የሰሜን ጎንደር ህዝብ እኛን ምረጡንና የማዳበሪያ እዳችሁን ቀስ ብላችሁ ትከፍላላቸሁ እየተባሉ ነው።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች ህዝብ አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ የማደናገርያ ቃል እየገቡለት መሆናቸውን ተገለፀ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው- የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘውን ህዝብ በማዳበሪያ እዳ ተማርሮ እንደሚገኝ አስቀድመው ስለተረዱ ሱሪያችሁን በጭንቅላታችሁ አውጡ አይነት አስገዳች መመሪያ በመስጠት እያስጨነቁት እንዳልቆዩ አሁን ላይ ደርሰው ከህብረተሰቡ በርካታ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው የወሰዳችሁትን የማዳበርያ እዳ ቀስ ብላችሁ በሚቀጥለው አመት ትከፍሉታላችሁ በማለት በመጪው ግንቦት ወር ላይ ተመርጠው የስልጣን እድሜአቸውን ለማስረዘም ህዝቡን እያታለሉት መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስረድቷል፣

የኢህአዴግን ተንኮል የተረዳው ህዝቡ በዚህ ተታለን እናንተን አንመረጣችሁም፤ የስልጣን እድሜያችሁን ለማስረዘም የምታደርጉት የማታለያ ቃል እንጂ ካዘናችሁልን ለምንድን ነው እዳችንን የማትሰርዙልን በማለት እንደተቃዎሟቸው ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣

posted  by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to የሰሜን ጎንደር ህዝብ እኛን ምረጡንና የማዳበሪያ እዳችሁን ቀስ ብላችሁ ትከፍላላቸሁ እየተባሉ ነው።

  1. Pingback: የሰሜን ጎንደር ህዝብ እኛን ምረጡንና የማዳበሪያ እዳችሁን ቀስ ብላችሁ ትከፍላላቸሁ እየተባሉ ነው። - EthioExplorer.com

Leave a comment