ የሚያጸና አይደለም፡፡ ስለዚህ ከአባላቱ ብዙዎቹ እንኳ እየከዱት ይገኛሉ፡፡ እርሱ ግን ቆም ብሎ ራሱን ከመመርመር ይልቅ በወግና በልማድ ተተብትቦ ማሳደዱን ቀጥሏል፡፡
ማቅ በዚህ ማሳሳቻው የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እየከሰሰና ተጠርተው ሳይጠየቁ በአንድ ወገን ክስ ብቻ ህገ ወጥ ውግዘት ሲያስተላልፍ እንደኖረና አሁንም ሌሎችን ለማስወገዝ እየተራወጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ስንት ሊቃውንት እንዳላላፉባትና ትምህርቷ መጽሀፍ ቅዱሳዊ እንዳልነበረ ዛሬ ግን ሰው የሌለባት የምትመስለው ቤተክርስቲያን እውነተኛ ልጇችንና ሊቃውንቷን የምታወግዘው በአብዛኛው የስህተት ትምህርት ተገኝቶባቸው አይደለም፡፡ ቀደም ያሉት ሊቃውንት እንደዋና ትምህርት በማይቆጥሩትና በልማዳዊ ትምህርትነት በፈረጁት ማቅ ግን እንደ ትልቅ ዶክትሪን በተቀበለውና በሚመራበት የአዋልድ መጻህፍት ትምህርት መሰረት መሆኑ ደግሞ ቤተክርስቲያኗ ከትናንት ይልቅ ዛሬ ይዞታዋ እየወረደ መምጣቱንና ከቅዱሳት መጻህፍትና ከአበው ምስክርነት እየራቀች መምጣቷን ያሳያል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ማቅ የሚያቀርበው ክስ በእውቀት ተፈትሾ ሳይሆን በግፊት እንዲያልፍ መደረጉ ማቅ ያቀረበው ሁሉ ትክክለኛ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ደግሞ ስህተት እየተባለና በሲኖዶስ እየተወገዘ መምጣቱ ቤተክርስቲያን መራቆቷን ያሳያል፡፡
ባለፈው ግንቦት የተላለፈው ውግዘት ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ እስካሁን በተከታታይ እያወጣን ያለነው በውግዘቱ ላይ የተመሰረተ ሀተታም ይህንኑ ያሳያል፡፡ ሲኖዶሱም እውነትን አውጋዥ ሐሰትን አንጋሽ መሆኑ ለቤተክርስቲያኗ ትልቅ አደጋ ነው፡፡ ውድቀቷንም ያፋጥነዋል፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ቆም ብላ ነገሮችን መመርመር አለባት፡፡
የወንድሞች ከሳሽ ማቅ ለእርሱ ያልተመቹትን ሁሉ መናፍቅ የሚል ስም እየሰጠ በርካቶችን ከእናት ቤተ ክርስቲያናቸው እንዳፈናቀለና አሁንም ለማፈናቀል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በ22/5/05 ለጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ባቀረበው ክስ በጀርመን አገር በቪዝባደን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቄስ ገዳሙ ደምሳሽ እንዲወገዙለት የጠየቀበትና የአውግዙልኝ እንቅስቃሴ የጀመረበት ደብዳቤ ከእጃችን ገብቷል፡፡
ቄስ ገዳሙን ለመክሰስ ማቅ ያቀረባቸው ሶስት ማስረጃዎች መሆናቸው የክሱ ደብዳቤ ያሳያል፡፡ የመጀመሪያው በቄስ ገዳሙ ደምሳሽ የተጻፉ ሶስት የኑፋቄ መጻህፍት አጭር መግለጫ 9 ገጽ የሚል ነው፡፡ የቄስ ገዳሙን መጻህፍት ገና ከመነሻው የኑፋቄ መጻህፍት ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸው በሊቃውንት ጉባኤ መች ተረጋገጠ? ማንኛውንም ጉዳይ ኑፋቄ ማለት የማቅ የተለመደ ክስ ነው፡፡ እስካሁን ከታየው ለማረጋገጥ እንደተቻለው የማቅ ክስ ቅዱሳት መጻህፍት በአዋልድ መጻህፍት መታረም አለባቸው የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ኑፋቄ አለ? ከማቅ በላይስ መናፍቃዊ ድርጅት የት አለ? ነገር ግን ቤቱ ሰው የሌለበት የተፈታ ቤት ስለሆነ መናፍቃን ይከበሩበታል፤ እውነተኞች ይወገዙበታል፡፡
የቄስ ገዳሙ መጻህፍት ኑፋቄ የተባሉት በምን ሚዛን ነው? ለማቅ አስተምህሮ ስላልተስማሙ ነው ወይስ እንደተባለው ኑፋቄ ስለተገኘባቸው? ይህን የሚያረጋግጠው ማነው? ማቅ ነው ወይስ የሊቃውንት ጉባኤ? የሊቃውንት ጉባኤው ከማቅ ተጽእኖ ነጻ ሆኖና በራሱ በመተማመን ይሰራል ወይ? ከግንቦቱ ሲኖዶስ ልምድ ስንነሳ ግን ማቅ ያቀረበው ክስ በቅዱሳት መጻህፍትና በቤተ ክርስቲያኗም መሰረታዊ አስተምህሮ ሳይመረመር በግልብ ስሜት በመነዳት ነው ውግዘቱ የተላለፈው፡፡ ዛሬም አዲስ ነገር አይኖርም፡፡ ሁሉም እንደተጻፈለት ይኖራል፡፡ ማቅ ቄስ ገዳሙ ትክክለኛና ሕይወት የሚገኝበትን ወንጌል ስላስተማሩ መናቅፍ ይላቸዋል፤ ያሳድዳቸዋል፡፡ ቄስ ገዳሙም ከኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ሳይወጡ ለክርስቶስ ወንጌል ዘብ ስለቆሙ መናፍቅ ይባላሉ ይሰደዳሉ። “በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።” (2ጢሞ. 3፡12)፡፡ ክሱ በዚህ መንገድ የመጣና በሌላ ወንጀል ባለመሆኑ ለቄስ ገዳሙ ትልቅ እድል ነው፡፡
ሁለተኛው የክስ ነጥብ “የሦስት መቶ ሰላሳ አምስት ምእመናን ፊርማ የያዘ ማመልከቻ”የሚል ነው፡፡ በቅድሚያ በአድማና በምእመናን ፊርማ አንድ ቄስ መናፍቅ ይባላል ወይ? አድማውን ያስተባበሩትና ፊርማውን ያሰባሰቡት የማቅ ሰዎች ቢሆኑስ? የሃይማኖት ጉዳይ በሃይማኖት ትምህርት እንጂ በምእመናን ፊርማ የሚታየውስ ከመቼ ጀምሮ ነው? በመጀመሪያ አድመኝነት የሥጋ ስራ አይደለም ወይ? ዳሩ ይህ በማቅ ሰፈር መች ይታወቃል!
