የተመድና የአውሮፓ ህብረት በአገሪቱ የተፈጸሙ ግድያዎችን ለማጣራት ያቀረበውን ጥያቄ የወያኔ መንግስት ሳይቀበለው ቀረ

ሁለቱ አለም አቀፍ ተቋማት ማለትም የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት ባለፈው አመት በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሃይል ዕርምጃ በመውሰድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ሲገልጹ ቆየተዋል።
ይኸው የጸጥታ ሃይሎች ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲካሄድበትና ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ለፍትህ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
ይሁንና ከቢቢሲ ጋር ቃለምልልስን ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ከአውሮፓ ህብረት የቀረበውን የምርመራ ጥያቄ እንደማይቀበለው አስታውቀዋል።
መንግስታዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉዳዩን በቸልተኝነት የሚመረምር አካል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸውን አቋም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሚሽኑ ገለልተኛ ነው ቢሉም አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በመንግስት የሚካሄደው ምርመራ ነጻና ገለልተኛ እንደማይሆን ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛል።
የአለም አቀፉ ማህብረሰብ ጥያቄን እንደማይቀበሉ የተናገሩት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሃገሪቱ ሉዓላዊነት መከበር ይኖርበታል ሲሉ በቃለ-ምልልሳቸው አስረድተዋል።
ለአንድ አመት ያህል በኦሮሚያ ክልል የዘለቀውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከ700 የሚበልጡ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ሂውማን ራይስት ዎችና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሃላፊ የሆኑት ዘይድ ራድ አል ሁሴን የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሰልፈኞች ላይ ቀጥተኛ የተኩስ ዕርምጃ መውሰዳቸውን በቅርቡ አመልክተዋል።
በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ቃለምልልስን ያደረጉት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ ለአራት ወር እንዲራዘም የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጋጋትን እያመጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይሁንና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ድረስ በእስር ላይ እንደሚገኙና ለህግ እንደሚቀርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አተገባበር የሚከታተለው ኮማንድ ፖስት ወደ አምስት ሺ የሚጠጉ ሰዎች ከህዝባዊ ተቃውሞው ጋር በተገናኘ በቅርቡ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
አሁንም ድረስ በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች አለመረጋጋት በመኖሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም መደረጉን ኮማንድ ፖስት አመልክቷል።

የሱዳን ወታደሮች ወያኔን ለመርዳትና የነፃነት ሀይሎችን ለመውጋት ኢትዮጵያ ገቡ!

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው ወያኔ የባርነት እረገጣ ያስመረረው ህዝብ በጉበዝ አለቃ እራሱን አደራጅቶ ድር ቤቴ ብሎ ጫካ ከገባበት ቀን አንስቶ የተለያዩ ጥቃቶችን በአገዛዙ ላይ ሲያደርስ ቆይታል፥፣

የአካሄዱንም አድማስ በማስፋት ቀንደኛ የሆኑትን ያገዛዙ ባለስልጣኖችን በህዝብ ላይ የመከራ ቀንበር ጥለው የተደላደለ ንሮ በሚኖሩ ካድሬወች እና የስርአቱ አሹክሻኪወች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ የቆረጠው የጉበዝ አለቃ ገዱ እና አለምነን መኮንን ያላዳች ቅድመ ሆኔታ ከስፍራው ለቀው እንዲወጡ ጥብቅ መልእክት እንዲደርሳቸው አድርገዋል፣፣

ይህን የመጨረሻ የሆነውን መልእክት ሰምተው እራሳቸውን ከስፍራው እንዲያስወግዱ የተነገራቸው የህዝብ ጠላቶች ህዝብን ለትግራይ ወንበዴ ለማስጨፍጨፍ የሱዳንን ጦር እንዲረዳቸው ወያኔ የሱዳኑን አልበሽርን ኢትዮጵያ ድረስ ጠርቶ ያናገረው የትግራይ ፋሺስት ወያኔ የአገዛዙ ዘመን ከእጅ እያመለጠው እንደሆነ የተረዳው ባንዳ በአልበሽር ይሁንታ ወታደሮችን የኢትዩጵያን ድንበር ጥሰው መግባታቸው ታውቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የነፃነት ሀይሎች በነሱም ላይ አይቀጡ ቅጣትእንደሚቀጣቸው አስገንዝበዋል፣፣

የሱዳን ወታደር አይደለም ጣሊያንን ያንበረከኩ የጉበዝ አለቆች ዛሬም በሰሜን የተነሳውን አውሎ ንፋስ ማንም እንደማያስቆመው ተናግረዋል ።

ቀጣዩ ኢላማ የሆነው የወያኔ ስሪት የሆነው ብአዴን አለምነ መኮንን እና ደጉ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስታውቀዋል፣፣

ህዝብን ለባርነት ማግዶ መኖር አይቻልም ያለው የጉበዝ አለቃ የቆረጠ በትግራይ የጨካኝ እጆች ሳይቀጠፍ ላገር ለወገን የሚሆን የጅግንነት ትግል እድርጉ መሰዋት የክብር ሞት ነውና የሱዳን ጦር ገባ አልገባ ከጀመርነው የመኖር ወይም ያለመኖር ትንንቅ ማንም እንደማያስቆማቸው ተናግረዋል።

ከጉበዝ አለቃ ምድር መላኩ እሸቱ

ማዕከላዊ ከጎንደር ታፍነው በሚገቡ ንፁኃን ዜጎች ከፍተኛ ስቃይ ተሞልቷል

ማዕከላዊ ከጎንደር ታፍነው በሚገቡ ንፁኃን ዜጎች ከፍተኛ ስቃይ ተሞልቷል…የሞት አፋፍ ላይ ናቸው፡፡ በስልክ ተጠልፈው የተያዙ ብዙ ናቸው፡፡ በተለይ አርማጭሆ ትልቅ ትኩረት ተሰጦት እየተለቀሙ ነው። እናም ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።
፨፨ ከአርማጮሆ በጣም ያረጁ ሴቶች ሳይቀር በሰፊው ተይዘው እየገቡ ነው። እጅግ በዘገነነ ሁኔታ ሌት ተቀን በሞት አፋፍ ሆነው ከፍተኛ ድብደባ ላይ በመሆናቸው የነሡን ሲቃ እየሰሙ ሁሉም እስረኛ እንቅልፍ እንኳን አይተኛም። ሌላውም እንዲሰማ ጣራ ላይ ተረኛ ፖሊሶች ጠጠር በመወርወር እንቅልፍ ይነሳሉ፡፡ ስለዚህ መረጃው በተጣራው መሠሰረት በስልክ ተጠልፈው እና የሸፈቱትን አምጡ ተብለው ነው የሚሰቃዩት፡፡ ስለሆነም የግድ የማንቂያ ስራ ይሰራ፡፡ ከመያዝ 10 እጥፍ ታግሎ መሞት ይሻላል የሚል በቁጭት የተሞላ መረጃ ነው የወጣው።

፨፨የማእከላዊ የግፍ እስረኞች በፍርድ ስም በድጋሜ የሚቀጡበት አራዳ ምድብ ችሎት!

አራዳ ምድብ ችሎት በመባል ግዙፍ ስም ግን ባዶና የፈረሰ ገላጭ ታፔላ እንኳ የሌለው በጣም የፈራረሰ ከመደበኛው ፍ/ቤት ከመድረሳቸው በፊት በቀጠሮ ብቻ በማመላለስ ፍትህ ሳይሆን ተጨማሪ መረጃ በእጅ ካቴና ሁለት እና ሶስቶችን አጣምሮ በማሰር የሚቀበሉበት። ከመደበኛው ፍርድ ቤት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው። በማዕከላዊ የሚሰቃዩትን የፖለቲካ እስረኞች በትግራይ ተወላጆች በሆኑ ዳኞች አማካኝነት በማመላለስ ፍትህ የሚሰጡ በመምሰል የሐሰት የዳኝነት ካባ በመልበስ ለማዕከላዊ ቅልብ ደብዳቢዎች ተጨማሪ ድብደባ እንዲፈፀምባቸው ባሳዛኝ ሁኔታ መረጃን ተቀብለው የሚያስተላልፉ የአንድ መንደር ስብስብ ዳኞች ግቢ በፎቶው እዩት፡፡

20 ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ያለ ገለልተኛ አካል ድርድር እንደማይኖር አስታወቁ

