በግንደ በረት በተማሪዎች እና በክልሉ ፖሊስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተከሰተ

ምእራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል በግንደበረት ወረዳ በተማሪዎች እና በወያኔ የፖሊስ ሃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት አንድ
ተማሪ ሞቶ አራት መቁሰላቸውን የአከባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
ከትላንትና ጀምሮ ሲንከባለል የመጣው ግጭት ከዚህ ቀደም በኦሮምያ ክልል ውስጥ ከተነሱ የተማሪዎች አመጽ ጋር ተያያዥነት ያለው እና ጥያቂውም
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሞቱ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር የተያያዘ ሲሆን ዛሬ በቀጠለው ተቃውሞ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እና
የወረዳው ነዋሪ በጋራ ሰልፍ በመውጣት ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ ድረስ በመሄድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የፌዴራል
ፖሊስ በመምጣት የበተናቸው ቢሆንም
ቀኑን ሙሉ በከተማው ከባድ ረብሻ እንደነበር እና ከቆሰሉ ተማሪዎቹም አንዱ መሞቱን የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲሉ
ምንጮቹ ጠቁመዋል።
በነገው እለት የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ፈትና ከወሰደ በኋላ የተገደለውን ተማሪ ለመቅበር ይወጣል የተባለው ሕዝብ ተቃውሞ
እንዳያሰማ የወረዳው እና የከተማው ባለስልጣናት በመስጋት ፖሊሶች ያሰፈሩ ሲሆን ሕዝቡ ቁጣው እንዳልበረደ እና በስፋት
ተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

2 Responses to በግንደ በረት በተማሪዎች እና በክልሉ ፖሊስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተከሰተ

  1. This is contempt to the Ethiopian people, not only to the Oromos whose children are being killed, wounded and humiliated by the agazi security forces of TPLF/EPRDF. Opposition political entities and the Ethiopian people have legal and moral obligation to act in unison to stop the ongoing tyranny being perpetrated by the brutal misruling regime

    Like

  2. Pingback: በግንደ በረት በተማሪዎች እና በክልሉ ፖሊስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተከሰተ - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

Leave a comment