ሰበር ዜና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባሁኑ ሰዐት ሰሜን ሸዋ ናቸዉ

አቶ ገዱ አንዳርጋቸውማጀቴ የተገደሉባትን ወገኖች ገዳዬች ለፍርድ ይቅረቡ ተብሎ ወደ ፊት ሊወጣ የታሰበውን ተቃውሞ ሰልፍ እና የማጀቴን ሕዝብ ጥያቄ ለማኮላሸት ወያኔ አቶ ገዱን ተደማጭነት ይኖራቸዋል በማለት ወደ ሰሜን ሸዋ ላከብን ይላሉ የሰሜን ሸዋ ማጀቴ ኗሪዎች ።
አቶ ገዱ ባሁኑ ስዐት ከሠሜን ሸዋ ም/አስተዳዳሪ ከአቶ ተፈራ ጋር እየዞሩ ይገኛሉ ፡፡
ሕዝቡም ሰልፋችን ወንጅለኞች ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ ፤ ጥያቄአችን እስካልተመለሰ ድረስ በድርድር የምንቆምበት ምንም ምክኒያት የለንም በማለት እየመከረ ነው ።

ለመላው የሰሜን ሸዋ ሰው ተነስ በሉልን ያለው የማጀቴ ሕዝብ መላው ያማራ ሕዝብም ከጎኑ እንዲቆምና ድጋፉን እንዲያሳየው ጥሪውን አስተላልፏል ።

Aseged

ሰበር ዜና: በጎንደር የተነሳው ውግያ ተባብሷል! – ከታች አርማጨሆ ህዝብ ወደከተማ እየገባ ነው

https://soundcloud.com/dceson-radio/dceson-radio-breaking-news-july-12-2016?fb_action_ids=1235145806529896&fb_action_types=soundcloud%3Apublish

ማራኪ እየተባለ በሚጠራው የጎንደር 18 ቀበሌ የተነሳው ውግያ እየተባባሰ መምጣቱን የ ኢ.ኤም. ኤፍ ዘጋቢ ከስፍራው አስታውቋል:: ዛሬ ማለዳ በጎንደር ህዝብ እና በሀወሃት ታጣቂዎች በተነሳው በዚህ ውግያ በርካታ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ማለቃቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል::
ለውግያው ምክንያት የሆነው ልዩ የተባለው ጦር ከቀበሌ 18 (ማራኪ) የወልቃይት የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ከሚቴዎችን አፍኖ ለመውሰድ በመሞከሩ መሆኑን ከስፍራው የነበሩ የአይን ምስክሮች የገለጹ ሲሆን ይህንን በአይነ ቁራኛ ይጠባበቅ የነበረው ህዝብ መንገዶችን በሙሉ ዘግቶአቸዋል::

ህዝቡ “ጸጉረ-ልውጦች” ያላቸው እነኝህ ባእድ ወታደሮች በንጹኃን ዜጎች ላይ የጥይት እሩምታ ከፍተዋል፡፡ የአካባቢው ፖሊሶች እና ወታደሮች ከህዝቡ ጎን በመሆን ውግያው ላይ እንዳልተሰተፉም መረጃዎች ጠቁመዋል::

ማምሻው ላይ የደረሰን ዘገባ መሰረት ከሳንጃ (ከታችኛው አርማጨሆ) ህዝብ በአውቶብስ እና በልዩ ልዩ ትራንስፖርት እየተሳፈረ ወደ-ጎንደር በመግባት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ቤትን የጎረፈ ነው:: ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አስተባባሪ ከሚቴዎች አንዱ ሲሆኑ ለወያኔ እጅ አልሰጥም በማለት ልዩ ከተባሉት የወያኔ ወታደሮች ጋር እየተፋለሙ ናቸው:: ወታደሮቹ ሞርታር እና ላውንቸር እየተጠቀሙ መሆነቸው ነው እየተሰማ ያለው::

እየተረገጥን ማንነታችንን ከምንቀማ ሞትን እንመርጣለን ያለው የጎንደር ህዝብ ወረራውን ለመከላክል አደባባይ ወጥቷል:: በግጭቱ በርካታ ህዝብ አልቋል:: “ሰላም ባስ”ን ጨምሮ በርካታ የህወሃት ተቋማትም በመጋየት ላይ ነቸው::

ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ግዜ ውግያው ተባብሷል:: በሺዎች የሚቆጠሩ የታች አርማጨሆ ቆለኞች መሳርያቸውን እያነገቡ ወደ ከተማው በመጉረፍ ላይ ናቸው::

በሁኔታው የተደናገጡት የህወሃት ባለስልጣናት ባንኮችንና የደህንነት ተቋማት በደንብ እንዲጠብቁ ለውታደሮቻቸው ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

መላው የጎንደር ህዝብ በነብስ ወከፍ መሳርያ መታጠቁ አይዘነጋም::

በኤርትራ ምድር በምርኮ ተይዘው የሚገኙ የወያኔ ወታደሮች አርበኞች ግንቦት ለመቀላቀል እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

በቅርቡ በፆረና ግንባር ወያኔ በቆሰቆሰው ጦርነት በኤርትራ ወታደሮች ተማርከው በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያወታደሮች የኦሮሞና የአማራ እንዲሁም ከተለያዩ ብሄሮች የተውጣጡት ወደዚህ ጦርነት የገቡት በትግሬ የጦር አዛዦች አስገዳጅነት መሆኑን በመናገር

የኤርትራ መንግሥት ይቅርታ የሚያደርግላቸው ከሆነ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ዘረኛውን ገዳዩን የወያኔ ስርዓት ለመዋጋት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ከኤርትራ ምድር የወጣው መረጃ በታማኝ ምንጮቻችን በኩል ሊረጋገጥ ችሎዋል።

የጦር ምርኮኞቹን ጉዳይ አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ በአቶ ጌታቸው ረዳ‬ በኩል የተሰጠው ምላሽ

<<ምንም የተማረከ ወታደር የለም እንዲያው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እስከ 200 ሜትር ድረስ ለትንኮሳ የመጡትን የኤርትራን ወታደሮች እያሳደደ አጥቅቷል>>

የሚል እንደነበር የሚታወስ ነው።

የነዚህን የኢትዮጵያ ምርኮኛ ወታደሮች የወደፊት እጣ ፈንታ አስመልክቶ የኤርትራ መንግስት ምን ሊወስን እንደሚችል እስካሁን ድረስ ምንም የታወቀ ነገር ባይኖርም በጉዳዩ ዙሪያ የኤርትራ ባለስልጣናት ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር ሊነጋገሩበት እንደሚችሉ መረጃውን ካደረሱንታማኝ ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።

Aseged Tamene pictursAseged Tamene pictur

Aseged Tamene

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት ኰሚቴ፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ አዲስ ህግ አጸደቀ

እአአ ባለፈው ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በ114ኛው ኮንግሬስ ላይ የቀረበውና የጸደቀው ህግ፣ በኢትዮጵያ ሁሉን ያካተተ አስተዳደር እንዲኖርም ያበረታታል። የቴኔሲው ሬፓብሊካን ሴናተር ቦብ ኮርከር ህጉን በመደገፍ፣ ዋናውን የህጉን አቅራቢ ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲንን፣ እንዲሁም ተባባሪ አቅርቢ ሴናተሮችን አመስግነዋቸዋል።

የS.Res.432 የሰብዓዊ መብት ማስከበሪያ ህግን ከሜሪላንዱ ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲን ጋር በመተባበር ያቀረቡት፣ የዴልዌሩ ዲሞክራት ክሪስቶፈር ኮንስ፡የማሳቹሴትሱ ዲሞክራት ኤድዋርድ ማከርይ፡ የኒው-ጄርሲው ዲሞክራት ቦብ መንደዝ እንዲሁም የፍሎሪዳውን ሬፓብሊካን ሴናተር ሩብዮ ናቸው፣ የሴናተር ኮርከርን ምስጋና ያገኙት።

የቴኔሲው ሬፓብሊካን ሴናተርና የውጪ ግንኙነቱ ኰሚቴ ሊቀ-መንበር ሴናተር ቦብ ኮርከር ስለ ህጉ በሰጡት አስተያየት፣ ይህን ብለዋል።

“ይህ ውሳኔ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ባለን የጋራ ግንኙነት ውስጥ ጠቃሚ ናቸው ለምንላቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጥ ህግን ያካተተ ነው። ሁሉን ያካተተ የመልካም አስተዳደርና የሰብዓዊ መብት አያያዝ ማሻሻል የመሰሉ፡ ከኢትዮጵያ በኩል መሰራት ያለባቸው ገና ብዙ ጉዳዮች አሉ።”

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት ዛሬም ቀጥሏል፣ ሁለቱም ሀገሮች ተጨማሪ ጦር እያንቀሳቀሱ ነው

by Aseged Tamene

በተጨማሪም  የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት ዛሬም ቀጥሏል፣ ሁለቱም ሀገሮች ተጨማሪ ጦር እያንቀሳቀሱ ነው

https://soundcloud.com/dceson-radio/7-patriotic-ginbot-7-press-release

መንግስት ግጭት አይሎ ከሚታይባት ፆረና አካባቢ በተጨማሪ በተለያዩ የድንበር አካባቢዎች ጦሩን በተጠንቀቅ እንዲቆም አድርጓል። “ኢትዮጵያ ወረራ ልትፈፅምብኝ ነው” ያለችው ኤርትራ ከጦር ሰራዊቷ ከፍተኛ ልምድ ያለውን ዕዝ በሶስት አካባቢዎች እንዲስፍር አድርጋለች። የኤርትራ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ክተት ሊያውጁ እንደሚችሉ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ ሁሉም የክፍለ ጦር አዛዦችን ወደ ግንባር እንዲንቀሳቀሱ የደረገች ሲሆን በእረፍት ላይ የነበሩ ሁለት ከፍተኛ አዛዦችም በአስቸኳይ ወደ ምድባቸው እንዲመለሱ ታዘዋል።

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለሁለት አስርት አመታት በቀኝ ግዝት ይዞ የቆየዉ ይህዉ የወያኔ ቡድን በተለያየ የሐገሪቷ ክፍሎች ከገባበት የጦር አጣብቂኝ ዉጥረት የተነሳ ሲሸሸዉና ሲሸሽገዉ የነበረዉን ጦርነት ሳይወደዉ በግዱ እየተጋፈጠዉ ይገኛል።

በዚህ ጦርነት ወያኔ ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበት የተረጋገጠ ሲሆን የ 25ኛ ክፍለ ጦር የደጀን ጦርን ለማጠናከር በሚል ወደ አዉድማዉ ተጠግቷል።
በጦርነቱ የደረሰዉ የጉዳት መጠን ያልተረጋገጠ ከመሆኑ ባሻገር ከትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን መከላከያ ዘመቻ ስምሪት መምሪያ አካሎች የተገኘዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ በወያኔ በኩል የተሞከረዉ ትንኮሳ በተዘዋዋሪ መንገድ በኤርትራ ከሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ጋር እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ድንበር ዘለልነቱ የኤርትራ ወታደሮችንም ተሳታፊ እንዳደረጋቸዉ እንዲሁም እንደሚያደርጋቸዉ በጉልህ ያሳየ ነዉ።

በአፍሪካ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ልዩ ሬንጀር ኮርስና የበረሃና የከተማ ልምምድ ስልጡን ሐይል የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የጦርነት ትንኮሳ ወደ ፈጸመባቸዉ አካባቢዎች መንቀሳቀሱን ምንጮች እየጠቀሱ ይገኛሉ!
በተልይም የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን ወታደራዊ ምንጮች ከዉስጥ እንደጠቆሙት በህወሃት ወታደሮች ክንፍ አጥብቆ የሚፈራዉ በሜጀር ጄነራል ዳዊት አብረሃ የሚመራዉ ብዛት ያለዉ የኤርትራ ሰራዊት መንቀሳቀሱን ሲሆን….
ህወሃት ኢትዮጵያዊነት የሚሰማቸዉ በወያኔ ሰራዊት ዉስጥ የሚገኙ ወታደሮችን ጥያቄ ለማስተናገድ ወታደራዊ ፖለቲካ ክፍሉ እንደተሳነዉ እየተገለጸ ይገኛል።
ሰራዊቱ ለወራቶች ዉጊያዉን በተመለከተ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ቢደረግለትም በትንኮሳዉ ጦርነት ላይ ያለ አግባብ የሚደረግ ደም መፋሰስ መሆኑን እየገለጸ እንደሚገኝ ያሳወቁት ወታደራዊ ምንጮች ህወሃት በዚህ ከቀጠለች ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ህዝብ ጋር በምታደርገዉ ግብ ግብ ወታደሩ የሚያደርገዉ እገዛ እጅግ አናሳ ከመሆኑ የተነሳ ከወዲሁ አጣብቂኝ ዉስጥ ገብታል ተብላል