ፓርቲዎቹ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 9፣ ቀኑን ሙሉ ባደረጉት ውይይት ቀደም ሲል በዙር መድረክ እየመራን እንደራደር የሚል ሃሳብ ያቀረቡ ተቃዋሚዎች አቋማቸውን ለውጠው፣ ድርድር ያለ ገለልተኛ አደራዳሪ አይሆንም ሲሉ የተፈጠሙ ሲሆን ኢህአዴግና አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በዙር መድረክ እየመራን መደራደር አለብን በሚል አቋም በመጽናታቸው መግባባት ላይ ሳይደረስ ቀርቷል። ይሄን ተከትሎም ኢህአዴግ ጉዳዩን በድጋሚ ለማጤን ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን በመጪው ረቡዕ መጋቢት 20፣ አቋሙን እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡
የቅዳሜውን ውይይት አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የመኢአድ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ፤ በእለቱ ሁሉም ተቃዋሚዎች ገለልተኛ አካል ያደራድረን የሚል አቋም መያዛቸው ያልጠበቁት መሆኑን ገልፀው፤ “ፓርቲያችን በአደራዳሪዎች ገለልተኛነት ላይ የተሸራረፈ አቋም የለውም›› ብለዋል፡፡ ኢህአዴግ አቋሙን ካልቀየረ የድርድሩ ቀጣይነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረውም አቶ ሙሉጌታ አስታውቀዋል፡፡
የኢዴፓ ዋና ፀሃፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ በበኩላቸው፤ ከአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በስተቀር ሌሎቹ ገለልተኛ አካል ያደራድረን የሚለው አቋማቸው የፀና መሆኑን ጠቁመው፤ ኤዴፓም ይሄን አቋም እንደማይቀይር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ገለልተኛ አካል ካላደራደረ ኢዴፓ በድርድሩ ሊቀጥል አይችልም›› ብለዋል – አቶ ዋሲሁን፡፡
“ኢህአዴግ ወደ ብዙኃኑ አቋም ይመጣል የሚል ተስፋ አለኝ” ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ፤ የድርድሩ ቀጣይ እጣ ፈንታ በኢህአዴግ እጅ ነው ብለዋል፡፡
21 ፓርቲዎች የሚያደርጉት ስብሰባ ውይይት እንጂ ድርድር ሊባል አይችልም የሚል አቋሙን ያፀናው መድረክ በበኩሉ፤ በዚህ ሁኔታ በድርድሩ እንደማይቀጥል የአመራር አባሉ አቶ ጥላሁን እንደሻው ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል። መድረክ ለገዥው ፓርቲ ሁለት አማራጮችን ማቅረቡን የጠቆሙት አቶ ጥላሁን፤አንደኛው ተቃዋሚዎች በመድረክ እንዲወከሉና ከኢህአዴግ ጋር እንዲደራደሩ አሊያም ኢህአዴግ ከሌሎቹ ጋር ከሚያደርገው ድርድር ጎን ለጎን ለብቻው ከመድረክ ጋር እንዲደራደር ሀሳብ አቅርቦ ምላሹን በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢህአዴግ ለዚህ ፍቃደኛ ካልሆነ መድረክ ከ21 ፓርቲዎች ጋር  ለድርድር እንደማይቀርብና ከድርድሩ እንደሚወጣ አቶ ጥላሁን አስታውቀዋል፡፡
‹‹ምንም ውጤት ያላመጣውን የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን የሚመስል ውይይት እንዲደረግ አንፈልግም” ያሉት የአመራር አባሉ፤ ‹‹የህዝቡን ችግር ነቅሰን አውጥተን ተጨባጭ መፍትሄ እንዲሰጥባቸው ነው የምንፈልገው” ብለዋል፡፡ ‹‹የታሰሩ ፖለቲከኞችም እንዲፈቱ ከተፈለገ ጠንካራ ድርድር ማድረግ አለብን›› ሲሉም አክለዋል፡፡

በሚሊዬን የሚቆጠር ህዝብ በተራበበት ኦሮሚያ፣ ኦህዴድ በዓሉን በከፍተኛ ወጪ እያከበረ ነው

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተመሰረትኩበትን 27ኛ ዓመት ‹‹እያከበርኩ ነው›› አለ፡፡ ድርጅቱ የምስረታ በዓሉን የሚያከብረው ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ እንደሆነም መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ፣ ድርጅቱ የምስረታ በዓሉን ለማክበር በሚሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ በጅቷል፡፡ በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ በተራበበት ኦሮሚያ በሚሊዬን የሚቆጠር በጀት በጅቶ፣ የፈንጠዝያ በዓል ለማክበር መዘጋጀት ከሞራል አንጻር አስነዋሪ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የገባው ድርቅ አራት ክልሎችን ክፉኛ እየጎዳ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ድርቅ ከገባባቸው ክልሎች በተጊጂዎች ቁጥር ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው ኦሮሚያ ክልል ሲሆን፣ በክልሉም 2 ነጥብ 3 ሚሊዬን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል፡፡ ዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፉን እንዲያደርግ ተማጽኖ በሚቀርብበት በዚህ ወቅት፣ የክልሉን ህዝብ ‹‹አስተዳድራለሁ›› ባዩ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት፣ ተመስርቶ የትም ላልደሰረ ድርጅቱ የምስረታ በዓል ብሎ የመደበው ገንዘብ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ሊውል እንደሚገባ አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡
በእነ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ በእነ አቶ አባዱላ ገመዳ እና በሌሎችም ተማራኪ የደርግ ወታደሮች አማካይነት ለህወሓት የፖለቲካ ዓላማ ሲባል የተመሰረተው ኦህዴድ፣ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ‹‹አሁን ላይ የኦሮሞ ህዝብ የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ የጭቆና ቀንበሩን ከጫንቃው አንስቶ፣ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እኩል መብት የተጎናፀፉባትን ሀገር እውን አድርጓል፡፡›› ሲል ለመሳለቅ ሞክሯል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በራሱ አንድ የጭቆና ቀንበር መሆኑን የገለጹት አስተያየት ሰጪዎች፣ ገዳይ አዋጅ በጫንቃው ላይ እንዲሸከም የተፈረደበት ህዝብ ‹‹ከጭቆና ነጻ ወጥቷል›› መባሉ አስቂኝ መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ኦህዴድ ራሱ ህወሓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የጫነው የጭቆና ቀንበር መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡ በአስቸኳይ አዋጅ ስር በምትገኝ ሀገር ውስጥ የሚከበርም ሆነ የተከበረ የህዝቦች ነጻነት እንደማይኖር የሚገልጹ ወገኖች በበኩላቸው፣ በተለይ ደግሞ የከፋ ግድያ እና እስራት ከተፈጸመበት የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንዲህ ያለው መግለጫ መውጣቱ እንደሚያበሳጭ ይገልጻሉ፡፡

BBN

%d bloggers like this: