በእስር ላይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድረሱልን እያሉ ነው
March 13, 2018 Leave a comment
ቦረና አበራ፣ ወየቻ ታምሩ፣ ወሰኑ ገረመው፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ፣ ገዳ ገመቹ፣ እዮብ ሙሊሳ እና ሳሎ ነጋሳ የዲላ ዩ…ኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን በሚከታተሉበት ወቅት ለእስር ተዳርገዋል።
የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ምክንያት በነበረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ አራት ወራት ከታሰሩ በኋላ “ወንጀሉ በተፈፀመበት አካባቢ ይዳኙ” ተብሎ ሚያዝያ 28/2008 ወደ ዲላ ከተማ ተዛውረዋል። ሀምሌ 7/2008 ዓም ወደ ሀዋሳ ተዛውረው በእስር ላይ ይገኛሉ።
የካቲት 7/2010 በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ቦረና አበራ በነፃ ሲሰናበት፣ ቀሪዎቹ እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል። ተከላከሉ ከተባሉት 6 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ሳሎ ነጋሳ (4ኛ አመት ተማሪ የነበረ) ብቻ “እከላከላለሁ” ሲል ወየቻ ታምሩ (የ3ኛ አመት ተማሪ)፣ ወሰኑ ገረመው (3ኛ አመት)፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ (3ኛ አመት)፣ ገዳ ገመቹ (3ኛ አመት) “አንከላከልም” ብለዋል።
ተከሳሾቹ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው የታሰሩ በመሆናቸው ችግር ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። “የሚረዳን የለም፣ ሚዲያም እያስታወሰን አይደለም” ሲሉም ገልፀዋል።በጌታቸው ሺፈራው