ሰበር ዜና: በጎንደር የተነሳው ውግያ ተባብሷል! – ከታች አርማጨሆ ህዝብ ወደከተማ እየገባ ነው

ማራኪ እየተባለ በሚጠራው የጎንደር 18 ቀበሌ የተነሳው ውግያ እየተባባሰ መምጣቱን የ ኢ.ኤም. ኤፍ ዘጋቢ ከስፍራው አስታውቋል:: ዛሬ ማለዳ በጎንደር ህዝብ እና በሀወሃት ታጣቂዎች በተነሳው በዚህ ውግያ በርካታ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ማለቃቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል::
ለውግያው ምክንያት የሆነው ልዩ የተባለው ጦር ከቀበሌ 18 (ማራኪ) የወልቃይት የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ከሚቴዎችን አፍኖ ለመውሰድ በመሞከሩ መሆኑን ከስፍራው የነበሩ የአይን ምስክሮች የገለጹ ሲሆን ይህንን በአይነ ቁራኛ ይጠባበቅ የነበረው ህዝብ መንገዶችን በሙሉ ዘግቶአቸዋል::

ህዝቡ “ጸጉረ-ልውጦች” ያላቸው እነኝህ ባእድ ወታደሮች በንጹኃን ዜጎች ላይ የጥይት እሩምታ ከፍተዋል፡፡ የአካባቢው ፖሊሶች እና ወታደሮች ከህዝቡ ጎን በመሆን ውግያው ላይ እንዳልተሰተፉም መረጃዎች ጠቁመዋል::

ማምሻው ላይ የደረሰን ዘገባ መሰረት ከሳንጃ (ከታችኛው አርማጨሆ) ህዝብ በአውቶብስ እና በልዩ ልዩ ትራንስፖርት እየተሳፈረ ወደ-ጎንደር በመግባት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ቤትን የጎረፈ ነው:: ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አስተባባሪ ከሚቴዎች አንዱ ሲሆኑ ለወያኔ እጅ አልሰጥም በማለት ልዩ ከተባሉት የወያኔ ወታደሮች ጋር እየተፋለሙ ናቸው:: ወታደሮቹ ሞርታር እና ላውንቸር እየተጠቀሙ መሆነቸው ነው እየተሰማ ያለው::

እየተረገጥን ማንነታችንን ከምንቀማ ሞትን እንመርጣለን ያለው የጎንደር ህዝብ ወረራውን ለመከላክል አደባባይ ወጥቷል:: በግጭቱ በርካታ ህዝብ አልቋል:: “ሰላም ባስ”ን ጨምሮ በርካታ የህወሃት ተቋማትም በመጋየት ላይ ነቸው::

ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ግዜ ውግያው ተባብሷል:: በሺዎች የሚቆጠሩ የታች አርማጨሆ ቆለኞች መሳርያቸውን እያነገቡ ወደ ከተማው በመጉረፍ ላይ ናቸው::

በሁኔታው የተደናገጡት የህወሃት ባለስልጣናት ባንኮችንና የደህንነት ተቋማት በደንብ እንዲጠብቁ ለውታደሮቻቸው ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

መላው የጎንደር ህዝብ በነብስ ወከፍ መሳርያ መታጠቁ አይዘነጋም::

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: