በብራሔራዊ መረጃ የመረጃ መረብ ኤጀንሲ ሐገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ስጋት ላይ መሆናን ተናገሩ

መስከረም 10/2010 በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ጥቅል ዉስጥ የሚገኘዉ የብሄራዊ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ጉዳዮች ተጠሪ ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት ሐገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ስጋት ላይ በድጋንሚ እንደምትወድቅ በመተንበይ የቀድሞ መከላከል የሳይበር ጦርነት የሶሻል ሚዲያ ጥቃቱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የተሰመረበት ስብስባ ነበር።

የብሄራዊ መረጃ ከፍተኛ ሚስጥራዊ መኮንኖች እንደተገኙበት የተነገረዉ የሁለት ቀናት ድብቅ ስብሰባ የሳይበር ጥቃቱ በተጠናከረ መልኩ እና ተጨማሪ ሐይሎችን አሰልጥኖ እንዲቀሳቀስ በተለይም በሶሻል ሚዲያ ሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ትኩረት እንዲደረግ አመላክቷል።

በኢንፎርሜሽን መረቡ ጥናት የተዋቀረዉ የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት ያስመዘገባቸው ዉጤቶችና ድክመቶች የተገመገሙ ሲሆን በተቃራኒ አካል የሚንቀሳቀሱ መሐበራዊ መገናኛ ሰራዊት ተዋጊዎች ሆን ብለዉ የቃዋሚ ክንፍ ድርጅታቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስተዋወቅ በራሳቸዉ ላይ ያተኮረ ተጻራሪ የሚመስል ቅስቀሳና አላማቸዉን የማሰራጨት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ያለዉ የደህንነት ጉዳዮች በሐገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ አክቲቭ አጥቂዎች ላይ ትኩረት በመዉሰድ እንዲያተኩርም ተወስኗል።

ተቃዋሚ ሐይሎች ሆን ብለዉ መረጃቸዉ እንደወጣ በማስመሰል የሚፈልጉትን መልእክት በሚገባ እያስተላለፉ እንደሚገኙ የጠቆመዉ ክንፍ እደዚያ ያሉ የመረጃ ስልቶች በአግድሞሽ እየጎዱን ነዉ ሲል አሳስቧል።

የብሐራዊ መረጃዉ በለድርሻ የተባሉ ከመከላከያ ፣ ከፌደራል ፖሊስ ፣ ከክልል ፖሊስና ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የማሐበራዊ መገናኛ ዘርፍ ላይ ያበረከቱት ድርሻ ዝቅተኛ መሆኑን አስቀምጦ ሁሉም በዘርፍና በኩነት በአጭር እና እረጅም ግዜ የስልጠና እገዛ እንዲደረግላቸዉ ሐሳብ ሰጥቷል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Advertisements

የኢትዮጵያው አገዛዝ ዜጎቹን እንዲሰልል የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲ እገዛና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ተነገረ

ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲው በኢትዮጵያ የስለላ መረብ እንዲዘረጋ ትልቅ እገዛ ማድረጉን መረጃዎቹን ያሰባሰበው ይሄው ተቋም ገልጿል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየአመቱ የሀገራትን ሰብአዊ መብት አያያዝ በማስመልከት በሚያወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ዜጎቿን መሰለሏንና ማፈኗን ቢያወግዝም የዚሁ ድርጊት ተባባሪ መሆኑ ግን ትክክል አለመሆኑን ተቋሙ ተችቷል።

አሜሪካ የኢትዮጵያ ዜጎች እንዲሰለሉና እንዲታፈኑ በሚያስችለው የደህንነት ቴክኖሎጂ መረብ ዝርጋታ እጇ አለበት መባሉ ጉዳዩን ውስጡን ለቄስ አስብሎታል። በአንድ በኩል ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ረገጣ ትፈጽማለች በማለት የምታወግዘው ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በሌላ በኩል የጉዳዩ ተባባሪ ሆና መገኘቷ ብዙዎችን አስገርሟል። ኢንተርሴፕት የተባለው ተቋም ሚስጥራዊ ሰንዶችን በመመርመር ይፋ እንዳደርገው የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት መስሪያ ቤት ኢትዮጵያ የዜጎቿን የስልክ ግንኙነትና ንግግሮችን የሚጠልፍ የቴክኖሎጂ መረብ እንድትዘረጋ ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የስልጠና ድጋፍ አድርጓል።

 

በአንድ በኩል በልማትና በጤና እንዲሁም በሰብአዊ ጉዳይ ላይ ብቻ እርዳታ እሰጣለሁ እያለች የምትፎክረው አሜሪካ በሌላ ሁኔታ የኢትዮጵያውያን መብት እንዲጣስና እንዲታፈን በሚያደርግ ወንጀል ተባባሪ መሆኗ ትልቅ ችግር መሆኑን ኢንተርሴፕት ዘርዝሯል። እንደ ተቋሙ ገለጻ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የስለላ መረብ መረጃ የቴክኖሎጂና የስልጠና አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚል ሰበብ ነው።

ይህም ሆኖ ግን የኢትዮጵያ አገዛዝ ይህን ቴክኖሎጂ ለሰብአዊ መብት ረገጣና ለአፈና እየተጠቀመበት መሆኑን አሜሪካ እያወቀች ይህን ማድረጓ አግባብነት የለውም ብሏል።

 

ኢትዮጵያ የተቃዋሚ መሪዎችንና ጋዜጠኞችን በማሳደድና በማሰር እንዲሁም ዜጎችን በመግደል ወንጀል እየፈጸመችበት መሆኑንም ኢንተርሰፕት የተባለው ተቋም ገልጿል። አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግስት የስለላ መረብ የሰጠችው የቴክኖሎጂ መረብ የአንበሳው ኩራት ወይም ላየንስ ፕራይድ የተሰኘ ነው። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2002 በትንሽ የሰው ሃይል ጀምሮ በ2005 ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያደገ ነው ተብሏል። በዚህ ፕሮጀክት 8 አሜሪካውያንና 103 ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል ተብሏል።

ፕሮጀክቶቹም በአዲስ አበባ፣በድሬደዋና በጎንደር ከተሞች የተዘረጉ መሆናቸው ነው የተገለጸው። በእነዚህ ፕሮጀክቶችም 7 ሺ 700 ሰንዶችና 900 ሪፖርቶች ከስለላ ስራው በኋላ የተዘጋጁ መሆናቸውን ኢንተርሴፕት አጋልጧል።

 

የህወሓት የስለላ ድርጅት የስጋት እርምጃና ህዝብን የማሸበር ተግባር – በባህርዳር

በተከታታይ በአማራ አርበኞች ህዝባዊ ሃይል በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ግንባሮች ባደረገው የሽምቅ ውጊያ ክፋኛ የተደናገጠውና ከፍተኛ ጥቃትና ውርደትን የተከናነበው የህወሓት ዘረኛ ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ የነፃነት ትግሉ ከህዝብ ያለውን ድጋፍ እያየ እንዳቀረቀረ ማስታገሻ እንዲሆነው በማሰብ ህዝብን የማሸበሩን ሴራ ማንሰላሰሉን አላቆመም።
* በከፍተኛ ሁኔታ የሸቀጦችና የምግብ ፍጆታ ዋጋ እንዲንር ያደረገው ወያኔ ፤ነዳጂ አለ እየተባለ እንዲጠፉ ያደረገው ማስመሰል ዛሬም አዲስ ማሸማቀቂያና ማፈኛ ስልትን ይዞ መጥቷል።
* ከአመታት በፊት የከተማ ገፅታ ያበላሻል የተባለው መንደር እንዲፈርስ ሲወሰን ትክ ቦታ
ሳይሰጣቸው ነበር።አሁን ይሄን ሃሳብ ዳግም በማስፈፀም በዚህ ሰበብ ወጣቱን ማሰርና ማፈን አንድ የማስታገሻ ውጥረቱን ማርገቢያ መንገድ መስሎታል።
* እንዲህ ሆነ ባህርዳር ቀበሌ 13 ከኢሜግሬሽን ጀርባ አካባቢ ያለው የወያኔው የኢትዩጲያ መርብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ) ብሎ እራሱን የሚጠራው አፍኝ የስለላ ቡድን በተደጋጋሚ ባቀረበው የስጋት ሀሳብ “በባህርዳርና ጎንደር ያለው የወጣቶች አደረጃጀት እጂጉን ያስፈራል፤በየመንደሩ የሚሰባሰቡት ወጣቶች እጂግ የሚተዋወቁና
የነቁ ናቸው::በዚህም ምክንያት ተፈልጎ አስቸኳይ ዘመቻ እና ከተቻለ መዋቅሩን ጫፉ ከተገኘ ማፍረስ ካልተቻለ ውጥረቱን ማርገብ በዝምታ የሚገሰግሰውን ነበልባል ማፈን
አለብን” በማለት በቅርብ የተገኘ የህገወጥ መኖሪያ ቤት ምክንያት በመላ ከተማው ዳናውን ለመያዝ የተደረገ ሙከራ ሲጠኑ የነበሩ እየታደኑ ከ100 በላይ ወጣቶች ለእስር ዳረጉ፣ብዙወች ተደበደቡ ለአካል ጉዳት ተዳረጉ ፣ሁለት ወጣቶች በጥይት ተገደሉ።
* ከዚህ ላይ የፍራቻው ጥግ የደረሰው የስጋት እርምጃ ባለፈው ሰኞ በክልሉ ምክር ቤት ለዛሬ ሐሙስ ለመፍትሄ ሃሳብ የተቀጠሩት ነዋሪወች ሐሙስን ሲጠብቁ ማክሰኞ ዕለት
ደራሽ ጎርፉን ለቀቁት በዚህም ህገወጥ ናችሁ የተባሉ ቤቶችን ፈረሱ በዚህ አምባገነናዊ ተግባራቸውን አላከው በቦታው ያልነበሩ ወጣቶችን ሰብስበው ማስገባታቸውን የህወሓት ህዝብን የማሸበር ተግባር ለከት የሌለው እንደሆነ ያሳያል።
* የህወሓት የስለላ ድርጂት ከጠረፋማ ድንበሮች እስከ ማዕከላዊ ያለው ሰንሰለት እየተቆራረጠበት ይገኛል።ለዚህ የበሰበሰ ስርዓት ማገልገል የማይፈልጉና ቂም ቋጥረው የቆዩት ባገኙት አጋጣሚ ጥለው እየጠፉ ነው ።
* ለዚህም ማሳያው ላለፉት 3 ወራት ብቻ ብዙወች ወታደራዊና ሲቪል ሰላዩች ድራሻቸው አይታወቅም። አፈሳውና እስሩ በአጎራባች
አካባቢወች ሊቀጥል እንደሚችል ፍንጮች ወጥተዋል።
*በተለይ ወጣቶች እንቅስቃሴያችሁ በጥንቃቄ እንዲሆንና በስነልቦና ዝግጁ እንድትሆኑ ከወዲሁ እንመክራለን።

ብሄራዊ መረጃ የህዝብ ግንኙንት ተደማጭንት አላቸው የሚባሉ ግለስቦች እንዲታፈኑ እንዲደርስባቸው በሚስጥር ማሳሰቡ ተሰማ

በብሄር ብሄረሰብ አስተዳደር ክልል ውስጥ የተዋቅሩ የብሄራዊ መረጃ ቅርንጫፍ አስተዳደር ባለስልጣን አካሎች እነርስም ተጠሪነታቸው ለክልል የደህንነት ብሄራዊ መርጃ ክንፍ የሆኑ የየወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዋች በአካባቢያቸው የሚኖሩ የተቃራኒ ፓርቲ አባላቶችንና አመራሮችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ በማጥናት እንዲያቀርቡ ከብሄራዊ መረጃ የህዝብ ግንኙንት እና መምሪያ አምራር ባልስልጣናት ቀጭን ትእዛዝ ወርዶላቸዋል::

ብሄርዊ መረጃው ያወረደው ትእዝዝ በተለየ መልኩ ሕዝብን በማሳመን ተደማጭንት አላቸው የሚባሉ ግለስቦች እንዲታፈኑ የሚያዝ ከመሆኑ ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ፖርቲዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ 2000 ሺ ይሚጠጉ ግልስቦችን ስም ዝርዝር አዳብሎ ከጥብቅ አጽንኦት ጋር ያስተላለፈ ሲሆን ድንገትኝና አደገኛ ሐገርዊ ጥቃት በእነዚግለስቦች እንደተቀናበረ. አውስቷል::


የህወሀቱ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት ከተራ የአካባቢና የወረዳ ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ጋር በብርቱ ያወራረደው ትእዛዝ አርበኞች ግንቦት 7 ለ 460 አባልት ህቡሕ አደራጆች ከፍተኛ የጥቅም በጀት ያፈሰሰ ነው ከማለቱ ባሻገር 900 የታጠቁና የተበተኑ ግዳጅ ተወጪዎች መሰማራታቸውን ፍንጭ ሰጥቷል::


ከህወሀት የወታደራዊ ደህንነት ኮማንድ ፖስት እውቅና ውጭ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ብሄራዊ መረጃ ስውር ደህንነቶች በብዛት እየተገደሉበት ከፍተኛ ችግር ላይ የወደቀው የመረጃው ክንፍ እጅግ በወረደ ሁናቴ ከአካባቢ የጸጥታ ዘርፍ ሐላፊዋች ጋር ለመስራት እንደተገደደ ምንጮቻችን አጣምረው ገልፀዋል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
( ጉድሽ ወያኔ )c702cfe8

ሰበር መረጃ . . . የህወሃት ሶሻል ሚዲያ ሰራዊት የጥቃት ስልት ይፋ ሆነ

በመሃበራዊ ግንኙነት ዙሪያ ላይ መበለጣችን ለህዝባዊ አመጽና ለስልጣን መፈረካከስ አድርሶናል በማለት በአዲስ እራይ ልሳኑ በይፋ ያወጀዉ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የተቃዉሞ ምንጭ በሚል ድምዳሜ በግንባር ቀደምትነት የፌስ ቡክ ሚዲያ ዘርፍን ለማጥቃት ዘመቻ መዉጣቱን ተንተርሶ ለቅጥረኞች የሶሻል ሚዲያ አጥቂ ሰራዊቱ የተሰጣቸዉን ግዳጅ በጥንቃቄ እንመለከተዉ ዘንድ በዘርፉ ከተሰማሩ ምንጮቻችን መረጃ ደርሶናል።
• የሰራዊቱ ዋነኝ አላማ……………….
_በተቃዉሞ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው ወያኔን በከፍተኛ ሁኔታ ከሚሞግቱት ጋር ተመሳስሎ የትግላቸዉ አካል በመሆን እና መረጃዎችን በመቀባበል ትግሉን ማጥቃት እና ማኮላሸት ህወሃትን ማዳን ።
_ አላማዉን ለማሳካት እነዚህ የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት አባላት በተቃዋሚ ሰራዊቶች ዉስጥ ታማኝነትን በማፍራት እና ሰርገዉ በመግባት በዉስጥ መስመር የማሳመን ስራ መስራት የማህበራዊ ግንኙነት የጥምር ቡድን ስብሰባዎችን መቀላቀል ሐሳቦችን እና ሆን ተብለዉ የተጠኑ መረጃዎችን በማቀበል ሙሉ እምነት እንዲጣልበት አድርጎ ለዘርፍ ሐላፊ የብሄራዊ ደህንነት ተጠሪዎች ማሳወቅ።
_ ይህ ተግባር በተለየ መልኩ ከነጻነት ሐይሎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸዉ የሚባሉ ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በመካከል በሚፈጠር ጠንካራ ታማኝነት ምክንያት የሚዲያ ሰራዊቱ አባላት እስከ ግንባር ድረስ እንዲዘምቱ እና የማፍረስ ስራ እንዲያከናዉኑ ይታገዛሉ።
_ አብዛኛዎቹ የህወሃት የሶሻል ሚዲያ አባላት አዲስ አካውንት ከመክፈት ይልቅ ነባር አካዉንታቸዉን ስም በመቀየር እንዲገለገሉበት ተደርገዋል።
_ የሶሻል ሚዲያ ሰራዊቱ ሆን ተብለዉ በፖለቲካ ምክንያት ከሐገር እንዲሰደዱ በማድረግ በተልይ የኮማንድ ፖስቱ ባለ ቀይ መስመር ሐገሮች ላይ እነርሱም አሜሪካ ፣ ኖርዌይ ፣ ሲዉዲን ፣ እንሊዝ ፣ ኒዘርላንድ ፣ ካናዳ ፣እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ ፣ ኬንያና ፣ ዩጋንዳ ላይ ልዩ የጥቃት ስልት ተንድፎ ይቀርብላቸዋል።
_ የህወሃት ሰራዊት የተሳሳቱ መረጃዎችን በመስጥት ታማኝነት እንዲጠፋ መተማመን እንዳይኖር በብርቱ ይተጋሉ
• አፈጻጸም…………………
_ ጥቂትና እዉነተኛ መረጃዎን ከሁሉም ቀድሞ በማሰራጨት ታማኝነን ማዳበር
_ የተቃዋሚ ክፍል አደገኛ ተግባራቱን ማጥናትና ማቅረብ በግል ደረጃ እነማን እንደሆኑም በጾታዊ ወይም በመመሳሰል የትግል ስልት በማሳመን እና በማግባባት ማወቅ የት እና ከየትኛዉ ማህበረሰብ ከምን አይነት ቤተሰብ የወጡ ናቸዉ ? እስከሚባሉት ድረስ መሄድ..
_ ለታዋቂ የፌስ ቡክ ገጾች የተጠኑ መረጃዎችን ማቀበል ለተለያዩ ድህረ ገጾች በተለይም ዘ_ሐበሻና ኤካዴፍ ለመሳሰሉት መረጃ መስጠtና በሌሎች ዉስጥ ቦታ መያዝ።
• የምርመራና ከሳሽ ዘርፍ……
_ይህ ዘርፍ በቀጥታ ከህወሃት የደህንነት ሰራተኞች ጋር በቅንጅት የሚሰራ ሲሆን ዋነኛ አላማዉ አዝማች የተቃዋሚ አጥቂ ግለሰቦችን በህግ ሽፋን ክስ ለመመስረት በሚያስችል መልኩ አሳልፎ ለመስጠት መረጃ መሰብሰብ ዋና ስራዉ ነዉ::
_ በዚህ ክፍል ዉስጥ የተሰማሩ ቅጥረኞች የተቃዋሚ ክንፍ ባለ አካዉንቶችን በዉስጥ መስመር በመልእክት ወይም በድምጽ እንዲሁም በጽሁፍ መስቀለኛ ጥያቄ መጠየቅ ሲሆን
ጥያቄዎቹ . . . መዝመት እፈልጋለዉ? በየት በኩል ልጓዝ ? ከእነማን ጋር ልገናኝ ?. . . እነ እገሌን ታዉቃቸዋለህ? እነማን ሲባል _ የሚጠየቁት ግለሰቦች በሽብር የተከሰሱ ሊሆኑ ይችላሉ ) እና የመሳሰሉት………..።
• ህወሃት ያሰማራቸዉን የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት አባላት ከተቃዋሚ ሰራዊቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸዉን ስሞች በመቅረጽ የማደናገር ተግባር መፈጸም
• በተቃዋሚ የመረጃ ዘርፍ ዉስጥ በዘላቂነት ከርሞ አቋምን በመቀየር የማደናገር ተግባር መፈጸም።
• የልማትና የስራ ዘርፍ…….
_ ከተራ አካዉንት እስከ ኢቢሲና የተለያዩ የህወሃት ልሳኖችን በመጠቀም ልማታዊ ክንዉኖች ቦታ እንዲይዙ የሚጥር የሚዲያ ክንፍ

ዉድና የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ይህ አንባገነኑን ህወሃት በዚህ ዘርፍ ላይ በብርቱ እያማከረች የምትገኘዉ ቻይና ስትሆን ለዚህ የሚዲያ ዘርፍ የሚዉል የግፍ ገንዘብ 1 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ተመድቦለት ወደ ተግባር ተገብቷል፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
( ጉድሽ ወያኔ )

%d bloggers like this: