የአሜሪካ ኮንግረስ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ሕጎች ረቂቆችን እያወጣ ነው

በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚቀርቡ የውሣኔ ሀሳቦችን «በተሳካ ሁኔታ አምክኛለሁ» ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ቢናገርም ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ህጎች አሁንም በኮንግረሱ እየረቀቁ መሆናቸውን የህዝብ ተወካዮች አመልክተዋል።

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በመጋቢት መጨረሻ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሁለት ረቂቅ ህጎችን እንዳጨናገፈ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የኮንግረሱ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት ማብራሪያ «ኮንግረስ በምርጫ ሲቀየር ህጎች እንዳዲስ ለውሳኔ ይቀርባሉ እንጂ የተጨናገፈም ሆነ እንዲዘገይ የተደረገ ህግ የለም» ብለዋል።

ሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

http://amharic.voanews.com/pp/3818900/ppt0.html

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሰማያዊ ፓርቲ እና የጌዲዮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ታወቀ

ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ከአንድ አመት በፊት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲባባስ አድርገዋል ተብለው ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ታወቀ።
ከቀናት በፊት በህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲመረምር የቆየው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ተቃውሞ እንዲቀሰቅስና እንዲባባስ የተለያዩ አስተዋጽዖ አድርገዋል ሲል ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። የኮሚሽኑን ሪፖርት ያቀረበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ ህዝባዊ ተቃውሞን አባብሰዋል በተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ክስ እንዲመሰረት ሃሙስ ውሳኔን ሰጥቷል።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሰማያዊ ፓርቲ እና የጌዲዮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ክስ እንዲመሰረትባቸው የተወሰነ መሆኑን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።


ኦፌኮ እና ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ህዝባዊ ተቃውሞዎች እንዲባባስ አስተዋጽዖ አድርገዋል ተብለው ህጋዊ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው የተወሰነ ሲሆን የጌድዮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች በበኩሉ በጌዲዮ ዞን የዘር ግጭት እንዲቀንስ አድርጓል ተብሏል።
በሶስቱ ክልሎች ከተካሄዱ ተቃውሞዎች ጋር በተገናኘ 669 ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለፓርላማ አቅርቦ በነበረው ሪፖርት አመልክቷል።
ይኸው ሪፖርት ሃሙስ ለፓርላማ አባላት ለውይይት ቀርቦ እንዲጸድቅ የተደረገ ሲሆን፣ የፓርላማ አባላቱ በአብዛኛው ድምፅ ሶስቱ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲከሰሱ ድምፅ ሰጥተዋል። የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ዕርምጃው የፖለቲካ ፓርቲዎችን ህልውና በፍ/ቤት በመሰረዝ ህጋዊነታቸውን ያሳጣቸዋል።
መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የፖለቲካ ድርጅቶቹን ተጠያቂ ከማድረጉ በተጨማሪ የሃይል ዕርምጃን ወስደዋል የተባሉ የጸጥታ አባላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መወሰኑ ይታወሳል።


ይሁንና ምክር ቤቱ ተጠያቂ እንዲሆኑ በተወሰነው የጸጥታ አባላት ላይ የሰጠው ትዕዛዝ የለም።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የሶስት ወር ዕርምጃ 699 ሰዎች መሞታቸውን ቢገልፅም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ግን በሪፖርቱ አለመካተቱንና ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ከተገለጸው ቁጥር በላይ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋምት ይገልጻሉ።


ኮሚሽኑ ጥናቱ ከሃምሌ 2008 አም እስከ መስከረም 2009 አም መሸፈኑን አመልክቷል። ይሁንና ከሃምሌ ወር በፊት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ እንደነበርና ከ100 የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን መንግስት በወቅቱ ማረጋገጡ አይዘነጋም።


ህዝባዊ ተቃውሞን ለመቆጣጠር መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፣ የአዋጁ መውጣትን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንን ከ24 ሺ በላይ ሰዎችም ለእስር መገደላቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች ሲገልጽ ቆይቷል።
አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራቶች እንዲራዘም መደረጉን እስራትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲባባስ ማድረጉን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይገልጻሉ።

ጎንደር አስረኛውን የቦንብ ፍንዳታ ትናት አስተናገደች

በጎንደር ከተማ በቀበሌ 15 ቀጠና 1 ፋሲለደስ እስታዲየም አካባቢ ነዋሪ የሆነው የሆነው የህውሀት የሰሜን ጎንደር ፣ የደቡብ ጎንደር ፣ የምእራብ ጎጃም የአካባቢው ማለትም የቀጠናው የህውሀት ሰብሳቢ ሊቀምንበር እና የትግራይ ልማት ማህበር ሊቀመንበር የሆነው አምባየ አማረ በተባለው ግለሰብ ሚያዚያ 12 ቀን 2009 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡47 ሰዓት ሲሆን መኖሪያ ቤቱ በቦምብ ጥቃት ተፈፅሞበታል ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ በትላንትናው እለት በጎንደር የተፈጠረውን ችግር ለማረጋጋት ከሙሴ ባምብ ወታደራዊ ካምፕ ወታደር ጭኖ የተንቀሳቀሰ አንድ ኦራል መኪና ምሽት 4፡40 ላይ ልዩ ስሙ የኢትዮጵያ ካርታ የሚባለው ቦታ ላይ በጥይት ተመትቶ መኪናው ሲገለበጥ 4 ወታደሮች ወዲያውኑ ሲሞቱ 5 ቀላል ቁስለኛ ሆነዋ ኦራል መኪናው ዛሬ 13/08/2009 ከቀኑ 5 ፡ 00 ሰዓት ተጎትቶ ወደ ጎንደር አዘዞ ወደሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ የመጣ ሲሆን የቆሰሉ ወታደሮች አዘዞ በሚገኘው የጦሩ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ ሟቾችም አዘዞ ሎዛ ማሪያም ቤ/ክርስቲን ተቀብረዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት7 አባላት የሆኑ ታጋዮች በደምቢያ ወረዳ ሰረባ መስኖ አጠገብ ሌሊት ላይ ጥቃት ፈጽመው

2 ገልባጭ መኪኖችና አንድ እስካቫተር መኪና የተቃጠሉ ሲሆን፣ በታጋዮች እና ድርጅቱን በሚጠብቁት መካከል ለ30 ደቂቃ ያክል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንና አንድ ወታደር መገደሉን ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ አስታውቋል።

ኢሳት ወደ አካባቢው ነዋሪዎች ስልክ በመደወል በመኪኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ሲያረጋግጥ፣ በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰው ጉዳት ግን ማረጋገጫ ሊያገኝ አልቻለም። የአይን እማኞች ጉራምባ ቀበሌ ላይ በተለይም በቀበሌው ሊቀመንበር አቶ መንግስቱ መኖሪያ ቤት አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ለውውጥ መካሄዱን ገልጸዋል።

አካባቢው በወታደሮች ቁጥጥር ስር በመውደቁ የተቃጠሉትን መኪኖች ብዛት በትክክል ለማወቅ እንዳልቻሉ፣ ነገር ግን 3 መኪኖች ጠዋት ላይ ተቃጥለው ማየታቸውን ተናግረዋል።

ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሱት ወታደሮች የአካባቢው ሚሊሺያ እርምጃ ባለመውሰዱ መሳሪያቸውን እየቀሙ እያሰሩዋቸው ነው። በሌላ በኩል ትናንት ምሽት በጎንደር ከተማ ተጨማሪ የቦንብ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን፣ አንድ ታጣቂ ግለሰብ ጥቃቱን ባደረሱት ሃይሎች ተመትቶ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

ጥቃቱ በቀጠናው የህወሃት ወኪል በመሆን የደህንነት ስራ ይሰራል በተባለው በአቶ አማረ አምባየ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያሳያል። ግለሰቡ እና ጠባቂው ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መላካቸውንም መረጃው አክሎ አመልክቷል።

ጥቃቱን ተከትሎ ከሙሴ ባምብ ወታደራዊ ካምፕ የተንቀሳቀሰ አንድ ኦራል መኪና ከምሽት 5 ሰአት አካባቢ ልዩ ስሙ የኢትዮጵያ ካርታ በሚባለው ስፍራ ላይ በጥይት ተመትቶ ሲገለበጥ 4 ወታደሮች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 5 ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል።

መኪናው ዛሬ ተጎትቶ ጎንደር አዘዞ ወደሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ተወስዷል። የቆሰሉ ወታደሮችም አዘዞ በሚገኘው የጦር ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፣ ሟች ወታደሮችም አዘዞ ሎዛ ማሪያም ቤ/ክርስቲን ተቀብረዋል፡፡

የአሁኑ ጥቃት በአንድ ሳምንት ጉዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መፈጸሙ ነው። በሰራባ የመስኖ ፕሮጀክት አካባቢ ተደጋጋሚ ጥቃቶች የተፈጸሙ ሲሆን፣ ጥቃቱን በሚያደርሱ ታጋዮች ላይ እስካሁንም ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም።

ገዢው ፓርቲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አማካኝነት ማንኛውንም አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተቆጣጥሬዋለሁ ቢልም፣ አሁንም በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች ጥቃቶች እየተፈጸሙ ነው።

በአቶ ዓባይ ጸሃዬ የቀረበውና አስፈጻሚ አካላት ከህግ በላይ ሆነዋል የሚለውን ጥናት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይማሪያም ደሳለኝ አጣጣሉት

በኢትዮጵያ የፖሊሲ ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በአቶ ዓባይ ጸሃዬ የቀረበውና አስፈጻሚው አካላት ከህግ በላይ ሆነዋል የሚለውን ጥናት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይማሪያም ደሳለኝ አጣጣሉት።


አቶ ሃይለማሪያም ከተመረጡ የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በቅርቡ በአቶ አባይ ጸሃዬ እና በተወሰኑ የመንግስት ተጠሪዎች የቀረበውን ጥናት አላውቀውም፥ ትክክለኛ ግምገማም አይደለም ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።


ይህን የሚያመለክተው የአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መግለጫ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሚተላለፈው ቴሌቪዥን ተቆርጦ እንዲወጣ ተደርጓል።
ኢ. ኢን. ኤን. የተባለውና በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔል የሚመራ አዲሱ የኢህአዴግ ቴሌቪዥን ግን በዚያ ዘገባው ጉዳዩን ይፋ አድርጎታል።


የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማሪያምና የአቶ አባይ ፀሃዬ የሃሳብ ልዩነት በህወሃት ውስጥ ሁለት ጎራ መኖሩን አመላካች መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

%d bloggers like this: