ሰይፉ ፋንታሁን ሽማግሌ ሰብስቦ ጥላሁን እልፍነህን ይቅርታ ቢጠይቅም ሌላ ክስ እየተዘጋጀለት ነው

ሰይፉ የኢቴቪን የቆረጣ መቀስ ተውሶ በኢቤኤስ አገልግሎት ላይ ባዋለው ፕሮግራሙ የአርቲስት ጥላሁን እልፍነህን ንግግር ቆርጦ በማውጣቱ አሸው ሰይፉን በፍርድ ቤት ሊያሸው መዛት በመጀመሩ ሰይፉ ሽማግሌ ሰብስቦ ‹‹ይቅርታ››መጠየቁ ተሰምቷል፡፡ሰይፉ ከአሸው ክስ ቢገላገልም በቅርቡ በኢትዮ ፓረንትስት ትምህርት ቤት ሴት ተማሪ መምህሯን በጩቤ የወጋችው አስተማሪው የወሲብ ትንኮሳ ስላደረሱባት ነው በማለት በራዲዮ ፕሮግራሙ በመዘባረቁ በጩቤ የተወጉት መምህር የህግ ባለሞያዎችን ማናገር መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡
በነገራችን ላይ በጩቤ መምህሩን የተዋጋችው ልጅ ወላጅ አባት የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ሲሆኑ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንትና የአንድነት ሊቀመንበር የነበሩት የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የመጀመሪያ ባለቤታቸው ከዶክተሩ ጋር ከመጋባታቸው አስቀድሞ ከመጀመሪያ ትዳራቸው የወለዷቸው ልጅ ናቸው፡፡

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ሰይፉ ፋንታሁን ሽማግሌ ሰብስቦ ጥላሁን እልፍነህን ይቅርታ ቢጠይቅም ሌላ ክስ እየተዘጋጀለት ነው

  1. Pingback: ሰይፉ ፋንታሁን ሽማግሌ ሰብስቦ ጥላሁን እልፍነህን ይቅርታ ቢጠይቅም ሌላ ክስ እየተዘጋጀለት ነው - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

Leave a comment