ተቃዋሚዎች የድርድር ቅድመ ሁኔታዎቻቸውን ገለጹ!!!የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ይጠይቃሉ

ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ቅድሚያ ሰጥተው ሊደራደሩባቸው የሚሿቸውን አጀንዳዎች ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን፤ ሁሉም ፓርቲዎች የጋራ አቋም ላይ ለመድረስ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡
መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲ፤ ከኢህአዴግ ጋር ወደ ሌላ ውይይት ከመግባታቸው በፊት የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እንደሚጠይቁ ገልጸው፤ ማንኛውንም የህዝብ ጥቅም በድርድሩ አሳልፈው እንደማይሰጡ ተናግረዋል፡፡
ኢዴፓ በበኩሉ፤ ከምንም አስቀድሞ፣ ላለፉት 25 ዓመታት ኢህአዴግ በተቃዋሚዎች ላይ ሲፈፅም የነበረውን የመብት ጥሰት አምኖ እንዲቀበል እደራደራለሁ፤ ብሏል፡፡
የመኢአድ ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን፤ በተጀመረው ድርድርና ውይይት ከተቃዋሚዎች ባሻገር በሀገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ቡድኖችና ግለሰቦችም መሳተፍ አለባቸው፤ የሚል አቋም እንዳለው ጠቁመው፤ “የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና በፖለቲካ ሰበብ የተመሰረተ ክስ እንዲቋረጥ” የሚሉ ጥያቄዎችን ለድርድር እናቀርባለን፤ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም፣ አሁን በስራ ላይ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳና የፀረ ሽብር አዋጁ ለፓርቲዎች እንቅስቃሴ እንቅፋት በመሆኑ እንዲፈተሽ ወይም እንዲሰረዝ የሚል አቋም ይዘው ወደ ድርድሩ እንደሚገቡ ዋና ጸሐፊው ጠቁመዋል።
መኢአድ በአገሪቱ ተከስቶ የነበረው ግጭት እንዲበርድና የፖለቲካ ድርድር እንዲካሄድ ተቋማት ጣልቃ ገብተው እንዲሸመግሉ፤ ለሁሉም ዋና ዋና የእምነት ተቋማት ማመልከቻ አስገብቶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አዳነ፤ በጎ ምላሽ የሰጠችው ግን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነበረች፤ ብለዋል፡፡
“ይህን የመሳሰሉ ጥረቶች ስናደርግ የቆየን በመሆኑ፣ ወደ ድርድሩ ልንገባ ችለናል፤” ያሉት አቶ አዳነ፤ “በአንዳንድ የማህበረሰብ ሚዲያዎች፣ መኢአድ የህዝብን ጥቅም አሳልፎ እንደሸጠ መቆጠሩ አግባብ አይደለም፤” ሲል ወቅሰዋል፡፡
ኢዴፓ በበኩሉ፤ ወደ ድርድር ከመገባቱ በፊት፣ ባለፉት 25 ዓመታት በተቃዋሚዎች ላይ ከህገ መንግስቱ ውጪ ለተፈፀመባቸው በደል መንግስት ተጠያቂ መሆኑንና ስህተት መስራቱን አምኖ መቀበል አለበት፤ የሚል አቋም መያዙን፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ አስታውቀዋል፡፡“ብዙዎቹ ሲጣሱ የነበሩ መብቶች፣ በህገ መንግስቱ ላይ የሰፈሩ ናቸው” የሚሉት አቶ ወንድወሰን፤ “መንግስት ህገ – መንግስቱን፣ በመጣስ ፓርቲዎችን ሲበድል መቆየቱን መቀበል አለበት፤” ብለዋል፡፡ “ህዝብ ሲያነሳቸው የነበሩ ሁሉም ጥያቄዎች መመመለስ አለባቸው” የሚል አቋም ይዞ ወደ ድርድሩ እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊው፤ እነዚህንም ለማሳካት በፅናት እንደሚደራደር አመልክተዋል፡፡
የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር፤ (በሊቀመንበርነታቸው ጉዳይ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ይጠበቃል) አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ በአርቲስት ዘለቀ ገሠሠ የሚመራ ቡድንን ጨምሮ ሌሎች ቡድኖች በተደጋጋሚ ለድርድሩ እንዲቀርቡ እያነጋገሯቸው እንደነበርና ጥሪውንም ከኢህአዴግ ሳይሆን ከነዚህ ወገኖች ይጠብቁ እንደነበር አብራርተው፣ አሁን በኢህአዴግ መጠራቱ ያልጠበቁት መሆኑን ይገልፃሉ።
ፓርቲያቸው ከዚህ ድርድር የሚጠብቀው ውጤት ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርአት የሚደረግ ሽግግር መሆኑን የጠቆሙት አቶ የሸዋስ፤ “ዋናው አላማችን ሃገርና ህዝብን ማዳን፣ የህዝብን ጥያቄ ማስመለስና ለህዝብ መብቶች መከራከር ነው፤” ብለዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በድርድሩ ተሳታፊ መሆን የነበረባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታሠሩ ሰዎች በቅድሚያ እንዲለቀቁ›› የሚል አቋም ይዞ ወደ ድርድሩ እንደሚገባ አቶ የሸዋስ አስታውቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥያቄ እንደሚያቀርብ አቶ የሸዋስ ጠቁመዋል፡፡
ፓርቲዎች፣ “ማን ድርድሩን ይምራ፤ እነማን ይታዘቡት፤ ሚዲያዎች እንዴት ይዘግቡት፤›› በሚሉ ጉዳዮችና በድርድሩ እንዲወያዩባቸው የሚፈልጓቸውን ርዕሠ ጉዳዮች በዝርዝር በማዘጋጀት እስከ ጥር 25 ለፓርላማ ጽ/ቤት እንደሚያስገቡ ይጠበቃል፡፡

 16265194_1624845137532016_2342086131720387933_n

የጋምቤላ ታጋች ህፃናት ለፖለቲካ ፎጆታ እየሆኑ ነው!

ህፃናቶቻቸውን እና እንስሶችን እንደፈለጉ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት የሚነጥቁባቸው ዞን ውስጥ ከፍተኛ ሹመኛ የሆነ ሰው ነው ያደረሰን።
ሚስጥሩን በደረስኩበት መረጃ መሠረት ገና ከዚህ በላይ የወረዳው ሰው ሁሉ ሊወሰድ ይችላል ይላል፡፡ ምክንያቶቹን እንዲህ ዘርዝሮ ልኮታል፡-
1. ለም የእርሻ መሬት ከእኛ እስከ አጎራባች አለ ይህን በሚያርሱ የወያኔ ኢንቨስተሮች ለበርካታ አመታት ከህይወት እስከ ንብረት መስዋትነት አስከፍሏቸዋል።

2. #ወያኔን ሊያሰጋ የሚችል ሁሉ እስካሁን በሙሉ ሃይል በየቦታው ባይንቀሳቀስም በወታደራዊ ጥናታቸው መሰረት ያሰጋልና ስለሚሉ እስከዛው እኛም የስጋት ምንጭ ተደርገን ስለምንቆጠርና ለጥቃትም በቀላሉ ተጋላጭ ስለሆንን ዘራችን የሚጠፋበት አደጋ ውስጥ ገብተናል።

3. ከደቡብ ሱዳን ውሎገብ የፈለግነውን የጦር መሳርያና የእለት ፍጆታ ሸቀጥ ያለስጋት እናስገባ ነበር። ያንንም ለማስቀረትና እኛል ለመፍጀት ነው።

4. የወያኔ ሴረኛ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር በጥበብ በመመሳጠር በግጦሽ በማመሳሰል ምንም የማያውቀውን ህዝቡን እያስገደለ ነው።

5. ለወረዳው ቅርብ በሆነ ሁኔታ የሠፈረው በትግራይ ኃላፊዎች ብቻ እንደፈለጉ የሚያዙት ልዮ ኃይል፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ሽምቆች እንዲሁም መከላከያም አለ። የመጀመርያዋ ጥይት ሳትጮህ ለመከላከያ አዛዡ ተደውሎ ነበር እንደርሳለን ብለው አውቀው የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ፡፡

6. ቢያንስ በቅርብ ርቀት አስተማማኝ የአየር ኃይል አለ። ታድያ በትንሽ ደቂቃ ብቻ እስከ ወረዳው መድረስ ይችል ነበር ግን አልሆነም። ለምን አትበሉ። ዘር ፍጅቱ በወያኔ የተቀነባበረ ነው።
7. መሬታችንን ያለግብር የሚያርሱት የትግራይ ዜጎች ቢሆኑ ኖሮ የተጠቁት 57ቱ ወገኖቻችን ሳይመለሱ ተጨማሪ 16 ህፃናት መወሰዳቸው ሌሎችም ሊሞቱ ቀርቶ ደቡብ ሱዳንን በጨፈለቀ ነበረ፡፡
8. #በመጨረሻም የሱማሊያን አልሻባብ ተሻግሮ ለመግጠም ሰራዊት የሚልክ እንዲሁም አልፎ ላይቤርያና ሱዳን ሄዶ ሰላም አስከብራለሁ እያለ ኃይል የሚገብር የወንጀለኞች ጥርቅም ለራሳችን ዜጎች መሆን ሳይችል ይብስ ብሎ በአስቸኳይ አዋጅ ስም ሰላማዊ ህዝብ ሲያሸብርና ሲጨፈጭፍ ማየት እጅግ ያማል።
9. አሁን እኛም በስለናል። በተለይ የእኛን ወጣቶች በገፍ ለውትድርና የማያውቁትን ገጠራማው አካባቢ የሚመለምለው እንዳይሳካ ተግተን እየሰራን ነው። ለነፃነታችን መከበር ደቡብ ሱዳንን ሣይሆን ህዋህትን/ወያኔን ከአጋሮች ጋር ተደራጅተን እንታገላለን፡፡
ድል ለጭቁኑ ህዝብ! በማለት ይህን ብርቱ ሚስጥር ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለአለም እንዲታወቅ በአስቸኳይ ይድረስልን ብሏል።
ማሳሰቢያ፡-
ይህን ወደእንግሊዝኛና ወደተለያዪ ቋንቋወች በመተርጎም በቶሎ ስራ ልትጋሩ የምትችሉ በፍጥነት በውስጥ መስመር አግኙኝና የህዝባችንን ብሶት እናስተጋባ ለጋምቤላ ወገኖቻችን እንድረስላቸው።
አሁንስ ያማል!
ሙሉነህ ዮሃንስ11257193_1694823434078480_9109119436834128683_o

በባህር ዳር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከተቃጠሉ የመኪና ጋራዥ ባለቤቶች አንዱ በቃጠሎው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት poster-with-pic-a-%e1%88%9b%e1%8b%ad-14
በባህር ዳር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከተቃጠሉ የመኪና ጋራዥ ባለቤቶች አንዱ በቃጠሎው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። የትግራይ ተወላጅ የሆኑትና በባህር ዳር ከተማ ለረጅም አመታት የኖሩት በህዝብ ዘንድ አለሙ ገንዳ በሚል የሚታወቁት አቶ አለሙ ካህሳይ የታሰሩት በሳምንቱ መጀመሪያ ነው።
ግለሰቡ የተጠረጠሩትና ለእስር የተዳረጉት ባለፈው ቅዳሜ የአመፅ ወረቀት ሲበትኑ መያዛቸውን ተከትሎ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። አቶ አለሙ ካህሳይ ባለፈው ቅዳሜ “ትግሬዎች ተነሱ” የሚል ወረቀት ሲበትኑን በተመረጡ ሰዎች ቤት ሲያድሉ አለበል ካሴ በተባሉ የክልሉ ባለስልጣን እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ ጋራዡንም ራሳቸው ስለማቃጠላቸው መረጃ መገኘቱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ አለሙ ካህሳይ ወይንም አቶ አለሙ ገንዳ ከጋራዥ በተጨማሪ የቤት እቃዎች ማምረቻ ድርጅት ባለቤት ሲሆኑ፣ በአማራ ክልል ለሚገኙ በርካታ ት/ቤቶች የመማሪያ ጠረጴዛና ወንበር እንዲያቀርቡ ልዩ ድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱንም ምንጮች ገልጸዋል።
ሰኞ ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ አለሙ ካህሳይ ጋራዡን ያቃጠሉት ከኢንሹራንስ ጋር በተያያዘ ለሚገኝ ካሳ ይሁን በሌላ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ለትግራይ ተወላጆች “እንነሳ” የሚል ወረቀት ሲበትኑ መገኘታቸው ግለሰቡ ድርጊቶቹን የሚፈጽሙት በተቀነባበረ መንገድ በድርጅታዊ መዋቅር ይሆናል የሚል ጥርጣሬ መጋበዙም ተመልክቷል።
ግለሰቡ ድርጊቱን የሚፈጽሙት በህወሃት መመሪያ ከሆነ፣ ግለሰቡ ሲታሰሩ ህወሃቶች እንዴት ዝም አሉ የሚል ጥያቄ እየተነሳ ሲሆን፣ በድርጊቱ አፈጻጸም ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች በግልጽ የታወቀ ምላሽ የለም።
ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አቶ አለሙ ካህሳይ ወይንም አለሙ ገንዳ ንብረት በማውደም እንዲሁም የዘር ቅስቀሳ በማድረግ ተወንጅለው በምርመራ ላይ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።

ሕወሓት በሕዝቡ መካከል አዲስ ግጭት ለመፍጠር መሬት እየጫረ ነው ! አዳዲስ ግጭት ለመፍጠር የአከላለል እርማቶች የሚሉ በሌሎች ክልሎች ላይ ያተኮሩ ዜናዎች ሰሞኑን ጠብቁ

ትናንት የራስ ደሸኑን ተራራ ጉዳይ ከ6ኛ እና 10ኛ ክፍል መማርያ መፃሕፍት ላይ ተጠቅሶ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እንዲነገር የተደረገበት ዋና ዓላማ ይህንን ተከትሎ በሌሎች ክልሎች መካከል አዲስ መተራመስ ለመፍጠር ታስቦ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።የራስ ዳሸንን እንዳረምን ሁሉ እየተባለ በሌሎች ክልሎች ለምሳሌ በኦሮሞ እና ሱማሌ፣ በአፋር እና ሱማሌ እና በአማራ እና ኦሮሞ መካከል የአከላለል ስህተት ነበር እየተባለ ሰሞኑን አዳዲስ ግጭት ለመፍጠር የአከላለል እርማቶች የሚሉ በሌሎች ክልሎች ላይ ያተኮሩ ዜናዎች ሰሞኑን ጠብቁ።
ለእዚሁም ተግባር በክልሎች መጋጠምያ ወረዳዎች ደረጃ ካድሬዎች ሥራ እንዲሰሩ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ለመስራት ሲሞክሩ ከርመዋል።አላማው የተነሳበትን ተቃውሞ ወደ ህዝቡ መሃል ወርውሮ ፋታ ለማግኘት ነው። ነገር ግን አይሳካም። ምክንያቱም ሕዝብ አሁን ያለው አስተዳደር እስከ ወረዳ ድረስ ያለውን ምንም አይነት ሕጋዊ ዕውቅና ነስቶታል።ቢያንስ በኢትዮጵያውያን አእምሮ ደረጃ አሁን ሕጋዊ መንግስት አለ ብሎ የሚያምን የለም።ስለሆነም ለምን ብሎ ይጋጫል? አይሳካም።

14322264_372264999828952_4916939376608374295_n Aseged Tamene

በጃዊ ባለፈው ሳምንት 37 የሚሆኑ አጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል

ባንኮች ከ10 ሺህ ብር በላይ ወጪ እንዳያደርጉ እቀባ ተጥሏል፤ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2.3 ቢሊዮን ብር ደንበኞች ከባንኮች አውጥተዋል
 ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረግ በረራ ሁሉ በመከላከያ እውቅና እንዲሆን ተደርጓል
ጎንደር፤ ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ የመብራት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በጎንደር ከተማ በማቋረጥ ከአየር ማረፊያ ጀምሮ በሁሉም ቀበሌዎች የአጋዚ ጦር አባላት ቤት ለቤት በመግባት መሣሪያ በመፈተሸ ሲቀሙ ውለዋል፤ የመገናኛ ዘዴዎች ሁሉ በመቋረጣቸው ብሎም ወጣቶች መነጋገር ባለመቻላቸው የተነሳ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ዐማሮች መታሰራቸው ተሰምቷል፤ የባጃጅና የታክሲ ትራንስፖርት በግዴታ እንዲቆም ተደርጎ መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዳይደርስም ጥረት ተደርጓል፡፡
ጎንደር በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የመከላከያና የፖሊስ አባለት የተጥለቀለቀ ሲሆን ከፍተኛ የትግሬ ወታደራዊ መከነኖች ፍሎሪዳ ሆቴል ይህ ሪፖርት እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስብሰባ ላይ ነበሩ፡፡
በተያያዘ ዜና አራዳ የሚባለው የገበያ አካባቢ የዐማራ ወጣቶችና በአጋዚ ወታደሮች መካከል ፍጥጫ መኖሩን መረጃው ደርሶናል፡፡ የጎንደር ወጣቶች ወንድሞቻችን አሳልፈን አንሰጥም እያሉ ሲሆን ከባሕር ዳርና ከቻግኒ ወደ ብር ሸለቆ የተወሰዱ ወጣቶች ከፍተኛ ስቅይት እየደረሰባቸው እንደሆነም እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ከጎንደር ከተማ ዛሬ ነው የወጣነው የሚሉ ሰዎች እንደነገሩን የመረጃ አውታሮችን ሙሉ በሙሉ በመቆለፍ የጎንደር ከተማን ዳግም ወደ ዕልቂት ለመውሰድ የታለመ ይመስላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ጃዊ፤ በጃዊ ነዋሪውን በማሰርና በማንገላተት ላይ በነበሩ 37 የሚሆኑ የትግሬ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ መገደላቸውን ተሰምቷል፡፡ ቁጥራቸው ያልታወቁ ወታደሮች ደግሞ ጃግኒ ሆስፒታል ለእርዳታ መምጣታቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን ድረስ በአካባቢው ይህ ነው የሚባል ሰላም የለም ብለዋል መረጃውን ያቀበሉን ምንጮቻችን፡፡
አጠቃላይ፤ በአገሪቱ ያሉ ባንኮች አንድ ደንበኛ በቀን ከ10 ሺህ ብር በላይ እንዳያወጣ በአገዛዙ ታዘዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንኮች ደንበኞች ገንዘባቸውን ወጪ አድርገዋል፡፡ ይህም በጥቂት ቀናት ብቻ የባንኮች ካዝና ባዶ ይሆናል በሚል ስጋት አገዛዙ ደንበኞች በቀን የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን እንዲወስ እንዳስገደደው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባና በአንዳንድ ትልልቅ ከተሞች 10 ሺህ ብር ይባል እንጅ በብዙ የወረዳና የዞን ከተሞች ከአንድ ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እንዳያወጡ ታግደዋል፡፡
በባሕር ዳር ያሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ለደንበኞቻቸው ለመክፈል ከግል ባንኮች እየተበደሩ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል፡፡
በተያያዘ መረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደርገውን በረራ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሚንስትር እውቅና እንዲሆን ተወስኗል፡፡ አንድ የመንገደኞች አውሮፕለን ከመነሳቱ በፊት በየአካባቢው ያሉ የትግሬ መከላከያ ክፍለ ጦሮች እውቅና ከተሰጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን መሥሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ተጠልፈው ድንበር የሚሻገሩ የአውሮፕላን አብራሪዎችን በመፍራት የሲቪል አቬሽን መስሪያ ቤት ምንም ሥራ በመከላከያ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

13942395_10205155496405616_1008799724_n