የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ

ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ  የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡

የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው እንደ አንድ ምክንያት መነሳቱን ያስረዳሉ፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ አንዳንድ አስተያት ሰጪዎች ለሦስቱም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነት መነሳት የአመራር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ችግሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡ 

በሥነ ሕይወት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዓሣ ዕርባታ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ታገሠ ጫፎ እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ከ2000 እስከ 2003 ዓ.ም. መስከረም ድረስ ብቸኛው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣ እንዲሁም ወደ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊነት እስከተዛወሩበት ህዳር 2005 ዓ.ም. ድረስ አራተኛው ምክትል ርዕስ መስተዳድር ሆነው ቆይተዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በላይ በኃላፊነት የቆዩበት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አንዳንድ ሠራተኞች፣ ‹‹ከአራት መቶ በላይ ሠራተኞች ያሉበትን ቢሮ ሲመሩ አንድም ቀን ሠራተኞችን ሰብስበው አናግረው ችግር የፈቱበት ጊዜ አልነበረም፡፡  ግንኙታቸው ከሥራ ሒደት ባለቤቶች ጋር ስለነበር ዕርምጃም የሚወስዱት ከነዚያ ሰዎች በሚያገኙት መረጃ ብቻ ነበር፤›› በማለት በርካታ ሠራተኞች ሳያውቁዋቸው እሳቸውም የሚያስተዳድሩዋቸውን ሠራተኞች በቅጡ ሳያውቁ መነሳሳታቸውን ይናገራሉ፡፡

እስከ መስከረም 2003 ዓ.ም. ድረስ የደኢሕዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን የክልሉን የፖለቲካ እንቅሰቃሴን ሲመሩ የቆዩትና ከዚያ በኋላ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ የነበሩት አቶ አለማየሁ አሰፋ፣ ‹‹ሜትሮ ፖሊታን›› የተሰኘውንና የሐዋሳ ከተማ አስተዳዳር 70/30 (ሰባ በመቶ ብሔር ብሔረሰቦች ተዋፅኦ፣ ሰላሳ በመቶ በሲዳማ ተወላጆች እንዲዋቀር) ባለፈው ሚያዚያ 2004 ዓ.ም. አዘጋጅተው ለውይይት ያቀረቡት መመርያ በተለይ በሲዳማ ተወላጆች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እንዳስከተለባቸው ይታወሳል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ አፈትልኮ የወጣውን ያንን መመርያ የዞኑ ሕዝብ ዘንድ በመድረሱ በወቅቱ ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሮ ነበር፡፡ በቅርቡ የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የማረጋጊያ መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው፡፡

አቶ አለማየሁ አሰፋና አቶ ሳኒ ረዲ ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባለፈው ሐምሌ 2005 ዓ.ም. ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሥራ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ አግኝተው የተመረቁ ሲሆን፣ በአመራር ብቃት ማነስ ስለመገምገማቸው የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡

     ሦስቱም ከኃላፊነት የተነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሮች ለሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ከተዋጡት ዘጠኝ አባላት ውስጥ የሚገኙ ቢሆንም፣ ኢሕአዴግ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ባህር ዳር ከተማ ባደረገው ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎና አቶ ደበበ አበራ በመተካካት መርህ መነሳታቸው ይታወሳል፡፡ አቶ ታገሠ ከንግድ ኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊነት ለወራት ብቻ ወደ መሩት ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የተዛወሩት ከባህር ዳር ጉባዔ በኋላ መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የተነገረላቸው እነዚህ ሦስቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የካቢኔ አባላትም እንደሚኖሩበት ምንጮች ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ በምትካቸው የሚሾሙትን ተተኪዎች አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ በመጪው መስከረም 2006 ዓ.ም. በሚደረገው ጉባዔ ላይ ይፋ በማድረግ በምክር ቤቱ እንደሚያፀድቁ  ይጠበቃል፡፡ 

የደቡበ  ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ

ethiopian reporter

posted by Aseged Tamene

“አዜብን ማሰር፣ መለስን ከሞት ቀስቅሶ ለፍርድ ማቆም ነው”

መለስ ዜናዊ ሆን ብለው ለፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያ ሲገለገሉበት በነበረው “የሙስና ባህር” ያልተነከረበት የለም። ባህሩ ውስጥ ያልዋኘ የለም። ከባህሩ ራሳቸውን ያገለሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የባህሩ ዋናው አጥማቂና የውሃው ባለቤት እንደሆኑ በርካታ ምስክሮች አሉ።

አቶ መለስ “ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን” ትተው ካለፉ በኋላ አገሩን አከርፍቶት የነበረው የሙስና ባህር በስንጥር መነካካት ተጀመረና አሁን ቁንጮዎቹ ግድም ደርሶ እያሸበረ ነው። ይህንኑ የሙስና ማዕበል ተከትሎ የባለቤታቸውን ውርስ ታኮ ያደረጉት ወ/ሮ አዜብና በተሸናፊው የፖለቲካ መስመር ያሉ ሁሉ ተሸብረዋል። አንዳንድ ጥቆማዎችና የህዝብ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ወ/ሮ አዜብ ታውከዋል።

ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ከነሱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት “ባለሃብቶች” መካከል ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር እንደሚነግዱ የሚታወቁ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የስጋታቸው መነሻና እምብርት ስለመሆኑ አብዛኞች ይስማማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ያለታክስ በሚገቡ ምርቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ በቴሌ የህገወጥ ማስደወል ወንጀል፣ በጫት ኤክስፖርትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በስፋት ቢዝነስ እንደሚያጫውቱ የሚታወቁት ወ/ሮ አዜብ በገንዘብ የከበሩትን ያህል በርካታ ጠላት እንዳፈሩም የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።

azeb 2ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ያስረከቡት አቶ ስብሃት ነጋ በተደጋጋሚ ስለሙስና መናገር የጀመሩት አቶ መለስ አፈር ሳይቀምሱ ነበር። ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ጡንቻና በዘመቻ በጀት ተመድቦለት “ባለራዕይ፣ ታላቁ መሪ” በሚል የተሰጣቸውን የሸቀጥ ስም ተገን አድርገው ሙስና ውስጥ መነከራቸውን የሚያውቁት አቶ ስብሃት ስም አይጥቀሱ እንጂ ነገራቸው ሁሉ ከወ/ሮ አዜብ ደጅ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሚናገሩት የአደባባይ ምስጢር ነው።

አቶ ስብሃት ነጋ ከመለስ ሞት በኋላ ይህንኑ አቋማቸውን አጠንክረው የገፉበት ቢሆንም በፖለቲካ አሰላለፋቸው ተሸናፊ በመሆናቸው ለማፈግፈግ ተገደው እንደነበር የሚናገሩ አሉ። ከውስጥ አዋቂዎች እንደሚሰማውና በተባራሪ እንደሚነገረው አቶ ስብሃት ዳግም አሸናፊውን ቡድን ተመልሰው ተቀላቅለዋል። ለዚህም ይመስላል እሳቸው ምን ያህል የጸዱ ስለመሆናቸው መረጃ ባይኖርም አሁን ከተጀመረው የሙስና ዘመቻ ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቆመው። አንዳንዶች እንደሚሉት ህወሃት በትከፋፈለ ጊዜ (ዘመነ ህንፍሽፍሽ) አቶ አባይ ጸሐዬ ውህዳኑን ተቀላቅለው መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ አቶ መለስን በመቀላቀል የተጫወቱትን የ”መንታ”/ደብል/ ስልት፣ የመለስ ሞትን ተከትሎ ለተነሳው የሃይል ሰልፍ ትንቅንቅ አቶ ስብሃት ነጋም ተጠቅመውበታል። በዚሁ ስልታዊ አካሄድም የእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ክንፍ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ አስችለዋል።

አዜብ መስፍን ለምን አይታሰሩም?

ከሙስና ጋር ስማቸው በስፋት የሚነሳው ወ/ሮ አዜብ፤ በባለቤታቸው እንደ ቪኖ ቡሽ ድንገት ሲፈተለኩ በሃዘን ድባብ ውስጥ ሆነው የጀመሩት ዘመቻ የቀልድ መሃላ ይዘት ያለው ነው። በ”ፖለቲካ ቁጭ በሉ” እንዲመለኩ የተደረጉትን አቶ መለስን ደጋግሞ በመጥራት አዜብ መስፍን “የመለስ ራዕይ ካልተቀየረና ሌጋሲው እስካልተበረዘ ድረስ …” እያሉ ካድሬውንና ቀሪውን የህወሃት ሰዎች መማጸን ላይ አተኩረው ነበር። በሄዱበትና ባገደሙበት የባለቤታቸው ስምና ዝና ላፍታም ካንደበታቸው የማይለያቸው ወ/ሮ አዜብ ጀርባቸውን ስለሚያውቁት የመለስን ስም የሚያንጠለጥሉት ራሳቸውን ለመከላከል እንደሆነም ከታች እስከ ላይ ስምምነት አለ።

ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከደረሱት አስተያየቶች መካከል “ካድሬው ባብዛኛው፣ የበላይ አመራሩ በከፊል አዜብስ?” በማለት ለምን በቁጥጥር ስር እንደማይውሉ የሚጠይቁትና የሚነጋገሩት በገሃድ ነው። ይሁን እንጂ አዜብ ለምን እንዲታሰሩ የፍርድቤት ትዕዛዝ (ዋራንት) አይቆረጥባቸውም? ለሚለው የሚሰጠው መልስ “የመለስ ሌጋሲ እንዳይወድም፣ እንዳይቆሽሽ፣ የተሰራው የረከሰና የሸቀጥ ያህል በፖለቲካ ውዳሴ የተገነባው ከንቱ ዝና እንዳይቆሽሽ፣ ብሎም ሌላ ጥያቄ እንዳያስነሳ ነው” የሚል ነው።azeb 1

አቶ ስብሃት ሲመሩት የነበረው ኤፈርትን በሳቸው አዲስ አመራርና በመለስ ልዩ አመራር ሰጪነት በሺህ ለሚቆጠሩ የትግራይ ልጆች የስራ እድል ማዘጋጀቱን፣ ትግራይ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች እንደሚከፈቱና ሲደበቅ የነበረው በጀት በዶላር ተሰልቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን በማድረግ ስብሃት ነጋን የማሳጣት እጅ አዙር ዘመቻቸውን አጣድፈው የጀመሩት ወ/ሮ አዜብ የትግራይን ህዝብ ልብ ለማግኘትና አቶ ስብሃት የሚከፍቱባቸውን ዘመቻ አስቀድሞ ለመቋቋም በማሰብ ነበር።

ህወሃት የክልሎችን በጀት እልብ አድርጎ የሚጠባበት የብር ማሽኑ የሆነውን ሜጋ ኢንትርፕራይዝን ይመሩ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከምርጫ1997 በኋላ በድርጅት አቋም፣ በአቶ መለስ ፊርማና ውሳኔ እንዲነሱ መደረጉን፤ ከሃላፊነት የተነሱበት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አኩርፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው “በሽማግሌ” ከባለቤታቸው ጋር እንደታረቁ፣ ሽምግልናውን ባከናወኑት ሰው አማካይነት ወ/ሮ አዜብ የተነጠቁት ሹመት እንዲመለስላቸው መደረጉን እንደሚያውቁ የሚናገሩ ክፍሎች “ኢትዮጵያ ውስጥ ህግና ፍትህ ለሰከንድ ቢተገበር ህገወጥ ስልክ በማስደወል የሜጋን ቢሮ ለዋና ማቀናበሪያና የተጠቀሙበት ወ/ሮ አዜብ የመጀመሪያዋ ተጠያቂ ሊሆኑ በተገባ ነበር። የመለስ ሌጋሲ እንግዲህ ይህን ነው” በማለት ይጠይቃሉ።

እነዚህ ክፍሎችም ሆኑ ሌሎች ወገኖች አዜብ መስፍን የፖለቲካ ሃይላቸው የተቦረቦረ፣ ከበዋቸው የነበሩት ሃይሎች የተመናመኑ፣ እንደ ተርብ የሚናደፈው አንደበታቸውና ባህሪያቸው እንደበረዶ የቀዘቀዘበት ወቅት ላይ እንደሚገኙ እየተገለጸ ነው። በጸለመ ልብስ የሚታዩትና የሃዘን ጥቁር ልብሳቸውን ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት ወ/ሮ አዜብ ተቅለስላሽ ሰው ሆነው መታየታቸው ስጋታቸው ማየሉን የሚያሳይ እንደሆነ የሚመሰክሩት ክፍሎች “አዜብ መስፍን ወዳጅ እንደሌላቸውና በተለይም በህወሃት ሰዎችና ካድሬዎች ዘንድazeb-mesfinስለማይወደዱ ዙሪያቸውን ከሚዞራቸው የሙስና ደወል ማምለጥ ስለሚችሉበት ሁኔታ ሊያስቡ እንደሚችሉ እንገምታለን” ይላሉ። ለአብነትም ሲያኮርፉ ወደ ሳዑዲ እንደሚሄዱና በዱባይ ሪል ስቴት እንዳላቸው ስለሚታሙ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደዚያው ሊያመሩ እንደሚችሉ ምልክት እንዳለ ይጠቁማሉ። በዱባይ አላቸው ስለሚባለውና በሌሎች ተቋራጭ ድርጅቶች ስም ስለተገነቡት ቤቶችና ንብረቶቻቸው እነዚህ ክፍሎች ለጊዜው ዝርዝር አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በሌላ ወገን ግን አሁን የባለቤታቸውን የፋውንዴሽን ስራ እንዲሰሩ የተመደቡት ወ/ሮ አዜብ የእነ በረከት ስምዖን ቡድን በመሆናቸው፣ ለዚሁ ቡድን ቀኝ እጅ የሆኑት የደህንነቱ አውራ አቶ አሰፋና ሸራተን ያሉት ባለሃብት እጅግ ወዳጃቸው በመሆናቸው ቀስ በቀስ እንዲከስሙ ይደረጋል እንጂ አይታሰሩም ሲሉ በድፍረት ይናገራሉ። ወ/ሮ አዜብን ማሰር ማለት አቶ መለስን ከመቃብር አውጥቶ እንደገና ፍርድ አደባባይ የማቅረብ ያህል እንደሆነ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች “ታላቁ፣ ባለራዕዩ፣ አስተዋዩ፣ አርቆ አሳቢው፣ የደሆች አባት፣ ራሱን ‘ለኢትዮጵያ’ አንድዶ የሞተ፣ አንዲት ሃሳብ ይዞ ወደ (ኢትዮጵያ) ምድር የመጣው አዳኝ፣ እረፍት የማያውቀው፣ ዜጎቹን በቀን ሶስቴ እንዲበሉ ያስደረገው፣ የአፍሪካ አንደበት፣ የዓለም ቅርስ፣ የወደፊቱ ኢትዮጵያ ተምሳሌት፣ የታሪክ አውራ፣ እርምና ወንጀል የሌለበት … በማለት ህወሃት ሆን ብሎ የገነባውን ስም አዜብን በማሰር አፈር አይከተውም” በማለት አዜብ ሊታሰሩ የማይችሉበትን ምክንያት ያመላክታሉ።

የመጨረሻው መጀመሪያ

birhane

ብርሃነ ኪዳነማርያም

ወ/ሮ አዜብ የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ስለመሆናቸው ምልክቶች እንዳሉ የሚጠቅሱ አሉ። ያለ ከልካይ ሲመሩትና ሲነዱት ከነበረው ግዙፉ የህወሃት የገንዘብ ቋት ኤፈርት ተሰናብተዋል። ወንበራቸውን እንዲቀሟቸው የተደረጉት የዋልታ ኢንፎርሜሽን ዋና ስራ አስኪያጅና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የሆኑት ብርሃነ ኪዳነማርያም (ብርሃነ-ማረት) የቀድሞው የፍቅር ወዳጃቸው ናቸው። በደህንነት ውስጥ አድራጊና ፈጣሪ የነበሩት የቅርብ የንግድ ሸሪካቸው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የሚጠየፉትን ወህኒ ገብተውበታል። በከፍተኛ የንግድ ቅርርብና ሽርክና የሚወዳጇቸው አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር ከታሰሩ ወራት ተቆጥሯል። የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ከቀረጥ ነጻ በመፍቀድ አብረዋቸው በኤፈርት ታርጋ ገንዘብ ሲያልቡ ኖረው አሁን ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። የቴሌ የሙስና ቅሌትና በኦሮሚያ የመሬት ንግድ አብረዋቸው ሲሳተፉ የነበሩ ሁሉ ዋራንቲ ተቆርጦባቸው እስር ቤት ገብተዋል። እንግዲህ በዚህ ሁሉ መዓት ውስጥ ያልተነኩት ወ/ሮ አዜብ ብቻ ናቸው።

ለፌደራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ በምርመራ ወቅት ወ/ሮ አዜብን በትዕዛዝ ሰጪነትና በንግድ አጋርነት ዋና ተባባሪ መሆናቸውን በማመልከት መስክረዋል። ከዚህም በላይ በርካታ ጥቆማ አለ። በነዚህና በበርካታ ምክንያቶች ጣት የተቀሰረባቸው ወ/ሮ አዜብ አሁን የቀብርና የተስካር፣ ሙት ዓመት ዘካሪና የማስታወሻ ግንባታ ኮሚቴ ሃላፊ ሆነው ተቀምጠዋል። የመጀመሪያው መጨረሻ “መገለል” እንደሆነ፣ ከዚያም እውነተኛው መጨረሻ ሊገጥማቸው እንደሚችል ግምታቸውን የሚሰጡ ተበራክተዋል። “ከቶውንም አይታሰሩም። ለመለስ ሲባል “የሚሉት ደግሞ መጨረሻቸው ከኢህአዴግና አሁን ካለው የቡድን ፍትጊያ ጋር እንደሚሆን ይናገራሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

posted by Aseged Tamene

ጓደኛውን በገጀራ ቆራርጦ የጣለው ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ነው

በተስፋሁን ብርሃኑ
ፖሊስና ርምጃው

‹‹እኔ ስራ አስገብቼው ሳለ ለአለቃዬ ዘወትር ስለ እኔ መጥፎ ነገር ይናገራል ያለውን ጓደኛውን ሶስት ቦታ ቆራርጦ የጣለው በፍርድ ቤት ጉዳዩ እየታየ ነው፡፡

ተጠርጣሪ ሀጎስ ገብሩና ሟች አምሳሉ ምትኩ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 ልዩ ቦታው አራት ኪሎ ዩንቨርሳል ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኙ ነበር፡፡ ተጠርጣሪው ‹‹ዋና ፀባችን ነው ያለው እኔ ስራ አስገብቼው ልወደድ በማለት ዘወትር ስለ እኔ መጥፎ ነገር መናገርና እያመሸ እየመጣ ስራ ተበድሏል በማለት ያጣላኝ ነበር›› ብሏል፡፡ በምርመራ ወቅት፡፡ ይሄኔ ቂም የያዘው ተጠርጣሪ ሀጎስ ገብሩ ከሁለት ወር በፊት ለግድያ መዘጋጀት ይጀምራል፡፡

ለግድያ የሚያስፈልገውንም ከብረት የተሰራ ገጀራ ከመርካቶ እንደገዛ ተናግሯል፡፡ ሟች አምሳሉ ሲመጣ ‹‹እባክህ ራት በልቼ ልምጣ ስለው ባትበላ ምን አገባኝ አፈር ብላ ብሎኝ ወጣ›› ይላል ተጠርጣሪው በምርመራ ወቅት፡፡ ሟች በዚሁ ቀን አምሽቶ ሲመጣ በደሉ በዛብኝ ያለው ተጠርጣሪ በሩን ከከፈተለት በኋላ ሟችን በሩን እንዲዘጋው ከነገረው በኋላ ፊቱን ወደ በሩ ሲያዞር በያዘው ገጀራ ፊቱን ይመታዋል፡፡ ከዚያም ከመሬት ከወደቀ በኋላ አንገቱ አካባቢ ሲመታው ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ተጠርጣሪው የሟችን አስክሬን ውሃ ወዳለበት ቦታ በመውሰድ በገጀራው ወገቡንና ሁለት እግሮቹን ቆራርጧል፡፡ ከወገብ በላይ አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኝ ድልድይ መሻገሪያ ውስጥ የጣለው ሲሆን ግራና የቀኝ እግሩን ደግሞ በቢጫ ኩርቱ ፌስታል ጠቅልሎ የሚሰሩበት አካባቢና ብርሐንና ሰላም ማተሚያ ቤት ከፍ ብሎ በሚገኘው ሳጠራ ጠጅ ቤት አካባቢ ሊጥለው ችሏል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰው መግደል ወንጀል መርማሪ ቡድን ወንጀሉ በተፈፀመ ሰሞን ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገ ቅንጅት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ችለዋል፡፡ መርማሪ ግሩም ታረቀኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ የግድያ ወንጀል መርማሪ አስፈላጊውን የሰውና የሰነድ ማሰረጃ አሰባሰበው ካጠናቀቁ በኋላ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መዝገቡን ልከው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

freedom4ethiopian

posted by Aseged Tamene

መንግስት ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ለሁለት ቀናት የቆየ ልዩ ሰልጠና ሰጠ:;

መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙትን ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ለሁለት ቀናት የቆየ ልዩ ስልጠናና ቅፅ 09 የተሰኘ የአባልነት መታወቂያ መስጠቱን ምንጮች አስታወቁ፡ የተሰጠው መታወቂያም ለአምስት አመት የሚያገለግል የአባልነት መታወቂያ መሆኑ ታውቋል፡፤

ለነሃሴ 26 በእለተ እሁድ በአዲስ አበባ በእያንዳዱ ወረዳ አስር አስር ሺ ሰዉ ባጠቃላይ በአዲስ አበባ ሁለት መቶ ሺ ሰዉ የሚሳተፍበት “አሸባሪነትን እንዋጋ!” በሚል መሪ ቃል የኢህአዴግ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ያዘጋጀ ሲሆን ቅድመ ዝግጅቱንም ማጠናቀቁን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ይህንን የተቃውሞ ሰልፉንም የሚመሩትም ለሁለት ቀናት የተሰጠውን ልዩ ስለጠና በመካፈል ቅፅ 09 የተሰኘ መታወቂያ የተሰጣቸው አባሎች እንደሆኑ ታዉቋል::

በተያያዘም በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በጥቃቅን አና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ማህበራት በሙላ፣የመንግስት እና ቀበሌ ሰራተኞች፣የኢህአዴግ የሁሉም ሊግ አባላት፣የቴኳንዶ ማሰልጠኛ ተቋማት ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎች ማህበራት አንዲካፈሉ ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የማይካፈል ማህበርም ሆነ ተቋም በመንግስት የፍቃድ ስረዛ በማድረግ እርምጃ እንደሚወሰድ የተገለጸላቸው ሲሆን ደጎስ ያለ አበልም አንደሚሰጣቸው ተገልፆላቸዋል፡፤

ድል ለኢትዬጲያ

Abu Dawd Osman

posted by Aseged Tamene

የኢሳት የውይይት መድረክ ከየት ወዴት!!?

ይህ ርዕስ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በቀጣይነት ብዙ ልንወያይባቸው የሚገቡ ሃሳቦችን ይጠቁማል፤ እኛም ለወደፊት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ የምንል መሆኑን ከወዲሁ ማሳወቃችን አስፈላጊ ነው። ስለሆነም ለመንደርደሪያነት ይጠቅም ዘንድ ለዛሬ ሃሳባችንን ባጭሩ እንደሚከተለው ጠቆም አርገን ማለፍ ግድ በመሆኑ አነሆ እንላለን።
የኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን ትላንት እሁድ በአሜሪካን ሃገር በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚያወያይ ስብሰባ ማዘጋጀቱን ሁላችንም ሰምተናል፣ አይተናልም። ይህ ዝግጅት ሁሉንም የኢትዮጵያውያን አስተሳሰቦች ለማስተናገድና፤ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት በጋራና በቅንጅት ትግሉን በማስኬድ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ካለበት የኢህአዲግ የባርነት አገዛዝ ቀንበር ውስጥ ለማውጣት፤ ብሎም የሃገራችንን እንደ ሃገር የመቀጠል ህልውና ከጥፋት ለመታደግ በሚል ቅዱስ ሃሳብ የተነሳ በመሆኑ፤ እሰየሁ ሊባል እንደሚገባ ሁላችንንም ያስማማል። በተለይ ባሁኑ ጊዜ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ ዋናው ምክንያት፤ ለሃገሪቱም መጥፋት ሌት-ተቀን የሚሰራውን ኢህአዲግን መጋበዙ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው ይገባል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ተቃዋሚ ሃይሎች በተደጋጋሚ እንደሚነግሩን፤ “ገዢው ፓርቲ ለውይይት ፈቃደኛ አይደለም፤ ተወያይተን መፍትሄዎችን በጋራ እናምጣ ብለን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ኢህአዲግ ፊቱን አዙሮብናል፤…” ሌላም ሌላም ተመሳሳይ ወቀሳዎችን ሲገልጹ ማየትና መስማት ለኢትዮጵያውያን አዲስ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ኢህአዲግ የሃገሪቱን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ለመጠበቅ በሚል ሰበብ የጎረቤት ሃገራትን ፤ ኤርትራን ጨምሮ ፤ ዳጎስ ያሉ ጉርሻዎችን እያቀረበ ሲማጸን ማየቱ ለኢትዮጵያውያን የተለመደ ትዝብት ሆኗል። እንደኛ አረዳድ ይህን መሰሎቹ የተቃዋሚ ሃይሎች ወቀሳዎች እውነት ከሆኑ፤ የኢህአዲግ መንግስት ያልተረዳው ዋናው ቁምነገር፤ ማንኛውም የሃሳብ ልዩነት በመወያየት ወደ ስምምነት መምጣት ካልተቻለ፤ ወደ ሌላ ትልቅ ልዩነት አድጎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚመኘውን ዘለቄታዊ ሰላም ማምጣት ፈጽሞ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ነው። በርግጥ ኢህአዲግ የተሳነው የፖለቲካ ተቃዋሚ ሃይሎች የሃሳብ ጉልበትን መለካትና ማወቅ መቻል ነው። ነገር ግን አበው “የናቁት…” እንዲሉ ከኢህአዲግ ልንማርና አካላዊ የጉልበት ልዩነቶችን ከማስተናገድ ይልቅ የሃሳብ ልዩነቶችን ለማስተናገድ ብንጥር የተሻለ ነው እንላለን።
ይህንን የኢሳት መድረክ የዝግጅት ሂደቶችን በተመለከተ ብዙ የታዩ የግድፈት መረጃዎች ቢኖሩንም ብዙ ከማለት መቆጠቡ ለጊዜው አስፈላጊ ስለመሰለን ወደ ዝርዝር ሁኔታዎች አንሄድም። ነገር ግን እዚህ ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ፤ የኢህአዲግ ካድሬዎች እንደሚሉን “ሺሺ… ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም…” ሊሆን ስለሚችል፤ ኢሳቶችም ይህንን ማሰብ ይችሉ ዘንድ እንመክራለን። የኢህአዲግ መንግስት በህዝብ ላይ እየጫነ የሚገኘውን ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልት፣ ግድያ ፣ እንዲሁም ሌሎች አሰቃቂ በደሎችን ለማስቆም በጋራ መፍትሄዎችን እንፈልግ ዘንድ እናሳስባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ስምንቶቹ

posted by Aseged Tamene