የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ መግለጫ ማውጣቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ለአሜሪካ አምባሳደር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫ ሰራተኞቹ ከአዲስ አበባ ውጪ በምንም አይነት መንቀሳቀስ አደገኛ ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል ብሏል።
እናም በሀገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን የሚሰጡትን መረጃ በመከታተል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋልም ነው ያለው። በኤምባሲው መግለጫ መሰረት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ሰልፎችና ሕዝባዊ አመጾች ድንገት ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ቀውስ ሊባባስ እንደሚችል ነው ያስጠነቀቀው።

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫ መነሻ በማድረግም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ ማሳሰቢያ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአዲስ አበባ ከአሜሪካው አምባሳደር ማይክል ሬይነር ጋር በሀገሪቱ ባለው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተነግሯል።

አቶ ደመቀ አምባሳደሩን በጽሕፈት ቤታቸው ለማናገር የተገደዱት አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳይ በእጅጉ ያሳሰባት በመሆኑ ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በኩል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ ስብሰባ ላይ መሆኑ ይነገራል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለ3 ወራት ወይም ለ6 ወራት ሊደነገግ እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭትና ግድያ ማስተናገዳቸው እንዳሳዘኑት ገለጸ፡፡

ኤምባሲው ደረሰኝ ያለውን ዘገባ ጠቅሶ እንዳስታወቀው በግድያ እና ግጭቱ ተጠያቂዎችን ለመለየት ግልጽ ምርመራ መደረግ እንደሚገባው ሁኔታው ያመለክታል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ሰላማዊ ሰልፎችን የምትመለከተው እንደ ህጋዊ የሀሳብ እና የፖለቲካ ተሳትፎ መግለጫ እንደሆነ ኤምባሲው ዛሬ ያወጣው መግለጫ ያትታል፡፡

በቅርቡ በተካሄዱ በርከት ባሉ ሰልፎች ሰልፈኞች በሰላማዊ ሁኔታ ሀሳባቸውን መግለጻቸውን እና ይህን እንዲያደርጉም የጸጥታ ኃይሎች መታገሳቸውን በአድናቆት እንደሚመለከተው ኤምባሲው ገልጿል፡፡

ኤምባሲው ሁሉም ኢትዮጵያውያን አመለካከታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጻቸውን እንዲቀጥሉ አበረታቷል፡፡ ባለስልጣናትም ይህንኑ አንዲፈቅዱ ጠይቋል፡፡ በጥቅሉም «ኢትዮጵያዊያንን በሚጠቅም ጉዳይ ገንቢ፣ ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታች ብሔራዊ ተዋስዖ» መኖሩን እንደሚደግፍም በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

The United States sees peaceful demonstrations as a legitimate means of expression and political participation.  We note with appreciation a number of recent events during which demonstrators expressed themselves peacefully, and during which security forces exercised restraint in allowing them to do so.

We are saddened by reports that several recent protests ended in violence and deaths.  All such reports merit transparent investigation that allows those responsible for violence to be held accountable.

We encourage all Ethiopians to continue to express their views peacefully, and encourage Ethiopian authorities to permit peaceful expression of views.  More generally, we encourage constructive, peaceful, and inclusive national discourse on matters of importance to Ethiopian citizens.

በኢትዮጵያ ሶማሌ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ያለው ግጭት እንዳሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች

በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ግልፅ ማጣራት እንዲያካሂድና አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9፤ 2010 ዓ.ም. – በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች በተለይም በሐረርጌ  የጎሳ ግጭትን እና የበርካታ ሰዎችን መፈናቀል አስመልክቶ በሚወጡ አሳሳቢ ዘገባዎች ተረብሸናል፤ ምንም እንኳ ዘገባዎቹ ስለሁኔታው ዝርዝር መረጃ ስለማቅረባቸው ግልጽ ባይሆንም፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱን ግልጽ በሆነ አካሄድ እንዲያጣራ እና አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፤ ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲሹ መበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጠንካራ፤ የበለጸገች እና ዴሞክራሲያዊት ሀገር መሆን የምትችለው፤ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት፤ ግልጽ የመንግሥት አሰራር፤ እንዲሁም የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር ስትችል እንደሆነ እናምናለን፡፡ የሰሞኑ ሁነቶች በተጠቀሱ ዘርፎች ይበልጥ ፈጣን እና ተጨባጭ ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ አመላካች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያው አገዛዝ ዜጎቹን እንዲሰልል የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲ እገዛና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ተነገረ

ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲው በኢትዮጵያ የስለላ መረብ እንዲዘረጋ ትልቅ እገዛ ማድረጉን መረጃዎቹን ያሰባሰበው ይሄው ተቋም ገልጿል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየአመቱ የሀገራትን ሰብአዊ መብት አያያዝ በማስመልከት በሚያወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ዜጎቿን መሰለሏንና ማፈኗን ቢያወግዝም የዚሁ ድርጊት ተባባሪ መሆኑ ግን ትክክል አለመሆኑን ተቋሙ ተችቷል።

አሜሪካ የኢትዮጵያ ዜጎች እንዲሰለሉና እንዲታፈኑ በሚያስችለው የደህንነት ቴክኖሎጂ መረብ ዝርጋታ እጇ አለበት መባሉ ጉዳዩን ውስጡን ለቄስ አስብሎታል። በአንድ በኩል ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ረገጣ ትፈጽማለች በማለት የምታወግዘው ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በሌላ በኩል የጉዳዩ ተባባሪ ሆና መገኘቷ ብዙዎችን አስገርሟል። ኢንተርሴፕት የተባለው ተቋም ሚስጥራዊ ሰንዶችን በመመርመር ይፋ እንዳደርገው የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት መስሪያ ቤት ኢትዮጵያ የዜጎቿን የስልክ ግንኙነትና ንግግሮችን የሚጠልፍ የቴክኖሎጂ መረብ እንድትዘረጋ ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የስልጠና ድጋፍ አድርጓል።

 

በአንድ በኩል በልማትና በጤና እንዲሁም በሰብአዊ ጉዳይ ላይ ብቻ እርዳታ እሰጣለሁ እያለች የምትፎክረው አሜሪካ በሌላ ሁኔታ የኢትዮጵያውያን መብት እንዲጣስና እንዲታፈን በሚያደርግ ወንጀል ተባባሪ መሆኗ ትልቅ ችግር መሆኑን ኢንተርሴፕት ዘርዝሯል። እንደ ተቋሙ ገለጻ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የስለላ መረብ መረጃ የቴክኖሎጂና የስልጠና አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚል ሰበብ ነው።

ይህም ሆኖ ግን የኢትዮጵያ አገዛዝ ይህን ቴክኖሎጂ ለሰብአዊ መብት ረገጣና ለአፈና እየተጠቀመበት መሆኑን አሜሪካ እያወቀች ይህን ማድረጓ አግባብነት የለውም ብሏል።

 

ኢትዮጵያ የተቃዋሚ መሪዎችንና ጋዜጠኞችን በማሳደድና በማሰር እንዲሁም ዜጎችን በመግደል ወንጀል እየፈጸመችበት መሆኑንም ኢንተርሰፕት የተባለው ተቋም ገልጿል። አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግስት የስለላ መረብ የሰጠችው የቴክኖሎጂ መረብ የአንበሳው ኩራት ወይም ላየንስ ፕራይድ የተሰኘ ነው። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2002 በትንሽ የሰው ሃይል ጀምሮ በ2005 ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያደገ ነው ተብሏል። በዚህ ፕሮጀክት 8 አሜሪካውያንና 103 ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል ተብሏል።

ፕሮጀክቶቹም በአዲስ አበባ፣በድሬደዋና በጎንደር ከተሞች የተዘረጉ መሆናቸው ነው የተገለጸው። በእነዚህ ፕሮጀክቶችም 7 ሺ 700 ሰንዶችና 900 ሪፖርቶች ከስለላ ስራው በኋላ የተዘጋጁ መሆናቸውን ኢንተርሴፕት አጋልጧል።

 

የገዢው ፓርቲ ሰው መሆኑ የተነገረለት ግለሰብ ከታይላንድ በርካታ ፎርጅድ መታወቂያና መንጃ ፈቃድ ይዞ ለመግባት ሲሞር ተያዘ [ቪዲዮው ተያይዟል]

የገዢው ፓርቲ ሰው መሆኑ የተነገረለት ግለሰብ ከታይላንድ በርካታ ፎርጅድ መታወቂያና መንጃ ፈቃድ ይዞ ለመግባት ሲሞር ተያዘ [ቪዲዮው ተያይዟል]