ሶስተኛው የክስ ማስረጃ ደግሞ፣ “የምእመናንን ቁጣ የሚያሳይ የምስልና የድምጽ ዝግጅት 1 ሲዲ” ነው፡፡ ይህም ከሁለተኛው ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ከአድማ ጋር የተያያዘ እንጂ ሃይማኖታዊ ይዘት የለውም፡፡ ምናልባት በቪሲዲው ላይ የተባሉት ምእመናን የተቆጡት በሃይማኖት ጉዳይ ነው ቢባል እንኳን አሁንም መንፈሳዊነት የጎደለው ነው፡፡ ቁጣ የሥጋ ስራ ነው፡፡ የሃይማኖት ትምህርት እንጂ ቁጣ ለመናፍቅነት ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየው ማቅ በቄስ ገዳሙ ላይ የሚያስወገዝ ማስረጃ ሊያገኝላቸው አለመቻሉንና በሌሎች ላይ ሲያደርግ እንደነበረው ፊርማ በማሰባሰብና ቁጣን በማነሳሳት ትክክለኛ የቤተክርስቲያን አባቶችን የማሳደድ ተግባሩን እንደገፋበት ነው፡፡
እንደ ቄስ ገዳሙ ያሉና ሰው ከቤተክርስቲያኑ እንዳይወጣና ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት በእናት ቤተክርስቲያኑ ሆኖ እንዲማርና በሃይማኖቱ እንዲጸና የሚያደርጉትን እውነተኞች በማሳደድ ምእመናንን ከቤተክርስቲያን እንዲሰደዱ ማድረግ ትናንትም ሆነ ዛሬ የማቅ ዋና ሥራ ሆኗል፡፡ ማቅ የቤተክርስቲያን ልጆችን በዚህ መንገድ ባሳደደ ቁጥር እነርሱ እንደሚባዙ ግን አላስተዋለም፤ አላወቀም፡፡ ስደት ያበዛል እንጂ እኮ አያጎድልም፡፡ ማቅና የግብር አባቱ የወንድሞች ከሳሽ ሰይጣን በታሪክ ውስጥ የማይማሩት እውነት ቢኖር ይህ ነው፡፡ ሰይጣን ክርስቶስን በማሳደድና እንዲሞት በማድረግ የክርስቶስን ተልእኮ ያጨናገፈ መስሎት አይሁድን በእርሱ ላይ አነሳስቶ ነበር፡፡ አይሁድም የተሰጣቸውን ተልእኮ ፈጸሙ፡፡ የክርስቶስ ሞት ግን በእግዚአብሔር የተወሰነና ለእኛ ቤዛ የሆነ ሞት ነው፡፡ በክርስቶስ ትንሣኤ የእርሱ ሽንፈት ታወጀ፡፡ በክርስቶስ ላይ ባደረሰውና በውጤቱ መማር ያልቻለው ሰይጣን ሐዋርያትንም ማሳደዱን ቀጠለ፡፡ ነገር ግን ከግዛቱ ብዙዎች ወደ ክርስቶስ መንግስት ፈለሱበት፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ያድግና በየስፍራው ይበዛ የአማኞች ቁጥርም ይጨምር ነበር፡፡ ኧረ እንዲያውም ከካህናት ብዙዎቹ በወንጌል አመኑ ነው የሚለው የሐዋርያት ስራ፡፡ የወንጌል መንገድ ይኸው ነው፤ ዛሬም ከዚህ ውጪ የሚሆን ነገር የለም፡፡ የተጣለውን የወንጌል እሳት ማጥፋት አይቻልም፡፡ ክርስትና እንዲያውም በስደት ውስጥ ይስፋፋል፡፡ ስለዚህ ማቅ ሆይ እባክህን ዛሬ እንኳን ቆም በልና እያደረግክ ያለውን ነገር አስብ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል፡፡
source: aba selama.org
posted by Aseged Tamene