የመጀመሪያዋ በጐ ፈቃደኛ የኢቦላን የሙከራ ክትባት ወሰደች

አሜሪካ 300 ወታደሮች ወደ ላይቤሪያ ልትልክ ነው

እንግሊዛዊቷ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ሩት አትኪንስ ሰሞኑን በኦክስፎርድ ለ60 በጎ ፍቃደኞች ሊሰጥ የታቀደውን
የኢቦላ ቫይረስ የሙከራ ክትባት በመውሰድ የመጀመሪያዋ በጎ ፈቃደኛ እንደሆነች መሆኗን ቢቢሲ ዘገበ፡፡
የሙከራ ክትባቱን የሚወስዱ በጎ ፈቃደኞች እንደሚፈለጉ በቢቢሲ ሬዲዮ መስማቷን የገለፀችው አትኪንስ፣
በምዕራብ አፍሪካ ሁኔታው በጣም አሳዛኝ ስለሆነና የዚህ ክትባት ሂደት አካል መሆን ትልቅ ውጤት ለማምጣት
በሚደረገው ጥረት ማበርከት የምችለው ትንሹ ነገር እንደሆነ በማሰብ፣ ክትባቱን በበጎፈቃደኝነት ለመውሰድ
ወስኛለሁ” ብላለች፡፡
ክትባቱ ከኢቦላ ቫይረስ ትንሽ የዘረመል ንጥረ ነገር ብቻ የያዘ በመሆኑ ተከታቢው በበሽታው እንደማይያዝ
የተገለፀ ሲሆን በኦክስፎርድ የጄነር ኢኒስቲቲዩት ዳይሬክተርና የሙከራ ክትባቱ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አድርያን
ሂልም፤ “ይሄ ክትባት ማንንም ኢቦላ ያስይዛል የሚል ቅንጣት ስጋት የለም” ብለዋል፡፡
ክትባቱን ለመወጋት ስታስብ የደህንነቷ ጉዳይ እንዳላስጨነቃት የተናገረችው ሚስ አትኪንስ፤ የ15 ዓመት ታዳጊ
ልጇ የኢቦላ ቫይረስ ተሰጥቷት የምትሞት መስሎት እንደነበርና እንዳረጋጋችውም ገልፃለች፡፡
ብዙ ጊዜ አዲስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ከማግኘቱ በፊት ለዓመታት በሰዎች ላይ ሙከራ ሲደረግ
ይቆይ ነበር ያለው ቢቢሲ፤ በምዕራብ አፍሪካ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ አጣዳፊነት ግን ይሄ የሙከራ ክትባት
በአስደናቂ ፍጥነት ጥቅም ላይ እንዲውል ጥረቱ እንዲጠናከር አድርጓል ብሏል፡፡
በሰዎች ላይ የሚደረገው ሙከራ ውጤታማ ሆኖ ከተገኘ፣ ክትባቱ በፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ በቫይረሱ
በተጠቁ አካባቢዎች የሚገኙ የጤና ሰራተኞችን ከበሽታው ለመከላከል ጥቅም ላይ እንደሚውል ታውቋል፡፡
ያን ጊዜ ግን ለ10ሺ ሰዎች ያህል የሚሆን ክትባት እንደሚያስፈልግ የተገለፀ ሲሆን በምዕራብ አፍሪካ ክፉኛ
የተጠቁ አካባቢዎች ላይ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችን ከቫይረሱ ለመከላከል ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡
ክትባቱ እየተሰራ የሚገኘው ግላክሶስሚዝክላይን በተባለ ኩባንያና በአሜሪካ ብሔራዊ የጤና ተቋም ሲሆን፣
የእንግሊዝ ዓለምአቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ የምርምር ተቋማት ለሙከራ ክትባቱ የገንዘብ
ድጋፍ እንዳደረጉ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኢቦላ ቫይረስን ለመከላከል እገዛ የሚያደርጉ 3ሺ ወታደሮችን
ወደ ላይቤሪያ የመላክ ዕቅድ እንዳላቸው ባለፈው ማክሰኞ አስታወቁ፡፡ ኦባማ ይሄን ያስታወቁት የላይቤሪያዋ
ፕሬዚዳንት አለን ጆንሰን ሰርሊፍ በሽታውን ለመከላከል እገዛ ያደርጉላቸው ዘንድ ለኦባማ በቀጥታ ያቀረቡትን
ጥያቄ ተከትሎ እንደሆነ ታውቋል፡፡
የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል የህክምና ማዕከሎችን ግንባታ በመቆጣጠርና የጤና ሰራተኞችን በማሰልጠን
ለላይቤሪያ መንግስት እገዛ እንደሚያደርግ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በምዕራብ አፍሪካ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ፈጣን ያልሆነ ምላሽ ትችት ሲሰነዘርበት
፣ቆየቱ ይታወቃል፡፡
በበሽታው ክፉኛ የተጠቁት የምዕራብ አፍሪካ አገራት ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያና ጊኒ ሲሆኑ ወረርሽኙ ከ2400 በላይ
ሰዎችን ለህልፈት እንደዳረገ ተጠቁሟል፡፡ ከእዚህ የሞት አደጋ ውስጥ ግማሹ የተከሰተው በላይቤሪያ ነው፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት፤ አገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሰዎችን በቫይረሱ ልታጣ እንደምትችል በቅርቡ
አስጠንቅቋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊዎች፣ በጄኔቫ በሚያካሂዱት ስብሰባ ለወረርሽኙ
በተሰጠው ዓለም አቀፍ ምላሽ ላይ እንደሚወያዩ ቢቢሲ ጠቁሟል፡፡
የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ባለፈው ሰኞ ወረርሽኙን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤
“በምዕራብ አፍሪካ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከፍተኛና ፈጣን የውጭ እርዳታ ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡

posted by Aseged Tamene

Advertisements

How I Infected 324 Men with HIV – Female Student Reveals

A female student in Kenya has revealed that she has infected a total of 324 men with the Human Immunodeficiency Virus (HIV).

The HIV positive girl, who attends the Kabarak University in Nakuru, is said to have been infected by a man at a party.

The unidentified 19-year old is allegedly aiming to infect a total of 2000 men in revenge.

 

According to reports:

The girl allegedly contacted Kenyan Scandals on Facebook and claimed she had something to confess.

After she was assured her identity was going to be protected (the Kenyan Daily Post, however, published a picture from her Facebook profile along with the article) she wrote: “Sep 22nd 2013 is a day I”ll never forget, we went clubbing in town and got drunk with some senior students then went back hostels for party round 2″.

She then explained that when she woke up, the morning after, she realised a boy called Javan had had sex with her while she was drunk.

“I only asked if he used a condom and he said yes, however when taking bath I noticed sperms down there, I wanted to commit suicide, I feared getting pregnant and HIV.”

When she discovered she was HIV positive, the girl confronted Javan who insisted he was clean.

“I was so depressed and took alcohol to die, I even bought poison, the pain was just unbearable how was I gone face the world, I let my parents down, I gave up on the world and just wanted to end my life. My future had been ruined, somehow someone had to pay,” the girl said.

“I accepted my fate and promised to make all men I come across suffer, I know I’m attractive and men both married and unmarried chase me left right and centre.

 

“I buried the good girl in me and became the bad girl, my goal was to infect as many as possible,” she explained.

The girl then confessed she had already infected 324 men, 156 of which are students at the Kabarak University where she studies, the rest are married men, lecturers, lawyers, celebrities and politicians.

“Not a day passes without me having sex, mostly 4 people per day,” she continued in her confession. “Your day is coming, you men destroyed my life and I will make you and your people pay for it”

source: ynaija.com

posted by Aseged Tamene

ከዓለም ጠፍቶ የነበረው የጊኒ ዎርም በሽታ በደቡብ ሱዳን መታየቱ ተገለጸ!

እርስ በእርስ ግጭቱን ተከትሎ በሽታው በእጅጉ እንዳይስፋፋ አስግቷል

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከምድረ ገጽ ጠፍቶ የነበረው ጊኒ ዎርም እንዳዲስ ማንሰራራት መጀመሩ ታውቋል፡፡ በደቡብ ሱዳን ውስጥም በሽታው በ11 ሰዎች ላይ መታየት መጀመሩን የጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡ ከረዥም የእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ እ.ኤ.አ በ2011 ነፃነቷን ያገኘችው ደቡብ ሱዳን ባገኘችው የፖለቲካ መረጋጋት፤ የተስፋ ጭላንጭል እና የጤና ባለሙያዎች የጊኒ ዎርምን ከሃገሪቱ ለማጥፋት ችለው ነበር፡፡ ነገር ግን በሃገሪቷ ፕሬዘዳንትና ምክትል ፕሬዘዳንት መካከል በተነሳው አለመግባባት ምክንያት ዲንካ እና ኑር በተሰኙ ጎሳዎች መካከል ለተነሳው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ሆኗል፡፡

በእርስ በእርስ ግጭቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱ ሲሆን 1.3 ሚልዮን ሰዎችም ቤትና ንብረታቸውን ትተው ሊሰደዱ ችለዋል፡፡ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት የሆነው ኦክስፋም እንደገለጠው በግጭቱ ተጨማሪ 7 ሚልዮን ሰዎች ሊጎዱ እንደሚችሉ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዝናባማው ወቅት በመግባቱ ኮሌራ የተሰኘው በሽታ መዛመት መጀመሩን ታውቋል በዚህም ምክንያት በበሽታው 892 ሰዎች ለበሽታው ተጋልጠዋል፡፡

ድህነትና የውሃ እጥረት ለበሽታው መስፋፋት ከፍተኛ ደረጃ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን በአትላንታ የሚገኝ እና የጊኒ ዎርም ለመጥፋት አበክሮ እየሰራ የሚገኝ ዓለማቀፍ ድርጅት አስታውቋል፡፡

posted by Aseged Tamene

የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው ተባለ

የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው ተባለ

በከተማችን ካሉ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በትክክለኛ ባለሙያ የታገዘ ህክምና የሚሰጡት ከግማሽ በታች ናቸው

ለጥርስ ህክምና እስከ 25 ሺህ ብር ድረስ የሚያስከፍሉ ክሊኒኮች አሉ

               በፒያሣው አትክልት ተራ አካባቢ መደዳውን ከተደረደሩት የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በአንደኛው ነበር ቀንና ሌሊት እየጠዘጠዘ እንቅልፍ የነሳትን ጥርሷን ከ2 ዓመት በፊት ያስነቀለችው። በክሊኒኩ ያገኘችው ህክምና ለጊዜው ከሥቃይዋ ገላግሏታል። ትዕግስት (ለዚህ ዘገባ ስሟ የተቀየረ) ወደ ክሊኒኩ ገብታ፣ የጥርስ ህክምናዋን ለማድረግ ስትወስን፣ ምንም ዓይነት የጤና ችግር ያጋጥመኛል ብላ አላሰበችም። በዚያ ላይ በክሊኒኩ መግቢያ ደጃፍ ላይ በጉልህ ተፅፎ የተሰቀለው ማስታወቂያ፣ ህክምናው በሥራው ብቁ በሆኑ ባለሙያዎችና ንፅህናቸው በአግባቡ በተጠበቀ መሳሪያዎች እንደሚሰጥ ይገልፃል። ህክምናውን ያደረገላት “ሃኪም”፣ ህመምተኛ ጥርሷን ከነቀለ በኋላ፣ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችንና አሞክሳሲሊን የተባለውን ክኒን ሰጥቶ አሰናበታት። ትዕግስት ሌትና ቀን ያሰቃያት ከነበረው የጥርስ ህመሟ መገላገሏ ደስታን የፈጠረላት በወራት ለሚቆጠር ዕድሜ ብቻ ነበር። ከጥቂት ወራት በኋላ የተነቀለው ጥርሷ አካባቢ ሃይለኛ የህመም ስሜት ይሰማት ጀመር። ቀስ በቀስ ህመሙ እየጨመረ ሥቃዩ እየበረታባት ሄደ።

እዛው ጥርሷን የተነቀለችበት የጥርስ ክሊኒክ ሄደች። በክሊኒኩ ያገኘቻቸው “ሃኪሞች” ምንም አይነት ችግር እንደሌለባት ገልጸው፤ የህመም ማስታገሻ ክኒን ብቻ እንድትወስድ አዘው አሰናበቷት። ሥቃይዋ ግን ከምትችለው በላይ ሆነባት። በመንጋጋዋ አካባቢ ብቻ ተወስኖ የነበረው የህመም ስሜቷ፤ ጭንቅላቷን ክፉኛ ወደሚበጠብጥ ከባድ የራስ ምታት ህመም ተለወጠ። ዓይኗን መግለጥ እስከሚያቅታት ድረስ በራስ ምታት ህመሙ ተሰቃየች። አፏን እንደልቧ መክፈት መዝጋቱ የማይታሰብ ሆነባት። በስቃይ ለመናገርም ሆነ ምግብ ለመዋጥ አፏን በከፈተች ቁጥር የሚሰነፍጥና እጅግ የሚያስጠላ መጥፎ ጠረን ከአፏ መውጣት ጀመረ። ይህም ህይወቷን የበለጠ መራራና ከባድ አደረገባት። ቀናት እየጨመሩ በሄዱ ቁጥር፣ ሥቃይዋ ከአቅሟ በላይ እየሆነ ሔደ። ቢቸግራት እዛው ፒያሳ ወደሚገኝ ሌላ የጥርስ ክሊኒክ ለህመሟ ማስታገሻ ፍለጋ ሄደች። “የክሊኒኩ ሃኪም የረባ ምርመራ እንኳን ሳያደርግልኝ ሁለቱ መንጋጋዎቼ መነቀል እንዳለባቸው ነገረኝ” ትላለች። በቂ ገንዘብ አልያዝኩም በሚል ሰበብ ከክሊኒኩ ለ ቃ እንደወጣችም ት ናግራለች።

የ ህመም ስሜት ያላት ቀደም ሲል በተነቀለችው ጥርስ ቦታ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው ተባለ በከተማችን ካሉ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በትክክለኛ ባለሙያ የታገዘ ህክምና የሚሰጡት ከግማሽ በታች ናቸው ለጥርስ ህክምና እስከ 25 ሺህ ብር ድረስ የሚያስከፍሉ ክሊኒኮች አሉ ላይ መሆኑን እያወቀች፣ ሌላ ጥርስ መነቀል አለበት የሚለውን ውሳኔ አላመነችበትም። የትዕግስት ስቃይ እረፍት አልባ መሆኑ ካሳሰባቸው ጓደኞቿ አንዷ፣ ትዕግስትን ይዛ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል ሄደች። በሆስፒታሉ በተደረገላት ምርመራ፣ የጥርሷ ዋንኛው አቃፊ ውስጠኛው ክፍል (Root Canal) ቀደም ሲል በተፈፀመና አግባብ ባልሆነ የጥርስ መንቀል ሂደት ሳቢያ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱንና መመረዙን፣ ህክምናውንም በአገር ውስጥ ለማከናወን አስቸጋሪ እንደሆነ ተነገሯት። አስቸኳይ ህክምና ካላደረገችም ችግሩ እየጨመረ ሄዶ፣ ወደ ሌሎች የሰውነትዋ ክፍሎች በተለይም ወደ ጭንቅላት ነርቮቿ የሚሰራጭ መሆኑን ዶክተሮች አረዷት። ለህክምናው ያስፈልጋል የተባለችውን ገንዘብ ስትሰማ ሰማይ ምድሩ ዞረባት። “ውጪ አገር ሄደሽ ከ290 ሺህ ብር በላይ የሚፈጅ ህክምና ማድረግ አለብሽ” ተባለች። ይህንን ወጪ ሸፍና ህክምናውን ለማግኘት አቅም የላትም። ለዓመታት በስምንት መቶ ብር ወርሃዊ ደመወዝ የመርካቶው ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ውስጥ በልብስ መሸጫ መደብር ውስጥ ነው የሰራችው።

እሱንም ቢሆን በዚሁ የጥርስ ህመሟ ሳቢያ ከለቀቀች ወራት አልፈዋል እናም ለህክምናዋ የሚሆን ገንዘብ የምታገኝበት አማራጭ በማጣትዋ ቀደም ሲል በሥራ አጋጣሚ የተዋወቀቻቸውን ሰዎችና ሌሎች በጎ አድራጊ ግለሰቦችን እርዳታ ለመጠየቅ ተገዳለች። በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ የሚደረግላትን የህክምና እርዳታ በመከታተል፣ ከህመሟ ጊዜያዊ እፎይታን ለማግኘት እንደቻለችም ትናግራለች በራስ ደስታ ሆስፒታል በተደረገላት ህክምና የድዷ ቁስለት እየዳነ መሄዱን፣ ከሰዎች ጋር እንዳትነጋገር አድርጓት የነበረው የአፍ ጠረኗ፣ በእጅጉ እየተሻሻለ እንደሆነ ገልፃለች። ትዕግስት በጥርስ ህክምና ሰበብ የደረሰባትን ይህንን የጤና ችግር ልትነግረኝ አብረን የቆየንባቸው ጥቂት ደቂቃዎችን ለእኔ እጅግ የፈተና ነበሩ። “አሁን እጅግ ተሻሽሏል” የተባለው የአፍ ጠረኗ ቀደም ሲል ምን አይነት ቢሆን ነው አስብሎኛል። ትዕግስት በጥርስ ህክምና ሰበብ በየመንደሩና በየጉራንጉሩ ውስጥ እየተከፈቱ በታካሚው ህይወትና ጤና ላይ “ቁማር የሚጫወቱ” የምትላቸውን የጥርስ ክሊኒኮች የሚቆጣጠርና አሰራራቸውን የሚከታተል አካል ባለመኖሩ ምክንያት እንደእሷ ሁሉ እጅግ በርካቶች አደገኛ ለሆኑ የጤና ችግሮች መጋለጣቸውን ትናገራለች።

ክሊኒኮቹ የህክምና መሳሪያዎቻቸውን በንፅህና የማይጠብቁ በመሆናቸው፣ ኤችአይቪን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ከአንዱ ወደ አንዱ በቀላሉ የሚያስተላልፍ የበሽታ መፈልፈያ ቦታዎች ሆነዋል ስትል በምሬት ገልፀለች። ለካርድ ተብላ በከፈለችው 50 ብር እና ለጥርስ መንቀያ ባስከፈልዋት 120 ብር ጤናዋን ሳይሆን የእድሜ ልክ በሽታዋን ሸምታ መውጣቷ እጅግ እንደሚያሳዝናት የምትናገረው ትዕግስት፤ መንግስትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች የጥርስ ህክምና ክሊኒክ እየተባሉ በየጉራንጉሩ የሚከፈቱትንና በከተማዋ ውስጥ እንደ አሸን የፈሉትን ክሊኒኮች ቁጥጥር ሊያደርጉባቸውና አሰራራቸውን ሊከታተሏቸው ይገባል ትላለች። ለወገኖቻቸው ህይወት ቅንጣት ደንታ በሌላቸው አንዳንድ ራስ ወዳድ ሰዎች፣ የብዙ ሰዎች ህይወት ሊበላሽ አይገባውም ስትልም በቁጭት ትቆዝማለች። “ህብረተሰቡም ለጥርስ ህክምና በሚሄድበት ጊዜ ህክምናው በምን ዓይነት ሁኔታና በማን እንደሚሰጠው ማወቅ ይኖርበታል። ከእኔ ሊማርም ይገባል ባይ ናት።

የጥርስ ህክምና ሊሰጥ የሚገባው በሙያው በአግባቡ በሰለጠኑና ስፔሻላይዝድ ባደረጉ የህክምና ባለሙያዎች ሲሆን ሃኪሞቹ ማንነታቸውንና ደረጃቸውን የሚገልፅ ባጅ፣ በግልጽ በሚታይ ሁኔታ በደረታቸው ላይ ማንጠልጠል እንደሚኖርባቸው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያወጣው የህክምና መመሪያ (Guideline) ይጠቁማል። የህክምና መገልገያ መሳሪያዎቹ ጥራትና ንፅህናቸው በአግባቡ የተጠበቀ፣ የህክምና መስጫ ስፍራው የታካሚውን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቅና ለድንገተኛ የጤና ችግሮች አስተማማኝ ዝግጅት ያለው መሆን እንደሚገባውም ይገልፃል። ይሁን እንጂ ይህንን ዘገባ ለማዘጋጀት ተዘዋውሬ ካየኋቸው፣ በጎጃም በረንዳና በአትክልት ተራ አካባቢ ከሚገኙ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በአንደኛውም ከላይ የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ክሊኒኮችን አላየሁም። አብዛኛዎቹ ክሊኒኮች ለህክምና ሥራ አመቺ ባልሆነ ሥፍራ የተሰሩና የንፅህናቸው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላ ይ ነ ው። ከ ዚህ በ ተጨማሪም በ ክሊኒኮቹ ደጃፍ ላይ እንደተሰቀለው ማስታወቂያ ሁሉ ህክምናው በስቴራላይዘር ከበሽታ ንፁህ ሆነው በፀዱ መሳሪያዎች የሚሰጥ መሆኑን የሚያረጋግጡ ነገሮችን ለማየት አልቻልኩም።

ለቅኝት በተዘዋወርኩባቸውና በፒያሣው አትክልት ተራ አካባቢ በብዛት ከሚገኙት የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በአንዱ ውስጥ ያገኘሁት አንድ “የህክምና ባለሙያ” በክሊኒካቸው የስቴራላይዘር መሳሪያ አለመኖሩን ገልፆ “ህክምናውን የምንሰጠው ለአንድ ሰው አንድ በሆነ ወይንም ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎት ላይ በማይውሉ መሳሪያዎች ነው ብሎኛል። ይህ አባባሉ ግን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ አገራት ቀርቶ በለፀጉ በሚባሉት አገራት ውስጥ እንኳን ሊሆን እንደማይችል ግልፅ ነው። እጅግ ውድ ዋጋ የሚያወጡ መሳሪያዎችን ከአንድ ጊዜ በላይ አንጠቀምባቸውም ማለቱ የማይመስል ነገር ነው። ላለፉት 10 ዓመታት በጥርስ ህክምና ሙያ ውስጥ የቆዩት ዶክተር የኋላሸት ስመኘው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ፤ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ከሚገኙት የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች አብዛኛዎቹ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቁመው የመሣሪያዎቹ ንፅህና አጠባበቅና የባለሙያዎቹ ብቃት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል። የጥርስ ህክምና መሳሪያዎች ለአንድ ሰው አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ለሌላ ሰው ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት እስከ 30 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ በበረኪና በሚገባ መዘፍዘፍና በሚገባ መታጠብ ይኖርባቸዋል፤ በአግባቡ ተዘፍዝፈውና ታጥበው የፀዱት ዕቃዎች አውቶክሌቭ ወደተባለውና ዕቃዎቹን በአግባቡ ለመቀቀል ወደሚያስችለው መሳሪያ መግባት ይኖርባቸዋል።

ከዚህ በኋላ ነው ዕቃዎቹ ከበሽታ ነፃ ሆኑ የሚባለው። በዚህ ሁኔታ የፀዱ መሳሪያዎች፣ የታካሚውን ጤንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቁ ናቸው ብለዋል። ግን በተጠቀሱት ስፍራዎች ይህንን የዶክተር የኋላሸት ስመኘውን አባባል የሚያረጋግጡ አንዳችም ክሊኒኮች ለማየት አልቻልንም። ለቅኝት ከተዘዋወርንባቸው የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች ውስጥ በተሟላ መሳሪያና በሙያው በሚገባ በሰለጠኑ ብቁ ባለሙያዎች ተደራጀተው ለታካሚው አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ጥቂት ክሊኒኮችንም ታዝበናል። ፒያሳ እሪ በከንቱ አካባቢ፣ ሃያ ሁለትና መገናኛ አካባቢ ያየናቸው የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በእነዚህ ክሊኒኮች ለደንበኞቻቸው አግባብ ያለው ህክምና ሲሰጡ ከተመለከትናቸው ጥቂት ክሊኒኮች የሚሰጠው የጥርስ ህክምና በሙያው በሚገባ በሰለጠኑ ብቁ ባለሙያዎች እና ንፅህናቸው በአግባቡ በተጠበቀላቸው መሳሪያዎች መሆኑን በስፍራው ተገኝተን ለመታዘብ ችለናል። ክሊኒኮቹ ለአገልግታቸው የሚስከፍሉት ዋጋ ከሌሎች ክሊኒኮች ጋር ሲነፃፀር ዳጎስ ያለ ነው ሊባል ይችላል። በእነዚህ ክሊኒኮች ውስጥ አንድ ጥርስ ከመነቀሉ በፊት ሊታከም መቻል አለመቻሉ በራጅ ምርመራና ሌሎች መሰል የምርመራ አይነቶች እንዲረጋገጥ ይደረጋል። ታካሚው ለህክምናው የሚያወጣው ወጪም እነዚህን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

ታካሚው ጥርሱ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግለት የማይፈልግና መነቀል ብቻ እንደሚፈልግ ከተናገረ ባለሙያዎቹ አገልግሎቱን እጅግ በተመቻቸና ብዙም የህመም ስሜት በሌለበት ሁኔታ ያከናውኑታል። ለዚህ ህክምናም እስከ 400 ብር የሚደርስ ክፍያ ደንበኛው ይጠየቃል። ከዚህ በተረፈ የተወላገዱ፣ ያለአግባብ የበቀሉ፣ ነርቮቻቸው የተበላሹና ህክምና የሚያስፈልጋቸው ጥርሶች ሁሉ በእነዚህ ሥፍራዎች ተገቢው ህክምና ይደረግላቸዋል። ክሊኒኮቹ ለአገልግሎታቸው እስከ ሰላሳ ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ያስከፍላሉ። በዓለማችን የተለያዩ አገራት ለጥርስ ህክምና የሚወጣው ወጪ (የሚከፈለው ክፍያ) እጅግ ከፍተኛ ነው። በካናዳ አንድን ጥርስ ለመነቀል አሊያም ለማስሞላት እስከ አንድ ሺህ ሁለት መቶ የካናዳ ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን ይህም በእኛ ገንዘብ ሲመነዘር ከሃያ ሁለት ሺህ ብር በላይ የሚጠይቅ ነው። በስዊድን ተመሳሳይ ህክምና ለማግኘት ከአራት እስከ አምስት ሺህ ክሩነር (በእኛ ከ12 እስከ 15 ሺ ብር) የሚደርስ ገንዘብ ይጠይቃል።በዚህ ምክንያትም አብዛኛዎቹ ዲያስፖራዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ባሉ ቁጥር፣ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮችን ሳይጎበኙ አይሄዱም።

የፒያሣው ጎጀብ ክሊኒክ በበርካታ ዲያስፖራዎችና የውጭ አገር ዜጎች በመጎብኘት ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል። ዲያስፖራዎቹና የውጭ አገር ዜጎቹ የተበላሸና የሚታከም ጥርስ ባይኖራቸው እንኳን ስምንት መቶ ብር እየተከፈለ የሚሰጠውን ሙሉ የጥርስ እጥበት አገልግሎት ፍለጋ የክሊኒኩን በር ያንኳኳሉ። በአገራችን የሚገኙትንና በጣት ሊቆጠሩ የሚችሉትን የጥርስ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪሞች በእነዚህ ሥፍራዎች እንደልብ ማግኘት ይቻላል። አቅምዎ ከፈቀደና መክፈል ከቻሉ በመረጡትና ቀልብዎ በወደደው ብቁ ባለሙያ መታከም ይችላሉ።

posted by Aseged Tamene

በስትሮክ ህይወታቸውን የሚያጡ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ ነው

ሴቶች በስትሮክ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው
የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት ውስጥ ሰቃይ ከሚባሉ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚያደርገውን ቆይታ አጠናቆ ሊመረቅ የወራት እድሜ ቀርተውታል፡፡ 
ወላጆቹ የቤቱ የበኩር ልጅ የሆነውን ይህን ወጣት በታላቅ ተስፋ ነው የሚጠባበቁት፡፡ ለዓመታት ከኖሩበት የድህነት ኑሮ የሚታደጋቸው፣ ለታናናሽ ወንድምና እህቶቹ ተስፋ የሚሆናቸው እሱው እንደሆነ በማመን፣ ያቺን የምረቃ ጊዜውን የሚጠብቁት በጉጉት ነው፡፡ ጊዜው የፈተና ወቅት በመሆኑ፣ ዮናስ ቀንና ሌሊት በጥናትና በመመረቂያ ፅሁፍ ዝግጅት ላይ ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ አልፎ አልፎ ከባድ ራስ ምታት ህመም ይሰማው የጀመረውም በዛው ሰሞን ነበር፡፡ ሆኖም የህመም ስሜቱም የከፋ ጉዳት ሊያስከትልበት የሚችል ጠቋሚ ምልክት እንደነበር ፈፅሞ አልገመተም፡፡ ህመም በተሰማው ጊዜ ወፍራም ቡና በመጠጣት፣ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች በመውሰድ፣ ስሜቱን ለማስወገድ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዛው ሰሞን አንድ ሌሊት ለሰዓታት ከእንቅልፍ ጋር እየታገለ ሲሰራ ቆየ፡፡ ቀጣዩ ቀን የመመረቂያ ፅሑፉን ለአማካሪው የሚያቀርብበት ዕለት በመሆኑ ሃሣብ ገብቶታል፡፡ ወደ መኝታው ያመራው ሌሊቱ ከተጋመሰ በኋላ ነበር። ቀሪ ስራዎቹን ደግሞ በሌሊት ተነስቶ ለማጠናቀቅ በማሰብ፣ መፅሃፍቶቹን እንኳን ሳይሰበስብ ወደ መኝታው አመራ፡፡ የጠዋቱ ሰዓት እየገፋ ቢመጣም፣ የዮናስ የመኝታ ክፍል አለመከፈት ያሳሰባቸው ቤተሰቦቹ፤ በሩን በተደጋጋሚ አንኳኩ፡፡ ምላሽ የለም፤ ከውስጥ የሚሰማ የማንቋረርና የማቃሰት ድምፅ ክፉኛ አስደነገጣቸው፡፡  በሩን ሰብረው ሲገቡም ዮናስ ከመኝታው ተንሸራቶ በወደቀበት ሥፍራ ላይ ሆኖ ያንቋርራል፡፡ አይኖቹ ፈጠዋል። እጅና እግሮቹ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ እየተጯጯሁ ወደ ክሊኒክ ወሰዱት፡፡ በአቅራቢያቸው ያለው ክሊኒክ፤ ችግሩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ በመግለፅ ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ መከራቸው፡፡ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዱ፡፡ ምርመራ ያደረጉለት ሃኪሞችም ዮናስ የስትሮክ ችግር እንደገጠመው ግምት እንዳላቸው ጠቁመው፤ አስቸኳይ የሲቲ ስካን ምርመራ አዘዙለት፡፡ የምርመራው ውጤትም የቀኝ የአንጎሉ ክፍል ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የሚያሳይ ሆነ፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ ለዚህ ችግር መነሻ ምክንያቱ ዮናስ ለቀናት በውጥረትና በጭንቀት የተሞላ ጊዜ ማሳለፉ እንደሆነ ተናገሩ። ሃኪሞቹም ሆኑ ቤተሰቦቹ ዮናስ ባጋጠመው ክፉ እጣ እጅግ አዘኑ የዮናስን ህይወት ለማትረፍና የደረሰበትን ዘላቂ የአካል ጉዳት ለመቀነስ፣ ሃኪሞቹ ከፍተኛ ጥረት አደረጉ፡፡ የሃያ ሁለት ዓመቱ ወጣት፣ በዚህ እድሜው ግማሽ የሰውነቱን ክፍል ለማዘዝ አለመቻሉና አንደበቱ መያዙ ልብ የሚሰብር ገጠመኝ ነበር፡፡ የማሰብና የማስታወስ ችሎታውም በከፍተኛ መጠን ቀንሷል፡፡ ለቤተሰቦቹ አጋርና ደጋፊ ይሆናል ተብሎ ተሰፋ የተጣለበት ይህ ወጣት በ 22 ዓመት ዕድሜው ያለሰው ድጋፍ የማይንቀሳቀስ አካል ጉዳተኛ ሆነ፡፡ ሀሳቡን በአንደበቱ ብቻ ሳይሆን በፅሁፍ እንኳን መግለፅ አለመቻሉ የዮናስን ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቹንና በቅርብ የሚያውቁትን ሰዎች ሁሉ ልብ የሰበረ ጉዳይ ነበር፡፡ ይህንን የዮናስን አሳዛኝ ታሪክ ያጫወተኝ ለፊዚዮቴራፒ ህክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል በየጊዜው የሚያመላልሰው ታናሽ ወንድሙ ነው፡፡ (የዚህን ወጣት ገጠመኝ ማግኘት እንድችል የተባበሩኝ ሲስተር ትዕግስት አስቻለውን በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡) 
ዛሬ የእነዮናስ ቤት ተስፋ የራቀውና የሃዘን ድባብ ያረበበበት ቤት ሆኗል፡፡ ባላሰቡትና ባልጠበቁት ሁኔታ ተስፋቸውን ተነጥቀዋል፡፡ ለራሱ፣ ለቤተሰቦቹና ለአገሩ ብዙ ማድረግ ይችል የነበረው ወጣት፤ ገና ሩጫውን በጀመረበት የወጣትነት ዕድሜው የአልጋ ቁራኛ የመሆን ክፉ እጣ ወደቀበት፡፡ አሁን አሁን በዮናስ ዓይነት በሽታ የሚጠቁ ወጣት ኢትዮጵያውያን ቁጥር መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጠቅላላ ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ዳዊት አብርሃም እንደሚናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት በስትሮክ ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡና ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው፡፡ 
ዶ/ር ዳዊት ከአመታት በፊት Characteristics and outcomes of Stroke at Trkur Anbesa teaching Hospital Ethiopia” በሚል ርዕሰ በሆስፒታሉ የተካሄደን ጥናት ጠቅሰው እንደሚናገሩት፤ የስትሮክ ችግር ገጥሟቸው ወደሆስፒታሉ ከመጡ ህሙማን መካከል አብዛኛዎቹ ዕድሜያቸው የወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ስትሮክ የበርካታ ወጣቶችን ህይወት በመቅጠፍ እና ለአካል ጉዳት በመዳረግ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ያመለከተው ጥናቱ፤ በወጣትነት ዕድሜያቸው የስትሮክ ችግር ገጥሟቸው ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ ህሙማን መካከል ወደ አርባ በመቶ የሚጠጉት በዚሁ ችግር ሳቢያ ህይወታቸውን እንደሚያጡ ይጠቁማል፡፡ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ለመጣው የስትሮክ ችግር ዋንኛ መንስኤዎቹ፡- ሊቆጣጠሩት ያልቻሉት ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ህዋሳትና የደም ቧንቧዎች በቅባትና በሌሎች ነገሮች መዘጋት፣ በተደጋጋሚ የሚያጋጥምና በአግባቡ ታክመው ያልዳኑት የቶንሲል ህመም፣ የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን፣ ከልክ ያለፈ ክብደትና እንቅስቃሴ አለማድረግ እንደሆኑ ባለሙያው ገልፀው፤ በተለያዩ ሱሶች መጠመድና የአልኮል ሱሰኝነትም ለስትሮክ ተጋላጭነትን በእጥፍ እንደሚጨምር ተናግረዋል፡፡ 
ወደጭንቅላታችን የሚደርሰው የደም ኦክሲጂንና ንጥር ምግቦች በተለያዩ ምክንያቶች ሲቋረጡ የሚፈጠረው የጭንቅላት ህዋሳት መሞት (ስትሮክ) ሁለት አይነቶች ናቸው፡፡ ኢስኬ ሚክ ስትሮክ እና ሄሞራጂክ ስትሮክ በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ፡፡ 
ኢስኬሚክ ስትሮክ የምንለው፣ ኦክሲጂንና ንጥረ ምግቦችን ወደ ጭንቅላታችን የሚያስተላልፉት የደም ቧንቧዎች፣ በረጋ ደም ሳቢያ ሲዘጉና ደም የማስተላለፍ አቅም ሲያጡ የሚከተሉት የስትሮክ አይነት ሲሆን ጭንቅላት ኦክሲጂንና ንጥረ ምግቦችን ማግኘት ባለመቻሉ ምክንያት ስራውን በአግባቡ ለመስራት አይችልም፡፡ በዚህ ጊዜ ስትሮክ ተፈጠረ ይባላል፡፡ ሌላው ሄሞራጂክ ስትሮክ የሚባለውና በጭንቅላት ውስጥና በዙሪያው ያሉ የደም ቧንቧዎች በድገት በመፈንዳታቸው ምክንያት በሚከሰት የደም መፍሰስ ሳቢያ የሚከሰት ነው፡፡ ይህ በጭንቅላታችን ውስጥ የፈሰሰው ደም፣ ለጉዳት እጅግ ቅርብ በሆነው የጭንቅላት ህዋሳቶቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ጉዳቱም ህዋሳቶቹን ለሞት ይዳርጋቸዋል። የሞቱ የጭንቅላት ህዋሳት ደግሞ ህይወት ዘርተው ወደ ቀድሞ ተግባራቸው የመመለስ እድላቸው፣ በእጅጉ ዝቅተኛ ነው፡፡ በህክምና እርዳታ ሊደረግ የሚችለው ከሞቱት ህዋሳት አቅራቢያ ያሉትን በማከም፣ ለማዳንና ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ በማድረግ የጉዳቱን መጠን ለመቀነስ በመጣር እንደሆነ ዶክተር ዳዊት ይገልፃሉ፡፡ 
ስትሮክ ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ የመከሰት ዕድሉም በዛው መጠን እየጨመረ የሚሄድ ችግር እንደነበር የጠቆሙት ዶክተር ዳዊት፤ በአሁኑ ወቅት ግን በወጣቶች ላይ በስፋት መታየቱ ችግሩን አሳሳቢ አድርጐታል ብለዋል፡፡ በተለይ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ላይ በስፋት እየታየ ያለው የስትሮክ ችግር ዋንኛ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ በማለት ዶ/ር ዳዊት ከጠቆሟአቸው ጉዳዮች መካከል በውጥረት የተሞላና ያልተረጋጋ ህይወትን መምራት፣ በበርካታ ሃላፊነቶች በመወጠር አዕምሮን የሚያስጨንቁ ስራዎችን መስራት፣ የአልኮል መጠጥና የተለያዩ እፆች ሱሰኛ መሆን የጤና ምርመራዎችን አለማድረግ ዋንኞቹ ናቸው፡፡
 በድንገት በመከሰትና ያለማስጠንቀቂያ ለሞትና ለአካል ጉዳት በመዳረግ የሚታወቀው ስትሮክ ከመከሰቱ ጥቂት ቀናት ወይንም ሰዓታት በፊት የሚያሳያቸው ምልክቶች እንዳሉ የገለፁት ዶ/ር ዳዊት፤ እነዚህም ከፍተኛ ራስ ምታት፣ የመደንዘዝ ስሜት፣ ትኩረት ማድረግ አለመቻል፣ መፍዘዝና መሰል ስሜቶች ችግሩ እየመጣ መሆኑን አመላካቾች ናቸው ብለዋል፡፡ 
በቀድው ዘመናት፣ ያደጉት አገራት ህዝቦች ሥጋት የነበረውና በበለፀጉት አገራት ህዝቦች ዘንድ በስፋት የሚታየው ስትሮክ፤ ዛሬ በአብዛኛው የታዳጊ አገራት የጤና ችግር እየሆነ መምጣቱን የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በድሃ አገራት ህዝቦች ላይ ባደረገውና በ2012 ይፋ በሆነው ጥናት እንዳመለከተው፤ ስትሮክ በድሃ አገራት ህዝቦች ላይ በስፋት የሚከሰት የጤና ችግር እየሆነ መምጣቱን ጠቁሞ፤ ችግሩ ሞትና ዘላቂ የአካል ጉዳት የማስከተል ዕድሉም ከአደጉት አገራት በአራት እጥፍ እንደሚበልጥ አመልክቷል። በእነዚህ አገራት ከሚኖሩ 100ሺ ሰዎች መካከል ሃያ አምስት የሚሆኑት በህይወት ዘመናቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ በስትሮክ የመጠቃት እድል እንደሚገጥማቸውም ገልጿል፡፡ 
ስትሮክ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን ለሚበልጡ ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑን የጠቆመው የጤና ድርጅቱ፤ ከወንዶች ይልቃ ሴቶች ለስትሮክ ችግር የበለጠ እንደሚጋለጡም ገልጿል፡፡ ስትሮክን አክሞ ማዳን እንደማይቻል የሚናገሩት የህክምና ባለሙያው፤ ይህ ታውቆ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት በመከላከሉ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ይላሉ። ስትሮክ እንዳያጋጥም ለማድረግም የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል፣ የደም ግፊት፣ የኮሌስትሮልና የስኳር መጠንን መቆጣጠር፣ የልብ ህመምን፣ ያልተስተካከለ የሰውነት ክብደትን ማስወገድ፣ የቶንሲል ህመም በሚያጋጥም ወቅት ህክምናውን በአግባቡ ተከታትሎ ማዳን፣ ከአልኮልና ከዕፅ ሱሰኝነት መራቅ፣ አጠቃላይ የጤና ምርመራዎችን በየጊዜው ማድረግ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል – ባለሙያው፡፡ 

posted by Aseged Tamene

%d bloggers like this: