አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡

አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡ አርብ ዕለት እንደጉርጎሪያን አቆጣጠር ጥቅምት 10 በሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው የዳብሊው ሆቴል በዲሞክራቲክ ናሽናል ኮሚቴ /ዲኤንሲ/ አማካኝነት የተደረገለትን ግብዣ አጋጣሚ በመጠቀም ከፕሬዘዳንቱ ጋር አንድን ስብሰባ የተከታተሉ ሲሆን እንደሚሰጥ ቃል በገባው ለፕሬዘዳንቱም በተወካያቸው አማካኝነት ደብዳቤ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡
አበበም በዕለቱ ባስተላለፈው መልዕክት ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ሰፊውን ህዝብ እና የተከበረችውን ሃገራችን ኢትዮጵያን ድምፅ ማሰማት አለብን ብሏል፡፡ የምዕራባዊያን ሃገራት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ አምባገነን መንግስታትን እንደሚረዱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እና ፖሊሲና ስትራቴጅዎቻቸውን እንዲከልሱ እንዲሁም ከሰብአዊ መብቶች መጠበቅ አለመጠበቅ ጋር በቀጥታ ማያያዝ እንደሚገባቸው በሁሉም አጋጣሚዎች ማሳወቅ ይገባልም ተብሏል፡፡

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡

  1. Pingback: አበበ ገላው ፕሬዘዳንት ኦባማ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ለፕሬዘዳንቱ ደብዳቤ አደረሳቸው፡፡ - EthioExplorer.com

Leave a comment