የከምባታ ህዝብ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ

‹‹ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል››
የከምባታ ህዝብ ሆን ተብሎ መሰረተ ልማት እንዳይገነባለት በመደረጉና በተራድኦ ድርጅቶች የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ስራ ላይ እንዳይወሉ በደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እየተፈፀመበት የሚገኘውን በደል በመቃወም ዛሬ የካቲት 3/2007 ዓ.ም በዱራሜ ከተማ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉን የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በሰልፉ ወቅትም ነዋሪዎቹ መንግስት ለአካበቢው ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠቱ 10 ከተሞች ላይ መብራት በራሳቸው ገንዘብ ማስገባታቸውን፣ ትምህርት ቤቶችን ራሳቸው እንደሰሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን የተዘረጋው በህዝቡ ወጭ መሆኑን፣ መንግስት ሰራሁት ያለው ውሃ ከሶስት ሳምንት በኋላ መበላሸቱ ሙስና እንደተበላበትና እንዳልተሰራ እንደሚያምኑ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሰልፈኞቹ ‹‹ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል፣ ስራ አጥተው የሚሰደዱትን ልጆቻችን መንግስት ህገ ወጥ ስደተኛ ሊላቸው አይገባም፣ ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር፣ መንግስት ከምባታን የሚያውቀው በስም ብቻ ነው፣ ተንቀናል፣ መብታችን ለማስከበር እንታገላለን፣ ….›› እና የመሳሰሉትን መፈክሮች እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ የተገኙ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዳይገኙ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው የመንግስት ሰራተኞችም ሰልፉን መቀላቀላቸውንና በአጠቃላይ ከ20 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሰልፉ መሳተፋቸውንም አቶ ኤርጫፎ ገልጸዋል፡፡
ሰልፉ የተደረገው በከምባታ ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ በመምጣቱና የደኢህዴን ባለስልጣናት ችግሩን ለመቅረፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የሚፈጸመውን በደል ለማሰማት ሲሆን የተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ ራሱን በማስተባበር የጠራው መሆኑም ተገልጾአል፡፡

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

2 Responses to የከምባታ ህዝብ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ

  1. Robele Ababya says:

    Congratulations to the heroic people of Kambata. Your valiant ancestors
    walked on foot for seven months to Maichew in Tigray and gave headache to
    the Fascist Italian invaders. You are now doing the same to the TPLF
    bandas. I am exceedingly proud of you.

    Like

  2. Pingback: የከምባታ ህዝብ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ - EthioExplorer.com

Leave a comment