ከፍተኛ የኦሮሚያ ጦር አዛዦች ከሃላፊነታቸው እየተነሱ ነው ተባለ

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ መከላከያ ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ ኦሮሞ የሆኑ የጦር አዛዦች ቀጥታ ሰራዊቱን ከሚያዙበት ምድቦች እየተነሱ ምንም ስራ በሌለባቸው ቦታዎች እየተመደቡ እንደሆነ ታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ኦሮሞ የሆኑ የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች ተቃውሞውን ይደግፋሉ የሚል ምልከታ በህወሃት የጦር አዛዦች መያዙን ለመረዳት ተችሏል። ታችኛው ላይ ያለው አብዛኛው ሰራዊት ከሌላ ብሄር የመጡ በመሆናቸው እነዚህ የኦሮሞ ከፍተኛ መኮንንኖች ኦሮሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ምክንያት አድርገው ታች ላይ ያለውን ሰራዊት በማንቀሳቀስ ህወሃት ላይ አደጋ እንዳያመጡና የተቃውሞው አካል እንዳይሆኑ በማለት ቀጥታ ሰራዊት ማዘዝ የማይችሉባቸው ቦታዎች ላይ እንዲመደቡ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ከሃላፊነታቸው ተነስተው በሹመት ስም ምንም ጦር ማዘዝ በማይችሉበት ቦታ በሆነው የደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ሃላፊ በማለት እንዲመደቡ ተደርገዋል።

በብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ምትክ የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ በመሆን ኮ/ል የማነ ገ/ሚካኤል የተባሉ የህወሃት የጦር አዛዥ ተመድበዋል። የ13ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ከድር አራርሳ ቀጥታ ጦሩን ከሚያዙበት ሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጎ በሹመት ስም ምንም ጦር ወደ ማይመሩበትየማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ሃላፊ በመሆን ተመድበዋል።

የ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ከፍያለው አምዴ እንዲሁ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የ21ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ብ/ጄነራል ዋኘው አማረ ከሃላፊነታቸው ተነስተው በመሃንዲስ ዋና መምሪያ ውስጥ እንዲቀመጡ ተደርጓል።

የአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ሃላፊ የሆኑት ብ/ጄነራል ሙላት ጀልዱ ከላፊነታቸው ተነስተው በመከላከያ የስነምግባር መከታተያ ዳይሬክተር በማድረግ ከሰራዊቱ ጋር ቀጥታ ከሚያገናኛቸው ስራዎች እንዲገለሉ ተደርጓል።

በርካታ የአማራና የኦሮሞ ከፍተኛ መኮንኖች በሰላም ማስከበር ሰበብ ከሰራዊቱ እንዲገለሉ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ መከላከያ ውስጥ ያሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰራዊቱ ተቃውሞውን እንዳይቀላቀል በህወሃት በኩል ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ሲሆን ለህዝብ ወገኝተኝነት ያሳያሉ የሚባሉ የጦር አዛዦችን ከሃላፊነታቸው በማንሳት ምንም ወደ ማይሰሩበት ቦታዎች በሹመት ስም እየተዛወሩ መሆኑ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ሶማሌ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ያለው ግጭት እንዳሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች

በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ግልፅ ማጣራት እንዲያካሂድና አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9፤ 2010 ዓ.ም. – በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች በተለይም በሐረርጌ  የጎሳ ግጭትን እና የበርካታ ሰዎችን መፈናቀል አስመልክቶ በሚወጡ አሳሳቢ ዘገባዎች ተረብሸናል፤ ምንም እንኳ ዘገባዎቹ ስለሁኔታው ዝርዝር መረጃ ስለማቅረባቸው ግልጽ ባይሆንም፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱን ግልጽ በሆነ አካሄድ እንዲያጣራ እና አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፤ ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲሹ መበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጠንካራ፤ የበለጸገች እና ዴሞክራሲያዊት ሀገር መሆን የምትችለው፤ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት፤ ግልጽ የመንግሥት አሰራር፤ እንዲሁም የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር ስትችል እንደሆነ እናምናለን፡፡ የሰሞኑ ሁነቶች በተጠቀሱ ዘርፎች ይበልጥ ፈጣን እና ተጨባጭ ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ አመላካች ናቸው፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ አንደኛ መደበኛ ጉባኤን በሚመለከት የወጣ መግለጫ

የአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ ከጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባደረገው የመጀመሪያው ጉባኤ፣ የሀገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣የማህበራዊ ሁኔታዎችንና በአሁኑ ሰዓት የሚትገኝበትን የደህንነት ስጋት በስፋትና በጥልቀት ፈትሿል። በፍተሻው ሀገራችን ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ የገጠሟት እጅግ ፈታኝ ወቅቶች እንዳሉ አስታውሶ፤ በአሁኑ ወቅት የምትገኝበት ሁኔታ ግን ከዚህ በፊት ገጠሟት ከነበሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉ እጅግ የከፋ እንደሆነ ጉባኤው ድምዳሜ ላይ ደርሷል። አገራችን አሁን ለደረሰችበት አሳዛኝ አደጋ ደረጃ ላይ ለመድረስ ዋነኛው ምክንያት ላለፉት 26 ዓመታት በወያኔ የበላይነት የተዘራው መርዛማ የዘር ፖለቲካ መሆኑን አረጋግጧል።
በአሁኑ ወቅት የወያኔ መርዛማ የዘር ፖለቲካ በተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ውስጥ የዘራው የጠላትነት፣ የፍራቻና የጥርጣሬ ወረርሽኝ በራሱና የህወሀት/ኢህአዴግ ግንባር ድርጅቶች ውስጥ ጭምር ገብቶ፣ እርስ በእርስ በውስጥ ሽኩቻ እና የግንባር ድርጅቶቹ ደግሞ ከሌሎች የግንባር ድርጅቶች ጋር ወደ ጥፋት ጎዳና በፍጥነት በሚጓዝ የትንንቅ ሂደት ውስጥ ገብተዋል። የሀይለማሪያም ደሳለኝ አሻንጉሊት መንግስትም ለዚህ የጥፋት ሂደት፤ የአጋፋሪነት ሚናን በመጫወት ላይ ይገኛል። ይህ ሂደት በምን ሁኔታ ሊጠናቀቅ እንደሚችልና ሊያስከትል የሚችለውም እጅግ አስፈሪ ሀገራዊ ሁኔታ ጉባኤውን እጅግ አሳስቦታል።
በሀገሪችን ኢትዮጵያ ያለው የሽፍታ ኢኮኖሚ ወያኔን እና ለወያኔ ሥርዓት ያደሩ ጥቂት ሰዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የከፍተኛ ሀብት ባለቤት ሲያደርግ አብዛኛውን የሀገሪቷን ዜጋ ደግሞ ለከፍተኛ ድህነትና ረሀብ አጋልጦታል። ለዘረፋ እንዲያመች የተዘረጋው የኢኮኖሚ ሥርዓት ምንም ዓይነት መጠበቂያ ስለሌለው፣ ልክ እንደ ፖለቲካው እርስ በእርሱ መደጋገፍ አቅቶት በአንድ በኩል በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በየጊዜው ለረሀብ ሲያጋልጥ፣ ትንሽም ቢሆን ተፍጨርጭሮ የሚኖረውን የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን እንኳ መግዛትና መጠቀም ከማይችልበት የድህነት ወለል በታች እየወረደ መሆኑ ምን ዓይነት ሀገራዊ ቀውስ እያስከተለ እንደሆነ ጉባኤው ተገንዝቧል።
በህብረተሰቡ ውስጥ የነበረው ማህበራዊ ጥሪትና መተባበር ተሟጦ፣ በማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት ማንም ከማንም ጋር፣ በምንም ዓይነት ጉዳይ፣ በየትኛውም ደረጃ ተማምኖ፣ ምንም ዓይነት ማህበራዊ ግንኙነት ማድረግ ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። በአንጻሩ ያለመተማመን፣ አንዱ በሌላው ኪሳራ መበልጸግ፣ ሌብነት፣ ሸፍጥ፣ ክህደት፣ ብልጣብልጥነትን “የአዋቂነትና የትልቅነት መለኪያ”፣ የሚያስመስል አመለካከት ከቀን ወደ ቀን በማህበረሰቡ ውስጥ እየተንሰራፋ በመምጣቱ፣በሕዝቡና በሀገሪቷ ላይ እየደረሰ ያለው በቀላሉ የማይታከም በሽታ እየሆነ መምጣቱ ጉባኤውን እጅግ አሳስቦታል።
በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቷ ያለው የደህንነት ዋስትና የማጣት ሁኔታ ለተራው ዜጋ ብቻ ሳይሆን ለሥርዓቱ ተጠቃሚ ሰዎች ጭምር ምንም ዓይነት ዋስትና ወደ ማይሰጥበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ተራው ዜጋ ፣ ውሎ የመግባት፣ ሰርቶ የማግኘት፣ ለነገ የማሰብ፣ ዋስትና ማጣቱ እንዲህ ካለሥርዓት የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ይህ የደህንነት ዋስትና ማጣት የደረሰበት ደረጃ የሥርዓቱንም ተጠቃሚዎች ሰለባ ማድረግ መጀመሩም በገሀድ እየታየ መጥቷል። የአንደኛው ተጠቃሚ ቡድን የሌላውን ቡድን ዓባላት ሰበብ አስባብ እየፈጠረ የሚያጠፋበት ሁኔታ ሥርዓቱ ወደ ለየለት የአራዊት ስርዓት እየወረደ መሆኑን የሚያሳዩ የአደባባይ ትዕይንቶች በተደጋጋሚ መታየት ከጀመሩም ውለው አድረዋል። የአግ7 ጉባኤ፣ የሥርዓቱ አውሬዎች እርስ በእርስ መበላላት ብዙም የሚያስጨንቀው ጉዳይ ባይሆንም፣ በዜጎች ላይ የሚያስከትለው ፈጽሞ የለየለት ሥርዓት ዓልባ ሁኔታ ግን በቀላሉ የሚገመት ሊሆን እንደማይችል ጉባኤው ለማየት ችሏል።
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከዚህ በላይ ጉባኤው የተነጋገረባቸው እጅግ አንገብጋቢ አገራዊ ቀውሶች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት ሊደረግ የሚገባውን አገር አድን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ መጨመር እንዳለበት በአንድ ልብ ተስማምቷል። ለዚህም እንቅስቃሴ መጨመር የሚያረጋግጠውን ግብ፣ ከግቡ የሚያደርሰውን ስትራቴጂ፣ ስትራቴጂውን የሚሸከም ድርጅታዊ አቅም፣ ድርጅቱን የሚመራ ብቃት ያለው አመራር የሚኖርበትን ሁኔታ፤ የጉባኤውን ሰፊ ጊዜ በመስጠት በአግባቡ ፈትሾ አስፈላጊውን ማሻሻያዎች እና ማስተካከያዎች አድርጓል። ቀጣዩም አገር አድን የትግል ትንቅንቅ ዘመን ውጤታማ እንዲሆን ጉባኤተኛው የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ተገባብቷል፤ ይህም ሁኔታየጉባኤተኛውን መንፈስ በከፍተኛ ሁኔታ አድሶታል።
ከዚህም በመነሣት ለመላው ህዝባችንና አገራችን ያለቺበት እጅግ አደገኛ ሁኔታ ለሚያሳስበው የህብረተሰባችን ክፍል በሙሉ የሚከተለውን ጥሪ ማቅረብ ይፈልጋል።
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
በቀደምት ሥርዓቶች በደረሰብህ የፍትህ፣ የእኩልነትና የነጻነት እጦት፣ የሥልጣን ባለቤትነትህ ተክዶ በገዛ ሀገርህ እንደ ጠላት እጅግ ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ ሲደርስብህ ኖረሀል። በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ግን በግፍ መኖር እራሱ ትልቅ ነገር ሆኖ፣ ሀገርም እንኳ ወደ ማይኖርህ ደረጃ እየወረደ በሚሄድ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለህ። ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7፣ ይህ የደረስንበት እጅግ አደገኛ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ለመድረስ የቻልነው፣ እስከ ዛሬ የነበሩ ሥርዓቶች፤ በሕዝብ ላይ የግፍ አገዛዝን በመጫን ሌላውን ዜጋ በማሰቃየት ሥራ የተጠመዱ ስለነበሩ እንደ ወያኔ ላለው ዘረኛና ዓምባገነን ቡድን መንገድ በመጥረጋቸው ነው ብሎ ያምናል። ከዚህ መሰረታዊ እውነታ በመነሳትም ነው ንቅናቄያችን በዋናነት፤ የሀገራችን ትንሳኤ የሚጀመረውና ተጠናክሮ የሚቀጥለው የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት በሚያረጋግጠው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ብቻ ነው የሚል መድምደሚያ ላይ የደረሰው። ስለሆነም፤ ንቅናቄያችን ሀገራችን ኢትዮጵያን ካንዣበበባት አደገኛ ሁኔታ የማዳንና የዴሞክራሲ ሥርዓትን በሀገራችን ለማስጀመር የጀመረውን እቅስቃሴ አጠናክሮ ለመቀጠል፣ እንዲሁም ጉባኤው የደረሰበትን ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ በሚያደርገው ሕዝባዊ እቅስቃሴዎች፣ በምትችለው ሁሉ ከጎኑ እንድትቆም ጥሪውን ያቀርባል።
ህወሀት/ኢህአዴግን ለምትቃወሙ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ!
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከዚህ ቀደምምባደረጋቸውም ሆነበእዚህ ጉባኤ በድጋሚ ያረጋገጠው፤ ንቅናቂያችን ለሥልጣን የሚታገል የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን፤በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ፣ሥልጣን ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በዕኩልነት ተወዳድረው በሕዝበ-ውሳኔ የሚዳኙበትንሀገራዊ የፖለቲካ ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ የሚሰራ መሆኑን ነው።በመሆኑም ከንቅናቄያችን ጋር በየትኛውም ደረጃ በጋራ በመንቀሳቀስ ሀገራችንን ከተጋረጠባት የጥፋት አደጋ አድነን ሕዝብ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ጥያቄዎቹን የሚፈታበትን ስርዓት በጋራ ዕውን እንድናደርግ የንቅናቄያችን ጉባኤ ልባዊ ጥሪውን ያቀርባል።
ለህወሀት (ኢሕአደግ) ግንባርና አጋር ድርጅቶች ዓባላት በሙሉ፣
በተለያዩ ምክንያቶች የወያኔ ከፋፋይ የዘውግ ፖለቲካ ለብሄሮች እኩልነት የሚሰራ መስሏችሁ ከወያኔ ጋር የተሰለፋችሁ ወገኖች፤ ውሎ እያደር በተግባር እንዳያችሁት ግን ህወሀት/ኢህአዴግ የሚተጋው ዘውጎች በእኩልነት እንዲኖሩ ሳይሆን፣በወያኔ አሽከርነት ሰጥ ለጥ ብለው እንዲገዙ ጫናውን ዕለት ከዕለት እየጨመረ መሆኑን በገሃድ እያያችሁነው። ይህ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እየተሳተፋችሁበት ያለው የአገዛዝ ሥርዓት፤ ወከልነው በምትሉት ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የግድያ፣ የእስራት፣ የማፈናቀል፣ የማዋረድ፣ የማሸማቀቅ የግፍ ስርዓትና በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ እና በአገር ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት ይብቃ ብላችሁ፣ ንቅናቄያችን በሚያካሂደው የአገር አድን እቅስቃሴ ውስጥ በሚቻላችሁ ደረጃ እና ሁኔታ ሁሉ በመሳተፍ ሀገራችንን በጋራ ለመታደግ እንድትሳተፉ ጉባኤያችን ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ለኢትዮጵያ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት ዓባላት በሙሉ፣
የወያኔ ዘረኛና አምባገነን ሥርዓት፤ እድሜውን የሚያራዝመው፣ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚታገለው ወገናችሁ ላይ በየጊዜውና በየቦታው አሰቃቂ ርምጃ እንድትወስዱ በማድረግ ሲሆን፣ በሌላው ጎኑ ይህ ሥርዓት ከአናቱ እየፈረሰ መሆኑ ደግሞ ከእናንተ የተሰወረ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በቅርብ የምታውቋቸው አለቆቻችሁ ከሲቪል አቻዎቻቸው ባልተናነሰ ሁኔታ በከፍተኛ ዘረፋ በተዘፈቁበት አጸያፊ ድርጊት ምን ያህል ሀብት እንዳካበቱ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን ታውቃላችሁ። ስለዚህ የእናንተ ከዚህ ከበሰበሰና ሊወድቅ እያዘመመ ካለ ሥርዓት ጋር መቆም፤ በሀገራችሁ እና በወገናችሁ ላይ ከሚያስከትለው ሰቆቃ በሻገር፤ እናንተም የስርዓቱ አሰቃቂ ርምጃዎች አስፈጻሚ እና ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆናችሁ የተለየ ሀላፊነትን አሸክሟችኋል። በመሆኑም የወያኔን ያበቃለት የአገዛዝ ሥርዓት ዛሬውኑ ትታችሁ እና በሚቻላችሁ ሁሉ በሕዝብ ላይ የምታደርሱበትን ሰቆቃ አቁማችሁ፣ ከወገናችሁ ጎን እንድትቆሙና በምትችሉት አጋጣሚ ሁሉ ንቅናቄያችንን እያካሄደ ያለውን ትግል እንድታግዙ፤ ከተቻለም ንቅናቄያችንን እድትቀላቀሉ በራችን ክፍት መሆኑን ጉባኤያችን ያረጋግጥላችኋል።
በመጨረሻም፣ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7፤ ከጳጉሜ 1 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ መስከረም 1 2010 ዓ.ም ድረስ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔዎች፣ አገራችን ኢትዮጵያ ሁላችንም በእኩልነት የምንኖርባት አገር ለማድረግና የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ትግል እስከ መጨረሻው በጽናት እንደሚገፋ ቃል ኪዳኑን አድሷል። በተጨማሪም ጉባኤው የንቅናቄያችንን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስፈልገውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ሂደት እንዲጀመርና አገር የማዳኑም ትንቅንቅ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጀመረውን እንቅስቃሴ እስከዳር ለማድረስ የገባውን ቃል ኪዳን እንደገና በማደስ በዲሞክራሲያዊ ሂደትና በከፍተኛ ስኬት ጉባኤውን አከናውኗል። በያዝነው 2010ዓ.ም የአገራችንን ትንሳኤ በአስተማማኝ ደረጃ ለማስጀመር የሚያስፈልገውን ድርጅታዊ ሁኔታ ማመቻቸቱን ጉባኤው በድጋሚ ያረጋግጣል።
መልካም አዲስ ዓመት ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ!
አንድነት ሀይል ነው!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነት ለዴሞክራሲ ንቅናቄ፣
መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም

በአማራ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ተጠቆመ

በአማራ ክልል ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ህዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ እንደሚችል
ተጠቆመ፡፡ የክልሉን ህዝብ አስተዳድራለሁ ባዩ ብአዴን፣ ከወልቃይት ጋር የተያያዘ መሬት ለትግራይ
አሳልፎ መስጠቱ ብዙዎችን እያስቆጣ ይገኛል፡፡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ከሆነ፣ ብአዴን መሬቱን
ለትግራይ ክልል መንግስት ወይም ለህወሓት አሳልፎ መስጠቱ ከተሰማ ወዲህ፣ በአማራ ክልል
ከፍተኛ ቁጭት አጭሯል፡፡ ውሳኔውን የተቃወሙ የአማራ ተወላጆች በማኅበራዊ ሚዲያ
ተቃውሟቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡


ሐሙስ ጳጉሜ 2 ቀን 2009 ህወሓት ከብአዴን ጋር በሰጠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹ከዚህ በኋላ
የወልቃይት ጉዳይ አብቅቶለታል፡፡›› በማለት ከድንበር ጉዳይ ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ
መቋጨቱን ገልጸው ነበር፡፡ ምንም ዓይነት ህዝባዊ ውሳኔ ባልተካሔደበት ሁኔታ፣ በህወሓት ትዕዛዝ
ተመርቶ መሬቱን ለትግራይ ክልል አሳልፎ የሰጠው ብአዴን፣ ከክልሉ ተወላጆች ከፍተኛ ተቃውሞ
እየገጠመው እንደሚገኝ ታውቋል፡፡


‹‹ብአዴን የአማራን ህዝብ እያስጠቃ ይገኛል›› ያሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ ለራሱ አሽከር መሆኑ
ሳያንሰው ህዝቡንም የህወሓት አሽከር ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለትግራይ ክልል
ተላልፈው የተሰጡት ጎቤ እና ግጨው የተባሉት የድንበር አዋሳኝ መሬቶች የአማራ ክልል ሀብት
መሆናቸውን የክልሉ ተወላጆች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም በብአዴን አማካይነት መሬቱ ለማይመለከተው
ህወሓት ተላልፈው ተሰጥተዋል-ይላሉ ታዛቢዎቹ፡፡ ይህን ህገ ወጥ ድርጊት ለመቃወምም በቅርቡ
ህዝባዊ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል ከአማራ ክልል የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ላይ ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውጊያ መደረጉ ተገለጸ

በሶማሌ ልዩ ሃይልና በኦሮሞ አርሶአደሮች መካከል በተደረገው ውጊያ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው የታወቀ ሲሆን አንደኛው የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ወደ አዳማ ሆስፒታል መወሰዱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ውጊያው መኢሶን በተባለች ከተማ አቅራቢያ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች መካሄዱ ተገለጿል።

በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የተሳካ የአድማ ጥሪ ያደረጉት የኦሮሞ ወጣቶች በቀጣይ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወጣቶች ጋር ለመስራት እየተዘጋጁ መሆናቸውን በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል።

ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ በአንዳንድ አከባቢዎች ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ግጭት የተፈጠረ ሲሆን መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውንም ለማወቅ ተችሏል።

ባለፈው ሳምንት ለ3 ቀንየተደረገው ከቤት ያለመውጣት ተቃውሞ 1ኛው ምክንያት በሱማሌ ልዩ አይል በህወሀት ትህዛዝ የሚደርሰው ሰብሀዊ ጥሰት በመቃወም ነበር

እነ ጀዋርያን ግባችን ላይ ደርሰናል ቢሉም የኦሮሞ ልጆች እስካሁን የተገደሉ ነው የህወሀት ዘረኛና ጨካኝ ስርሀት እስካልተወገደ ድረስ በየተናጥልም የምናደርገው ትግል አቁመን በጋራ ለጋራ አላማ እስካልታገልን ድረስ ወገኖቻችን በአረመኔው አገዛዝ መገደላቸው አይቀርም ..