ሰበር ዜና ጎንደር በተኩስ ስትናጥ አርፍዳለች።

በጎንደር ከተማ ብቻ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ የገደለውን ሰው ብዛት ማንም ቆጥሮ አይዘልቀውም፡፡ ይህ ሥርዓት በ85/86 ዓ.ም. በአዲስ ዓመት ዋዜማ አደባባይ ኢየሱስ ገብቶ ከ60 በላይ ምዕመንን ረፈረፈ፤ የቤተ መቅደስ መጋረጃዎች በደም የጨቀየ የቤተ መቅደስ መወልወያ ሆነ፡፡ የሞተ አስከሬን የከፈን ጨርቅ ሆነ፡፡ በ2006/7 ዓ.ም. ጥረው ግረው የሠሩትን ቤት በገንፎ ቁጭ አካባቢ አፈራረሰ፤ ብዙ ሰዎችንም በጠራራ ፀሐይ ገደለ፡፡ በ2008 ዓ.ም. ማረሚያ ቤት አቃጥሎ በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ከ100 የሚልቁ ዐማሮችን በጅምላ ጨረሰ፡፡

ይኸው ዛሬ የማኅበራዊ ሚዲያን ዘግቶ የጎንደር ዐማሮችን ለመጨፍጨፍ በንጹኃን ሰዎች ላይ የጥይት እሩምታ ከፍቷል፡፡ ከፊል የወልቃይት የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ከሚቴዎችን አፍኖ ወስዷል፤ ቀሪዎችን ለመውሰድ በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ አካባቢው ከቧል፡፡ አንድ የወልቃይት ዐማራ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል ገብቷል፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ በየአደባባዩ ያፈሰሱት ደም ቆሌያቸውን የሚያረካው አልሆነም፡፡

ሞት ለዐማራ ሕዝብ አዲስ አይደለም፤ የፋሽስቱ የትግሬ መንግሥት ሃያ አምስት ዓመት ሲገድለው ኖሯል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ለሁሉም እየኖረ ብቻውን ሲሞት ነው ታሪክ የሚያውቀው፡፡ የጎንደር ዐማሮችም የወልቃይት ዐማራ የማንነት ኮሚቴዎችን (ያልተወሰዱትን) አሳልፈው እንደማይሰጧቸው አምናለሁ፡፡ እርግጥ ነው ወያኔዎች ብዙ ሰው ይገድላሉ፤ መቼስ ያልገደሉበት ጊዜ አለና፡፡

ይህ እብሪት በዐማራ ሕዝብ የተባበረ ክንድ የሚተነፍስበት ቀን ሩቅ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ስለራሳቸው መጻኢ እጣ ፈንታ ሲሉ ወገኖቻቸው በዐማራው ላይ የሚያደርሰውን በደል እንዲያቆሙ መናገር አለባቸው፡፡ እስካሁን የተዘረፈው፤ እስካሁን የተገደለው ከበቂም በላይ ነው፡፡ ጥጋብ ከልክ ካለፈ ያቅራል፡፡

ማሳሰቢያ፡ በአካባቢው ያላችሁ ዐማሮች መረጃዎችን በመለዋወጥ እንድትተባበሩ አሳስባለሁ፤ ገለልተኛ ነን የሚሉ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ይከታተሉት ዘንድም እጠይቃለሁ፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: